ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

ETHIO ≈ SCHOOL

сообщение · 2026-07-19 03:30 UTC
F
Фотография
click to show
#ጥቆማ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት (AAU-MCS) በማቋቋም በ2019 ዓ.ም ከ1ኛ-7ኛ ክፍል ለማስተማር ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል። በመሆኑም ልጆቻችሁን በሚከፈተው የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት ማስመዝገብ የምትፈልጉ ወላጆች የሚከተሉትን መረጃዎች ልታውቁ ይገባል፦ የምዝገባ ጊዜ ከሐምሌ 14-21/2018 ዓ.ም የምዝገባ ቦታ 5 ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂና ቢዩልት ኢንቫይሮንመንት ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር E04 ትምህርት ቤቱ የሚገኝበት ቦታ፦ 5 ኪሎ (በቀድሞው የድኅረ ምረቃ/ፋርማሲ ትምህርት ቤት ግቢ) የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 1,000 ሲሆን፤ በቀጣይ ወርሃዊ የክፍያ መጠን ይገለጻል ተብሏል። የሚያስፈልጉ ሰነዶች ● የተመዝጋቢ ልጆች የልደት ካርድ ● ከቀድሞ ትምህርት ቤት ያጠናቀቁበት ሰርተፊኬት ● ሁለት የወላጅ እና አራት የልጅ ፎቶግራፍ ● ወላጆች ህጋዊ አሳዳጊ መሆናቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ● የክፍያ ደረሰኝ እና የመመዝገቢያ ክላሰር ትምህርት ቤቱ ቅድሚያ ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ልጆች ዕድል የሚሰጥ ቢሆንም፣ ባለው ክፍት ቦታ መሠረት ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ውጭ ላሉ ተማሪዎች በውድድር ተደራሽ የሚሆን መሆኑ ተገልጿል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
117 ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Feed t.me/s Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog