14 August 2026
15 August 2026
16 August 2026
18 August 2026
19 August 2026
«በሌላዉ ዉድቀት አትሳቅ ጊዜ በአንተ ላይ ምን እንደሚያመጣ አታዉቅምና»
አሊይ ኢብኑ አቢጧሊብ ረ,ዐ
https://t.me/+05iEttbAV91lMWE0
22 August 2026
24 August 2026
25 August 2026
26 August 2026
የሸይኽ ሙሐመድዘይን አደም ደርሶች፦
01- ከሽፉ ሹቡሃት
02- ከሽፉ ኒቃብ
03- ቡሉጉል መራም
04- ሶሒሕ ሙስሊም
05- ሶሒሑል ቡኻሪ
06- ሱነኑ አቢ ዳውድ
07- ሠላሠቱል ኡሱል
08- መሳኢሉል ጃሂሊያ
09- አዱሩሱል ሙሂማ
10- ዐቂደቱ ጦሓዊያ
11- ኡሱሉን ፊ ተፍሲር
12- አረሒቁል መኽቱም
13- ሙልሐቱል ኢዕራብ
14- ሪሳለቱል ዑቡዲያ
15- አልፈዋኪሁል ጀንያ (1)
16- አልፈዋኪሁል ጀንያ (2)
17- ኹላሶቱ ኑሪል የቂን
18- አልአርበዑነ ነወዊያህ
19- አልቀዋዒዱል ሒሳን
20- አሉእሉእ ወልመርጃን
21- አሠባት ዐለል ኢስላም
22- አልፊየቱ ኢብኒ ማሊክ
23- ደዓኢሙ ሚንሃጂ ኑቡዋ
24- ሸርሑ ሱንና ሊል በርበሃሪ
25- አልወጂዝ ፊ ዐቂደቲ ሰለፍ
26- ኡሱሉ ሱንና የኢማም አሕመድ (1)
27- ኡሱሉ ሱንና የኢማም አሕመድ (2)
28- ሙዘኪረቱን ፊ አሕካሚ ሲያም
29- ሪያዱ ሷሊሒን
30- ሙስጦለሑል ሐዲሥ
31- ሙቀዲመቱ ተፍሲር
32- መትኑል አጁሩሚያ
33- ሱነኑ ቲርሚዚ
34- ፈትሑል መጂድ
እንዚህ ዱሩሶች በደንብ ተከታተሉዋቸው
28 August 2026
29 August 2026
30 August 2026
Ссылка
click to show
click to show
በአካባቢያችሁ ስም ዲናችሁን መማማሪያ፣ አንገብጋቢ መልእክቶችን መለዋወጫ፣ መሻይኾችን፣ ደረሶችንና አቅመ ደካማ ወገኖችን ማገዣ፣ ጎበዝ ተማሪዎችን ማበረታቻ፣ ... የቴሌግራም ወይም መሰል መሰባሰቢያ ግሩፕ/ ቻናል ይኑራችሁ።
* ከቻላችሁ የራሳችሁን፣ ካልተቻለ ከሌሎች ምንጮች በመውሰድ ጠቃሚ መልእክቶችን ማሰራጨት፣
* ከማህበራዊ ሚዲያ ባለፈ መሬት ላይ ስራ እንዲኖር እንዳቅማችሁ ሞክሩ።
* አካባቢያችሁ ኢስላማዊ እውቀት የራቀው ከሆነ የትምህርት አሰጣጡ የህብረተሰቡን የግንዛቤ መጠን ያገናዘበ ይሁን። በቅድሚያ መሰረታዊ የእስልምና ክፍሎች ማሳወቅ፣ ከከባባድ ወንጀሎች ማስጠንቀቅ፣ መተዛዘንና መተባበር እንዲኖር መስራት ላይ ማተኮር፣
* በተቻለ መጠን ትምህርታችን ቁርኣን እና ሐዲሥ ላይ ያተኮረ ይሁን። የመሻይኾች ስም በሌሎች አካላት ቀድሞ የጠለሸ ከሆነ ስም እየጠቀስን ከምናስበረግግ የምንፈልገውን መልእክት ቁርኣን እና ሐዲሥ ላይ ተመስርተን ብናስተምር። ካስፈለገ ብዙም ስማቸው ግርታ የማያስነሳ የሆኑ የጥንት ዑለማኦችን ማጣቀስ፣
* ስብስቡ ከህብረተሰቡ አቅም በላይ የሆኑ ቡድናዊ ጉዳዮችን በማቀንቀን መነታረኪያ እንዳይሆን መጠንቀቅ፣
* ቁርኣን ለልጆች የምናስተምርበት መንገድ የተሻለ ጥራት እንዲኖረው መጣር፣
* በደረስነት ላይ የተሰማሩ ተወላጆች ካሉ በምንችለው መልኩ ከጎናቸው መቆም። ሁልጊዜ ኡስታዝ ፈልጉልን ከማለት የራስን ልጅ እንደማብቃት ያለ የተሻለ አማራጭ የለም። ሩቅ የመሰለን ነገር ባጭር ጊዜ ይሳካል። ከጎኑ ስንቆም አደራም እያሸከምነው እንደሆነ ይታወቅ።
* ለአቅመ ደካማ ተማሪዎች የዓመቱ መጀመሪያ ላይ ዩኒፎርም፣ ደብተር፣ ... አስተባብሮ ማቅረብ እና የተሻለ አፈፃፀም ያላቸውን መጨረሻ ላይ በመሸለም ሌሎቹን ማነቃቃት ትልቅ ስራ ነው። ሲታገዝ የነበረ አንድ ተማሪ ተሳክቶለት ቁም ነገር ላይ ቢደርስ አካባቢውን፣ ወገኑን አይረሳም።
* በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ መተጋገዝ ለደዕዋ ስራ በጣም አስፈላጊ ነውና በዚህም ላይ መስራት ይገባል። ረዳት የሌላቸው እናቶችንና አባቶችን ማገዝ፣ ያዘመመ ጎጇቸውን ማቃናት፣ እርሻ ካላቸው አስተባብሮ ማረስ፣ የቲሞችን መርዳት፣ ወዘተ.
* ወጣቱን ከሱስ ለማውጣት ከማስተማር ባሻገር ከዲናቸው እንዳይርቁ አድርጎ አማራጮችን መዘርጋት። ለምሳሌ የእግር ኳስ እና የመረብ ኳስ ማመቻቸት፣ የቴኳንዶና መሰል ስልጠናዎችን ማመቻቸት፣
* በዓመቱ መጨረሻ ላይ የተሰሩ ስራዎችን ለህበረተሰቡ በማቅረብ የተሻለ ትስስርና መነቃቃትን መፍጠር፣
* በተለያዩ አካባቢዎች የተበተኑ ተወላጆችን ማስተባበር። ለስራው እገዛ የሚያደርጉ ከሆነ አፈፃፀሞችን በማሳየት ላይ ማስረጃ የሚሆኑ የፎቶና የቪዲዮ ማስረጃዎችን ለሚመለከታቸው አካላት ማቅረብ የተሻለ መተማመን እንዲኖር፣ ሌሎች አህለል ኸይሮችን ለማሳየት እና ማህበረሰቡን ለማነሳሳት መጠቀም ዑለማኦች የሚፈቅዱት ነው። ለምሳሌ ሸይኽ ኢብኑ ዑሠይሚን፣ ሱለይማን አር-ሩሐይሊይ፣ ወዘተ.
* በማስተባበር ላይ የሚደክሙ አካላትን ሞራላቸው እንዳይቀዛቀዝ ትርጉም ያለው እገዛ ማድረግ፣
* ወሳኝ እገዛ የሚያደርጉ ወገኖችን ማመስገን እና ኢኽላሳቸውን በማይጎዳ መልኩ እውቅና መስጠት፣
* ባጠቃላይ ሂደቱ ላይ አላህን መፍራት፣ ኢኽላስ፣ ሙታበዐህ፣ ስሜትን መቆጣጠር፣ ስክነት፣ ... እንዳይርቀው አጥብቆ መመካከር ይገባል። እንዲህ አይነት ስራ ላይ ንትርክና መለያየት የመከሰት እድሉ ከፍተኛ ነውና አስቀድሞ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።
እነዚህ እና መሰል ስራዎች በያካባቢው ቢሰራባቸው ውጤታቸው ቀላል አይደለም። ድንገት አላህ ያለለት ሊሰራው ይችላል በሚል ነው ማስታወስ የፈለግኩት።
=
የቴሌግራም ቻናል፦
ht
15.7K · 2 September 2026
3 September 2026
4 September 2026