ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

ETHIO ≈ SCHOOL

сообщение · 2026-07-10 13:16 UTC
F
Фотография
click to show
ጅማ ዩኒቨርሲቲ 10 የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞቹ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘታቸውን ገልጿል። ዩኒቨርሲቲው ከፈረንሳይ የጥናትና ከፍተኛ ትምህርት ግምገማ ኤጀንሲ (High Council for the Evaluation of Research and Higher Education - HCERES) በአስር የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞች ዓለም አቀፍ ዕውቅና አጊኝቷል። ፕሮግራሞቹ ዕውቅና ያገኙት ሳይንሳዊ የዕውቅና አሰጣጥ ሂደቶችን በማለፍ የፊት ለፊት የመስክ ላይ ምልከታ፣ የሰነዶች ግምገማና ትንተና እንዲሁም በተቋም ደረጃ ጥልቅ ግለ ግምገማ ከተካሔደ በኋ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡ በግምገማውም ዘጠኝ ፕሮግራሞች ሙሉ የአምስት ዓመት እውቅና ሲያገኙ፣ አንድ ፕሮግራም ደግሞ የሦስት ዓመት እውቅና ከተጨማሪ ክትትል ጋር ተሰጥቶታል። ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያገኙ 10 ፕሮግራሞች፦ ● ከጤና ሳይንስ ፋኩሊቲ (ነርሲንግ እና ሚድዋይፈሪ) ● ከሕክምና ሳይንስ ፋኩሊቲ (ሕክምና እና አንስቴዢያ) ● ከቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (ሲቪል ምህንድስና፣ ኬሚካል ምህንድስና እና ሜካኒካል ምሕንድስና) ● ከኮምፒዩቲንግና ኢንፎርማቲክስ (ኮምፒዩተር ሳይንስ፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ኢንፎርሜሽን ሳይንስ) ዓለም አቀፍ ዕውቅናው ጅማ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን ለመሳብና የዩኒቨርሲቲውን ተመራቂዎች ዓለም አቀፍ ተፈላጊነት ለማሳደግ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
193 ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Feed t.me/s Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog