ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
የ

የአቡነ ጎርጎርዮስ ትምህርትና ሥልጠና ማእከል ኦፊሸያል የቴሌግራም ግሩኘ

сообщение · 2026-09-16 07:22 UTC
A
Фотография
click to show
ማኅበረ ቅዱሳን ወደ ሀገር የተመለሱ የብራና መጻሕፍትን ከኢትዮጵያ የቅርስ ባለሥልጣን ተረከበ። መስከረም ፮/፳፻፲፱ ዓ.ም   በትናትናው ዕለት የኢትዮጵያ የቅርስ ባለሥልጣን ከሀገረ አሜሪካ በግለሰብ እጅ የነበሩና የተመለሱ 17 የብራና መጻሕፍን ለ7 ተቋማት የማስረከብ ሥነ ሥርዓት አከናውኗል።   ከተረከቡት ተቋማት መካካል አንዱ ማኅበረ ቅዱሳን ሲሆን የማኅበሩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መምህር ዋሲሁን በላይ 2 መጻሕፍትን ተረክበዋል፡፡   ፕሮፌሰር አበባው አያሌው የባለሥልጣኑ ዳይሬክተር በንግግራቸው የኢትዮጵያ መንግሥት ላለፉት 5 እና 6 ዓመታት ቅርስ የማስመለሱን ሥራ በትኩረት እየሠራበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡   ለዘመናት ቅርሶችን ስናስመልስ ኖረናል ያሉት ዳይሬክተሩ በዚህም በትናትናው ዕለት ቅርሶቹን ለመረከብ የቻላችሁ ተቋማት እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡   የባለሥልጣኑ ምክትል ዳይሬክተር አቶ ኤልያስ ሽኩር በበኩላቸው ላለፉት 7 ዓመታት ቅርሶችን ለማስመለስ በተደረገው ሁሉን አቀፍ ርብርብና ጥረት 67 ቅርሶች ወደ ሀገር መመለሳቸውን አንሥተዋል፡፡   በብራና መጻሕፍቱ ውስጥ የተመዘገቡ ጽሑፎችና ስንኞች የኢትዮጵያን ሥልጣኔ፣ባህልና ታሪክ ለመረዳት የማይተካ ሚና እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡
5.4K ·

All messages on 16 September 2026 · Whole feed · оригинал в Telegram

Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog