ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

ETHIO ≈ SCHOOL

сообщение · 2026-07-21 07:41 UTC
F
Фотография
click to show
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል። በክልሉ በ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 85,531 ተማሪዎች መካከል 83,342 ተማሪዎች ወደ 9ኛ ክፍል የሚያሸጋግራቸውን ውጤት አምጥተዋል፡፡ ዘንድሮ ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች 97.4% የሚሆኑት ያለፉ ሲሆን፤ ይህም በክልሉ ባለፉት ዓመታት ከተመዘገበው ከፍተኛው ውጤት መሆኑን የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አንተነህ ፈቃዱ ገልፀዋል፡፡ የማለፊያ ነጥብ ለመደበኛ ተፈታኞች 50% እና ከዚያ በላይ ሲሆን፤ ለአካል ጉዳተኞች እና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ደግሞ 45% እና ከዚያ በላይ ሆኖ ተቀምጧል። ፈተናውን ካስፈተኑ 1,538 ትምህርት ቤቶች መካከል 1,017 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ማሳለፋቸውን የገለፁት ኃላፊው፤ ዘንድሮ አንድም ተማሪ ያላሳለፈ ትምህርት ቤት የለም ብለዋል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
108 ·

Вся лента · оригинал в Telegram

Open in Telegram Feed t.me/s Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog