ሀሎ ሀሎ ወገን እንዴት ናችሁ? የክረምት ክፍያችን በተመለከተ ዝም አንልም እንጠይቃለን!!! በዚሁ አጋጣሚ የቦነስ ክፍያ ለምትሉ የቦነስ ሳይሆን በክረምት በዕረፍታችን ሰዓት የሰራነው የስራ ክፍያ እንጅ ቦነስ አይደለም አስተካክሉ ቦነስ ማለት እንደ ‘’thank you’’ በትርፍ የሚሰጥ እንጅ በመንግስት ደረጃ መመሪያና ማስፈፀሚያ ዝርዝር ተዘጋጅቶለት የሚከፈል አይደለም፡፡
ይሄ ግን በክረምት ወራት የትምህርት ተቋማት የእረፍት ጊዚያቸው ላይ በመንግስት በጀት የሚከናወን የስራ ተግባር እና ለዚሁም ስራ ከደሞወዝ ውጭ ሁለቱን ወር የአንድ ወር ደሞወዝ በመክፍል መመሪያ ወጥቶለት እየተሰራ ያለ ስራ ነው፡፡
ስለዚህ የተማሪ ቁጥር የሚወስነው ወይም የተቋሙን ሃላፊ የበጎ ፈቃድ የሚጠይቅ ሳይወን ተወደደም ተጠላም አገልግሎት እስከ ተሰጠ ድረስ የሚከፈል እንጅ፡፡
መመሪያው በመንግሥት በጀት ለሚሸፈኑ ወጪዎች የክፍያ ተመን መመሪያ ቁጥር 913/2014 ገጽ 8 ተራ ቁጥር 3 ላይ እንዲህ ይላል፡፡ “በክረምት ወራት በመንግስት በጀት መድቦ እንዲማሩ የሚደረጉ ተማሪዎች አገልግልት በዕረፍት ጊዚያቸው በአመቱ ተጨማሪ አስተደዳራዊ ስራ የሚሰሩ አስተዳደር ሠራተኞች በግለሰብ የአንድ ወር ደመወዝ እንዲከፈላቸው የሚደረግ ሲሆን የሚሰሩት ስራ ክፍል ጸባይ ምክንያት የዓመት ዕረፍት መውሰድ የማይችለትን ብቻ የሚመለከት ይሆናል” ይላል፡፡ ስለዚህ ይህንን እያየን እንዴት እንዘረፋለን???