ጠያቂ:- የሙነወር ልጅ (ኢብኑ ሙነወር) ከትክክለኛው መንሀጀ'ሰለፍ የወጣበትን ነጥብ በዝርዝር ብትጠቅሱልን?
🔶 ክፍል ②
መልስ:- ከሸይኽ ዶ/ር ሑሰይን ቢን ሙሀመድ አስ-ሲልጢ (ሀፊዘሁላህ)
ክፍል ① ለማግኘት ⤵️
https://t.me/IbnShifa/6004
ዐረቢኛውን ለማንበብ ⤵️
https://t.me/IbnShifa/6002
ከክፍል አንድ የቀጠለው ፅሁፍ እነሆ…
3ኛ, ከዚያም የገባበትን የተምይዕ መንሀጅ ሊያጠናክርበትና ለእራሱ ለመከላከል ብሎ በጀርህና ተዕዲል ዙሪያ አዳዲስ የሆኑ የእነ ሀለቢንና የአቢል ሀሰን አል'መእሪቢይን መርሆዎችን ማሰራጨት ጀመረ።
4ኛ, በተለያዩ ሙሃዶራዎቹም ጀርህና ተዕዲል የኢጅቲሃድ ነጥብ እንደሆነ፣ ማንም ማንንም ሊያስገድድበት የሚችል ነጥብ እንዳልሆነ አስረግጦ ተናግሯል፣ ይህን ያደረገውም በመርከዝ ኢብኑ መስዑድ ሰዎች ላይ ግልፅና ትክክለኛ የሆነውን የሰለፊይ አቋም ግልፅ እንዲያደርግ በጠየቁት የሱንና መሻይኾች ላይ ምላሽ ለመስጠት ብሎ ነው።
5ኛ, ከንግግሮቹም:- አገሌ የሚባል ዓሊም አገሌን ሙብተዲእ ብሎት ሌላኛው ዓሊም ደግሞ ሙብተዲዕ አላለውም፣ ስለዚህ ያላለውን ዓሊም ሙብተዲዕ ብላችሁ ታስጠጉታላችሁን? በማለት በተብዲዕ ላይ የጋራ ስምምነት ግድ እንደሆነ አስመስሎ ልክ እንደ ሀለቢይ ይናገራል፣ በዚህ የሀለቢይ ንግግር ደግሞ የሱንና ሊቃውንት የተሳሳተ በመሆኑ ላይ ምላሽ ሰጥተውበታል።
6ኛ, የሙነወር ልጅ በመልክተኛው ﷺ ላይ ኸዋሪጆችን ጥፋታቸውን ከመናገራቸውም ጋር አወድሰዋል በማለት መዋሸቱ ነው፣ ይህም አዲስ ፈጠራ የሆነውን ከቢድዐህ ባለቤቶች ለመከላከል ብሎ የሙዋዘነህ መርህ ለማስቀመጥ የሄደበት ርቀት ነው። የአላህ መልክተኛ ﷺ ኸዋሪጆችን "ከዲን ሾልከው ይወጣሉ…" "የጀሀነም ውሾች ናቸው…" በማለት ተናግሯቸው እያለ እንዲህ በድፍረት መዋሸቱ ልቡ እጅጉን ለተምይዕ ፊክራ የተመቻቸና ብዥታዎቹን ከልቡ የጠጣቸው እንደሆነ ያሳያል።
7ኛ, ሸይኽ ረቢዕ (ረሂመሁላህ) አሻዒራዎችን አወድሷል በማለትም በሸይኽ ረቢዕ ላይ ዋሽቷል፣ ይህን ውሸቱንም አጋልጠናል።
8ኛ, በኢማሙል አልባኒይ (ረሂመሁላህ) ላይም ኢኽዋን የሆነውን ሰይድ ሳቢቅን "ፊቅህ አስ-ሱነህ" ኪታቡን ተዕሊቅ ባደረገበት ወቅት ላይ አወድሶታል በማለት ዋሽቷል። በመሰረቱ ኢማሙል አልባኒይ ኪታቡን ራሱ ሶሂህና ዶዒፉን እንዲለዩ፣ የተለያዩ ሸሪዓን የሚጥሱ አስተሳሰቦችን እንዲያርሙ ተጠይቀው ነው ያረሙት።
9ኛ, በታላቁ ዓሊም በሸይኽ ሙሀመድ ዐሊ ኣደም አል ኢትዮጲ ላይ (ረሂመሁላህ) ከኢኽዋኑ ቀርዷዊ ኪታብ ላይ አንስተዋል በማለትም ዋሽቷል።
10ኛ, ልክ እንደ ኢኽዋኑል ሙስሊሚን፣ ሱሩሪዮችና ሂዝቢዮች ሰለፊዮችን መዳኺላ በማለት ወርፏል።
11ኛ, ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሓዲል መድኸሊ (ሀፊዘሁላህ) ከዑምራ በኋላ ሸይኽ ረቢዕን የማይዘይር ሰለፊይነቱ ያጠራጥራል በማለቱ ተችቷል።
12ኛ, ከአህሉል ቢድዐህ ጋር ተባብሮ መስራት ይፈቀዳል ብሎ መናገሩና ኢትዮጵያ ውስጥም ሙስሊሞች ከመጅሊስ ጋር ይተባበራሉ ብሎ በመናገር "አላህን በመፍራትና በመልካም ነገር ላይ ተባበሩ" የሚለውን የቁርኣን አንቀፅ ከፍጡራን ሁሉ መተባበር ማለት ነው ብሎ አዙሮ ተርጉሟል።
13ኛ, የሙነወር ልጅ በከንቱ የተለያዩ ኺላፋቶችን በማውሳት የተሞላ ሰው ነው፣ ሁሌም ሸይኽ በክር አቡ ዘይድ ከሰይድ ቁጥብ ተከላክሏል፣ ሸይኽ ረቢዕ ደግሞ ሰይድ ቁጥብን ሙብተዲዕ ብለውታል በክር አቡ ዘይድ ወደ ሰይድ ቁጥብ ታስጠጉታላችሁ? ይህ ሰው (ኢብኑ ሙነወር) ሰለፊያን ያልተረዳ መሀይም ነው፣ ይህቺ አካሄድ ለመርከዙ ሰዎች ለመከላከል የሱፊይነትና ሂዝ