ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
ኦ

ኦርያ፯፯፯

385 members
I
እሷን መሳይ ቆንጆ ... አይን ይበዛባታል... 🌗<*<🌒
460 ·
A
ሀገሬ እንዴት ነሽ ሀገሬ፤ እኔስ እንደምንም ውስጤን እየጠማኝ ለውጥ እንደ ውሃ ጥም እየለበለበኝ ዘር እንደ ነበልባል ሁሌ እያሳከከኝ ችግር እንደ ቁስል እንደ ካሮት ጉዞ ሁሌ ወደ ቁልቁል የዜጎችሽ ሀሳብ ሁሌ ወደ ቁልቁል መሆኑ ቢከፋም እያደር ወደ ታች ወደ ላይ ለመውጣት እስከምንመቻች ወደ ላይ ለመውጣት መውረዳችን ከታች ቀና እንል ይሆናል ካጎነበስንበት ትል ነበር እናቴ ከመሞት መሰንበት እናስብ ሁል ጊዜ መሽቶ እየነጋ ወደፊት እንጓዝ ሁል ጊዜ ወደፊት ወደፊት አጥርተን ለይተን ክፋትን በወንፊት ሁሌ ሀሳብ ይዘን እንጓዝ ወደፊት
I
Check out this TikTok I posted! https://www.tiktok.com/@edi_0095/video/7646012989866364168?_r=1&u_code=ddgcfediik36k4&preview_pb=0&sharer_language=en&_d=f2glie1jll9mi4&share_item_id=7646012989866364168&source=h5_m&amp;timestamp=1780226616&user_id=6853133057744110597&sec_user_id=MS4wLjABAAAA28kmgAByne5Yke8n8nkfj8TtnuZ45k5DWoAARpttNuTwOR_lV3Rx5UUTyzyMPPUI&social_share_type=0&utm_source=telegram&utm_campaign=client_share&utm_medium=android&share_iid=7644508074707158804&share_link_id=8543a057-a9f2-43cd-b6c4-7d5466bc3fc8&share_app_id=1233&ugbiz_name=MAIN&ug_btm=b8727%2Cb2878&sp_root_share_link_id=8543a057-a9f2-43cd-b6c4-7d5466bc3fc8&link_reflow_popup_iteration_sharer=%7B%22click_empty_to_play%22%3A1%2C%22dynamic_cover%22%3A1%2C%22follow_to_play_duration%22%3A-1.0%2C%22profile_clickable%22%3A1%7D&panel_source_v2=share_panel&share_enter_from=personal_homepage&item_author_type=1&enable_checksum=1&sp_level=1&sp_root_u=ddgcfediik36k4&sp_root_d=f2glie1jll9mi4
እ
💃🕺ካለፈው የፍቅር ህይወቴ የተማርኩትና አሁን እንደ ፍቅር አጋር ያለኝ አስተሳሰብ👩‍❤️‍👨 $ በምታደርጊው ጥረትና መልካም ነገር ሁሉ ልደግፍሽና ላበረታሽ ከጎንሽ ነኝ። $ አምንሻለሁ መልካም ነገር አስበሽ እንኳ ቢሆን በፍጹም እንዳትዋሺኝ $ በጠንካራ ንግግሮቻችን መሀል ወጥቼ ከሄድኩ፣ ንቀት ሳይሆን በስሜታዊነት የማይሆን ውሳኔ ላይ ከመድረሳችን በፊት ተረጋግቼና ጥሩ ጭንቅላት ይዤ መመለስን ስለምመርጥ ነው። $ በምንም አይነት አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ብትሆኚ ብቻሽን አልተውሽም $ ቀሽም ነኝ ብለሽ ስለምታስቢው ነገር ምንም ግድ አይሰጠኝም፣ ስሜትሽን ግን ማዳመጥና መጋራት እፈልጋለሁ። ያለምንም መፍረድ እንደምሰማሽም ቃሌን እሰጥሻለሁ። $ በተለያዩ ሁኔታዎች ተጠምደሻል? ከሆነ አሳውቂኝ የዘጋሽኝ እንዳይመስለኝ $ ከጓደኞችሽ ጋር ወጣ ብለሽ ጊዜ ማሳለፍ ትፈልጊያለሽ? ትችያለሸ፣ ማሳወቅ እንጂ ማስፈቀድ አይጠበቅብሽም። $ ቂመኛ አትሁኚ! የሆነ ስህተት ከሰራሁ በእርጋታ ንገሪኝ እታረማለሁ $ ስለ ግንኙነታችን በየ social media መለጠፍ፣ እዩኝ እዩኝ ማለቱን አልወደውም። ስለማፍርብሽ አይደለም፣ ያለማንም ጣልቃ ገብነት፣ ካለ ሶስተኛ ወገን relationshipu እንዲቀጥል ስለምፈልግ እንጂ። $ የትም ብሆን ላንቺ የሚሆን ጊዜ ግን አላጣም፣ ቢያንስ text አደርግልሻለሁ። $ መቼም ሙሉ አይደለሁም፣ አብረሸኝ የምትሆኚው ድክመቶቼንም አይተሽ ነው። እኔም በድክመቶችሽ በኩል አፈቅርሻለሁ❤️ ......................................................................................... አንቺስ ምን ታስቢ ይሆን❤️❤️❤️? በአለም ላይ መልካም መዓዛ ያላቸው  አበቦች ሁሉ🌹🌹🌹🌹ላንቺ ይገባሻል ✍ታዚ
368 ·
እ
🏵️🏵️🏵️🏵️🏵️🏵️🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸 አንዳንድ ሰዎችን ከህይወታችን ጠቅልሎ ማስወጣቱ ከባድ ነው። በእያንዳንዱ የህይወታችን ጥጋጥግ ላይ እነሱን የምናስታውስበት ነገር አለን፣ even በጥቃቅን ነገሮች እንኳን እናስባቸዋለን።  ምናልባትም እነዚህ ሰዎች ለሌሎች ሰዎች የሚያደርጉትን ይሆናል ያደረጉልን ለእኛ ሲሉ የከፈሉት የተለየ መስዋዕትነት ምንም የለም። እንደውም ያን ያህል ስለኛ ስሜት ሀሳብና ፍለጎት ግድ የሚላቸው አይደሉም። በጣም ያፈቀርናቸው ሰዎች ሁሉ የሚፈቀር ማንነት ስላላቸው አይደለም በተቃራኒው እኛ አብዝቶ የሚያፈቅር ማንነት ስላለን እንጂ። ፍርፋሪ ፍቅር ሲሰጡን እንደ ውሻ ጭራችንን እየቆላን የምንከተላቸው በደልና ክፋታቸውን እያየን አሁንም የምናፈቅራቸው ሞኞች ስለሆንን አይደለም። አፍቃሪ ልብ፣ ስስ ልብ ስላለን እንጂ። someone said ፍቅርን ከሌለበት አትፈልገው፣ ካለበትም አትሽሸው። ፍቅር ከሌላቸው ሰዎች ፍቅርን መጠበቁ ባቡር ጣቢያ ሄዶ መርከብ እንደመጠበቅ ነው። እድሜና ጊዜያችሁ ያልቃል እንጂ አታገኙትም። የማያፈቅሩንን ዝም ብሎ ማፍቀር የአእምሮ ጤናችንን ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል። ✍ታዚ
363 ·
እ
"ብቻዬን ስላልተውከኝ አመሰግናለሁ።" ቴክስት ገባልኝ ማሂ ናት "ብቻዬን ስላልተውከኝ አመሰግናለሁ " የሚለው ብቻ በጉልህ ታየኝ ። በቀደም "አብረኸኝ ሁን በጣም ...በጣም ከፍቶኛል" ብላኝ ያለሁበትን ጠቆምኳት ያለሁበት መጣች ። እየጠጣን፣ ትንሽ ፈገግ ቁዝምም እያለች፣ ነፍ ነገር እየቀደድን እየተጫወትን አመሸን ። ወደ ቤቷ መሄድ እንደማትፈልግ ገባኝ ፣ ራይድ ደወልኩ፣ መነሻ እና መድረሻ ተናገርኩ ቤቴ ወሰደን ። ቆሎ ከኮመዲኖ፣ ከፍሪጅ ቢራ አቀርብኩላት ። ቆሎ እየቆረጠምን፣ ቢራ እየጠጣን ቢጃማ አውጥቼ ሰጠኋት እና ሱቅ እቃ ገዝቼ መጣው ብዬ ወጣሁ። ትንሽ የማልገዛውን እቃ እየጠየኩ ቆይቼ ተመለስኩ ቢጃማዬን ለብሳ ቆየችኝ ። ቢጃማዬን ገላዋን አስገብታበት አሳምራዋለች ። መሞናደሏን ቢጃማዬ አሳበቀባት ። አይኗ፣ ሁኔታዋ፣ አወራሯ ሁሉ ነገሯ መሞናደሏን ከልሎታል ። ሰው ስሜትን ሳያነብ ስሜታዊ ከሆነ ምኑ ጋር ነው ስውነቱ ? ትንሽ እንደተጨዋወትን የአልጋዬን አንሶላ ገልጠን ገባን ። አቀፍኳት ሳቅፋት ሰውነቷን ኩምትር እንዳደረገች  ነበር ። መሳቀቋ ገብቶኛል፤ ግን እንዳልገባኝ ሆኜ ግንባሯን ሳምኩት። አሳሳሜ  'አትሳቀቂ  ይሄው ትከሻዬ' የሚል መልእክት ለማስተላለፍ ነበር ግንባሯን በታላቅነት በአለሁልሽ ነው የሳምኳት። መልዕክቴ  በትክክል ይድረስ አይደረሳት አላወኩም ። ሲያጉረመርም የነበረው  ዶፍ ዝናብ ዘነበ አቀፍኳት ፣ በረዳት ወይ አመነችኝ  መሰል በደንብ ጥግት ብላብኝ ታቀፈች ። "ለምንድን ነው የምወደው ነገር ሳፈጥበት ገሸሽ የሚለው ?፣ የምጠላው ሳይቀር እኮ መውደድ ስጀምር ጥላ ያጠላበታል ።  እያጡ ማዘን እኮ  ደከመኝ። እንደ እናቶች ተረግሜ  ፣ተደግሞብኝ  ወይ ደግሞ አይነጥላ ይሆን? ለማለት ጫፍ ላይ እየደረስኩ ነው። " በለሆሳስ ስታወራ በጨለማው ውስጥ ኩልል ያለ እንባ ያፈሰሰች መስሎኛል ። ይሄን የቅሬታ ድምፅ ከእንባ ውጪ መተንፈስ የሚቻል አልመሰለኝም ። "አይዞሽ ሁሉም በግዜው ይስተካከላል። ሳንካ የሆነብሽ ሁሉ ወደ ጥሩ ይለወጣል ። ትላንት የከበደን ስንት ነገር ቀሎልን የለ?" የበለጠ አቀፍኳት ፤ ደረቴ ላይ ተኛች ። የሆነች ነፍስ አምናኝ የተጠለለችብኝ መሰለኝ ። ሙሉ ሰው የሆንኩ መሰለኝ ።  ስጋዬን ችላ ማለት የምችል አይነት  ስሜት ተሰማኝ ደረቴ ላይ እንደተኛች በደስታ ፈገግ አልኩ ። እንዳቀፍኳት እንደታቀፈችኝ  ለሊት ላይ ነቃሁ፣ አየኋት እንቅልፍ ውስጥ ጭልጥ ብላለች። አምናኝ ባዶ ክፍል ራሷን ገላዬ ላይ ጥላ  ተኝታለች ። ደስስ  እንዳለኝ ተኛሁ። ጠዋት ቁርስ በላን እና ሄደች።  አስራ እንድ ሰአት ከሃያ ቴክስት ላከችልኝ : "ብቻዬን ስላልተውከኝ አመሰግናለሁ። መሄጃ አጥቼ መሄጃ ስለሆንከኝ አመሰግናለሁ።" ቴክስቱን እንዳየሁት አለቀስኩ ። ለመዋሰብ ታግያት  ቢሆን ኖሮ እንዴት ነበር የሚሰማት? ብዬ አሰብኩ። አባቴ   እግሩ በተቆረጠበት ሰዓት ፣ ስራ በተባረረበት ሰዓት፣ ንብረቱን በተቀማበት ሰዓት፣ የዘመዶቹን የጓደኞቹን የብዙ ሰው ስም እየጠራ   "ብቻዬን ተውኝ: ብቻዬን ተውኝ"  ብቻውን መተውን እየተናዘዘ  በዛው አእምሮ እንደታወከ ስላስታወሰቺኝ ይሆን ብቻ መተው ማለት ትርጉሙ ገብቶኝ ይሆን ? ከብዙ ግዜ በኃላ ቃሉን ስለሰማሁት ይሆን? የአባቴ ሁኔታ አይኔ ላይ ስለመጣብኝ ይሆን? ብቻዬን ስላልተውከኝ አመሰግናለሁ የሚለው 'message' አስለቀሰኝ ። ጌታዬን ወደ ሰማይ አንጋጥጬ አመሰገንኩት ። "መሸሸጊያ ያጣች ድክም ያላትን ነፍስ : በኔ ምክንያት  የበለጠ እንዳታዝን ስላደረከኝ አመሰግናለሁ ጌታዬ።"    
472 ·
እ
በልጅነታችሁ በቂ ፍቅርና ትኩረት እንዳላገኛችሁ የሚያሳዩ ምልክቶች 1/  ፍቅር እንደማይገባችሁ ወይም ማንም እንደማይወዳችሁ ይሰማችኋል 2/  ሰዎች ደስ እንዲላቸውና እንዲወዷችሁ ከመጠን በላይ ትጥራችሁ( Even  የማትፈልጉትን ነገር እንኳን ቢሆን ታደርጉታላችሁ ለመወደድና ትኩረትን ለማግኘት ስትሉ)😔 3/ ጤናማ ያልሆኑ ግንኙነቶች ውስጥ ደጋግማችሁ ትገባላችሁ👬👭👬 4/  ሰዎች ከእናንተ ህይወት እንዳይወጡባችሁ የትኛውንም አይነት ዋጋ ትከፍላላችሁ😒 5/ ለስሜታችሁና ለራሳችሁ ቀይ መስመር አታበጁም ( ሰዎች ደጋግመው እየጎዷችሁ  Advantage እየወሰዱባችሁ እራሱ መልሳችሁ ዝምታ ነው) 6/ የተሰማችሁን በግልፅ መናገር ይከብዳችኋል (መጮህ😡፣ ማልቀስ😭፣ ለብቻ መሆንና ራሳችሁን አደጋ ላይ የሚጥል ነገር ማድረግ ይቀላችኋል) ከዚህ ውስጥ የሚሰማችሁ ስሜት ካለ ቆም ብላችሁ አስቡ። እወዳችኋለው😘😘😘 ✍በኃይሉ (ታዚ)
406 ·
I
Ссылка
click to show
ሰላም ሰላም ቤተሰብ እንዴት ናችሁ።በቶጳዝዮን መወያያ ግሩፓችን ላይ የግጥም ወጋችን ለረጅም ጊዜያት ተቋርጦ እና ተቀዛቅዞ እንደነበር ይታወቃል። ዛሬም እንደተለመደዉ ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ የግጥም ወጋችን ይጀመራል።ሀሳባችንን በግጥም መልክ እንገልፃለን። ያልተቀላቀላችሁ ገባ ገባ እያላችሁ።የተቀላቀላችሁ ወዳጅ ጓደኞቻችሁን Add እያደረጋችሁ ጠብቁን።😊😊🙏 https://t.me/topazionnn_gp
8.8K ·
እ
Фотография
click to show
አንድ ሰው relationship ውስጥ በስሜት የበሰለ (emotionally matured) መሆኑን የምናውቅባቸው የpsychology ነጥቦች 1/ በዝምታ እና በኩርፊያ አይቀጡም (silent treatment) በመሀላችሁ ግጭት ሲፈጠርና ሲበሳጩ ድንገት ስልካቸውን ዘግተው በመጥፋት እናንተን ጭንቀት ውስጥ አይከቱም። ይልቁንም አሁን ተከፍቻለሁ ስሜቴ ሲረጋጋ እናወራለን ብለው በግልፅ ይናገራሉ። 2/ ጥፋታቸውን አምነው ይቅርታ ይጠይቃሉ ስህተት ሲሰሩ ለጥፋታቸው ምክንያት አይደረድሩም፣ አሊያም ሀላፊነቱን ወደ እናንተ አያዞሩም። ይልቁንም ጥፋታቸውን አምነው ለዚያም ኃላፊነት በመውሰድ ይቅርታ ይጠይቃሉ። 3/ በጥሞና ያዳምጣሉ (Active listening ) ሀሳባችሁን ስትገልፁ ለመከራከርና ለመርታት ሳይሆን የእናንተን ፍላጎት፣ሀሳብና ስሜት ለመረዳት በጥሞና ያዳምጧችኋል። 4/ የራሳቸውን ደስታ ሙሉ በሙሉ እናንተ ላይ አይጥሉም Emotionally matured የሆኑ ሰዎች የራሳቸው የሆነ ህይወት ስራና የሚያስደስታቸው ነገር አላቸው። እናንተ bussy ስትሆኑ ወይም በተለያየ ምክንያት ትኩረት ልትሰጧቸው ሳትችሉ ስትቀሩ ወዲያውኑ አይቀየሙም ወይም አይደናገጡም። የራሳቸውን ስሜት በራሳቸው ማረጋጋት ይችላሉ እንጂ ደስተኛ ሆኖ ለመኖር ሙሉ ለሙሉ እናንተ ላይ ጥገኛ አይሆኑም። 5/ ድንበር ያከብራሉ አይሆንም ወይም አልፈልግም የምትሉትን ነገር ያከብራሉ። ፍላጎቶቻቸውንም በግድ እናንተ ላይ ለመጫን አይሞክሩም። ተጨማሪ ከፈለጉ Like and comment ያድርጉ ✍ታዚ
322 ·
እ
Фотография
click to show
ታውቂያለሽ ..... ? ተኩሰሽ ብትገይኝ ይታረድ ስለተባለ ስቃይ እንዳይበዛብኝ ነው የተኮሰችብኝ  ነው የምለው.... አንቺ ለኔ እንደህልሜ ከልቤ ጠፍተሽ አታቂም ። ሌላ ቦታ ያለዉ  ቸልታዬ አንቺ ጋ ሲደርስ አቅም አንሶት ይተጋል ተጎድቼ እምጨነቀው ጉዳቴን የምነገርሽ መንገድ ነው....  ድንገት ተለያየን  እንደዋዛ ታውቂኝ የለ ስቃይን መሸከም ፣ የተሰማኝን አምእሮዬ ውስጥ ማስቀመጥ እችላለሁ .... እንዳልናፈቀ፣ እንዳልተጎዳ መሆን መንገዴ አስተምሮኝ የለ? ብንለያይም ልቤ አልተለየሽም ነበር   .  .... ልቤ ያላዜመሽ ያላወሳሽ ያልተረከሽ ቀን የለም ..... ሲሳካልኝ  ፣ስወድቅ ፣ ሲደብረኝ ፣ የልቤን ሳወራ ከትውስታ ከትዝታዬ መሀል እየወጣሁ የማወሳሽ ሚስጥሬ ነሽ ታሪኬ ነሽ .....ትዝታዬም አንቺ ግን ሶስት ወር የምታቂውን ሰው ልታገቢ ነው??! ታድለሻል .....! እኔ  የዘገየሁት እራሴን እየጠረብኩ፣ እየቀረፅኩ ፣ እያበጃጀሁት ነበር፣ ...... ያልመጣሁት መቀየሬን ላሳይሽ ፣ ማደጌን ላስዳስስሽ ነበር... ስደርስ ግን በሌላ መንገድ እየሄድሽ ነው.... የውነት ግን ደስተኛ ነሽ ?? ይሁን.....            የኔን ግን እንዳልኩሽ ነው . . . ©Adhanom Mitiku ✍ታዚ
386 ·
እ
ስላመንኩት፥ ለሰጠኝ ፍቅር ዋጋ ስለሰጠሁ፥ እየተመቸኝ አልችልም ስለማልል፥ ስለሚወዱኝና ደጅ ስለሚጠኑ ወንዶች አያወራሁ ስለማልመጻደቅበት ... እኔን ማግኘት መጓጓት ቀነሰ ጥፋቱ ላይ ስለማላተኩር፤ ቅሬታዬን ስለማላሳየው፣ በልቤ ከሌሎች ጋ ስለማላወዳድረው     የማይገባኝ መሰለው! ቅር ይለዋል ብዬ የማስበውን ስለማላደርግ፥ ቅድሚያ ስለምሰጠው፥ ስለምወደው ዋጋዬ አልገባውም።  እየተወኝ ሁኔታው ሁሉ ውለታ እንደዋለ ነው። እየበደለ ውለታ ዋልኩ እንደሚል ሰው ክፉ የለም! ክፉ አለመሆኔን እንዴት እንዳለማወቅ መቁጠር ተቻለው?! ረስትቶ ነው !? እንዴት አድርጎ ቀልቤን ለመግዛት እንደደከመ ፥ እንዴት አድርጎ ደጅ ጠንቶ እንደቀረበኝ፥ እንዴት አንቆለጳጵሶ እጁ እንዳስገባኝ... ሲያገኘኝ እና ሳገኘው የነበረውን ሁኔታውን ሁሉ ረስቶታል! ሰነፍ እንዲህ ነው....በእጁ የያዘው ውድ አይመስለውም !! ሰነፍ እንዲ ነው..... የሚደረግለት  ካልተነገረው አይገባውም !!  ሰነፍ እንዲ ነው .....  ሲቆጠርበት አያይም !! ሰነፍ አንዲ ነው .......የሚፈልገውን ሲይዘው ያንስበታል !! ሰነፍ እንዲ ነው .....መከተል እንጂ ማስከተል አይችልበትም !! ሰነፍ እንዲ ነው ......ደስታው ያለው ሽምያ ውስጥ ነው !!                      እኔ  እና ልቤ ግን ታዝበነዋል !!   ©Adhanom Mitiku ✍ታዚ
438 ·
እ
ብዙ አልፈለኩም ነበር ልቤም የማይቻልን ነገር አልተመኘም በጣም ቀላል ነገር ነበር ስጠብቅ የነበረው... ሸክሜን የሚያቀልልኝ አንዲት ቃል ወይም ደግሞ ብቻዬን በናፍቆትህ ስባዝን እንዳልከረምኩ " እኔንምኮ በጣም ትናፍቂኝ ነበር" የምትል  ቃል፣ አንተን እያሰብኩ ላፈሰስኳቸው የእንባ ዶፎች መፅናኝ የሚሆን የፍቅር ቃል ስጠብቅ ነበር።  ከሁሉም ከሁሉም ግን ልቤን ሰቅዘው የያዙኝ ወደ ነገዬ አላራምድ ያሉኝ ሁለት ጥያቄዎች ነበሩኝ።  የመጀመሪያው አፍቅረኸኝ ታውቅ ይሆን... በእኔ ልክም ባይሆን ለኔ የፍቅር ስሜት ኖሮህ ያውቅ ይሆን.. ካልሆነ ለምን ያ ሁሉ ማስመሰል፣ የቃላት ጋጋታ እእ፣ እኔ አንቺን ባልወድሽ ቅብርጥሶ... ለምን??? ሌላኛው የልብህ ሚዛን ላይ የጎደልኩት፣ ላንተ በቂ ሆኜ ያልተገኘሁት፣ ምርጫህ ያልሆንኩት ምን ጎሎኝ ነበር? አለኝ የምለውን ሁሉ ላንተ ለመስጠትኮ አለሰሰትኩም ምንድን ነው የጎደለኝ?... እንኳን ሌላውን ቀርቶ ከሌሎች አርቄ ያስቀመጥኩትንስ ልቤን ሰጥቼህ አይደል። ምኔ ይሆን ላንተ ያነሰው??? ለእነዚህ ጥያቄዎች ምላሽ አመታትን ጠብቂያለሁ፣ ስትመጣ እየተቀበልኩ ስትሄድ ሸኝቼሃለው፣ ያለበደሌ ይቅርታን ለምኜሃለው... ካንተ "አፈቅርሻለሁ" የምትለውን ቃል ብቻ ለመስማት ምን ያህል ርቀት እንደተጓዝኩ አታውቅም። የምፈልገው ባንተ ልብ ውስጥ ትንሽ ቦታ አጊኝቼ እንደሆን ማወቅ ነበር። ሴት አይደለሁ ባንተ ለመወደዴ ዋስትና ለማግኘት ነበር ድካሜ። አፌ ደጋግሞ ቢሰናበትህም ልቤ ግን በየቀኑ መመለስህን ሲጠባበቅ ነበር። አሁን ለምን??? ማለቱን ቢከብድም ትቼዋለሁ። እባብ ሆነህ ስትነድፈኝ እኔ ለምን እያልኩ ምክንያትና ማብራሪያ ፍለጋ ስከተልህ ደጋግመህ በመርዝህ ጎድተኸኛል...። አሁን ግን ራሴን ማከም እንጂ ያንተ ማብራሪያ የተጎዳውን ልቤን እንደማይጠግን ገብቶኛል። ደግሞስ እባብ ሲናደፍ ለምን? አይባል ተፈጥሮውም አይደል። ምላሽ የሌለው ጥያቄ መሸከሜ ነበር ለስቃዬ ምንጭ የሆነው አሁን ግን ትቼዋለሁ። እያንዳንዱን ቀናት በእንባ እየሰፈርኩኝ ቻው ስልህ ኖሪያለሁ እየሸራረፍኩኝ፣ ዛሬም ለበደልህ ላረከኝ ጣል ጣል ቻው ማለት ብቻ ነው የቀረኝ አንድ ቃል፣ በል ቻው ቻው ባንተ አለመመረጤን አምኜ ተቀብዬዋለሁ ✍በኃይሉ(ታዚ)
430 ·
G
Фотография
click to show
👑 A New Game Has Arrived! Start with a small castle... Gather resources, build your army, outsmart your enemies— and rise to become the most powerful ruler of the season. 🔥 ⚔️ Real-time battles & sequential attack queue 🛡 Defense, shields & moats 🤝 Form alliances with friends & fight in team battles 🏆 Seasonal competitions & ranked champions The game is free to play—only on Telegram: 🎮 Play now → @KingdoriaBot 🎮 Play now → @KingdoriaBot 🎮 Play now → @KingdoriaBot 🎮 Play now → @KingdoriaBot 📢 Official channel → @kingdoria 🤝FAQ : https://t.me/+a0CeerzHhkZlNjcx #StrategyGame #TelegramGame
2.1M ·
@
Фотография
click to show
ጠለሸት ክፍል ፩ (መግቢያ) ከተገለጥን የሚያስፈራ ገፅታ ስለሚኖረን ይመስለኛል በሆነ ነገር መከለል መሸሸግ መደበቅ የሁልግዜ ስራችን ነው። አንዳንዶቻችን በገንዘብ:በዝና: በስልጣን በወገን ተከልለን ማንነታችን ምንነታችንና ግብራችን በግልፅ ሳይታወቅ ስንቱን አሳልፈን ዘመን ያልፍብናል። ግማሾቻችን በስርአት ተከልለን እንኖራለን ወይ እያስተማርን እየመሰልን ወይ እየተማርን: አልያ አንድ የሸመደድናትን ጥቅስ እያነበነብን ወይም የአንድ ፈላስፋ ንግግር እየተረክን እንሸሸጋለን። በልብሳች: በምላሳችን: በዝምታችንም ተደብቀን የምንኖር ብዙ ነን። እያንዳንዳችን በእውነተኛው ስራችን ጠለሸት የሰራ ገፃችን እንዳይታይ የተደበቅንበት የሆነ ነገር ይኖረናል። ምናልባትም የአንዳንዶቻችን ግዜ ሊሆን ይችላል ግዜ ትልቅ ከለላ ነው። ቀሪዎቻችን በአስማታችን በጥበባችን በፈገግታችን በለዘብተኛነታችን ውስጥ ተቀብረን ስንሮር አንዳንዶቻችን ደግሞ በቁጣችን በንዴታችን በአንባገነንነታችን ውስጥ ተደብቀናል። በሀዘን በትካዜ በሰመመን ውስጥ ቁዝምትን የተከለልንም አንጠፋም።  ሁሉም የአህያን ያህል መደበቂያ አለው። አህያ አፋን የሆነ በታ ውስጥ ትደብቅና ቂጧን ሜዳ ትጥላለች። እኛም እንዲሁ የሆነ የምንሰጋለትን ነገር ብቻ ከልለን ቀሪውን ለጅብ እንተዋለን እንጂ ጨርሶ አንለብስም። ግን የሆነ ነገራችንን የምንከለልበት ነገር አለ።  ይቀጥላል... በረከት መኩርያው።
255 ·
Archive by month
Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog