Link
click to show
click to show
አስተዳደራዊ ቅጣት በልዩ ሁኔታ ስለማንሳት
በታክስ ሕጉ መሠረት የተጣለብዎትን አስተዳደራዊ ቅጣት በልዩ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል እንዲነሳልዎ መጠየቅ ይችላሉ። ይህን ሂደት ለመረዳትና ለመጠቀም የሚከተሉትን ዋና ዋና ነጥቦች ይከተሉ፦
1. ቅጣቱ በልዩ ሁኔታ ሊነሳ የሚችለው መቼ ነው?
በታክስ ሕጉ መደበኛ ደንቦች መሠረት ቅጣት የሚነሳበት አሰራር ቢኖርም፤ በልዩ ሁኔታ ቅጣት ሊነሳ የሚችለው በሚከተሉት ምክንያቶች ነው፦
ኢኮኖሚያዊ ምክንያቶች፣
አስተዳደራዊ ምክንያቶች፣ ወይም
ማህበራዊ ምክንያቶች ሲያጋጥሙ።
ማስታወሻ፦ ቅጣቱን በልዩ ሁኔታ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የማንሳት ሥልጣን የታክስ ባለሥልጣኑ የበላይ ኃላፊ (ወይም እርሱ የሚወክለው ኃላፊ) ብቻ ነው። ጥያቄው በልዩ ሁኔታ እንዲታይሎት በራስዎ ማመልከት ይችላሉ፤ ወይም ታክስ ባለሥልጣኑ በራሱ ተነሳሽነት ሊያየው ይችላል።
2. ማመልከቻ እንዴት እና የት ይቀርባል?
ማመልከቻ ማቅረብ፦ ጥያቄዎን ጉዳዩ ለሚመለከተው የታክስ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ያቀረባሉ።
አስፈላጊ መረጃዎችና ማስረጃዎች፦ ማመልከቻዎ ከበቂ ማስረጃዎች ጋር መቅረብ ያለበት ሲሆን፣ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ የሚከተሉትን ነጥቦች አጣርቶ የውሳኔ ሃሳብ ያዘጋጃል፦
ከእርስዎ የሚፈለገውን ጠቅላላ የታክስ ዕዳ መጠን እና የታክስ ዓይነት፣
የታክስ ዕዳው ያለበትን ሁኔታ እና የእርስዎን የታክስ አከፋፈል ታሪክ (የትራክ ሬኮርድ)፣
ቅጣቱ በልዩ ሁኔታ እንዲነሳ የጠየቁበትን ተጨባጭ ምክንያት እና ያቀረቡትን ማስረጃ።
ሃሳብ ማስተላለፍ፦ የቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ የተዘጋጀውን ዝርዝር የውሳኔ ሃሳብ ፈርሞ ለታክስ ባለሥልጣኑ የበላይ ኃላፊ ይልካል።
3. የውሳኔ አሰጣጥ ሂደት (በዋናው መሥሪያ ቤት)
የታክስ ባለሥልጣኑ የበላይ ኃላፊ ወይም የበላይ ኃላፊዉ የሚወክለዉ ሰዉ ጥያቄውን ከተቀበለ በኋላ ጉዳዩን ለታክስ ዕዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ይመራዋል።
የበላይ ኃላፊ ወይም የበላይ ኃላፊዉ የሚወክለዉ ሰዉ የቀረቡትን ማስረጃዎች፣ የእርስዎን ጥያቄ እና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ሃሳብ መርምሮ የውሳኔ ሃሳብ ያቀርባል።
በበላይ ኃላፊው የመጨረሻ ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ፣ ውሳኔው በታክስ ዕዳ አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በኩል ለቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ ተልኮ ተፈጻሚ ይደረጋል ።
4. እንደገና የመታየት ዕድል (ይግባኝ/ድጋሚ ዕይታ)
ቅጣቱን በልዩ ሁኔታ ለማንሳት ጥቅም ላይ የዋለው ማስረጃ ወይም ሁኔታ በአግባቡ ሳይታይ ቀርቷል ተብሎ ከተገመተ፣ የታክስ ባለሥልጣኑ የበላይ ኃላፊ ጉዳዩን በድጋሚ አይቶ ውሳኔ ሊሰጥበት ይችላል ለተጨማሪ ማብራሪያ (189/2017) ያንብቡ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ቲክቶክ፡-https://www.tiktok.com/@mto2education
ኢሜል፡- [email protected]
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2
❤9
43 · 5.7K · Link
click to show
click to show
ታክስ እውቀት ለሁሉም!
ከምዝገባ እና ስረዛ ጋር የተያያዙ አስተዳደራዊ የታክስ ጥፋቶች እና ህጋዊ ውጤቶቻቸው
(በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 መሠረት)
በሕግ የታክስ ከፋይነት መመዝገብ ሲገባቸው አለመመዝገብ ወይም ሥራ ሲቆም ምዝገባን አለመሰረዝ ሕጋዊ ቅጣት ያስከትላል! አዋጁ በዚህ ረገድ የሚከተሉትን ቅጣቶች ደንግጋል፦
1️⃣ መመዝገብ ሲገባው ያልተመዘገበ ታክስ ከፋይ ቅጣት
ታክስ የሚከፍል ከሆነ፦ መመዝገብ ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ እስከ አመለከተበት (ወይም ሚኒስቴሩ በራሱ አነሳሽነት እስከመዘገበው) ቀን ድረስ መክፈል ከሚገባው ታክስ ላይ 25% ቅጣት ይከፍላል።
የሚከፍለው ታክስ ከሌለ፦ መመዝገብ ከነበረበት ቀን ጀምሮ እስከ ተመዘገበበት ቀን ድረስ ለእያንዳንዱ ወር ወይም የወሩ ክፍል 1,000 ብር ቅጣት ይከፍላል።
ልዩ ማስታወሻ፦ የ 25% ቅጣቱ መጠን ከ 1,000 ብር ያነሰ ከሆነ፣ ተፈጻሚ የሚሆነው አነስተኛው 1,000 ብሩ ቅጣት ነው።
2️⃣ ምዝገባ እንዲሰረዝ ያላመለከተ ታክስ ከፋይ ቅጣት
የንግድ ሥራውን ካቆመ በኋላ ያለበቂ ምክንያት ምዝገባው እንዲሰረዝ ያላመለከተ ሰው፣ ማመልከት ከነበረበት ቀን ጀምሮ እስከ አመለከተበት (ወይም ሚኒስቴሩ በራሱ አነሳሽነት እስከሰረዘው) ቀን ድረስ ለእያንዳንዱ ወር 1,000 ብር ቅጣት ይከፍላል።
💡 ለስረዛ ዘግይቶ ማመልከት "በቂ ምክንያት" የሚባለው ምንድን ነው?
ታክስ ከፋዩ ሥራ ካቆመ በኋላ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ በጽሑፍ ያላመለከተው በነዚህ ምክንያቶች ከሆነ ቅጣቱ አይጣልበትም፦
ሊያስወግዳቸው የማይችሉ የተፈጥሮ ወይም የሰው ሰራሽ አደጋዎች ሲያጋጥሙ፣
ታክስ ከፋዩ ወይም የታክስ ወኪሉ (እንደራሴው) በጽኑ ሕመም ላይ ሲሆኑ፣
ወይም ከዚህ ዓለም በሞት ሲለዩ።
⚠️ ማስታወሻ፦ እነዚህ ቅጣቶች ተፈጻሚ የሚሆኑት በሕግ የመመዝገብ ግዴታ ላለባቸው እና ሥራቸውን ሲያቆሙ ምዝገባ የማሰረዝ ግዴታ በተጣለባቸው ታክስ ከፋዮች ላይ ብቻ ነው!
👉 ሕግን ማወቅና በሰዓቱ መመዝገብም ሆነ ማሰረዝ ከአላስፈላጊ ቅጣት ያድናል! ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ቲክቶክ፡-https://www.tiktok.com/@mto2education
ኢሜል፡- [email protected]
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2
❤11
24 · 4K · Photo
Photo
Photo
Photo
Photo
Photo
Photo
Photo
Photo
የተሻለ ሙያዊ ሥነ-ምግባርን በመገንባት ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን መከላከል እንደሚገባ ተገለጸ
ጥቅምት 09/2019 ዓ.ም (የገቢዎች ሚኒስቴር)
የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ ከመካከለኛ ቁጥር ሁለት ቅ/ጽ/ቤት አመራር እና ሠራተኞች ጋር ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ የመክፈቻ ንግግራቸው ያደረጉት የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ እንደ ሀገር የተሰጠንን ትልቅ ኃላፊነትና ተልዕኮ ለመወጣት የተሻለ ሙያዊ ስነ ምግባርን መገንባት፣ ሙስናን መዋጋት እንዲሁም ግልፅ እና ተጠያቂነት የሰፈነበት አገልግሎት መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡
በትብብር ሙስናን እና ብልሹ አሰራርን መዋጋት፤ ተቋማዊ የመፈፀም አቅምን ማሳደግ፤ ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመዘርጋት የአገልግሎት ጥራት እና ቅልጥፍናን ማሳደግ፤ ግልጽነትና ተጠያቂነት ማስፈን እንዲሁም የተሰጠንን ተቋማዊ ተልዕኮ በብቃት መወጣት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች መሆናቸውን ሚኒስትሯ አክለው ገልጸዋል፡፡
የሚኒስትር የታክስ አማካሪ የሆኑት አቶ ስመኝ ንጉሴ የሙስናና የብልሹ አሰራር መከላከል ልዩ የንቅናቄ እቅድ የመወያያ ሰነድ አቅርበዋል።
የገቢው ዘርፍ ለሙስና እና ብልሹ አሰራር ይበልጥ ተጋላጭ በመሆኑ በሁሉም ዘርፍ የሚገኙ አመራርና ሰራተኞች ራሳቸውን ከሙስና እና ብልሹ አሰራር በማራቅ የተጣለባቸውን ሀገራዊ ኃላፊነት በብቃት መወጣት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
የመካከለኛ ቁጥር ሁለት ቅ/ጽ/ቤትን የ2019 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ያቀረቡት የገቢዎች ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ፕላን እና ፕሮጀክት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ተመስገን ተሰማ በበኩላቸው በሩብ ዓመቱ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አፈጻጸም አበረታች መሆኑን ገልጸው በቀሪ ጊዜያት የተሰጠን ኃላፊነት በትጋት እና በቁርጠኝነት በመከወን የተያዘውን የገቢ ዕቅድ ማሳካት እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በመድረኩ ከተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየትና ጥያቄዎች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ለሙስናና ብልሹ አሰራር በር የሚከፍቱ አሰራሮችን ፈጥኖ በማስተካከል ለበጀት ዓመቱ እንደ ተቋም የተያዘውን የገቢ እቅድ ሙሉ በሙሉ እንዲሳካ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በልዩ ትኩረት ሊሰራ እንደሚገባ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
በበላይነሽ እጅጉ
ፎቶ:- የትናየት እንዳያፍሩ
❤8👍1
1 · 3.3K · Link
click to show
click to show
በዲጂታል መንገዶች (ፕላትፎርሞች) ለሚሰጡ የትራንስፖርት አገልግሎቶች
በዲጂታል መተግበሪያዎች (እንደ ፈረስ እና ራይድ መሰል ፕላትፎርሞች) አማካኝነት የትራንስፖርት አገልግሎት ለምትሰጡ አሽከርካሪዎች እና የቴክኖሎጂ ፕላትፎርም አቅራቢዎች ማስታወሻ፡
በዲጂታል የትራንስፖርት አገልግሎቶች ላይ የሚከተሉትን ግልጽ ግዴታዎች ደንግጓል፦
📌 1. ለፕላትፎርም አቅራቢዎች የሚመለከቱ ዋና ዋና ኃላፊነቶች፡
· የታክስ ስሌት እና አሰባሰብ፡ ፕላትፎርም አቅራቢዎች ከተሳፋሪዎች ከሚከፈለው ጠቅላላ ክፍያ (ማናቸውንም ክፍያዎች እና ኮሚሽኖችን ጨምሮ) ላይ ተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) የመሰብሰብ ኃላፊነት አለበት።
· ደረሰኝ አሰጣጥ፡ ፕላትፎርም አቅራቢው በየዕለቱ መጨረሻ ለትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪው (ለአሽከርካሪው) የቫት ደረሰኝ መስጠት አለበት።
· መረጃዎችን የመያዝ ግዴታ፡ አገልግሎቱ የተሰጠበትን ቀን፣ ሰዓት፣ ቦታ፣ የክፍያ መጠን እና ቫትን ጨምሮ ሙሉ ዝርዝር መረጃዎችን መያዝ ይጠበቅበታል።
· ታክስን ማስተላለፍ እና ማስታወቂያ፡ የተሰበሰበውን ቫት በአዋጁ መሰረት ለታክስ ባለሥልጣኑ ማስተላለፍ እና ተገቢውን ማስታወቂያ ማቅረብ አለበት።
· የአገልግሎቱ ቦታ፡ አገልግሎቱ የተከናወነበት ቦታ ተሳፋሪው አገልግሎቱ በሚሰጥበት ጊዜ የሚገኝበት ቦታ ተደርጎ ይወሰዳል።
🚙 2. ለትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች (አሽከርካሪዎች) የሚመለከቱ ነጥቦች፡
· የግብአት ታክስ ተቀናሽ፡ አሽከርካሪዎች ከመንገደኞች ትራንስፖርት አገልግሎት አቅርቦት ጋር በቀጥታ ለተያያዙ ግዥዎች የከፈሉትን የግብአት ታክስ በአጠቃላይ የቫት ተቀናሽ አሰራር ስርዓት መሰረት ተቀናሽ እንዲደረግላቸው ሊጠይቁ ይችላሉ።
· የምዝገባ ገደብ፡ ፕላትፎርም አቅራቢው ታክሱን የመሰብሰብ እና የማስተላለፍ ኃላፊነት ቢኖረውም፤ የትራንስፖርት አቅራቢዎች ዓመታዊ የሽያጭ መጠን ለቫት ምዝገባ የተቀመጠውን ገደብ የሚያሟሉ ከሆነ ለቫት መመዝገብ አለባቸው።
· ከፕላትፎርም ውጪ የሚሰጡ አገልግሎቶች፡ አሽከርካሪዎች መተግበሪያዎችን (ፕላትፎርምን) ሳይጠቀሙ በቀጥታ ለሚሰጡት ለእያንዳንዱ የትራንስፖርት አገልግሎት ራሳቸው ቫት የመሰብሰብ እና ደረሰኝ የመስጠት ግዴታ አለባቸው ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ቲክቶክ፡-https://www.tiktok.com/@mto2education
ኢሜል፡- [email protected]
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2
❤9
20 · 3.2K · File
በገቢ_ግብር_አዋጅ_ማሻሻያ_ላይ_የገንዘብ_ሚኒስቴር_የሰጠው_ማብራሪያ_.pdf · 4.5 MB · click to show
29 · 2.8K · በገቢ_ግብር_አዋጅ_ማሻሻያ_ላይ_የገንዘብ_ሚኒስቴር_የሰጠው_ማብራሪያ_.pdf · 4.5 MB · click to show
Photo
Photo
Photo
Photo
Photo
የክፍል አንድ ተከታታይ የሞጁለር ስልጠና ለ40ኛ ዙር ሰልጣኞች መሰጠት ተጀመረ
(ጥቅምት 10 ቀን 2019 ዓ.ም፤በመካከለኛ ግብር ከፋዮች ቁጥር 2 ቅርንጫፍ ጽ/ቤት)
**********************************
በታክስ ሕጎች፣ ደንቦች እና መመሪያዎች ላይ የሚያተኩረውና ለግብር ከፋዮች በመደበኛነት የሚሰጠው የሞጁለር ስልጠና ለ40ኛ ዙር ሰልጣኞች መሰጠት ተጀመረ።
የስልጠናው የግብር ከፋዮችን የታክስ ህግ ግንዛቤ በማሳደግ የሕግ ተገዢነትን ማጎልበት፤ ሰልጣኞች መብትና ግዴታዎቻቸውን እንዲያውቁ እንዲሁም በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱና በግብር ከፋዮች መካከል ያለውን ቅንጅታዊ አሰራር ማጠናከር ነው።
የታክስ አጣጣል መሠረቶች እና የታክስ ሥርዓት ዓይነቶች ፤ ከመቀጠር የሚገኝ ገቢ ግብር እና የታክስ ምጣኔ፤ ከመቀጠር የሚገኙ የዓይነት ጥቅሞች ፤ከታክስ ነፃ የሆኑ እና በገደብ ነፃ የተደረጉ ገቢዎች ፤የወጪ መጋራት አከፋፈል ሥርዓት የሚሉት በስልጠናው ሰፊ ማብራሪያ ከተሰጠባቸው ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች መካከል ይገኙበታል::
በስልጠናው ወቅት ተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎችን ያነሱ ሲሆን፣ ለቀረቡት ጥያቄዎችም በቂ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል። ስልጠናውን የሰጡት አቶ አወቀ ግዛው የታክስ ከፋዮች ትምህርት ዋና መሪ ባለሙያ ናቸው።
ግብር÷ለሀገር ክብር!
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ቴሌግራም፦ https://t.me/mormto2
ፌስቡክ፡- https://web.facebook.com/info.mto2/
ቲክቶክ፡-https://www.tiktok.com/@mto2education
ኢሜል፡- [email protected]
ዩትዩብ፡- https://www.youtube.com/@ministryofRevenues-MTO2
❤2
5 · 2.4K ·