Web appOpen in Telegram
Ммυѕтєfα иσтєѕ📝

мυѕтєfα иσтєѕ📝

@mustefa_Notes · channel · indexed since 2026-08-25
1 200subscribers
459average post reach
38.2%ER — reach to subscribers
22posts in 30 days
мυѕтєfα иσтєѕ📝
ቆይ የዚ ቻናል ሰዎች የት ሂዳቹ ነው እሄንን ያክል ቻናሉ የደከመው እስቲ ያላቹ እጃቹ አውጡ🖐 ወይም መኖራቹ በሆነ ነገር አሳውቁኝ
1 · 840 ·
М
мυѕтєfα иσтєѕ📝
ከሰሃቦችን ጋር እንተዋወቅ በሚል እርዕስ ተከታታይ ትምህርቶች እጀምራለን በየ ቀኑ ማታ 3 ሰዓት ላይ
754 ·
М
мυѕтєfα иσтєѕ📝
Replyከሰሃቦችን ጋር እንተዋወቅ በሚል እርዕስ ተከታታይ ትምህርቶች እጀምራለን በየ ቀኑ ማታ 3 ሰዓት ላይ
ከሰሃቦች ጋር እንተዋወቅ ክፍል 1 ▪️የረሱል (ﷺ) ቅርብ ጓደኛ ነበር። ▪️ከወንዶች መጀመሪያ በረሱል (ﷺ) ያመነና እስልምናን የተቀበለው ነው። ▪️ለእስልምና ሲል ንብረቱን በሙሉ አውጥቷል። ▪️በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው። ▪️ልክ ረሱል (ﷺ) በሞቱ እለት ኺላፋውን የተረከበውና የመጀመሪያው ኸሊፋ ነው። ▪️የተለያዩ ጦርነቶች አድርጓል፣ ሻምና ዒራቅን ከፍቷል፣ የዐረብ ግዛትን ባጠቃላይ ኢስላማዊ መንግስት ያደረጋትም እርሱ ነበር። ▪️ኺላፋው ላይ 2 አመት ከቆየ በኋላ ረሱል (ﷺ) በሞቱበት እድሜ/63 ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ … ➡️ትክክለኛ ስሙ አብደላህ ኢብኑ ዑሥማን (አቢ ቁሃፋህ ይባላል። ነገር ግን አቡበክር አሲዲቅ ተብሎ ይታወቃል፣ ምክኒያቱ ደግሞ የተለያዩ ንግግሮች አሉ: ከነዛ ውስጥ… ① ከእስልምና ህይወቱ በፊት በጣም እውነተኛ እና ታማኝ በመሆኑ ነበር። አንድ ነገር ከተናገረ ቁረይሾች ምንም ሳይከራከሩት ያምኑት ነበር። ለዛም ነው አሲዲቅ ብለው የሰየሙት። ② ሌላኛው ንግግር ደግሞ ረሱል (ﷺ) ወደ ኢስራእና ሚዕራጅ ሄደው ከተመለሱ በኋላ ሁሉም ውሸታም ሲሏቸው እሱ ብቻ ስላመናቸው አሲዲቅ ተባለ‥ ▪️እናቱ ኡሙል ኸይር ሰልማህ ቢንት ሰኽር ትባላለች። ክፍል 2 ይቀጥላል.... ቻናሉ➥https://t.me/mustefa_Notes ┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒   ይቀጥላል  ከ50 ላይክ ቡሀላ ┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚
6 · 1K ·
М
мυѕтєfα иσтєѕ📝
Replyከሰሃቦች ጋር እንተዋወቅ ክፍል 1 ▪️የረሱል (ﷺ) ቅርብ ጓደኛ ነበር። ▪️ከወንዶች መጀመሪያ በረሱል (ﷺ) ያመነና እስልምናን የተቀበለው ነው። ▪️ለእስልምና ሲል ንብረቱን በሙሉ አውጥቷል። ▪️በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው። ▪️ልክ ረሱል (ﷺ) በሞቱ እለት ኺላፋውን የተረከበውና የመጀመሪያው ኸሊፋ ነው። ▪️የተለያዩ ጦርነቶች አድርጓል፣ ሻምና ዒራቅን ከፍቷል፣ የዐረብ ግዛትን ባጠቃላይ ኢስላማዊ መንግስት ያደረጋትም እርሱ ነበር። ▪️ኺላፋው
ከሰሃቦች ጋር እንተዋወቅ ክፍል 2 ▪️ከረሱል ﷺ ትላልቅ ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው። ▪️ሁለተኛው ኸሊፋ ነው። ▪️አሚሩል ሙእሚኒን በመባል ይታወቃል። ▪️በእስልምና ታሪክ ውስጥ በጣም ታዋቂ ከሚባሉ መሪዎች እንዲሁም በጣም ተፅኖ ፈጣሪው ነው። ▪️ከአዋቂ ሰሃቦች እና ተሰናቂ ነበር ▪️የሂጅሪን አቆጣጠር ያመጣው እሱ ነበር። ▪️በጀነት ከተበሰሩ 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው። ▪️በኺላፋው ዘመን እስልምና በጣም አድጎ ነበር ዒራቅ፣ ግብፅ፣ ሊቢያ፣ ሻም፣ ፐርሺያ፣ ኹራሳን፣ ሳጅስታንና የተለያዩ ሀገራቶች ድረስ ኢስላማዊ መንግስትን አዳርሶ ነበር። ▪️በ3ተኛ ደረጃ ቅዱስ የሆነችዋን ቁድስን (ፍሊስጤምን) ለመጀመሪያ ጊዜ የከፈታትና ኢስላማዊ ህግ ስር ያደረጋት እሱ ነበር። ▪️በኺላፋው ላይ 10 አመት ከቆየ በኋላ በአቡ ሉእሉአህ ፈይሩዝ አልፋሪሲ ሰላት ላይ ሆኖ 6 ቦታ ተወግቶ በሸሂድነት በረሱል ﷺ እና አቡበክር (ረ.ዐ) እድሜ ከዚህ ዓለም በሞት  ተለየ… ➡️ትክክለኛ ስሙ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ኢብኑ ኑፈይል ይባላል፣ ነገር ግን ዑመር አልፋሩቅ በመባል ይታወቃል። ምክኒያቱ ደግሞ እንደሚከተለው ይሆናል‥ ▪️ከእለታት አንድ ቀን ከፍ ከፍ እያለ ሰይፉን እየመዘዘ ረሱልን ﷺ ለመግደል ፈልጎ እየመጣ እያለ አንዱ ሰው አስቆመውና ሚስቱና እህቱ የአባቶቻቸውን ሀይማኖት ትተው እስልምናን እንደተቀበሉ ይነግረዋል። ልክ እንደሰማ በንዴትና በፍጥነት ወደ ቤት ሄደ በሩንም በርግዶ ከፈተባቸው ኸባብ ኢብኑል አረት (ረ,ዐ) ቁጭ ብሎ ቁርአን እያስቀራቸው አየ፣ ሊመታቸውና ሊበረታባቸው ፈለገ ድንገት ከመሀላቸው አንዱ ናና ትንሽ ቁርአንን አድምጥ ብሎ ጋበዘው፣ ልክ ሲሰማ ልቡ ውስጥ የእስልምናና የቁርአን ፍቅር ገባ፣ ከዛ ለእህቱ ባለቤት የረሱል ﷺ ቦታን ይጠይቅ ጀመረ፣ ከዛ ዳሩል አርቀም ሄዶ በሩን አንኳኳ፣ ረሱል ﷺ በሩን ከፈቱለት ቀሚሱን እየሳበ ከመሬት እያነሳ ነቢዩ ፊት ሸሃዳ ያዘ፣ ሙስሊሞች ደስ ብሏቸው አላሁ አክበር ማለትን ይደጋግማሉ‥ ➡️የዑመር መስለም ለሙስሊሞች በጣም ትልቅ ድል ነበር ከሰሃቦች እንዱ እንዲህ በማለት ገልፆ ነበር 👉ዑመር ወደ እስልምና ከገባ ጀምሮ አሸናፊዎች ከመሆን አልተወገድንም፣ ሙሰሊሞች ሰላታቸውን ግልፅ አውጥተው ያለምንም ፍራቻና ስጋት ካፊሮች ፊት ከዕባው ጋር ሄደው መስገድ ጀመሩ። ▪️የዛን ቀን ረሱል ﷺ ፋሩቅ ብለው ሰየሙት፣ ሀቅና ባጢልን ስለ ለየ ይህን ስያሜ አገኝ። ▪️ሙሰሊሞች ደዕዋውን ተደብቀው በፍራቻ ያደርጉት የነበረው ከመስለሙ በኋላ ፊትለፊት አውጥተው ደዕዋ ማድረግ ጀመሩ። ▪️እናቱ ሀንተመህ ቢንት ሂሻም ኢብኑ ሙጊራህ ትባላለች። ክፍል 3 ይቀጥላል.... ቻናሉ➥https://t.me/mustefa_Notes ┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒   ይቀጥላል  ከ50 ላይክ ቡሀላ ┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚
4 · 794 ·
М
мυѕтєfα иσтєѕ📝
Replyከሰሃቦች ጋር እንተዋወቅ ክፍል 2 ▪️ከረሱል ﷺ ትላልቅ ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው። ▪️ሁለተኛው ኸሊፋ ነው። ▪️አሚሩል ሙእሚኒን በመባል ይታወቃል። ▪️በእስልምና ታሪክ ውስጥ በጣም ታዋቂ ከሚባሉ መሪዎች እንዲሁም በጣም ተፅኖ ፈጣሪው ነው። ▪️ከአዋቂ ሰሃቦች እና ተሰናቂ ነበር ▪️የሂጅሪን አቆጣጠር ያመጣው እሱ ነበር። ▪️በጀነት ከተበሰሩ 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው። ▪️በኺላፋው ዘመን እስልምና በጣም አድጎ ነበር ዒራቅ፣ ግብፅ፣ ሊቢያ፣ ሻም፣ ፐርሺያ፣ ኹ
ከሰሃቦች ጋር እንተዋወቅ ክፍል 3 ▪️መጀመሪያ ከሰለሙት ውስጥ ነው። ▪️ከአቡበክርና ከዑመር (ረ.ዐ) ቀጥሎ 3ተኛው ኸሊፋ ነው። ▪️መላኢኮች የሚያፍሩት ነው። ▪️በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው። ▪️መጀመሪያ ወደ ሀበሻ የተሰደደው እሱ ነበር። ▪️በኺላፋው ዘመን ቁርአንን በሙስሀፍ የሰበሰበው እሱ ነው። ▪️አርማኒያ፣ ኹራሳን፣ ኩርማን፣ አፍሪካንና የተለያዩ ሀገራትን ከፈቶ ኢስላማዊ መንግስትን አስፋፍቷል። ▪️መስጂደል ሀረምንና መስጂደ ነበዊን አስፋፍቷል። ▪️ለመጀመሪያ ጊዜ ኢስላመዊ የባህር ሀይልን አቋቋመዋል። ▪️በሁለተኛው አጋማሽ ኺላፋው ወደ 12 አመት ከቆየ በኋላ ፊትና ብቅ አለች፣ በዛ ምክኒያት በሙናፊቆች ቁርአን እየቀራ ሸሂድ ሆነ፣ ተወግቶ ደሙ በአንዲት አንቀፅ ላይ ፈሰሰ «እነሱንም አላህ ይበቃሃል፣ እርሱም ሰሚው አዋቂው ነው።» [በቀራህ 137] ➡️ትክክለኛ ስሙ ዑስማን ኢብኑ ዐፋን አል ኡመዊ ይባላል። ዚን ኑረይን ተብሎም ይታወቃል። 👉ዚን ኑረይን የተባለበት ምክኒያት ደግሞ ๏ የረሱል (ﷺ) 2 ሴት ልጆችን ስላገባ ነው። ሩቀያን አግብቶ ከሞተች በኋላ ዳግም ረሱል ኡሙ ኩልሱምን ዳሩት፣ እሷም ስትሞት ረሱል (ﷺ) 3ተኛ ልጅ ቢትኖረኝ ዑስማንን እድረው ነበር ብለው ነበር። ▪️ይህን በማስመልከት ዐብደላህ ኢብኑ ዑመር እንዲህ ይላሉ: አጎቴ እንዲህ አሉኝ “ ዑስማን ለምን ዚን ኑረይን እንደተባለ ታውቃለህን? አላውቅም አልኩኝ:  ከአደም ፍጥረት ጀምሮ እስከ እለተ ቂያም ድረስ ዑስማን እንጂ የአንድ ነቢይ 2 ሴት ልጅ አግብቶ ማንም አያውቅም። ለዛም ነው ዚን ኑረይን የተባለው ” አለኝ። ▪️እናቱ አርዋ ቢንት ኩረይዝ ኢብኑ ረቢዐህ ትባላለች። ክፍል 4 ይቀጥላል.... ቻናሉ➥https://t.me/mustefa_Notes ┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒   ይቀጥላል  ከ50 ላይክ ቡሀላ ┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚
3 · 644 ·
М
мυѕтєfα иσтєѕ📝
Replyከሰሃቦች ጋር እንተዋወቅ ክፍል 3 ▪️መጀመሪያ ከሰለሙት ውስጥ ነው። ▪️ከአቡበክርና ከዑመር (ረ.ዐ) ቀጥሎ 3ተኛው ኸሊፋ ነው። ▪️መላኢኮች የሚያፍሩት ነው። ▪️በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው። ▪️መጀመሪያ ወደ ሀበሻ የተሰደደው እሱ ነበር። ▪️በኺላፋው ዘመን ቁርአንን በሙስሀፍ የሰበሰበው እሱ ነው። ▪️አርማኒያ፣ ኹራሳን፣ ኩርማን፣ አፍሪካንና የተለያዩ ሀገራትን ከፈቶ ኢስላማዊ መንግስትን አስፋፍቷል። ▪️መስጂደል ሀረምንና መስጂደ ነበዊን
ከሰሃቦች ጋር እንተዋወቅ ክፍል 4 ▪️ከልጆች መጀመሪያ በረሱል ﷺ ያመነና የተቀበለው ነው። 10 አመት ነበር እድሜው ሲሰልም። ▪️የረሱል ﷺ አጎት ልጅና አማችም ነው። ▪️ከዑስማን (ረ.ዐ) በኋላ 4ተኛው ኸሊፋ ነው። ▪️በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው። ▪️በኢስላም የመጀመሪያው ፊዳእ (መስዋእት) ነው። ▪️ወህይን ወይም ቁርአንን ከሚፅፉ ሰሃቦች (ከነቢዩ ፃሃፊዎች) አንዱ ነበር። ▪️የረሱል ﷺ አምባሳደርም ነበር። ▪️ልክ ዑስማን (ረ.ዐ) እንደተገደለ ኺላፋውን ተረክቦ 6 አመት ከ3 ወራት ከመራ በኋላ ፈጅር ሰላት እያሰገደ አብዱረህማን ኢብኑ ሙልጂም በሚባል የኸዋሪጆች ራስ የሆነው ከኋላው መጣና በተመረዘ ሰይፍ ራሱ ላይ መታው፤ ልክ ከተመታ በኋላ ወደ ቤቱ ተወሰደ፣ የመታኝን ከምግቤ አብሉት አጠጡትም ከሞትኩም፣ እንደገደለኝ ግደሉት ከተርፍኩ ደግሞ ውሳኔዬ እወስድበታለሁ አለ። ከዛ ብዙ ሀኪሞች መጡ ሊያተርፉት አልቻሉም ከ3 ቀን በኋላ ሞተ ➡️ትክክለኛ ስሙ ዐሊይ ኢብኑ አቡጣሊብ ኢብኑ አብዱልሙጠሊብ ነው። ብዙ ስያሜዎች አሉት ከነዛ ውስጥ 🔹አቡ ቱራብ ይባላል፣ የተባለበት ምክኒያት ከእለታት አንድ ቀን መሬት ካይ ተኝቶ ረሱል ﷺ መጡበትና እንዲህም አሉት “ከስሞችህ የሚገቡህ አቡ ቱራብ ነው አንተ አቡ ቱራብ ነህ” አሉት። 🔹ሀይደረህም ይባላል፣ ምክኒያቱ ደግሞ ሲወለድ እናትየው ሀይደራህ ብላ መሰየም ፈልጋ ነበር። ነገር ግን አባትየው እንቢ ብሎ ዐሊይ አለው ሀይደረህ ማለት ከአንበሳ ስሞች አንዱ ነው። 🔹አልከራር ተብሎም ይታወቅ ነበር። ስያሜውን ረሱል ﷺ ነበር የሰየሙት እዛው ኸይበር ዘመቻ ላይ ሙስሊሞች በተደጋጋሚ መክፈት ያቃታቸውን ምሽግ ረሱል (ﷺ) ዐሊይ (ረ.ዐ) እንዲከፍተው ባንዲራውን ሰጠው ሲሰጠውም እንዲህ ብሎ ነበር የሰጠው: “ባንዲራውን አላህንና መልእክተኛውን ለሚወድ፣ አላህና መልእክተኛውም ለሚወዱት ሰው እሰጣለሁ፣ ወደፊት የሚሄድ እንጂ የሚሸሽ አይደለም " ከራር ማለት ወደ ኋላ የማይል የማይሸሽ ማለት ነው ... ▪️የእናቱ ስም ፋጢማህ ቢንቱ አሰድ አልሃሺሚየህ ትባላለች.... ክፍል 5 ይቀጥላል.... ቻናሉ➥https://t.me/mustefa_Notes ┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒   ይቀጥላል  ከ50 ላይክ ቡሀላ ┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚
2 · 635 ·
М
мυѕтєfα иσтєѕ📝
Replyከሰሃቦች ጋር እንተዋወቅ ክፍል 4 ▪️ከልጆች መጀመሪያ በረሱል ﷺ ያመነና የተቀበለው ነው። 10 አመት ነበር እድሜው ሲሰልም። ▪️የረሱል ﷺ አጎት ልጅና አማችም ነው። ▪️ከዑስማን (ረ.ዐ) በኋላ 4ተኛው ኸሊፋ ነው። ▪️በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው። ▪️በኢስላም የመጀመሪያው ፊዳእ (መስዋእት) ነው። ▪️ወህይን ወይም ቁርአንን ከሚፅፉ ሰሃቦች (ከነቢዩ ፃሃፊዎች) አንዱ ነበር። ▪️የረሱል ﷺ አምባሳደርም ነበር። ▪️ልክ ዑስማን (ረ.ዐ) እን
ከሰሃቦች ጋር እንተዋወቅ ክፍል 5 ▪️መጀመሪያ ከሰለሙት ውስጥ ነው 3ተኛ ነበር የሚሉ ዘገባዎች አሉ። ▪️በጀነት ከተበሰሩት 10 ሰሃቦች ውስጥ አንዱ ነው። ▪️በጣም ለጋሽና ቸር የሆነ ሰሃቢይ ነበር። ▪️እድሜው ከ60 በላይ ከሆነ በኋላ መርዋን ኢብኑል ሀከም የሚባል ሰው በቀስት ገደለው። ➡️ትክክለኛ ስሙ ጠልሃህ ኢብኑ ዑበይዲላህ ኢብኑ ዑስማን ይባላል። ብዙ ስያሜዎች አሉት ከነዛ ውስጥ  ๏ በህይወት ያለው ሸሂድ ይባላል። ምክኒያቱ ደግሞ እንደሚከተለው ይሆናል ⇨ኡሁድ ዘመቻ ላይ ሙስሊሞች ሲሸነፉ ከረሱል ﷺ ጋር 11 ሰው እንጂ አልቀሩም ነበር። ከነዚህም መካከል አንዱ ጠልሃህ ነበር። የዛን ረሱል ﷺ እነዚህን 11ዱን ወደ ተራራ ይዟቸው እየወጡ ነበር የተወሰኑ ሙሽሪኮችም ለመግደል እየተከተሏቸው ነበር። ከዛም ረሱል ﷺ "ማነው እነዚህን የሚመልስልን ከኔም ጋር በጀነት ውስጥ ጓደኛዬ የሚሆን" ብለው ጠየቁ: ጠልሁ ከሁሉም በፊት እኔ አለ፣ የዚህን ጊዜ ረሱል ﷺ አይ ቆይ አንተ ቦታህን አሉት፣ ከአንሳሮች አንዱ እኔ ያ ረሱለላህ አለ፣ እሺ ብለው ፈቀዱለት። ያሰው እስኪገደል ድረስ ተፋለማቸው አሁን ወደ ተራራው እየወጡ ሙሽሪኮች መከተላቸውን አላቆሙም" አንድ ሰው ለነዚህ" አሉም፣ ረሱል ﷺ አሁንም ጠልሃህ ከሁሉም በፊት እኔ አለ፣ አይ ቆይ አንተ ቦታህን አሉት ከአንሳሮች አንዱ እኔ ያ ረሱለላህ አለ፣ ተፈቀደለት፣ ከዛ እስኪገደል ድረስ ተፋለማቸው እያሉ እያሉ ከረሱል ﷺ ጋር ጠልሃህ ብቻ ቀረ። ከዛም እንዲጋደል ፈቀዱለት፣ ለጠልሃህ እየተፋለማቸው ከረሱል ﷺ እየተከላከለ ወደ ተራራውም ይዟቸው እየወጣ ሙሽሪኮችን እስኪመልሳቸው ድረስ ተፋለማቸው‥ ▪️አቡበክር አሲዲቅ እንዲህ ይላሉ እኔና ዑበይደህ የዛን ቀን ከረሱል ﷺ ርቀን ነበርና መጥተን ልንወስዳቸው ስንል እኔን ተውኝና ሂዱ ለጠልሃህ አሉን። ጠልሃህ ጋር ስንሄድ ደሙ እየፈሰሰ ነው ከ70 በላይ የሰይፍ ወይም የጦር ወይ ደግሞ የቀስት ምት ነበረበት። ነዳፉም ተቆርጦ እራሱን ስቶ ጉድጓድ ውስጥ ወድቆ ነበር ‥ ከዛ አንዲት አንቀፅ ወረደች ረሱልም ሰሃቦቹ ፊት ቀሯት "ከአማኞቹ በእርሱ ላይ ለአላህ ቃል ኪዳን የገቡበትን በእውነት የፈጸሙ ወንዶች አልሉ ከነርሱም ስለቱን የፈጸመ (ለሃይማኖቱ የተገደለ) አለ። ከነርሱም ገና የሚጠባበቅ አለ (የገቡበትን ቃል) መለወጥንም አልለወጡም። "[አህዛብ 23] ▪️ከቀሯትም በኋላም ረሱል ﷺ ጣታቸውን ወደ ጠልሃህ በማመላከት እንዲህም አሉ "ሸሂድ ሆኖ ምድር ላይ የሚሄድን ሰው ማየት የፈለገ ጠልሃህን ይመልከት" ๏ ጠልሀተል ኸይርና ጠልሀተል ጁድም ይባል ነበር። ምክኒያቱ ደግሞ በጣም ሀብታም ነጋዴ ነበር። ▪️አንድ ጊዜ በጣም ብዙ ብር አገኘ 700 ሺህ ዲርሃም ነበር የዛን ቀን ለሊት በጣም አዝኖ ነበር ባለቤቱ ኡሙ ኩልሱም አቡበክር ገባችበትና አባ ሙሀምድ ሆይ ምን ሆነህ ነው? አለችው። ▪️አንድ ሰው በጌታው ምን አስቦ ነው ይህ ብር ቤቱ እያለ የሚተኛው? አላት ከሱ ምን ይጨንቅሃል ስታነጋ አከፋፍለው አለችው። አላህ ይዘንልሽ የተወፈቅሽና የተወፈቀ ልጅ ነሽ አላት። ከዛ ሲነጋ ለአንሳሮች እና ለሙሃጂሮች አከፋፈለው። ጠልሀተል ኸይር እና ጁድም ተባለ። ⇨የእናቱ ስም ሰዕበህ ቢንት ሀድረሚይ ኢብኑ ዐብደህ ትባላለች ክፍል 6 ይቀጥላል.... ቻናሉ➥https://t.me/mustefa_Notes ┎┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┒   ይቀጥላል  ከ50 ላይክ ቡሀላ ┖┈┈┈┈┈┈┈୨♡୧┈┈┈┈┈┈┈┚
1 · 653 ·
М
М
мυѕтєfα иσтєѕ📝
Photo
click to show
ይህ ሶዬ ግን😭😂
523 ·
М
мυѕтєfα иσтєѕ📝
ፈገግታ።🙂 አንዱ ስለ ጀነት ኒዕማ ስለ ሑረልዐይን ይነገረዋል አሉ “ውበታቸው የጉድ ነው አንዷ ስትስምህ 70 አመት ፌንት ታረጋለህ” 🫠ይለዋል “አሁንም ብትስመኝስ?”🥹 ይለዋል “አሁንም 70 አመት ፌንት” 🫠 “እዛው ብትደግመኝስ” 😍 “እዛው 70 አመት ትወድቃለህ” 🫠 “210 አመት ፌንት😟? ታድያ ምኑን ጀነት ገባሁ😕?” አለ አሉ 🤲😁
8 · 518 ·
мυѕтєfα иσтєѕ📝
አዎ ቆንጆ ነች ነገር ግን ከዛ ፈገግታዋ ጀርባ ያለውን ሀዘን አላህ ብቻ ነው ሚያውቀው
1 · 459 ·
М
ትምህርት በጣም ከመናፈቄ የተነሳ ዩኒፎርሜን ለብሼ መተኛት ጀምሪያለው ይለኛል እንዴ በ28 አመቱ 7ተኛ ክፍል እየተማረ                  #ይሄ_ሹገር_Student 😂
429 ·
М
мυѕтєfα иσтєѕ📝
Photo
click to show
ፈገግታ post😁 እስልምና አራት ፈቅዶልህ አንዷም የለለችህ አንተ😁 ምደረ ላጤ 😁😁
2 · 442 ·
М
мυѕтєfα иσтєѕ📝
የፖስቴ ላይክ ማነስ ከነዳጁ ጋር ይያያዛል እንዴ ? የኔን ላይክ ቆፍራቹ ነው እንዴ የምታወጡት😒😁
413 ·
М
ሰዎች:-ይላሉ እስኪ ወደ ወንጀሎችህ ተመልከት 😣 አላህም ይልሀል እስኪ እዝነቴን ተመልከት🫶🏼🥰
350 ·
мυѕтєfα иσтєѕ📝
ቀላል ሆነው ግን በጣም የምያሰለቹ ስራዎች የእንጀራ ላስቲክ ማጠብ ሽሮ ፣በርበሬ መቀነስ ተበልቶ ሲያበቃ እቃ ማነሳሳት የጫማ ክር ማስገባት ልብስ ማጠፍ 🤮
3 · 324 ·
. ለፈገግታ አንድ ወንድ ሁለቱን ባለቤቶቹን #ሳራንና_ሰሚራን አገባ፤ በሁለቱም መካከል በነገሮች ሁሉ ፍጹም ዕኩል አድራጊ ነበር። አላህ ቀድሮት... ሁለቱ ሚስቶቹ በአንድ ቀን ሞቱ። የባለቤቱ ፍትሐዊነት ታላቅነትም፦ « በአንድ ጊዜ እንዲታጠቡ» ጠየቀ። በዚያው ሰዓትም ሁለት አጣቢ ሴቶችን አስመጣ። ለቀብር ሊያወጧቸው በፈለገ ጊዜ ግን፦ መውጫው ያለው አንድ በር ብቻ ነበር! በአንድ ጊዜ ሊያወጧቸው ስለፈለገ ሌላ በር እንዲሠራ (እንዲገነባ) አዘዘ። ▢ አናፂውም መጥቶ ሥራውን አጠናቀቀ፤ በዚሁም መሠረት በአንድ ጊዜ ተቀበሩ፤ ጉዳዩም ተጠናቀቀ፤ አላህም ይህንን ፍትሕ እንዲያደርግ ስለገጠመው አመሰገነው። በአንደኛዋ ሌሊትም፦ ባለቤቱን ሰሚራን በሕልሙ ያያታል፤ እሷም እንዲህ አለችው፦ «እኔ በአንተ  ቅር ብሎኛል (አዝኜብሃለሁ)፤ ፈጽሞም ይቅር አልልህም»💔 እሱም፦ «ለምን በእኔ አዘንሽ ሰሚራ?» አላት። እሷም፦ «አንተ በደለኛ! ሳራን በአዲሱ በር አስወጣሃት፣ እኔን ግን ከቀድሞው (ከአሮጌው) በር! መቼም ይቅር አልልህም» አለችው ይባላል።😭
4 · 366 ·
М
ገራሚ እና አክቲብ የሆነ ኢስላሚክ ቻናል መግዛት የምፈልጉ በዚ ➥ @comment1_0 አናግሩኝ
356 ·
мυѕтєfα иσтєѕ📝
ችግርህን በሚዲያ አትልቀቅ ላይክ ያረጉብሃል አላለም 😁
2 · 367 ·
М
ሰዎች ያሰቡልኝን አይነት አወዳደቅ ያልወደኩት አላህን ስለተደገፍኩ ነው❤️‍🩹
2 · 340 ·
М
мυѕтєfα иσтєѕ📝
ትላንትና ሞተው የቀበርናቸው ሰዎች ሁሉም ትላንት እንደሚምቱ አያውቁም ነበር እኔና አናንተም ልክ እንደዚሁ አናውቅም‼
3 · 328 ·
М
мυѕтєfα иσтєѕ📝
💔 ችግሩ የሚጀምረው በጥፊ ማለት የነበረብህን ሰው ሰላም ስትለው ነው ።         ❣️
2 · 177 ·
М
мυѕтєfα иσтєѕ📝
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ሰላም ናችሁ ውድ ቤተሰቦቼ አላህ ዱንያ የሰጣችሁ እና በከባድ ሀጃ ውስጥ ያለን ሰው ማውጣት የምችሉ ውድ የተውሒድ እህት ወድሞቼ ካላችሁ በዚህ ➥@mustefa_1_2 አናግሩኝ
45 ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog · Search · How we count