Web appOpen in Telegram
SSci Tech

Sci Tech

@mindset_reset · channel · Tech · indexed since 2026-05-22
6subscribers
18posts in the index
Sci Tech
text not yet in the index
text not yet in the index
✳️ኮምፒውተር ላይ በአማርኛ ሲፅፉ ካልፈጠኑ ወይም መፃፍ ካልቻሉ የሚከተሉትን ኣጭር መግለጫ ይመልከቱ እና ይለማመዱ። ========================== • ሀ ፡ h ሁ ፡hu ሂ ፡hi ሃ ፡ ha ሄ ፡hy ህ ፡he ሆ ፡ho • ለ ፡l ሉ ፡lu ሊ፡li ላ ፡la ሌ፡ly ል፡le ሎ፡lo • ሐ፡shift +h ሑ፡shift +hu ሒ፡shift +hi ሓ፡shift +ha ሔ፡ shift + hy ሕ፡shift +he ሖ፡shift +ho • መ፡m ሙ፡mu ሚ፡mi ማ፡ma ሜ፡my ም፡me ሞ፡mo • ሠ፡shift + s ሡ፡shift + su ሢ፡shift + si ሣ፡shift+sa ሤ፡shift + sy ሥ፡shift + se ሦ፡shift + so • ረ፡r ሩ፡ru ሪ፡ri ራ፡ra ሬ፡ry ር፡re ሮ፡ro • ሰ፡s ሱ፡su ሲ፡si ሳ፡sa ሴ፡sy ስ፡se ሶ፡so • ሸ፡caps locks ሹ፡caps lock+su ሺ፡caps lock+si ሻ፡caps lock+sa ሼ፡caps lock+sy ሽ፡caps lock+se ሾ፡caps lock+so • ቀ፡q ቁ፡qu ቂ፡qi ቃ፡qa ቄ፡qy ቅ፡qe ቆ፡qo • በ፡b ቡ፡bu ቢ፡bi ባ፡ba ቤ፡by ብ፡be ቦ፡bo • ተ፡t ቱ፡tu ቲ፡ti ታ፡ta ቴ፡ty ት፡te ቶ፡to • ቸ፡c ቹ፡cu ቺ፡ci ቻ፡ca ቼ፡cy ች፡ce ቾ፡co • ነ፡n ኑ፡nu ኒ፡ni ና፡na ኔ፡ny ን፡ne ኖ፡no • ኘ፡shift +n ኙ፡shift +nu ኚ፡shift+ni ኛ፡shift +na ኜ፡ shift +ny ኝ፡shift + ne ኞ፡shift +no • ከ፡ka ኩ፡ku ኪ፡ki ካ፡ka ኬ፡ky ክ፡ke ኮ፡ko • ኸ፡capslock+ shift+ h ኹ፡capslock+shift+hu ኺ፡ capslock+shift +hi ኻ፡capslock+ Shift +ha ኼ፡ Capslock+ Shift +hy ኽ፡Capslock+ Shift+ he ኾ፡Capslock+ Shift + ho • ኀ፡ capslock + h ኁ፡ capslock + hu ኂ፡ capslock + hi ኃ፡ capslock + ha ኄ፡ capslock + hy ኅ፡ capslock + he ኆ፡ capslock + ho • አ ፡ x ኡ፡xu ኢ፡xi ኣ፡xa ኤ፡xy እ፡xe ኦ፡xo • ዐ፡shift +x ዑ፡shift +xu ዒ፡shift +xi ዓ፡shift +xa ዔ፡ shift +xy ዕ፡shift +xe ዖ፡shift +xo • ወ፡w ዉ፡wu ዊ፡wi ዋ፡wa ዌ፡wy ው፡ we ዎ፡wo • ዘ፡z ዙ፡zu ዚ፡zi ዛ፡za ዜ፡zy ዝ፡ze ዞ፡zo • ዠ፡shift + z ዡ፡shift + zu ዢ፡shift + zi ዣ፡shift +zaዤ፡shift + zy ዥ፡shift + ze ዦ፡ shift + zo • ፈ፡f ፉ፡fu ፊ፡fi ፋ፡fa ፌ፡fy ፍ፡fe ፎ፡fo • ፐ፡p ፑ፡pu ፒ፡pi ፓ፡pa ፔ፡py ፕ፡pe ፖ፡po • ገ፡g ጉ፡gu ጊ፡gi ጋ፡ga ጌ፡gy ግ፡ge ጎ፡go • ደ፡d ዱ፡du ዲ፡di ዳ፡da ዴ፡dy ድ፡de ዶ፡do • ጠ ፡ shift + t ጡ፡ shift + tu ጢ፡ shift + ti ጣ፡ shift+ta ጤ፡ shift + ty ጥ፡ shift + te ጦ፡ shift + to • ጨ፡ shift +c ጩ፡shift +cu ጪ፡shift +ci ጫ፡shift+caጬ፡shift +cy ጭ፡shift +ce ጮ፡shift +co • ጸ፡capslock + t ጹ፡capslock + tu ጺ፡capslock + ti ጻ፡capslock + ta ጼ፡ capslock + ty ጽ፡capslock + t ጾ፡capslock + to • ፀ፡capslock+ shift + t ፁ፡capslock + shift + tu ፂ፡capslock + shift + ti ፃ፡ capslock + shif
62 ·
አንድ አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት አፕሊኬሽኑ #ጎጂ ወይም #ጠቃሚ መሆኑን እንዴት ማረጋገጥ እንችላለን? ከGoogle Play Store ላይ የምናወርዳቸው አፕሊኬሽኖች ጠቃሚ መሆናቸው የተረጋገጠላቸው እና ጎጂ እንዳልሆኑ የተመሰከረላቸው ናቸው፡፡ ነገር ግን አንድ አንድ ግዜ ጠቃሚ መስለው ጎጂ አፕሊኬሽኖችን Play Store ላይ ልታገኙ ትችላላችሁ፡፡ ታድያ Play Store ላይ አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ስናደርግ አፕሊኬሽኑ ጠቃሚ ወይም ጎጂ መሆኑን እንዴት መለየት እንችላለን? 1. አፕሊኬሽኑ ምን ያህል ግዜ ዳውንሎድ እንደተደረገ መመልከት ዳውንሎድ ማድረግ የፈለግንው አፕሊኬሽን ዳውንሎድ ከማድረጋችን በፊት አፕሊኬሽኑ ምን ያህል ግዜ ዳውንሎድ (Download Count) እንደተደረገ በደንብ መመልከት ለምሳሌ ዳውንሎድ የምታደርጉት አፕሊኬሽን አንድ ሚሊዮን ግዜ ወይም ከዚያ በላይ ዳውንሎድ እንደተደረገ ካያችሁ ወድያው አፕሊኬሽኑ የተለቀቀበት ቀን በደንብ መመልከት፡፡ ምክንያቱም  አብዛኛው አፕሊኬሽን ከተለቀቀበት ግዜ ጀምሮ አንድ ዓመት ወይም ከዚያ በላይ የቆየ ሲሆን ነወ ከሚሊዮን በላይ ዳውንሎድ ሊኖረው የሚችለው፡፡ ስለዚህ እናንተ ማውረድ የፈለጋችሁት አፕሊኬሽን ከተለቀቀ አንድ ዓመት ካልሞላው እና ዳውንሎድ የተደረገው ከሚሊዮን በላይ ከሆነ አፕሊኬሽኑን ከማውረድ ብትቆጠቡ ይሻላል፡፡ 2.ስለ አፕሊኬሽኑ የተሰጡ የተወሰኑ አስተያየቶችን ማንበብ ዳውንሎድ ማድረግ የምትፈልጉት አፕሊኬሽን ከማውረዳችሁ በፊት ከዚህ በፊት  አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ያደረጉ ሰዎች ስለ አፕሊኬሽኑ አስተያየት (Reviews)ያስቀምጣሉ፡፡ እነዚህን አስተያቶች በጥንቃቄ ማንበብ፡፡ ስለ አፕሊኬሽኑ በጣም የሚያማርሩ አስተያየቶች ካነበባችሁ አፕሊኬሽኑ ከማውረድ እንደጥቆጠቡ እመክራለሁ፡፡ 3.የአፕሊኬሽኑ ስምምነት በጥንቃቄ ማንበብ አፕሊኬሽኑ ከላይ የተጠቀሱትን ፍተሸዎች ካለፈ ዳውንሎድ ታደርጉታላችሁ፡፡ ከዚያ ኢንስቶል ስታደርጉት የአፕሊኬሽኑን ስምምነት በጥንቃቄ ማንበብ ያስፈልጋል፡፡ ሁላችንም ማለት ይቻላል አፕሊኬሽን ኢንስቶል ስናደርግ ስምምነቱን ሳናነብ "Accept" እንላለን፡፡ ልክ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የሳይበር ወንጀለኞች ይህንን ባህሪያችን ስለሚያውቁ እኛን ሊጎዱ የሚችሉ ነገሮችን ስምምነቱ ላይ በማስገባት ጥቃት ሊፈፁሙብን ይችላሉ፡፡ ስለዚህ ስምምነቱን ስታነቡ ለምሳሌ  data mining, data sharing, pop-ups ወዘተ የሚሉ ቃላት ከተመለከታችሁ የአፕሊኬሽኑን ኢንስቶሊንግ ሂደት እንድታቋርጡ እመክራለሁ፡፡ ስለዚህ ዳውንሎድ ማድረግ የፈለጋችሁት አፕሊኬሽን ቢያንስ እነዚህን 3 ፍተሸዎችን ካለፈ ጎጂ አይደለም ማለት ነው፡፡ ➖➖❇️ Sci-Tech❇️ ➖➖
93 ·
Sci Tech
🌻ሞባይል ስልካችሁ በጣም እየተንቀራፈፈ ተቸግራችኋል? ሞባይል ስልካችሁ በጣም እየተንቀራፈፈ ወይም Busy እየሆነ ከተቸገራችሁ የሚከተሉትን ስቴፖች በመከተል የስልካችሁን ፍጥነት ማሻሻል ይቻላል 1ኛ፦ የሞባይላችሁ setting ውስጥ ትገባላችሁ፣ 2ኛ፦ በመቀጠል Developer option የሚል አለ እሱን ክሊክ ማድረግ። ነገር ግን አንዳንድ ስልኮች ላይ developer option በቀጥታ ስለማናገኘው about phone ውስጥ ገብተን build number የሚለውን ደጋግመን(ከ6-8 ግዜ) ስንነካው developer option ይመጣልናል። 3ኛ፦ በመቀጠልም developer option ውስጥ፦    3.1 window animation scale     3.2 transition animation scale እና     3.3 animation duration scale የሚሉ ምርጫዎች  ታገኛላችሁ።እነዚህ 3ቱንም በየተራ ክሊክ እያደረጋችሁ OFF አድርጓቸው። #አሁን_የስልካችሁ_ፍጥነት_ይሻሻላል። https://t.me/sci_tech101 🚀 ➖➖❇️ Sci-Tech❇️ ➖➖
45 ·
ብዙ ሰዉ የማያዉቃቸው የጂኤስኤም ሞባይል ሚስጥራዊ ኮዶች! 1. ስልክዎ ሲደወልሎት ይህ ቁጥር አገልግሎት አልዋለም እንዲልላቹ ከፈለጋቹ! ✅ወደ *21*900# ይደውሉ ወይም 1 ዲጂት በመቀነስ ወደ ራስዎ ስልክ ማድረግ! ለምሳሌ ስልክ ቁጥርዎ 0910654321 ከሆነ ወደ *21*091065432# ይደውሉ ለማጥፋት ሲፈልጉ #21# ብለው ይደውሉ! ከላይ የተገለጸው በ900 ቦታ የፈለጉት ሌላ ትክክለኛ የስልክ ቁጥር ያልሆነም ማድረግ ይችላሉ! *21*666# ብለው እንዳይደዉሉ! ➜ሁሉም ጥሪዎችና መልእክች ወደ ሌላ ቁጥር ዳይቨርት ለማድረግ ሲልጉ *21*0144123456# በ0144123456 ቦታ የፈለጉትን የሞባይል ወይም መደበኛ ስልክ ቁጥር ያስገቡ ቀድሞ ወደ ነበረበት ለመመለስ ከፈለጉ #21# ብለው ይደውሉ ማለትም ስልክዎ ዳይቨርት ከተደረገ #21# ሲደውሉ ወደ ኖርማል ይመለሳል ዳይቨርቱ ይጠፋል *#21# ከሆነ ስልኩ ዳይቨርት ተደርገዋል ወይስ አልተደረገም የሚል መረጃ ይሰጠናል 2. ስልክዎ ብዚ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ ✅*67*የፈለጉትቁጥር# ብለው ይደውሉ! ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #67# ይደውሉ 3. ስልክዎ ካልተነሳ ብቻ ዳይቨርት ለማደረግ ✅*61*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ! ይህንን ዳይቨርት ለማጥፋት #61# ይደውሉ 4. ስልክዎ ከኔትዎርክ ዉጪ ብቻ ሲሆን ዳይቨርት ለማድረግ ✅*62*የፈለጉትቁጥር# ይደውሉ! ይህንን ለማጥፋት ሲፈልጉ #62# ብለው ይደውሉ! 5. ኮል ወይቲንግ አክቲቭ ለማደረግ ሲፈልጉ ✅*43# ብለው ይደውሉ! ኮል ወይቲንግ ለማጥፋት ሲፈልጉ #43# ብለው ይደውሉ! ኮልወይቲንግ አክቲቬት መደረጉ ወይም አለመደረጉ ለማወቅ *#43# መደወል https://t.me/sci_tech101 🚀 ➖➖❇️ Sci-Tech❇️ ➖➖
44 ·
🔋የሞባይል ባትሪችን እድሜ ለማስረዘም ማድረግ የሚገባን 5 ነጥቦች፡- 1. የሞባይል አምራቹ ለገበያ ያላቀረበውን ቻርጀር አለመጠቀም ትክክለኛ ሳይሆኑ ለገንዘብ ተብለው በርካሽ ዋጋ ለገበያ የሚቀርቡ ቻርጀሮች በዋጋ ደረጃ ርካሽ ቢሆኑም ጥራታቸውን ያልጠበቁ በመሆናቸው ቻርጅ በምናደርግበት ጊዜ ለሞባይሉ ባትሪ ያልተመጣጠነ የኤሌትሪክ ሀይል በመስጠት ባትሪውን ይጎዳዋል፡፡ ይህም የባትሪውን እድሜ ያሳጥረዋል፡፡ 2. ሞባይል ቻርጅ ላይ እያለ አለመጠቀም ሞባይል ስልኮች ቻርጅ በሚደረጉበት ጊዜ ስልክ መደወል፣ ጌም መጫወት፣ ኢንተርኔት መጠቀም የባትሪውን እድሜ ከማሳጠር ባለፈ ለእኛ ለተጠቃሚዎቹ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ ከዚህም ባለፈ ሞባይሉ ራሱ ሊፈነዳ እንደሚችል ልብ ልንል ይገባል፡፡ 3. ሞባይልን ሌሊት ሙሉ ቻርጅ አለማድረግ፤ ጃርጅ ላይ ሰክቶ አለማሳደር በምሽት ወደ መኝት ከመሄዳችን በፊት ሞባይሉን ለነገ ሞልቶ እንዲያድር ብለን ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ እንዲያደርግ ማድረግ አንዱ ባትሪን ከሚገድሉ ስህተቶች መካከል ተጠቃሽ ነው፡፡ ባትሪው ከምሽት ጀምሮ ሌሊት ሙሉ ቻርጂ ሲያደርግ 100 ፐርሰንት መሙላቱ የማይቀር ሲሆን ከሞላ በኋላ የኤሌክትሪክ ፓወሩ ባትሪውን መደብደቡ የማይቀር ነው፡፡ የሞላ ነገር ሁሉ መፍሰሱ እንደማይቀር ሁሉ ሞቶ የሚፈስ ነገር ደግሞ እቃው ላይ ጉዳት ያስከትላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ ተሰክቶ ያደረ ባትሪ ከአቅሙ በላይ ስራ ይበዛበታል፡፡ 4. ሞባይል ስልክን አልፎ አልፎ ማጥፋት ሞባይል ስልክን አለማጥፋት ሌላው የባትሪን እድሜ ከሚቀንሱ ውስጥ አንዱ ሲሆን ሞባይል ስልኮች እንደማንኛውም ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች እና ማሽን እረፍት ያስፈልጋቸዋል፡፡ ቢቻል በምሽት ወደ መኝታ ስንሄድ አልፎ አልፎ ስልኮቻችንን ብናጠፋ ይመከራል፡፡ ብዙዎቻችን የሞባይል ስልካችን በስራ ላይ የሚመስለን ስንደውል፣ ሲደወልልን፣ አንዳንድ ነገሮችን በስልኮቻችን ስንጠቀም ብቻ ባትሪ የሚጠቀም ይመስለናል፤ ሆኖም ግን የባትሪው የመጠቀም መጠን ይለያያል እንጂ ሞባይሉ ሲከፈት በላዩ ላይ ያሉት ክፍት የተደረጉ ሰርቪሶች(ሰዓት፣ ብሉቱዝ፣ ዋይፋጥ፣ ጂፒኤስ፣ ዳታ ኮኔክሽን ወዘተ) ባትሪውን ይጠቀማሉ፡፡ 5. ባትሪው 0% እስኪሆን ድረስ አለመጠበቅ የማባይል ባትሪዎች የያዙትን ፓወር ጨርሰው 0% እስኪሆን ድረስ እየጠበቁ ቻርጅ ማድረግ የባትሪውን እድሜ የሚያሳጥር ሲሆን ባትሪው ግማሽም ይሁን ሩብ ሲቀረው ቻርጅ ብናደርገው ዜሮ እስኪሆን ድረስ ጠብቀን ከምናደርገው በተሻለ እድሜው እንዲጨምር ያደርጋል፡፡     https://t.me/sci_tech101 🚀 ➖➖❇️ Sci-Tech❇️ ➖➖
46 ·
🔆ለቴሌግራም አዲስ ገቢዎች ቴሌግራምን ልናስተዋውቃችሁ ነው አብራችሁን ሁኑ። 1.user_name ቢኖራችሁ ይመረጣል፤ ስልክ ቁጥራችሁን መስጠት ባትፈልጉ ይህን username ቢሰጡት ማንም እናንተን በቀላሉ ማግኘት ይችላል። ⚠️ setting ውስጥ ማግኘት ትችላላችሁ። 2.የሆነ ሰው እያዋራችሁ ስልክ ቁጥሩን ለማወቅ ከፈለጋችሁ ቀላል ዘዴ ልንገራችሁ። 👇 🤔እናንተ ብቻ ስልክ ቁጥራችሁን ላኩለት ያ ሰው ቁጥራችሁን contact ወይም dialer ውስጥ ካስገባው የእሱ ቁጥር በቀጥታ  ለናንተ ይታያችኋል። ⚠️ስልኳን አልሰጥ ላለች ሁላ ቁጥራችሁን ስትልኩ ዋሉ አሏችሁ ደሞ 😜 3.አዲስ Chanel (በፌስቡክኛ page የምንለውን) ወይም group ለመክፈት ከፈለጉ new group ወይም new channel የሚለውን በመጫንና ያላችሁን contact add በማድረግ ማስጀመር ትችላላችሁ።.                                                                                                  👇👇👇 4.ብዙ አይነት ቴሌግራም አፕ አለ ለምሳሌ telegram, plus, mobogram, supergram, multigram... እነዚህ 👆 ሁሉም የየራሳቸው feature አላቸው። 5.የሆነ ሰው አካውንት ውስጥ ስትገቡ start secret chat የሚል ይመጣል ከ normal chat ጋር ልዩነቱ ምንድነው? ✔️ከ 1ቀን በኋላ መልእክቱ ከእናንተም, ከተላከለትም ሰው, ከቴሌግራም ሰርቨርም ላይ ይጠፋል። ❌ ✔️እናንተ የላካችሁለትን መልእክት ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ(forward) ማድረግ አይችልም። 6. ፌስቡክ ላይ የምትጠቀሙበት chat off (ቻት ላይ እንደሆናችሁ ሌላ ሰው እንዳያውቅ ማድረጊያ) እዚህም አለ። ✅Setting ➡️ privacy and security ➡️ last seen እዚህ 👆 ውስጥ በመግባት... ✔️ሁሉም ሰው እንዲያያችሁ (everybody) ✔️ስልካችሁ ላይ ስልካቸው የተመዘገበ ሰዎች ብቻ እንዲያያችሁ (only contacts) ✔️እንዲሁም ማንም እንዳያያችሁ (nobody) ማድረግ ትችላላችሁ። 7.በቴሌግራም ማንኛውንም አይነት ዶክመንት መላክ ትችላላችሁ። ⚠️ከታች ያለውን attachment ምልክት በመንካት 👆 8.ቴሌግራም በየደቂቃው backup ስለሚይዝ ስልክዎ 📱 ቢጠፋ፣ ቢበላሽ 😭 መረጃዎ እንዳለ ይቆያል። 9.አሁን ያሉበትን ቦታ ⤴️ ለሌሎች ማጋራት ይችላሉ። ⚠️ከታች ያለውን attachment በመንካት 👆 10.ቴሌግራም በራሱ ምንም አይነት አሰልቺ ማስታወቂያዎችን ለተጠቃሚዎቹ አይልክም። ❌ ⚠️(AD-free) ነው። 11.አፑን ለራስዎ እንደሚመች theming ውስጥ በመግባት personalize ማድረግ.ይችላሉ።                                    12.ቴሌግራምዎን ከእርስዎ ውጭ ማንም እንዳይከፍተው password 🔑 መስጠት ከፈለጉ 👇 💢Setting ➡️ privacy and security ➡️ passcode lock ➡️ on ያድርጉና password ይስጡት ከዛም ✔️ 13.አንዳንድ ሰዎች ያለፍላጎትዎ ግሩፕ/ቻናል ላይ እያስገቡዎት ከተቸገሩ 👇 💢Setting ➡️ privacy and security ➡️ groups/channels ➡️ no one ✔️ 14.አፑን ሲከፍቱት ያለእርስዎ ትእዛዛት audio, video, document download እንዳያደርግ 👇 💢 Setting ➡️ data and storage ➡️ auto download media off ❌ 15. እርስዎ ባያዙትም 😡 ቴሌግራም ላይ ያዩዋቸውን ፎቶዎች 📸, ቪድዩዎች 🎥... አፑ
1 · 69 ·
S
📌ሰለ ቴሌግራም ማወቅ ያለብን 10 ወሳኝ  ነገሮች ✅ 1ኛ :- ያለንበትን #ቦታ ለጓደኞቻችን መላክ እንችላለን  መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የምንልክለትን ሰዉ እንመርጣለን ከዛ መላኪያዋን ከፍተን location የሚለውን ተጭነን ያለንበትን ቦታ መላክ ይቻላል :: ✅ 2ኛ :- ከኛ ወጪ ማንም ሰው ቴሌግራማችንን ማንም ሰዉ እንደይጠቀም ከፈለግን #password ማዘጋጀት ይቻላል መጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፈ ላይ ሦስት መሰመር አለ እሱን አንዴ እንነካለን ከዛ setting የምለውን  እንነካለን ከዛ privacy and security የሚለውን እንነካለን ከዛ passcode የሚለውን እንነካለን ከዛ passcode lock on እናደርጋለን ከዛ የምንፈልገውን password እናስገባለን ::   ✅ 3ኛ:-  እንዴት ቴሌግራም #ብር_እንዳይበላ ማድረግ ይቻላል    በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ያለውን ሦስቷን መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባለን ከዛ data and storage የሚለዉን እንነካለን ከዛ     when using mobile data -OF-አድርጉት :: ✅4ኛ :- የላክነዉን  message ከደረሰ በኃላ #delete  ማድረግ ይቻላል እንዴት መጀመሪያ የላክነዉን message እንከፍታለን ከዛ ቦታዉ ላይ አጥብቀን እንዛለን ከዛ ከላይ የሚለውን Also delete  receive የሚለውን ራይት እናደርጋለን ከዛ ሁለቱም ጋ delete ይሆናል :: ✅5ኛ :- እንዴት በአንድ የቴሌግራም አፕሊኬሽን ሁለት account እንጠቀማለን   በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ በቴሌግራሙ ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ ይህችን ምልክት ይንኩ ( v ) ከዛ new account ይለናል ከዛ መክፈት ✅6ኛ :- በተለይ ማታ ማታ ስንጠቀም ዓይናችን እንደይጎዳ ቴሌግራማችን #በጥቁር መልክ እንድሆን ከፍለግን dark ,, black ,, colour እንድትሆን ከፈለግን ...   በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ የቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ ገብተን ከሚሰጠን የመልክ ምርጫ የፈለግነዉን እንመርጣለን :: ✅7ኛ :- ቴሌግራም ያሉ ጽሁፎች አልነበብ እያሎት ተቸግረዋል ማለት ፊደሎቹ አንሰዉ ለዓይን አልታይ ካለ #ፊደሎቹን_ትልቅ ማድረግ ይቻላል እንዴት?   በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ chat setting ላይ እንገባለን ከዛ message text size የምል አለ እሱን እንነካና የፈለግነዉን ያህል ትልቅ ማድረግ ይቻላል :: ✅8ኛ:- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራም #ቻናል መክፈት እንችላለን?    በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ በቴሌግራም ጫፍ ላይ ያለውን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ New channel የሚለውን ነክተን create new channel የሚለውን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፈት የፈለግነዉን የቻናል ስም እናስገባለን :: ✅9ኛ :- እንዴት የራሳችንን የቴሌግራም #ግሩፕ እንከፍታለን ?    በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ ያለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ new group የሚለውን እንነካለን ከዛ create new group የሚለዉን እንነካለን ከዛ እኛ ለመክፍት የፈለግነዉን የግሩፕ ስም እናስገባለን :: ✅10ኛ :- እንዴት አድርገን #profile_photo መቀየር እንችላለን ?    በመጀመሪያ ቴሌግራም እንከፍታለን ከዛ ከላይ ያለዉን ሦስት መሰመር እንነካለን ከዛ setting ላይ እንገባ
64 ·
Sci Tech
📲ምንጊዜም ስልክ ቁጥሮቻችንን በ Backup መያዝ አለብን እንዴት Buckup እንያዝ? Step By Step 1:-contact ዉስጥ መግባት 2:-በተለምዶ setting botton የሚባለዉ Back ከማረጊያዉ ተቃራኒዉን መጫን 3:-ከዛ import/export የሚል ሲመጣ እሱን መጫን 4:-ከዛ Export to Storage ወይም export to SD Card ሲመጣ የሚል ሲመጣ እሱን መጫን በቃ በ 5 ሰከንድ ዉስጥ FileManager ላይ Coppy አርጎ ይጨርሳል ከዛ FileManager መክፈት 5:-Phone Storage ወይም Memory Storage መክፈት 6:- VCard file ወይም ሌላ አይነት ስም ይሰጠዋል በቃ Buckup ያዝን ማለት ነዉ 7:-ከፈለግን ደግሞ ወደ Computer ላይ Coppy ማረግ ይቻላል 8:- Computer ላይ ስልክ ቁጥሮቹን ማየት ከፈለጋችሁ Coppy ያደረግነዉን በ NotPad በመክፈት ስልክ ቁጥሮቹን ማየት ይቻላል 2:-እንዲሁም እያንዳንዱን ስልክ ቁጥር ወደ ሌላ ስልክ መገልበጥ ሳይጠበቅብን እንዴት በሰከንድ ዉስጥ ሁሉንም ስልክ ቁጥሮቻችንን ወደ ሌላ ስልክ መገልበጥ አንደምንችል 1:-በመጀመሪያ ከላይ እንዳሳየሁችሁ Memory Card ላይ Coppy ማድረግ አለብን 2:-ከዛ Contact ዉስጥ መግባት 3:-ከዛ setting botton ዉስጥ መግባት 4:-inport/ export ዉስጥ መግባት 5:-Import from Storage ማድረግ 3:-ስልክ ቁጥሮቻችንን SIM Card ሳንይዝ እንዴት በቀላሉ ሌላ ስልክ ላይ ማግኝት እንደምንችል፡፡ እዚህ ላይ የስልክ አድራሻዎቻችንን በጂሜይል / Gmail / ላይ ማሰቀመጥ ግዴታ ነዉ የአንድሮይድ ስልካችንን ከጂሜይላችን ጋር አገናኝተን የምንጠቀም ከሆነ ሁሉንም የስልክ አድራሻችንን እዛ ላይ ማኖር ያስችለናል። በዚህ መንገድም የስልክ አድራሻዎቻንን እንዳይጠፉብን ማድረግ የምንችል ሲሆን SIM Card ሳንይዝ በቀላሉ ሌላ ስልክ ላይ ማግኝት እንችላለን ድንገት ቢጠፉብን እንኳ ከጂሜይል መልሰን ማግኘት ያስችለናል። ለዚህም ይረዳን ዘንድ የጂሜይል አድራሻችን ውስጥ 1:-ኢንቦክስ / inbox / ውስጥ በመግባት አድራሻ / 2:-Contacts/ የሚለውን መጫን 3:-ከሚመጡንል ምርጫዎች ውስጥ / Restore contacts/ የሚለውን በመጫን የስልክ አግራሻችንን ጂሜይል ላይ ለማኖር እንችላለን https://t.me/sci_tech101 🚀 ➖➖❇️ Sci-Tech❇️ ➖➖
62 ·
S
📱በስልኮ ላይ ያሉ ስልክ ቁጥሮች(contacts) ባጣውስ ብለው ይሰጋሉ? እንግድያውስ የሚቀጥለውን መረጃ ያንብቡ። ስልክ ቁጥሮች ከሲም ካርዶ ወይም ሰልኮ በተጨማሪ በኢሜል በማስቀመጥ ስልኮ ሲጠፈ ፣ ሲበላሽ፣ በቫይረስ ሲጠቃ ከሚገጥሞት የመረጃ መጥፋት መካላከል እንችላለን። ከዚህም በተጨማሪ አዲስ ሲም ብንገዛ የስልክ ቁጥሮችን አንድ በአንድ ሴቭ ከማድረግ ከኢሜላችን ጋር በማገናኘት በአንዴ ወደ ስልካችን ማምጣት ያስችለናል። ለዚህም የሚከተለውን ስቴፕ ይመልከቱ። 1.የስልኮን menu button መጫን ከዛም “Settings.” 2. “Accounts and sync.” መጫን 3. “Add account” button መጫን 4. “Google.” የሚለው አማራጭ መጫን 5. “Next” button መጫን 6. የGmail login መረጃ በማስገባት “Sign in” በመጫን (ይህ ግን ከዚ በፊት አካውን ከነበሮት ነው Gmail አካውን ት ከሌሎዎት “Create” button የሚለው መጫን ከዛ አስፈላጊውን መረጃ በማስገባት አካውን መፍጠር። 7. “Sign in” button ስንጫን ስልካችን Gmail ላይ ያሉት የስልክ ቁጥር መረጃዎችን ያወርዳል። 8. “Sync Contacts/Sync now” አማራጭ መጫን 9. “Finish” button መጫን https://t.me/sci_tech101 🚀 ➖➖❇️ Sci-Tech❇️ ➖➖
65 ·
Sci Tech
⭕️ዳርክ ዌብ ምንድነው❓ 📌ዲፕ ዌብ/ዳርክ ዌብ ድብቁ የኢንተርኔት ክፍል ሲሆን ማንኛውም ሰው በቀላሉ Google,Yahoo,Bing ላይ መጠቀም ወይንም ማግኘት አይችልም! 🔴አሁን እየተጠቀምነው ያለው ኢንተርኔት Surface web ይባላል! 🔴ዲፕ ዌብ የራሱ የሆነ Domain አለው . com.net.edu.org ግን .Onion በሚባል በራሱ Domain name ይሸፈናል! ⭕️ከሊንኩ በፊት https ሳይሆን http ብቻ ብሎ ነው የሚጀምረው ምክነያቱም s የሚያመለክተው Secured የሆኑ ዌብሳይቶችን ሲሆን s የሌለው ደግሞ unsecured መሆኑን ነው! 🔴.onion ከዚህ በፊት surface web ላይ አይታችሁት አታውቁም! 🔴.onion ራሱ የ internet DNS root አይደለም! ወይንም በቀላሉ ከእነ .com .net .org .edu...ጋር አብሮ አይመደብም! ⭕️ዲፕ ዌብ/ዳርክ ዌብ ላይ ምን ልዩ ነገር አለ? 🔴እንግዲህ እጅግ አስገራሚና ሰምታችኋቸው የማታውቋቸው ነገሮች ይከናወኑበታል 🔘የጦር መሳሪያዎች ይሸጡበታል 🔘የተለያዩ አደንዛዥ እፆችና መድሀኒቶች ኬሚካሎች 🔘Fake ዲግሪ ፣ Fake ዲፕሎማ Fake passport ፣ fake መንጃ ፍቃድ የሰው ልጅ አካል(ኩላሊት...) 🔘የመመረቂያ እና Research ፅሁፍ 🔘የክሬዲት ካርድ ቁጥሮች 🔘የወሲብ ፊልሞች 🔘አደገኛ የሀኪንግ ሶፍትዌሮችና ሃርድዌሮች 🔘የክሬዲት ካርድ ሽያጭ(Visa, MasterCard, Amex..) 🔘ህገወጥ ሶፍትዌሮች 🔘የተሰረቁ ፊልሞች 🔘የሀከሮች ኪራይ(በገንዘብ ተስማምታችሁ የሆነ ነገር ሀክ እንዲያረጉላችሁ) 🔘የተለያዩ ድርጅቶችን ፓስዎርድ 🔘የኮንትሮባንድ እቃዎች(ኤሌክትሮኒክስ እና ልብሶችን በጣም በርካሽ ዋጋ) 🔘አደገኛ የሀኪንግ እና የተለያዩ ትምህርቶችን... 🔘ዘግናኝ ነገሮችም ይገኙበታል (Red ROOM, ISIS..) 🚩ምን አለፋን ብዛት ህገ ወጥ የሚባል ነገር ያለው እዚህ ነው..... 🚩በነገራችን ላይ ወደ 75% የሚሆኑ ዳርክ ዌብን የሚጠቀሙት ሀከሮች ናቸው! 🚩ከላይ የተጠቀሱትን ነገሮች ለመግዛትም ሆነ ለመሸጥ የሚጠቀሙበት Bitcoin ነው! ምክንያቱም ግዢ ሲፈፅሙ በባንክ እና በሌላ ዘዴ ከሆነ ሀከሮቹ የመያዝ እድላቸው የሰፋ ነው በBitcoin ከሆነ በምንም አይነት አይያዙም! https://t.me/sci_tech101 🚀
64 ·
S
‍ ‍ #በኢ_ሜይል አካውንቶች ላይ የሚቃጡ የመረጃ ጥቃቶች ምን ዓይነት ናቸው? #እንዴትስ_መከላከል_እንችላለን ? ✏️ፊሺንግ #Phishing አንዱ የሳይበር ጥቃት ዓይነት ሲሆን የኢ-ሜይል አድራሻችንን መሠረት በማድረግ ለሚፈፀም የጥቃት ዓይነት የተሰጠ ሙያዊ ቃል ነው፡፡ የፊሺንግ ጥቃት ወንጀለኞች ግላዊ የሆኑ መረጃዎቻችንን ለመስረቅ ወይም ላልተገባ ዓላማ ለማዋል የሚጠቀሙበት የማጭበርበሪያ መንገድ ነው፡፡ ለምሣሌ የባንክ የሒሳብ ቁጥራችንን ወይም የይለፍ-ቃሎቻችንን ለመመንተፍ በኢ-ሜይል አድራሻችን የሚላኩ የማደናገሪያ መልዕክቶች ናቸው፡፡ ✏️በኢ-ሜይል አድራሻ የሚላኩ የፊሺንግ መልዕክቶች ለተጠቃሚዎች እውነተኛ የሚመስሉ፤ ተጠቃሚውን ከተለያየ ዓይነት የጥቃት ሥጋት ለመጠበቅ ወይም ለመርዳት እንደሆነ የሚገልፁ እና አንዳንድ ጊዜም ተጠቃሚዎች ሎተሪ ወይም ነጻ የትምህርት ዕድል አሸናፊ እንደሆኑ የሚያበስሩ በመምሰል የማታለል ዓላማ ያላቸው ይዘቶች ናቸው ✏️የመረጃ መንታፊዎቹ ያዘጋጁትን አገናኝ #Link ተጠቃሚዎች እንዲከፍቱ በማግባባት እውነተኛ የዕድሉ አሸናፊ መሆናቸውን ለማረጋገጥ በሚመስል አግባብ አካውንታቸውን እና ምስጢራዊ የይለፍ-ቃል እንዲያስገቡ በመጠየቅ ጥቃት ለማድረስ የሚጠቀሙበት ዘዴ ነው፡፡ የፊሺንግ ጥቃት ፈጻሚዎች ዋና ዓላማ የግለሰቦችን የባንክ ቁጥር ለመመንተፍ ወይም ግላዊ መረጃዎችን ለሌሎች አሳልፎ ለመሸጥ በማቀድ የሚፈጸም ህገ-ወጥ ተግባር ነው፡፡ ✏️የፊሺንግ ጥቃትን ለመከላከል ሊወሰዱ የሚገቡ ጥንቃቄዎች ⚙የርዕሰ ጉዳዩ ትክክለኛነት መረጋገጥ /Subject Line and Tone/ #አብዛኛውን ጊዜ ከምንጠቀምባቸው ባንኮች ወይም የፋይናንስ ተቋማት የተላኩ የሚመስሉ የፊሺንግ መዝባሪዎች መልዕክቶች በኢ-ሜይል አድራሻዎቻችን ተልከው እናገኛለን፡፡ በዚህ ወቅት መልዕክቶቹን ከመክፈታችን በፊት ትክክለኛ አድራሻ መሆኑን ወደ ባንኮቹ ወይም ፋይናንስ ተቋማቱ በመደወል ልናረጋግጥ ይገባል፡፡ አንዳንድ የመልዕክት አድራሻዎች የትክክለኞቹን የፋይናንስ ተቋማት ስያሜ በተወሰነ ፊደል ለውጥ በማድረግ በቀላሉ ለማታለል የሚሞክሩ ናቸው፡፡ ⚙አባሪ /Attachments/ #የፊሺንግ ጥቃት ፈጻሚዎች ኢ-ሜይል አካውንታችንን ለመስረቅ የኛን ትኩረት የሚስቡ አባሪ ፋይሎችን የሚልኩልን ሲሆን ፋይሎቹን በምንከፍታቸው ጊዜ የተላኩልን መልዕክቶች ለህገወጥ ተግባር ሆን ተብለው የተሰሩ ማጥመጃዎች በመሆናቸው ኮምፒውተራችንን ለጉዳት ያጋልጣሉ፡፡ በመሆኑም ሁሉም አባሪዎች ጠቃሚ መረጃዎች ናቸው ብሎ ማሰብ ተገቢ አለመሆኑንና የሚላክልንን መልዕክት ከምናውቀው ትክክለኛ አካል የተላከ መሆኑን መረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡ ⚙አገናኝ /Link/ #ሁልጊዜም በኢ-ሜይል ለሚላኩ አገናኞችን በምንከፍትበት ወቅት ተገቢውን ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡ የተላኩልን ሊንኮች ትክክለኝነታቸውን ለማረጋገጥ ሊንኩን በቀጥታ በድረ-ገጽ ላይ በመተየብ እውነተኛ መሆኑን ማረጋገጥ ተገቢ ነው፡፡ አንዳንድ የፊሺንግ ሊንኮች “Click here”፣ “Preview document” ወይም “Sign In” የሚሉ እንድንከፍት የሚጋብዙ ቃላትን ይጠቀማሉ፡፡ ⚙ስልክ ቁጥሮች /Phone Numbers/ #በኢ_ሜይል የሚላኩ የማረጋገጫ ስልክ ቁጥሮችን መጠራጠር ተገቢ ነው፡፡ የተላከልን ስልክ ቁጥሩ ትክክለኛነቱን ከባንክ ደብተር ላይ ከሚገኝ አድራሻ በመውሰድ ደውለን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡ አለ በለዚያ በኢ-ሜይል የቀረበልንን መልዕክት በኢ-ሜይል አድራሻችን በተላከ ስልክ ቁጥር ትክክለኛ መሆኑን ለማረጋገጥ ከደወልን አጥፊዎች አስቀድመው ያዘጋጁት ቁጥር ከሆነ በሚፈልጉት መንገድ መረጃ በመስጠት ለጥቃ
72 ·
Sci Tech
✒☠ጥቁር መረብ (Dark web)💻📱 ✅ጥቁር መረብ የጥልቅ መረብ(Deep web) ትንሹ አካል ሲሆን ከሌላው መረብ( Standard Web) ወይም ኔትዋርክ የተደበቀ ሲሆን በተለመዱት አሳሽ ሶፍትዌር (Browser) ማልትም ፋየር ፋክስ፤ጎግል ክሮም፤ኦፔራ የመሳሰሉት  ጥቁር መረብን ማግኘት #አይቻሉም፡፡❌ ጥቁር ድር ብዙን ግዜ በህግ የተከለከሉ እቃዋች የሚሸጡበት እና ከፍተኛ የሆነ የጥቁ ገበያ (Black Market) የሚካሄድበት ቦታ ነው። በጥቁር ድር እንደ ናርኮቲክ, (Child porn), የተሰረቁ ክሬዲት ካርዶች, እና ሌሎች ህገወጥ እቃዎች  በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ። በጨለማ(ጥቁር) ድር ውስጥ የሚደረጉ አብዛኛዎቹ ግብሮች #በቢትኮይን (Bitcoin) እና በሌላ ኤሌክትሮ ሜል-መገበያያ ይከናወናሉ። ✒ጥቁር ድር የጥቁር መረብ ትንሽ አካል ሲሆን ሁለት አይነት ነትዋርክ ይጠቀማል።አንደኛው አቻ- ለ-አቻ-ኔትወርኮች(peer to peer network) እና ሁለተኛ ታዋቂ አውታረ መረቦች ያሉ ቶር(Tor)፣ ፍሪኔት(Freenet)፣ አይቱፒ( I2P)፣ ሪፍል(Riffle ) ፣በህዝባዊ ድርጅቶች እና ግለሰቦች የሚተዳደሩ ነትዋርክ ያካታል።የጨለማው ድር ተጠቃሚዎች መደበኛ ድርን(standard web) እንደሚከተለው ይገልጹታል፦" ሚስጥራዊ  ባለመሆኑ ምክንያት ማንም ሰው ልያጠቃን ወይም መረጃ ልንተውለት እንችለን" ብለው ያምናሉ። ✒ ጨለማ ድር  ከሚያስጠቅም ሶፍትዌር መካከል ዋናው እና ተዋቂው አንዱ ቶር ብሮዘር ነው። ቶር ብሮዘር ኦውየንላንድ በመባል የሚታወቀው የኔትወርክ ከፍተኛ ደረጃን (top domain) ቅጥያ(suffix) የሚጠቀም ሲሆን ከፍተኛ የሆነ መመስጠሪያ ስልተ ቀመር (encryption algorithm ) ይጠቀማል። ይህ ብሮዘሩን ተጠቃሚውን ለማግኘት ወይም ጠለፋ(hacking) ለማድረስ የተወሳሰበ  ያረገዋል። ✒በጥቁር ድር ያሉ #አገልግሎቶች፡ ☠ቦትኔት(botnet) ☠የብትኮይን አገልግሎቶች ☠የጥቁር ገብያ ☠የጠለፋ አገልግሎቶች(hacking Service) ☠ማጭበርበር አገልግሎቶች ☠ሽብርተኝነት 🚬አደገኛ እጽ እና ሌሌችም ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ 👇የቴሌግራም  ቻናላችን👇👇 ╔═══════════╗ ♨️  @Sci_tech101  ♨️ ╚═══════════╝ ━━━━━━⊱✿⊰━━━━━━ ➖➖❇️Sci-Tech❇️ ➖➖
74 ·
S
ሞባይል ዳታ በሚከፈትበት ጊዜ ካርድ ወይም የተሞላውን የዳታ ጥቅል በቶሎ የሚጨርስበት ምክንያትቶችና መፍትሔዎች: ምክንያቶች :- 1.የሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሳይዘጋ ሲቀር 2.ኢንተርኔት ክፍት ሆኖ ከተለያዩ ደህረ ገፆች ላይ ቀጥታ ቪዲዮች ሲታዩ 3.System settings እና Applications በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ 4.በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቃሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ 5.በሞባይል ስልኩ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር --------------------------- መፍትሔዎች :- 👉ሞባይል ዳታ ተከፍቶ ሲረሳና ሲቆይ እንደ ሶሻል ሚዲያና ኦንላይን የሚሰሩ አፕሊኬሽኖች ከተጠቃሚው እይታ ውጪ ስራቸውን ያከናውናሉ። በዚህ ጊዜ በሞባይሉ ላይ የተሞላው ክሬዲት ሰዓት ይቀንሳል ወይም ያልቃል ስለዚህም ኢንተርኔት ተጠቅመው ከጨረሱ በኋላ የሞባይሉን ዳታ ያጥፉ። 👉በሞባይል ዳታ ኢንተርኔት ከፍቶ ከተለያዪ ድህ ገፆች ላይ በቀጥታ ቪዲዮ መመልከት የተሞላውን ካርድ መጠን በጊዜ ከሚያሳጥሩት ነገሮች ወስጥ አንደኛው ሲሆን ለዚህም ዋነኛው ምክንያት በኢንተርኔት ቪዲዮ ቀጥታ መመልከት የሚቆጥረው የዳታ መጠን ከፍተኛ ስለሆነ ነው ስለዚህ ቪዲዮ ማየቱ ግዴታ ከሆነ በ Vidmate እና በሌሉች ቪዲዮ ዳውሎደር አፕሊኬሽኖች የቪዲዮ ይዘት በመቀነስ ጭኖ መመልከቱ ወጪን ይቆጥባል። 👉System settings እና Application በራሳቸው ጊዜ አፕዴት ሲያደርጉ የተሞላውን ዳታ(ካርድ) ይወስዳሉ ታዲያ ይህን ለማስቀረት Free wifi ከተገኘ አፕዴት ማድረግ ይህ ማድረግ የማይቻል ከሆነ system settings አፕዴት እንዳያደርግ ማስቆም:   👍Settings ----About----Software Update--- Automatic update የሚለውን ማጥፋት Applications አፕዴት እንዳያደርጉ ከተፈለገ ደግሞ -Google Play መክፈት. - hamburger የሚመስለውን በለ ሶስት ሆሪዞንታል ምልክት ያለበትንም አናት ላይ በስተግራ በኩል Settings በመንካት Auto-update apps.- disable automatic app updates, የሚለውን በመክፈት እና በመምረጥ መዝጋት ይቻላል 👉በሞባይሉ ላይ የሚገኙ አፕሊኬሽኖች ተጠቀሚው በማያቸው መንገድ ከበስተጀርባ ሲሰሩ ከእይታ ውጪ በመሆን የክሬዲት መጠን ይቀንሳሉ ታዲያ ይህን ለመከላከል:     👍Settings---- data usage ---Restricted Background data የሚለውን መክፈት... ከዚህ ይበልጥ ደግሞ Mobile data saver አፕሊኬሽኖች በመጫን መጠቀም   👉በሞባይል ሰልክ ውስጥ ቫይረስ ሲኖር የተሞላውን ሞባይል ዳታ ከመቅስፈት እድሜው እንዲያጥር ያደርጋል ብሎም ቫይረሱ በራሱ ጊዜ የሞባይሉን ኦፕሬቲንግ ሲስተም በማዘዝ ያለማንም ትዕዛዝ ዳታ ይከፍታል ዳውንሎድ ያደርጋል አላስፈላጊ ነገሮችና ማስታወቂያዋች ይለቃል ከዚህም የተነሳ በፍጥነት የሞባይል ካርድ( ዳታ ጥቅል) ይጨርሳል ይህ ነገር በሞባይሉ ላይ ቢከሰት አንቲ ቫይረስ በመጫ ሰካን ማድረግ ይህ መፍትሔ የማይሆን ከሆነ ለባለሙያ ማሳየቱ ተገቢ ነው:: ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ 👇የቴሌግራም  ቻናላችን👇👇 ╔═══════════╗ ♨️  @Sci_tech101  ♨️ ╚═══════════╝ ━━━━━━⊱✿⊰━━━━━━ ➖➖❇️Sci-Tech❇️ ➖➖
87 ·
S
Sci Tech
🤳 ስልኬ Copy ነው  Original? የሚለውን መለየት ሲያቅታቸው ይስተዋላል እኛም check የሚደረግበትን መንገድ እነሆ ልንጠቁማችሁ ወደድን ተከታተሉ። best method የሚባለው ወደ internet በመግባት imei.info ወይም #imei check በማለት search ማድረግ ከዚያም መጀመርያ ወደ ሚመጣው #website በመግባት የስልካችሁን #imei መጻፍና check የሚለውን መጫን። አለቀቀቀቀቀቀ!!! #imei ቁጥራችሁን ስታዩ ልብ ልትሉት የሚገባው ነገር *#06# ብላችሁ የምመጣውና የስልካችሁን ባትሪ አውጥታችሁ ከስልካችሁ ጀርባ የምታዩት መመሳሰል አለበት።ታድያ ይህንን አድርገን original መሆኑን እንዴት እናውቃለን? ➲#imei ቀጥራችሁን ጽፋችሁ ምንም ካልመጣ ያለጥርጥር ስልካችሁ highcopy ነው። ነገርግን ስለስልካችሁ የተለያዩ መረጃዎችን የሚያመጣ ከሆነ ስልካችሁ ኦርጅናል ነው።ይህንን ስልት አብዛኛው ሰው ይህን ሲስተም አያውቁም ከላይ እንዳያቹት የ ራሳቹን ስልክ check up አድርጉት ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈ 👇የቴሌግራም  ቻናላችን👇👇 ╔═══════════╗ ♨️  @Sci_tech101  ♨️ ╚═══════════╝ ━━━━━━⊱✿⊰━━━━━━ ➖➖❇️Sci-Tech❇️ ➖➖
92 ·
S
Sci Tech
ሳተላይት ኢንተርኔት ምንድን ነው? በድርጅቶችም ሆነ በግለሰቦች ደረጃ ሳተላይት ኢንተርኔትን የሚጠቀሙ እንዳሉ ሰምተን እናውቅ ይሆናል። ከቴሌኮም ፈቃድ ውጭ ሳተላይት ኢንተርኔትን ሲጠቀሙ ተያዙ የሚልም ዜናም እንዲሁ። ለመሆኑ ሳተላይት ኢንተርኔት ምንድን ነው? የ "ግርምተ ሳይቴክ" መጽሐፍ ደራሲና በፎርቹን መጽሔት ዝርዝር በዓለም ላይ በ2018 ከፍተኛ ገቢ ካስመዘገቡ 500 ድርጅቶች (Fortune500) መካከል በአንዱ የቴክኖሎጂ ኃላፊ እንዲሁም የቴክቶክ የቴሌቪዥን ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ ሰለሞን ካሳ ጋር ከወራት በፊት አጭር ቃለ ምልልስ አድርገን ነበር። 👉  ሳተላይት ኢንተርኔት ምንድን ነው?  ሳተላይት ኢንተርኔት ቴክኖሎጂ ማለት ልክ በዳያል አፕ፣ በብሮድባንድ፣ በፋይበር ኦፕቲክስ ወይም በሌላ ዓይነት መንገድ የምናገኘውን ዓይነት ኢንተርኔት ሊሰጠን የሚችል ሌላኛው አማራጭ ማለት ነው። በላንድ ላይን በምናውቀው ዓይነት በገመድ [ኬብል] አማካይነት የሚሰራጨውን ዓይነት ብዙዎቻችን እናውቀዋለን፤ እንጠቀምበታለን። ነገር ግን የሳተላይት ኢንተርኔት አጀማመሩ በፍፁም አሁን የምንጠቀመው ዓይነት የኢንተርኔት ቴክኖሎጂ የሌለበት ሁኔታ ሲሆን፤ ምንም ዓይነት ሌላ ምርጫ በሚጠፋ ጊዜ በተለይ ተደራሽ ያልሆኑ አካባቢዎችን እሳቤ በማድረግ የተሰራ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ነው። ሳተላይት ኢንተርኔት የሚሰራውም ሕዋ [ስፔስ] ላይ ካሉ ሳተላይቶች ጋር በመሆን ተጠቃሚዎች ደግሞ ዲሽ ቤታችው ላይ ቢሯቸው ላይ በማድረግ፤ በመሬት ላይ ደግሞ የኔትወርክ ኦፕሬቲንግ ሴንተር እና ቴሌፖርት የሚባሉ አሉ። በእነዚህ በሦስቱ ጥምረቶች ኢንተርኔትን ለተጠቃሚ የሚያደርስ ቴክኖሎጂ ነው። ይህ ቪሳት [Very small aperture terminal (VSAT) ይባላል። ሳተላይት ኢንተርኔት የሚሰራውም በዚህ አማካኝት ነው። ኢትዮጵያ ሳተላይት ማምጠቋ ለምን ይጠቅማታል? ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች መፈፀም የሌለባቸው ስህተቶች ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንተርኔት ሲቋረጥ ምን ይከሰታል? 👉 አምስት ጂ ኢንተርኔት ምን አዲስ ነገር አለው? ብሮድባንድ እና ሌሎች አማራጮች ባሉበት ሳተላይት ኢንተርኔትን መጠቀም ለምን ያስፈልጋል? የብሮድባንድ ኢንተርኔት የለም ወይ? ያን መጠቀም በፍፁም አይቻልም ወይ ? የሚለው በቅድሚያ የሚነሳ ጥያቄ ነው። አንድ ሰው የብሮድባንድ ኢንተርኔት እያለው ለምን ሳተላይት ኢንተርኔት ይጠቀማል? እኔ አሁን ቤቴ ጥሩ የብሮድባንድ ኢንተርኔት አለኝ። ስለዚህ ሳተላይት ኢንተርኔትን መጠቀም አያስፈልገኝም። ምክንያቱም አንደኛ ውድ ነው፣ ፍጥነቱም ከብሮድባንድና ከሌሎቹ ዓይነቶች እጅግ ያነሰ ነው። ስለዚህ ለመገጣጠም [Install] የሚያስፈልጉ ቁሶችም ተጨማምረው ጠቀሜታ የለውም። በመሆኑም ይህ እንደተጠቃሚው ዓላማ ነው የሚወሰነው። ምን አልባት ከመረጃ ደህንነት ጋር በተገናኘ የተለየ ፋይዳ አለው? ሳተላይት ኢንተርኔትና ከሳይበር ሴኩሪቲ አብሮ የሚነሳ ነገር ነው። ከመረጃ ጥበቃ አንፃር ምን አልባት ከዋናው የኢንተርኔት መሰረተ ልማት [Infrastructure] የወጣ ራሱን የቻለ ሊሆን ስለሚችል፤ ምን አልባት የቁጥጥር ሁኔታው [ Control feature] አነስ ሊል የሚችልበት ሁኔታ እንደሚኖር አስባለሁ። ማንኛውም ግለሰብ ተነስቶ ቴክኖሎጂው ስላለ ብቻ ሳተላይት ኢንተርኔትን መጠቀም ይችላል? ይህ እንደየ አገሩ ሕግና የቴሌኮም አጠቃቀም ይለያያል። ነገር ግን እንዲህ አይነት ነገር ሲጠቀሙ የዚያ አገር መንግሥት አስተዳዳር ይህን ማወቅ አለበት። ምክንያቱም ይህ ከአገር ደህንነት ጋር እንዲሁም ከብዙ ነገር ጋር ሊያያዝ ስለሚችል፤ ማንኛውም ሳተላይት ኢንተርኔትን ለመ
118 ·
Archive by month

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · Index limits · Remove a page · Catalog · Search · How we count