Web appOpen in Telegram
AAbu Ruhama

Abu Ruhama

@sunah13 · channel · indexed since 2026-08-14
971subscribers
19average post reach
2%ER — reach to subscribers
72posts in 30 days
Abu Ruhama
Photo
click to show
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ ⏰ #ጁምዓ 1⃣4⃣ #ረቢዓል‐አኽር1⃣4⃣4⃣8⃣ ሂ
15 ·
A
Photo
click to show
የ #አፍሪካ መሪዎች በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የጸጥታው ምክር ቤት ላይ ማሻሻያ እንዲደረግ ተጽዕኖ እያደረጉ ይገኛሉ የአፍሪካ መሪዎች በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚወሰኑ ውሳኔዎችን በታዛቢነት መከታተል ሳይሆን፣ የውሳኔዎቹ አካል እና አጋር መሆን ይፈልጋሉ። በዚህ ዓመት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ እየተሳተፉ የሚገኙ የአፍሪካ መሪዎች፣ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ፣ በአህጉሪቱ የሚገኙ ሀገራት በድርጅቱ ከፍተኛ የውሳኔ ሰጪ አካል ውስጥ ቋሚ መቀመጫ እንዲኖራቸው የሚያስችል የጸጥታው ምክር ቤት ማሻሻያ እንዲደረግ በጽኑ ጠይቀዋል። ጉባኤው ማክሰኞ ዕለት ከተጀመረ አንስቶ ንግግር ያደረጉ በርካታ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የህዝቦቻቸውን እና የመንግሥቶቻቸውን ህልውና በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በሚነኩ ዓለም አቀፍ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ በሚመከሩበት ወቅት አህጉሪቱ በጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ ቋሚ ውክልና ማጣቷን ተቃውመዋል። https://www.facebook.com/share/p/19mjU837RT/
15 ·
Abu Ruhama
Photo
click to show
ዳሩ ዚክር የቁርአን መድረሳ ‼️ 3ኛ ዙር የምዝገባ ፕሮግራም! ((ቁርአንን ማወቅ የእውቀቶች ሁሉ መሠረት ነው!)) ይህንን ታላቅ መጽሐፍ መቅራት እየፈለጉ በተለያዩ ምክንያቶች አልቻሉም? እንግዲያውስ አሁን ምኞቶን በአላህ ፈቃድ እናሳካልዎት። 📖ዳሩ ዚክር የቁርኣን እና የተጅዊድ ማዕከል📖 በእጅዎ ባለው ስልክ፣ በቀን ጥቂት ደቂቃዎችን ብቻ በመስጠት ካሉበት ቦታ ሆነው ይማሩ። 📈የምንሰጣቸው ትምህርቶች፦ 1️⃣ ቃኢደቱ-ን-ኑራንያ (ለጀማሪዎች) 2️⃣ ቁርኣን በዕይታ (ነዞር) 3️⃣ ቁርኣን በሽምደዳ (ሒፍዝ) ከሙራጃዓ ጋር 4️⃣ የኪታብ ትምህርቶች (ሐዲስ፣ ዐቂዳ፣ ሲራ፣ ፊቅህ፣ ተፍሲር) የምናስተምርባቸው አማራጮች፦ በቴሌግራም፣ ዋትስአፕ፣ ኢሞ፣ ዙም እና በቀጥታ ስልክ ጥሪ። ⏰ የክፍለ-ጊዜ ሰዓታት (ከሰላት ሰዓት ውጪ)፦ • ጠዋት፦ 12:00 – 6:30   • ከሰዓት፦ 7:30 – 9:30 • አመሻሽ፦ 10:00 – 12:00 • ምሽት፦ 1:00 – 5:30 ✅ ልዩ ገጽታዎቻችን፦ • ቁርኣንን ከማንበብ በዘለለ በተጅዊድ መቅራት • ለአንድ ተማሪ አንድ ኡስታዝ (1-on-1) • በቀን ከ25–30 ደቂቃ በተመችዎ ሰዓት • በሳምንት 5 ቀን (ከሰኞ እስከ ጁሙዓ) ለመመዝገብ እና ለበለጠ መረጃ፦ 📌በቴሌግራም፦ @alzikronline 📞 በስልክ፦ 0957577141 0703356515 🌐 የቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል: – https://t.me/+8CAjk9ixGAZiODk0!
14 ·
Photo
click to show
Bani Suheila area, east of Khan Yunis. Gaza 2026
13 ·
Photo
click to show
✅ ብትገፋም ዝምድናህን አጠንክረህ ያዝ ይጠቅምሃል! ከአቡ ሁረይራ (🤎) ተይዞ፡ እንዲህ ይላል፦ ﴿أَنَّ رَجُلًا قَالَ: يَا رَسُولَ اللَّهِ، إِنَّ لِي قَرَابَةً أَصِلُهُمْ وَيَقْطَعُونِي، وَأُحْسِنُ إِلَيْهِمْ وَيُسِيئُونَ إِلَيَّ، وَأَحْلُمُ عَنْهُمْ وَيَجْهَلُونَ عَلَيَّ. فَقَالَ: لَئِنْ كُنْتَ كَمَا قُلْتَ فَكَأَنَّمَا تُسِفُّهُمُ الْمَلَّ ، وَلَا يَزَالُ مَعَكَ مِنَ اللَّهِ ظَهِيرٌ عَلَيْهِمْ مَا دُمْتَ عَلَى ذَلِكَ﴾ “አንድ ሰው ወደ አላህ መልእክተኛ ዘንድ በመምጣት እንዲህ አላቸው፦ ‘አንቱ የአላህ መልዕክተኛ (🤎) ሆይ! እኔ ዘመዶቼን ዝምድናቸውን እቀጥላለሁ (እዘይራቸዋለሁ) እነሱ ግን ዝምድናዬን ይቆርጡብኛል። መልካም ነገርን አደርግላቸዋለሁ፤ እነሱ ግን መጥፎ ነገርን ይሠሩብኛል። እታገሳቸዋለሁ (በዕውቀት አሳልፋቸዋለሁ)፤ እነሱ ግን በድፍረትና በድንቁርና መጥፎን ይፈፅሙብኛል። በዚህን ግዜ እንዲህ አሉት፦ እንዳልከው ከሆነ (እነሱን የምትታገስና መልካም የምታደርግ ከሆነ) እነሱን ትኩስ አመድ (ከሰል) እንደማጋት ነው። በዚያ ሁኔታ ላይ እስከቀጠልክ ድረስ ከአላህ ዘንድ በምታደርገው ነገር ላይ አጋዥ (ረዳት) ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ይኖራል።’” 📚 ሙስሊም ዘግበውታል፡ 2558 ➖➖➖➖➖➖➖➖ ✅ በነዚህ አድራሻዎች ይከታተሉን፦ 📱 Telegeram 📱 Whatsup 📱 Facebook  📱 Instagram 📱 X 📱 Youtube 📱 Tik tok
13 ·
A
Photo
click to show
ጠያቂ የፍራንስ 24 ጋዜጠኛ፦ «በሀገራችሁ የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ወንጀል አድርጋችሁ ቅጣት መጣላችሁ ተገቢ ነው? የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ አስቆጥቷል።» የሴኔጋል ፕሬዝዳንት፦ «ስለ የትኛው የዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ነው የምታወራው?» ጋዜጠኛው፦ «ለምሳሌ፦ ፈረንሳይና አሜሪካ» ፕሬዝዳንቱ፦ «እነዚህ ሃገራት የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ህጋዊ ሲያደርጉ ሉዓላዊነታቸውንና መብታቸውን መጋፋት እንዳይሆን ብለን ዝም ብለናል። እኛ ደግሞ ህገ ወጥ (ወንጀል) ነው ስንል፤ ሉዓላዊነታችንንና መብታችንን እንዲጋፉ አንፈልግም። ይህ መብታችን መሆኑን አውቀው ሊያከብሩ ይገባል።» ጋዜጠኛ፦ ጸጥጥጥ፣ ፍጥጥጥ
24 ·
A
Abu Ruhama
🌱❷➎ በነቢዩ(ﷺ)ላይ አንድ ሶለዋት ያወረደ⁉️ ​┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈• © 𝐖𝐚𝐯𝐞⚡️@HikmaWave_bot
19 ·
Abu Ruhama
ከ20 አባላት እስከ አፍሪካ ዋንጫ ጀግኖች ማፍሪያ የሆነው የአወሊያ ክለብ 40ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በድምቀት ተከበረ ነጃሺ ቲቪ || መስከረም 17/2019 ባለፉት አራት አሰርት ዓመታት ስፖርትን ከዳዕዋ ጋር በማዋሃድ የበርካታ ወጣቶችን ህይወት በመቅረፅ ረገድ ግንባር ቀደም ሚና ሲጫወት የቆየው አንጋፋው "የአወሊያ ዳዕዋ እና ስፖርት ማህበር"፣ 40ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ዛሬ በደማቅ ሁኔታ አከበረ። በአንጋፋው የስፖርት ጋዜጠኛ እና የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት "ስፖርት ዞን" ፕሮግራም አዘጋጅና አቅራቢ በሰዒድ ኺያር የመድረክ መሪነት የተካሄደው ይህ ታሪካዊ የምስረታ በዓል፤ ክለቡ ከስፖርቱ ዓለም ጋር ያለውን ጥልቅ ትስስር እና የዕለቱን ዝግጅት ሙያዊ ድምቀት በጉልህ አሳይቷል። መርሃ ግብሩ በዑመር ሰይፈዲን ሑደር ማራኪ የቁርዓን ንባብ የተከፈተ ሲሆን፤ የዘምዘም ባንክ ኃላፊ ፕሮፌሰር ናስረዲን፣ የነጃሺ ቲቪ የዜና ክፍል ኃላፊ አንጋፋው ጋዜጠኛ ጀማል አሕመድ፣ የፌደራል መጅሊስ የወጣቶች ካውንስል አባል ሸይኽ አብዱል ዓዚዝ ሙሐመድ እና አቶ ሰዒድ አስማረን ጨምሮ በርካታ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የክብር እንግዶች እና ጥሪ የተደረገላቸው ታዳሚዎች በክብረ በዓሉ ላይ ተገኝተዋል። በዕለቱ የክለቡን አጠቃላይ የ40 ዓመታት ውጣ ውረድ፣ ወሳኝ የለውጥ ምዕራፎች እና ታሪካዊ ጉዞ የሚያስቃኘውን ባለ 6 ገጽ መግለጫ የማህበሩ አሚር ሸይኽ ያሲን ሰልማን ለታዳሚው አቅርበዋል። ከ40 ዓመታት በፊት በ20 አባላት ብቻ የተጀመረው ይህ ማህበር፤ እንደ ኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር በ1985  መገባደጃ አካባቢ እነ ቲጋና እና ናስርን የመሳሰሉ ታሪካዊ አባላትን በማፍራት፣ ከስፖርት ጎን ለጎን ቋሚ የዳዕዋ መዋቅርን ዘርግቶ አሁን ላለበት ገናና ደረጃ መድረሱ በሰነዱ ላይ ተብራርቷል። ማህበሩ አሁን ላለበት ደረጃ እንዲደርስ ከመነሻው ጀምሮ ከፍተኛ ጥረት ላደረጉ መስራቾች እና አባላትም የላቀ ምስጋና ቀርቧል። በተለይም ኢትዮጵያን ከ31 ዓመታት በኋላ ወደ አፍሪካ ዋንጫ መድረክ በመመለስ በታሪክ ውስጥ ስማቸውን በወርቅ ቀለም ካስመዘገቡት የብሔራዊ ቡድን አባላት መካከል፤ ታዋቂዎቹ ተጫዋቾች ሰለሐዲን ባርጌቾ፣ አቡበክር ናስር፣ እና ጀማል ጣሰው፣ እንዲሁም አንጋፋው አሰልጣኝ ኻሊድ ሙሐመድ የዚሁ የአወሊያ ዳዕዋ እና ስፖርት ማህበር ፍሬዎች መሆናቸው በዕለቱ በቀረበው መግለጫ ላይ ተነስቷል። የክለቡ መሰረታዊ ዓላማ እግር ኳስን መጫወት ብቻ ሳይሆን፣ ስፖርቱን እንደ ማሰባሰቢያ መሳሪያ በመጠቀም ዲንን ማገልገል፣ በአኽላቁ (በስብዕናው) ያማረ ወጣት ትውልድን ማፍራት፣ በጋራ ሶላት መስገድ እና የማይበጠስ ኢስላማዊ የወንድማማችነት ትስስርን መፍጠር መሆኑ በመድረኩ ላይ በስፋት ተገልጻል። በዚህም የአወሊያ አባቶች "ወጣቱን ለመቀየር ወደኛ እስኪመጣ ከመጠበቅ ይልቅ፣ ወጣቱ ወዳለበት መሄድ አለብን" በሚል የወሰዱት የላቀ እሳቤ፤ ከመሃል ከተማ በተለይም ከመርካቶ፣ አሜሪካን ግቢ፣ ተክለሃይማኖት፣ ፒያሳ እና መሳለሚያ አካባቢዎች የተውጣጡ ወጣቶችን በማሰባሰብ ስነ-ምግባራቸውን እንዲያስተካክሉ፣ እምነታቸውን እንዲያጠናክሩ እና የተሻለ ራዕይ እንዲሰንቁ በማድረግ ማህበሩ ትልቅ የህይወት መቀየሪያ ማዕከል ሆኖ እንዲያገለግል አስችሎታል። በስፖርት ስም ከተሰባሰቡት ወጣቶች መካከልም፦ "ወደዚህ ስፖርት እና ዳዕዋ ማህበር ከመምጣቴ በፊት ኢስላም ምን እንደሆነ አላውቅም ነበር፤ ከዚያ በኋላ ግን ሁሉንም ወንድሞቼን ወደዚህ ማህበር እንዲቀላቀሉ በማድረግ የማህበሩ አባላት እንዲሆኑ አድርጌአለሁ" ያሉ ድምፆች ተሰምተዋል። የ40ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ልዩ ከሚያደርጉት ክስተቶ
18 ·
"ከዘር አጥፊዎች ጋር እጅ አንጨባበጥም!" ያለው እና እስራኤልን በሜዳም በሞራልም የረታው የአየርላንድ ብሔራዊ ቡድን ዓለምን እያነጋገረ ይገኛል ነጃሺ ቲቪ || መስከረም 18/2019 በአውሮፓ የሀገራት ሊግ (UEFA Nations League) መርሃ ግብር እስራኤልን 3 ለ 0 በሆነ ሰፊ የግብ ልዩነት ያሸነፈው የአየርላንድ ብሔራዊ ቡድን፤ ተጫዋቾቹ በጋዛ እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ በመቃወም በሜዳ ውስጥ ባሳዩት ጠንካራ 'የህሊና አቋም' የዓለምን ትኩረት ስቧል። በሃንጋሪ በገለልተኛ ሜዳ በተካሄደው በዚህ ጨዋታ፣ አየርላንዳውያኑ ከተለመደው የስፖርታዊ ጨዋነት ሥነ-ሥርዓት ውጭ የእስራኤል ተጫዋቾችን እጅ ለመጨበጥ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል። የሁለቱ ሀገራት አምበሎች የባንዲራ ልውውጥ ያላደረጉ ሲሆን፤ የእስራኤል ብሔራዊ መዝሙር በሚዘመርበት ወቅትም የአየርላንድ ተጫዋቾች አንገታቸውን በመድፋት ለፍልስጤማውያን ያላቸውን አጋርነት እና በዘር ጭፍጨፋው ላይ ያላቸውን ጥልቅ ተቃውሞ አሳይተዋል። እንደ BBC Sport፣ የቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ሄይሚር ሃልግሪምሰን ከጨዋታው በኋላ በሰጡት መግለጫ፣ ተጫዋቾቻቸው በወሰዱት ደፋር አቋም በጋዛ ስላለው ሁኔታ "በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ ግንዛቤ መፍጠር ችለዋል" በማለት ድርጊታቸውን አድንቀዋል። በተለይም የቡድኑ ግብ ጠባቂ ጋቪን ባዙኑ፤ "በጋዛ የዘር ማጥፋት እየተፈጸመ ባለበት ሁኔታ ከእስራኤል ጋር መጫወት ስህተት ነው" በማለት ጨዋታው ከመጀመሩ በፊት ራሱን ከስብስቡ ማግለሉ በእስራኤል ላይ ያለውን ዓለም አቀፍ ጫና ይበልጥ አጠናክሮታል። ስፖርትን ከሰብዓዊነት ነጥሎ ማየት እንደማይቻል በተግባር ያሳየው የአየርላንድ ብሔራዊ ቡድን፤ ተጫዋቾቹ ለሟቾች መታሰቢያ ያሰሩትን ጥቁር የክንድ ባንድ (Black armbands) ለብሰው ወደ ሜዳ ገብተዋል። በጨዋታው ሶስተኛዋን ግብ ያስቆጠረው ጃክ ሞይላንም ኳስ ከመረብ ካሳረፈ በኋላ የክንድ ባንዱን በማውለቅ እና የሀገሩን አርማ በመሳም ታሪካዊ አቋሙን አንጸባርቋል። በአየርላንድ "ጨዋታው ይቁም" (Stop The Game) በሚል በ "Irish Sport for Palestine" አስተባባሪነት የተቀሰቀሰው ይኸው ማህበራዊ ንቅናቄ፤ እስራኤልን በስፖርቱ መድረክ እንድትገለል እያደረጋት ይገኛል። እስራኤል ከጥቅምት 2023 ጀምሮ በጋዛ በከፈተችው አረመኔያዊ ወታደራዊ ጥቃት እስካሁን ከ73 ሺህ በላይ ሰዎች መገደላቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ታማኝነቱን ያረጋገጠለት የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል። የዘር ማጥፋት፣ የጦር ወንጀል እና በሰብዓዊነት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ክሶችን በተደጋጋሚ የምታስተባብለው እስራኤል፤ በአየርላንድ ስፖርተኞች የገጠማት ይህ የተግባር ተቃውሞ በዲፕሎማሲውም ሆነ በስፖርቱ ዓለም ትልቅ ራስ ምታት ሆኖባታል። በ ሐቢብ በሽር
20 ·
Photo
click to show
Photo
click to show
Photo
click to show
በህንድ ኡጃይን  ከተማ ከ600 ዓመታት በላይ ዕድሜ ያለው ታሪካዊው ሻሂ መስጅድ በከፊል መፍረሱን ተከትሎ ከፍተኛ ውጥረት ነገሰ ነጃሺ ቲቪ || መስከረም 19/2019 በህንድ ማድያ ፕራዴሽ ግዛት በምትገኘው ኡጃይን ከተማ፣ በ1390 የተገነባው ታሪካዊው ሻሂ መስጅድ በመንግስት በከፊል መፍረሱን ተከትሎ በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት መንገሱ ዛውዲ ጋዜጣ ዘግቧል። የመስጅዱ ኮሚቴ የማፍረስ ትዕዛዙን በመቃወም ለማድያ ፕራዴሽ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ያቀረበው ይግባኝ ውድቅ መደረጉን ተከትሎ ነው እርምጃው የተወሰደው። እሁድ ምሽት ፖሊስ በአካባቢው ላይ የብረት አጥር በማጠር ጥበቃ የጀመረ ሲሆን፤ የማፍረስ እርምጃውን ለመቃወም በርካታ የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት በመስጅዱ ዙሪያ መሰባሰብ በመጀመራቸው ውጥረት አይሏል። ትናንት ሰኞ እለት ተቃውሞው ወደ ግጭት በማምራቱ ፖሊስ 15 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ያዋለ ሲሆን፤ ማህበረሰቡን በማነሳሳት የተጠረጠሩ የማህበራዊ ሚዲያ ተጽዕኖ ፈጣሪዎችን ጨምሮ በ7 ግለሰቦች ላይ ክስ ተመስርቷል። የመስጅዱ አስተዳዳሪዎች እና ኮሚቴው የማፍረስ እርምጃውን አጥብቀው የተቃወሙት፤ የከተማዋ አስተዳደር የወሰደው ይህ እርምጃ የመስጅዱን ዋና የሶላት መስገጃ አዳራሽ እና 120 ጫማ ርዝመት ያለውን ታሪካዊ ሚናራ (የአዛን ማማ) ክፉኛ የሚጎዳ መሆኑን በመግለጽ ነው። ይሁን እንጂ የኡጃይን ማዘጋጃ ቤት፣ "እርምጃው ሆን ተብሎ በመስጅዱ ላይ ብቻ ያነጣጠረ ነው" የሚለውን ክስ አስተባብሏል። አስተዳደሩ በ2035 የልማት እቅድ እና የትራፊክ ፍሰቱን ለማሳለጥ ሲባል፣ በዚሁ መንገድ ላይ እስካሁን 10 የሂንዱ ቤተመቅደሶች እና አንድ መስጅድ መነሳታቸውን፤ እንዲሁም በመላው ከተማዋ 80 በሚጠጉ ልዩ ልዩ የኃይማኖት ተቋማት ላይ ተመሳሳይ እርምጃ መወሰዱን አስታውቋ።   በ ሐቢብ በሽር
27 ·
A
እናንተ ዝሙተኛ የምትሉት ሰሎሞን ነቢይ ነው፦ መጽሐፈ ሜላድ ዘውርኃ ታኅሣሥ ምዕራፍ 5 ቁጥር 1 "ቤተ መቅደሱን ያነጸ "ነቢይ" ሰለሞን፦ "ማደሪያ ናት" ብሎ እንደተናገረ"።
19 ·
Photo
click to show
#USA የአሜሪካ ጦር እስከ ነገ ሮቡዕ (መስከረም 30) ድረስ በኢራቅ ከሚገኙት የመጨረሻ የጦር ሠፈሮቹ ሙሉ በሙሉ ለመውጣት መዘጋጀቱ ተገለጸ። ይህ ውሳኔ በኢራን እና በሀገሪቱ በሚደገፉ ታጣቂ ቡድኖች ዘንድ እንደ ትልቅ ስትራቴጂካዊ ድል እና የአሜሪካ ፕሮጀክት መክሸፍ ተቆጥሯል። የኢራቅ ደህንነት ተንታኞች እንደሚሉት፣ የአሜሪካ ጦር መውጣት ለቴህራን ሰፊ የመንቀሳቀስ ነፃነትን በመስጠት የፖለቲካ እና የደህንነት ተጽዕኖዋን እንዲያጠናክር የሚያስችላት ሲሆን፤ እንደ አይኤስ (ISIS) ያሉ አክራሪ ቡድኖች ዳግም እንዲያንሰራሩ በር ሊከፍት ይችላል። አሜሪካ ሳዳም ሁሴንን ከሥልጣን ለመገልበጥ እ.አ.አ መጋቢት 2003 ኢራቅን ወርራ የነበረ ሲሆን፣ ባለፉት ከሁለት አስርት ዓመታት በላይ በቆየችበት ቆይታ ከ4,500 በላይ ወታደሮቿን አጥታለች። #ቢቢሲ መስከረም 19 ቀን 2019 ዓ/ም @tikvahethiopia
19 ·
A
Link
click to show
ካሊፎርኒያ የኢድ አል-ፈጥር እና የኢድ አል-አድሃ በዓላትን በማካተት  ሁለተኛዋ የአሜሪካ ግዛት ሆነች ነጃሺ ቲቪ || መስከረም 20/2019 የካሊፎርኒያ ግዛት አስተዳዳሪ ጋቪን ኒውሰም የእስልምና እምነት ተከታዮች የሃይማኖት በዓላት የሆኑትን የኢድ አል-ፈጥር እና የኢድ አል-አድሃ  በዓላትን በይፋዊ የበዓላት የቀን መቁጠሪያ ውስጥ የሚያካትተውን ህግ ፈርመው አፀደቁ። ይህ ታሪካዊ እርምጃ የካሊፎርኒያ ግዛትን የሙስሊም በዓላትን የግዛቲቷ ብሄራዊ ባዕል እንዲሆን የተቀበለች ሁለተኛዋ  የአሜሪካ ግዛት አድርጓታል። እንደ American Bazaar እና New Nation መረጃ እሁድ እለት የጸደቀው "Assembly Bill 2017" የተሰኘው ይህ ህግ፣ የግዛቲቱ የህዝብ ትምህርት ቤቶች እና የማህበረሰብ ኮሌጆች በነዚህ ሁለት በዓላት ቀናት በነባር የአካባቢ አሰራሮች መሰረት ዝግ እንዲሆኑ ይፈቅዳል። በተጨማሪም መስፈርቱን የሚያሟሉ የግዛቲቱ የመንግስት ሰራተኞች ለበዓላቱ የዕረፍት ጊዜ ማካካሻ (holiday credit) ሊያገኙ እንደሚችሉ ተገልጿል። ይህ ህግ የሁለቱን በዓላት ባህላዊ እና ሃይማኖታዊ ፋይዳ በግዛቲቱ ማህበረሰብ ዘንድ ያለውን ትልቅ ትርጉም አምኖ የተቀበለ መሆኑን የህጉ ሰነድ ያብራራል። ረቂቅ ህጉን ባለፈው መጋቢት ወር ያቀረቡት የማህበረሰብ ተወካይ ማት ሀኒ  እንዳሉት፣ "በዓላቱን እውቅና መስጠት የካሊፎርኒያ ሙስሊም ማህበረሰብን አስፈላጊነት የሚያንፀባርቅ ከመሆኑም ባሻገር፤ ቤተሰቦች ትምህርታዊ ወይም ሙያዊ ጫና ሳይገጥማቸው በዓላቱን በነፃነት እንዲያከብሩ ያስችላቸዋል" ብለዋል። ህጉ ትምህርት ቤቶች እና የህዝብ ስራ ቦታዎች የኢድ በዓላትን አከባበር እንዲያመቻቹ የሚያስችል ግልጽ ማዕቀፍ የሚሰጥ መሆኑም ተጠቁሟል። የካሊፎርኒያ የእስያ እና የፓሲፊክ ደሴቶች አሜሪካውያን ጉዳዮች ኮሚሽን ሊቀመንበር ጃሰን ፓጉዮ በበኩላቸው፣ "ህጉ የህዝብ ተቋማት በዓላቱን ለሚያከብሩ ዜጎች የተሻለ ሁኔታን እንዲያመቻቹ የሚያደርግ እና ትልቅ ባህላዊ ፋይዳ ያለው ውሳኔ" መሆኑን ገልጸዋል። ይህንን እና መሰል ወቅታዊ የአገር ውስጥ እና የዓለም አቀፍ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የነጃሺ ቲቪ ቤተሰብ ይሁኑ! መረጃው ለሌሎች እንዲደርስ Like እና Share በማድረግ ያጋሩ፤ ሀሳብዎን እና የዜና ሽፋን እንዲሰጥልዎት የሚፈልጉትን መረጃ በ Facebook Comment መስጫው ላይ ያስቀምጡልን! Telegram: 👇 https://t.me/nejashitvofficial Facebook: 👇 https://www.facebook.com/share/1BqpVAzYZ5/ YouTube: 👇 https://youtube.com/@nejashitva?si=EbZJO2z5d6FETgII   በ ሐቢብ በሽር
20 ·
A
Abu Ruhama
🌱❷➌ ቡኻሪ የተሰኘውን የሐዲስ ስብስብ አዘጋጅ ስም ማን ይባላል⁉️ ​•┈┈•┈┈•⊰✿◇✿⊱•┈┈•┈┈• © 𝐖𝐚𝐯𝐞⚡️@HikmaWave_bot
15 ·
Abu Ruhama
ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ "አንድ አፍታ ላውጋችሁ" በተሰኘው መጽሐፋቸው የዘመናችንን ጳጳሳት ፈተናና ውድቀት ሲታዘቡ፣ የጋናዊውን ደራሲ አዪ ኬዌይ አርማህን "መልካሞቹ ገና አልተወለዱም" (The Beautiful Ones Are Not Yet Born) የሚለውን መጽሐፍ ርዕስ ያስታውሳቸዋል። እሳቸው እንዳስቀመጡት፣ እነዚህ የሃይማኖት አባቶች ለሌሎች የሚሰብኩትን የቤተክርስቲያን ሕግ እራሳቸው ፈጽሞ አይጠብቁትም። ተራ ሰው አፉን ከፍቶ ሊናገረው የሚቀፈው ጸያፍ ቃል እንኳ ከእነርሱ አፍ ይወጣል። ፕሮፌሰሩ የክህነትን ኃላፊነት መሸከም ስለማይችሉ ብቻ ካህን እንዳልሆኑ በመጽሐፋቸው ይናገራሉ። (በተለይም አሜሪካ የነበረውና በተለምዶ "ስደተኛው ሲኖዶስ" በመባል ይጠራ የነበረውና ኃላ በለውጡ ማግስት ሀገር ቤት የገቡ ጳጳሳትን አስመልክቶ በሰፊው ጽፈዋል) ​ከሰሞኑ በአንድ ጳጳስ ላይ የተሰማውና ብዙዎችን ያሳዘነው የዝሙት ቅሌት፣ ይህንኑ የፕሮፌሰሩን ትዝብት መሬት ላይ ያረጋገጠ ክስተት ነው። ሆኖም ይህን ጉዳይ ስንመለከት፣ አላማችን ግለሰቡን ነጥሎ ማዋረድ፣ ማሳነስ ወይም በሰው ስህተት ላይ ቆሞ ማላገጥ ሊሆን ይገባዋል ብየ አላምንም። ይልቁንም ይህ ውድቀት፣ አንድ ትልቅ ሃይማኖታዊ ጥያቄ እንድናነሳ ይጋብዘናል፦ "የሰው ልጅ ተፈጥሮአዊ ስሜቱን (ሥጋዊ ፍላጎቱን) ሙሉ በሙሉ ጨፍልቆ መኖር ይችላል ወይ?" ​እስልምና ምንኩስናን (ረህባኒያ) አጥብቆ የሚከለክለውና ፈጽሞ የማይቀበለው ለዚሁ ነው። አላህ (ሱ.ወ) የሰውን ልጅ ሲፈጥር ሥጋዊ ፍላጎትና ስሜት አብሮ ሰጥቶታል። ይህን ተፈጥሯዊ ስሜት በጋብቻና በሐላል መንገድ ማስተናገድ እንጂ፣ "ፈጽሞ አልነካም፣ ራሴን ከጋብቻ አግልዬ እኖራለሁ" ብሎ መቃረን ከአላህ ህግ ጋር መጋጨት ነው። ​እስልምና ምንኩስናን የከለከለበት ዋነኛው ምክንያት፣ የሰው ልጅ ተፈጥሮውን ማሸነፍ አቅቶት በአደባባይ ሲሰብክ በጓዳ ግን ከከፋ የሞራል ዝቅጠት ውስጥ እንዳይወድቅ፣ ክብሩም እንዳይዋረድ ለመጠበቅ ነው። ራስን ከተፈጥሮ ጋብቻ አቅቦ መኖር በሰው ሰራሽ መንገድ የሚጫን ከባድ ቀንበር በመሆኑ፣ ውሎ አድሮ መንበሩን ወደ መርከስ፣ ሰባኪውንም ወደ ግብዝነት ይመራል። ​እነዚህ የሀይማኖት አባቶች ቃል ኪዳናቸውን ጠብቀው መዝለቅ አቅቷቸው ሲወድቁ ስናይ፣ ሰው ምን ያህል ደካማ መሆኑንና ከተፈጥሮ ህግ ማምለጥ እንደማይችል እንረዳለን። ማንም ሰው መላዕክት መሆን አይችልም፤ ቢሞክርም መጨረሻው መፈረካከስ ነው። ​የሰሞኑ ክስተት የሚያስተምረን ትልቁ ቁምነገር ቢኖር፤ ሃይማኖት የሰውን ልጅ ተፈጥሮ የሚጻረርና የማይቻል ሸክም የሚጭን ሳይሆን፣ ተፈጥሮውን አውቆ በመልካም መንገድ (በጋብቻ) የሚያስተዳድር መሆን እንዳለበት ነው። ዲናችን "በእስልምና ውስጥ ምንኩስና የለም" ሲል የሰውን ልጅ ድካምና መፈተን ቀድሞ ያወቀ ዲን እንደሆነ የሚያብራራ ትልቅ የህይወት ትምህርት ነው። ለኮሜንትና ሀሳብ ለማጋራት
12 ·
Photo
click to show
ተጠየቅ ዘኦርቶዶክስ ትውፊት እውን ጌታ ዕውር ነውን? ዕውር ሆኖ ከዕውር ጋር ጉድጓድ ይገባልን? የአቡነ ሀብተ ማርያም ገድል ገጽ 163 "ጌታም፦ "ኃይል የምሰጥ እኔ ነኝ፤ ዕውር ዕውርን ቢከተል ሁለቱም ከጉድጓድ እንዲወድቁ #እኔ #ዕውር #ነኝ፤ በሰላም ወደ እውነተኛ መንገድ የምመራ አይደለሁም፤ ስሜ ብርሃን ነው። ማቴዎስ 15፥14 ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ #ዕውርም #ዕውርን #ቢመራው #ሁለቱም #ወደ #ጉድጓድ #ይወድቃሉ፡ አለ። ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
10 ·
Photo
click to show
ጥያቄ ለፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች! ዓይን ጨፍኖ መጸለይ የሩቅ ምሥራቅ የዳርሚክ እምነት ማለትም የሂንዱ፣ የቡድሂስት፣ የኮንፊሺየስ፣ የሺንቶ፣ የጃይኒዝ፣ የታኦ እምነት ልማድ ነው። ዓይኑን የሚዘጋ ጠማማ አሳብን ያስባል፦ ምሳሌ 16፥30 *"ዓይኑን የሚዘጋ ጠማማ አሳብን ያስባል"* ከንፈሩን የሚነክስ ክፋትን ይፈጽማል። የብዙ አስማታዊ ድርጊቶች ዓይንን ከመጨፈን ጋር የተያያዙ ናቸው። የባይብል ሰዎች ዓይናቸውን ጨፍነው አይጸልዩም፦ ዮሐንስ 17፥1 ኢየሱስም ይህን ተናግሮ ወደ ሰማይ *"ዓይኖቹን አነሣ"* እና እንዲህ አለ። መዝሙር 123፥1 *"በሰማይ የምትኖር ሆይ፥ ዓይኖቼን ወደ አንተ አነሣሁ"*። ከባይብል ውጪ አንቀበልም ስትሉ ብዙ ጊዜ ይሰማል፥ ጥያቄአችን፦ ይህንን ልምድ ከየት አገኛችሁት?
15 ·
A
Photo
click to show
📆 #በሂጅራ የቀን መቁጠሪያ ማስታወሻ ⏰ #ጁምዓ 2⃣1⃣ #ረቢዓል‐አኽር1⃣4⃣4⃣8⃣ ሂ
15 ·
A
Abu Ruhama
Link
click to show
በዲላ የመጅሊስ አመራሮች መታሰራቸውንና የመስጂድ ሱቆች መታሸጋቸውን ተከትሎ አስቸኳይ የአቋም መግለጫ ወጣ ነጃሺ ቲቪ || መስከረም 22/2017 የዲላ ከተማ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት (መጅሊስ) የከተማዋ ህዝበ-ሙስሊም በህጋዊ የሃይማኖት አመራሮች ላይ የተፈጸመው ህገ-ወጥ አፈናና በእምነት ተቋማት ላይ የተከፈተው ጥቃት በአስቸኳይ እንዲቆም ሲል የአስቸኳይ የአቋም መግለጫ ማውጣቱ ታውቋል። መጅሊሱ ትናንት መስከረም 22 ቀን 2017 ባወጣው መግለጫ፤ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዑለማእ ጉባኤ እና የዲላ ከተማ መጅሊስ ሰብሳቢ ኡስታዝ ዐብዱረሕማን ዐብዱቁ፣ የከተማው መጅሊስ ጸሐፊ መምህር ዐብዱልፈታሕ ኤልያስ እና የቢላል መስጂድ ሰብሳቢ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ የጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሌክቸረር ዶ/ር ዐባስ አሕመድ «ለውይይት እንፈልጋችኋለን» በሚል ጥሪ ትናንት ጁሙዓ ከህግ አግባብ ውጭ መታሰራቸውን አስታውቋል። እንደ መግለጫው ገለጻ፤ ችግሩ የተቀሰቀሰው ቀደም ሲል በአዲስ አበባ አንቢያእ መስጂድ በስነ-ምግባር ጉድለት ከመስጂድ የተባረሩትን «ሸኽ ሑሴን አወል» የተባሉ ግለሰብን በዲላ በሚገኙ መስጂዶች ላይ በጉልበት ኢማም ለማድረግ የተደረገውን ሙከራ መጅሊሱ በመቃወሙ እና በህጋዊ መንገድ በማገዱ ምክንያት ነው። ይህን ውሳኔ ተከትሎም የመስጂዱ የገቢ ምንጭ የሆኑ አገልግሎት ሰጪ ሱቆች በግብር ሽፋን ያለ አግባብ መታሸጋቸውን መግለጫው አመልክቷል። መጅሊሱ ባቀረበው የጥያቄ ነጥቦች የታሰሩት አመራሮች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣ የታሸጉት የመስጂድ ሱቆች ክፍት እንዲደረጉ፣ ከህግ ውጭ በተፈጸመው እርምጃ ላይ የተሳተፉ የፖሊስ አባላትና የጌዴኦ ዞን ባለስልጣናት ላይ ገለልተኛ ምርመራ እንዲካሄድ እና የዞኑ አስተዳደር ይፋዊ ይቅርታ እንዲጠይቅ በጥብቅ ጠይቋል። በመጨረሻም ጉዳዩ ወደ ከፋ ህዝባዊ ቁጣ ሳይያመራ የፌደራል፣ የክልል እና የዞን የመንግስት አካላት በአፋጣኝ የህግ የበላይነትን እንዲያስከብሩ እያሳሰበ፣ ፍትህ እስኪረጋገጥ ድረስ ሰላማዊ ትግሉ የሚቀጥል መሆኑን መጅሊሱ አረጋግጧል። ይህንን እና መሰል ወቅታዊ የሙስሊሙ ማህበረሰብ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የነጃሺ ቲቪ ቤተሰብ ይሁኑ!  ሀሳብዎን እና የዜና ሽፋን እንዲያገኝለወት የሚፈልጉትን መረጃ በ Facebook Comment መስጫው ላይ ያስቀምጡልን! Telegram: 👇 https://t.me/nejashitvofficial Facebook: 👇 https://www.facebook.com/share/1BqpVAzYZ5/ YouTube: 👇 https://youtube.com/@nejashitva?si=EbZJO2z5d6FETgII በ ሐቢብ በሽር
15 ·
Abu Ruhama
Video
3.3 MB · click to show
ዋቄፈና አንዳንዴ አለመናገር መናገር ቢሆንና፥ ባለመናገር የምናገርውን መናገር ብንችል፥ መናገር  ቆሞ አለመናገር መናገርን ባስረዳ ነበር። ሃይማኖትን ለፓለቲካ፣ ለጥቅም እና ለስልጣን ማትረፊያ ንግድ ባናደርግ ጥሩ ነው። ዋቄፈና ባዕድ አምልኮ ነው። ለፓለቲካ ስንል "ባህል ነው" "የተፈጥሮ ሥርዓት ነው" የምንል ሰዎች አሏን እንፍራ! ዱንያህ አጭር ናት፥ ለዱንያህ ብለን አኺራችንን የሚያሳጣ ቃላት አንጠቀም። በማንበብ እራስዎን እና ማኅበረሰብዎን ከሺርክ፣ ከኩፍር፣ ከቢድዓ እና ከኒፋቅ ይጠብቁ! ዲናችንን ዕንወቅ! የበለጠ የሃይማኖት ንጽጽር ከፈለጉ እንግዲያውስ ጎራ ይበሉ፦ https://t.me/Wahidcom
13 ·
🌱 በመጀመሪያ በእስልምና ውስጥ የተወለደው ሶሓቢ ማን ነው⁉️ © 𝐖𝐚𝐯𝐞⚡️@HikmaWave_bot
13 ·
A
በምዕራባውያ(አውሮፓውያን) መርሕ ሕፃን ልጅን መምታት በጥብቅ የተከለከለ ነው፥ ሕፃናትን የመታ ሰው የእስር እና የብር ቅጣት ይቀጣል። በባይብል ደግሞ ሕፃን ልጅ መምታት ሐላል ነው፦ ምሳሌ 23፥13-14 ሕፃንን ከመቅጣት ቸል አትበል፥ በበትር #ብትመታው አይሞትምና። በበትር #ትመታዋለህ፥ ነፍሱንም ትታደጋለህ። የምዕራባውያ መርሕ የምትከተሉ ክርስቲያኖች ይህንን ጥቅስ ስታነቡ ምን ይውጣችሁ ይሆን? ✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ https://t.me/Wahidcom
9 ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog · Search · How we count