English
Open in Telegram
©©ሶፊ

©ሶፊ

@sofiview · group · indexed since 2026-10-17
526members
25writing in 30 days
79messages in 30 days
3 146messages in the index
  1. ©
    ©ሶፊ
    ይሄ ለጥያቄው መልስ አይሆንም 😢
    😁5
Whole thread · 1 reply →
Z
📖 የተቀደደው ማስታወሻ ©ሶፊከመፅሐፍ ቅዱስ የገረመኝ ታሪክ #2 «ባልንጀራዬ ማን ነው?» 30። ኢየሱስም መልሶ እንዲህ አለ፦ «አንድ ሰው ከኢየሩሳሌም ወደ ኢያሪኮ ወረደ፤ በሌቦችም እጅ ወደቀ፤ እነርሱም ገፈፉት ደበደቡትም፣ ሞቶም ከሞላ ጎደል በቁስል ተሰቃይቶ ትተውት ሄዱ። ​31። ድንገትም አንድ ካህን በዚያ መንገድ ወረደ፣ አየውም፣ በባዶ ማዶም አለፈ። ​32። እንዲሁም ደግሞ አንድ ሌዋዊ ወደዚያ ቦታ መጣ፣ መጥቶም አየው፣ በማዶ አለፈ። ​33። ነገር ግን አንድ ሳምራዊ ሲጓዝ ወደ እርሱ መጣ፣
ይህንን ታሪክ በደንብ ለመረዳት ከዚህ ብትጀምር እንዲህ ይላል:- 25 እነሆም፥ አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው ተነሥቶ። መምህር ሆይ፥ የዘላለምን ሕይወት እንድወርስ ምን ላድርግ? አለው። 26 እርሱም በሕግ የተጻፈው ምንድር ነው? እንዴትስ ታነባለህ? አለው። 27 እርሱም መልሶ። ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም ኃይልህም በፍጹም አሳብህም ውደድ፥ ባልንጀራህንም እንደ ራስህ ውደድ አለው። 28 ኢየሱስም። እውነት መለስህ፤ ይህን አድርግ በሕይወትም ትኖራለህ አለው። 29 እርሱ ግን ራሱን ሊያጸድቅ ወድዶ ኢየሱስን። ባልንጀራዬስ ማን ነው? አለው። የሉቃስ ወንጌል 10:25-29 ማለት ሕግ ዐዋቂው(አይሁዳዊ) ማለት ነው እና አይሁዳዊዎችና ሳምራዊያኖች በጣም እርስ በርስ ይጠላላሉ እንዲሁም በቀጭን መንገድ ራሱ ስተላለፉ ከተገናኙ አይሁዳውያንዎች ተመልሰው ልብስ ቀይረው ሻውር ምና ምን ወስደው ይመለሳሉ ለሕግ ስለምጠነቀቁ እና ጌታችን በእነርሱ መሃል ያለው የጥል ግርግዳ ለማፍርስ ሳምራውያንን በጥሩ ሰው አድርጎ አስመሰለው መጨረሻ ላይ ጌታችን «እንግዲህ ከነዚህ ከሶስቱ ለሌቦች እጅ ለወደቀው ሰው ባልንጀራ የሆነው ማነው ከእነዚህ ይመስልሃል? ብሎ አይሁዳዊ(ሕግ አዋቂው) ስጠይቅ እርሱም፦ «ምሕረት ያደረገለት» አለ። ምክንያቱም ጥሩ ያደረገው ሕግ አዋቂው የሚጠላ ሰው ነውና ሳምራውያን ከማለት ይልቅ ምሕረት ያደረገለት ነዉ አለ። ከዚያሳ ሂድ አንተም እንዲሁ አድርግ አለው(አንተም ሂድና ለጠላት ለሳምራዊያን እንደዚህው አድርግ)ስለዚህ ባልንጀራችን ማለት ጠላቶቻችንም ጭምር ነውና ለሁሉም በእኩል ማድረግ ክርስቲያናው ግዴታችን ነው።
❤4
  1. 𝙹
    ከእለታት አንድ ቀን ነፍሴ ተደሰተች ከጌታዬ እግር ስር ይቅርታን አገኘች ሳምራዊ ብሆንም ከሰው የረከስኩኝ ምህረትን አግኝቼ በፍቅሩ ተማረኩኝ ለክብሩ ባይበቃም አልባስጥኑር ሽቶ ካረኩለት ይልቅ ያረገልኝ በዝቶ ሽቶዬን አፍስሼ ከእግሩ ስር ወድቄ በእንባዬ አጥቤ በጸጉሬ አድርቄ ይቅር በለኝ ብዬ ምህረትን ጠየኩኝ ከኃጢአት እስራት መላቀቅ ፈለኩኝ የረከሰች ብለው ሰዎች ቢንቁኝም ጌታዬ ግን ቸር ነው ንቆ አልተወኝም ልጄ ሆይ በማለት በጉያው ሸሽጎ ለሰው ልጅ ምህረትን ሊያስተምር ፈልጎ ይቅር ብዬሻለው ልጄ ተነሽ አለኝ ከኃጢአት አንጽቶ በፍቅሩ ማረከኝ ከጌታዬ እግር ስር መውደቄን የናቁ የአምላክን ቸርነት ፍቅሩን ያላወቁ ዝምታን መረጡ ማጉረምረሙን ትተው ይቅር ባይነቱን ቸርነቱን አይተው
    👍2❤2👏1
Whole thread · 1 reply →
R
M
በቃ በሰው ነገር አትግባ፡ የ ሰው ያርግት አንተን እስካልነካ
🥰2
🤞
  1. #
    ለዚህ ሚሆን ጥሩ telegram channel ተከፍቷል እየፖሰትን location እና feeling መፃፍ ነው 😊
Whole thread · 1 reply →
Whole thread · 1 reply →
D
👑 የንጉሡ መስታወት እና ምስጢራዊው መንገደኛ በአንድ ወቅት በአንድ ታላቅ ግዛት ውስጥ የሚኖር፣ ሁሉ ነገር የተሟላለት ነገር ግን በህይወቱ ሰላም ያጣ "ንጉሥ ኤልያስ" የሚባል መሪ ነበር። ንጉሡ በዙሪያው ያሉ አገልጋዮች፣ ሚኒስትሮችና የጦር አዛዦች ሁሉ የሚቀርቡት ለጥቅማቸው ብቻ እንደሆነ ይሰማው ስለነበር ማንንም አያምንም ነበር። "እውነተኛ ጓደኛ ወይም ታማኝ ሰው በዚህ ምድር ላይ የለም" የሚል ጽኑ እምነት ነበረው። አንድ ቀን ወደ ቤተመንግስቱ አንድ "ሳሙኤል" የተባለ በእድሜ የገፋ ምስጢራዊ መንገደኛ መጣ። ንጉሡን እያየው በኪሱ የነበረችን አንዲት ትንሽ በእጅ የምትያዝ መስታወት አውጥቶ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጣት። ንጉሡም "ይህች ተራ መስታወት ምንድን ናት?" ሲል ጠየቀው። ሳሙኤልም ፈገግ ብሎ "ንጉሥ ሆይ! ይህች መስታወት ተራ አይደለችም። 'የነፍስ መስታወት' ትባላለች። በዚህ መስታወት ውስጥ የሚያይ ሰው ሁሉ፣ በልቡ ውስጥ ያለውን እውነተኛ ማንነት እና በአንተ ላይ ያለውን ሃሳብ በግልጽ ያሳያል። ወደ አንተ የሚቀርቡ ሰዎችን ታማኝነት ለመፈተን ትረዳሃለች" አለው። ንጉሡ እጅግ ተደሰተ። ወዲያውኑ የአገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር አስጠራና በመስታወቱ ውስጥ እንዲያይ አዘዘው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ መስታወቱን ሲያይ፣ ንጉሡ በመስታወቱ ውስጥ ሚኒስትሩን እንደ ቀበሮ ሆኖ አየው። "ይህ ሰው ተንኮለኛ ነው!" ብሎ ከስልጣኑ አባረረው። በመቀጠል የጦር አዛዡን አስጠራው፤ እሱንም በመስታወቱ ሲያየው እንደ ተኩላ ሆኖ ታየው። "ይህም ከሃዲ ነው!" ብሎ አሰረው። በዚህ መልኩ ንጉሡ በቤተመንግስቱ ያሉትን የቅርብ ሰዎቹን ሁሉ በመስታወቱ እያየ አባረራቸው፣ ገለላቸው። በመጨረሻም ቤተመንግስቱ ባዶ ሆነ። ንጉሡ ሙሉ በሙሉ ብቻውን ቀረ። ነገር ግን ልቡ አሁንም ሰላም አላገኘም፤ ይልቁንም ፍርሃቱና ብቸኝነቱ ጨመረ። ሽማግሌው ሳሙኤል ከጥቂት ወራት በኋላ ተመልሶ መጣ። ንጉሡን ብቻውን ሆኖ፣ ተጨንቆና ከስቶ አገኘው። ንጉሡም በቁጣ "የሰጠኸኝ መስታወት ሰዎችን ሁሉ እንዳጣ አደረገኝ! ሁሉም ከሃዲና ክፉ ሆነው አገኘኋቸው" አለው። ሳሙኤልም በረጅሙ ተንፍሶ እንዲህ አለው፦ "ንጉሥ ሆይ! አንድ የቀረህ ትልቅ ፈተና አለ። እስኪ አሁን ደግሞ አንተ ራስህ በመስታወቱ ውስጥ ተመልከት።" ንጉሡ መስታወቱን አንስቶ ወደ ራሱ አቀናው። በመስታወቱ ውስጥ ያየው ግን የራሱን ፊት ሳይሆን፣ እጅግ የሚያስፈራ እና በጥርጣሬ የተሞላ ጭራቅ ነበር። ንጉሡ ደንግጦ መስታወቱን ጥሎት ጮኸ። "ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? እኔ እኮ ንጉሥ ነኝ!" አ አለ። ሳሙኤልም መስታወቱን ከመሬት አነሳና እውነተኛውን ምስጢር እንዲህ ሲል ገለጠለት፦ "ንጉሥ ሆይ! ይህች መስታወት እኮ የሌላውን ሰው ልብ አታሳይም። የምታሳየው የራስህን ልብና እይታ ብቻ ነው። አንተ በልብህ ሰዎችን ሁሉ ስለምትጠራጠርና እንደ ክፉ ስለምታያቸው፣ መስታወቱ ያንተኑ ጥርጣሬ አንጸባርቆ ሰዎቹን እንደ ቀበሮና ተኩላ አድርጎ አሳየህ። ሰዎችን የምናያቸው እነሱ በሆኑት ልክ ሳይሆን፣ እኛ በልባችን ባለን ማንነትና እይታ ልክ ነው።" ንጉሡ በዚያን ቀን ትልቅ ትምህርት ተማረ። ችግሩ የሰዎቹ ሳይሆን በውስጡ የነበረው የጥርጣሬና የፍርሃት በሽታ መሆኑን ተረዳ። ከዚያ ቀን ጀምሮ ልቡን በቅንነትና በበጎነት መሙላት ጀመረ፤ ሰላሙም ተመለሰለት። ✨ከታሪኩ የምንማረው ሰዎችን ወይም በዙሪያችን ያሉትን ነገሮች የምናይበት መንገድ የራሳችንን ውስጣዊ ማንነት ያሳያል። እኛ በጎ ከሆንን ሰዎችን በበጎነት እናያለን፤ እኛ ተጠራጣሪ ከሆንን ግን ሁሉም ሰው ክፉ ይመስለናል። 💗ከቃሎቼ 𝜗𝜚˚⋆ 💗 💗 💗
8 · 294 ·
𝓭
  1. ©
    ©ሶፊ
    Yes I'm fine...Ty for asking🙏
      1. ©
        ©ሶፊ
        ማርያምን 😁...I'm sorry I wouldn't share such sad contents anymore
          1. ©
            ©ሶፊ
            That's generous of you...keep this kind heart 🙏
            ❤1
Whole thread · 5 replies →
N
  1. ©
    ©ሶፊ
    Haha ናን እስካሁን አለመጀመሬ ነው የቆጨኝ እስከዛሬ ያመቅኹት ጩኸት 😁
Whole thread · 2 replies →

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · Index limits · Remove a page · Catalog · Search · How we count