ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
የ

የዩኒቨርሲቲ የአስተዳደር ሰራተኞች ድምፅ( voice of university admin staff) Chat

816 members
29 August 2026
I
ይዘገያል እጅ ብራችን አይቀርም ከሰን ቢሆን እንቀበላለን።
Файл
1788025981273.jpg · 268 KB · click to show
I
Файл
1788025985109.jpg · 266 KB · click to show
2 September 2026
I
አይ ሰው ግን ምንድነው የነካን?ዛሬ ነገ መሆኑ ጨለማ ብርሃን መሆኑ የተሾመ መሻሩ እንደማይቀር እያወቅን አለፍ ሲል ሁሉም ቀርቶ ማለፋችንን መርሳታችን ሳስበው ምን እንደነካን ግራ ይገባኛል፡ለማንኛውም ብሩ መቅረቱ ሳይሆን በስንት መከራ አስፈቅደን እዚህ እንደደረስን የነበራችሁ ታውቃላችሁ?ይህ ንቀት ነው መጠናከር አለብን ማንንም አልወቀስንም የ13ኛ ወር በጀት ተይዞለታል ይህ መብት እንጅ ድጎማ አይዴለም
I
አንድ ቀን ተገናኝተን ተወያይተን እንፈራረምና ሰው ወክለን እንክሰስ።
3 September 2026
I
ሀሎ ሀሎ ወገን እንዴት ናችሁ? የክረምት ክፍያችን በተመለከተ ዝም አንልም እንጠይቃለን!!! በዚሁ አጋጣሚ የቦነስ ክፍያ ለምትሉ የቦነስ ሳይሆን በክረምት በዕረፍታችን ሰዓት የሰራነው የስራ ክፍያ እንጅ ቦነስ አይደለም አስተካክሉ ቦነስ ማለት እንደ ‘’thank you’’ በትርፍ የሚሰጥ እንጅ በመንግስት ደረጃ መመሪያና ማስፈፀሚያ ዝርዝር ተዘጋጅቶለት የሚከፈል አይደለም፡፡ ይሄ ግን በክረምት ወራት የትምህርት ተቋማት የእረፍት ጊዚያቸው ላይ በመንግስት በጀት የሚከናወን የስራ ተግባር እና ለዚሁም ስራ ከደሞወዝ ውጭ ሁለቱን ወር የአንድ ወር ደሞወዝ በመክፍል መመሪያ ወጥቶለት እየተሰራ ያለ ስራ ነው፡፡ ስለዚህ የተማሪ ቁጥር የሚወስነው ወይም የተቋሙን ሃላፊ የበጎ ፈቃድ የሚጠይቅ ሳይወን ተወደደም ተጠላም አገልግሎት እስከ ተሰጠ ድረስ የሚከፈል እንጅ፡፡  መመሪያው በመንግሥት በጀት ለሚሸፈኑ ወጪዎች የክፍያ ተመን መመሪያ ቁጥር 913/2014 ገጽ 8 ተራ ቁጥር 3 ላይ እንዲህ ይላል፡፡ “በክረምት ወራት በመንግስት በጀት መድቦ እንዲማሩ የሚደረጉ ተማሪዎች አገልግልት በዕረፍት ጊዚያቸው በአመቱ ተጨማሪ አስተደዳራዊ ስራ የሚሰሩ አስተዳደር ሠራተኞች በግለሰብ የአንድ ወር ደመወዝ እንዲከፈላቸው የሚደረግ ሲሆን የሚሰሩት ስራ ክፍል ጸባይ ምክንያት የዓመት ዕረፍት መውሰድ የማይችለትን ብቻ የሚመለከት ይሆናል” ይላል፡፡ ስለዚህ ይህንን እያየን እንዴት እንዘረፋለን???
5 September 2026
I
ሰላም ቤተሰብ በዚህ ሳምንት ተገናኝተን ብንነጋገር ምን ይመስላችኋል?
10 September 2026
I
ለሰራተኛ ምቹ የሆነ አመራር በግቢው እንደሌለ ነው የሚያሳይ! በዚህ ሁኔታ ተቋሙ የእኔ ነው የሚል ሰራተኛ እየተፈጠረ አይደለም
I
ትለብሰው የላት ተኮናነበው አይነት ነው ላው ጥሩ ነው ለተቋሟችን ገጽታ። ነገር ግን ውስጡ ለቄስ ነው
I
እንቁጣጣሽ !!! እንኳን ከዘመን ዘመን በሰላምና በጤና አደረሳችሁ !!!  አዲሱ ዓመት የስኬት ዘመን ይሁንልን!!!
I
አይይይይ ላዩ ብልጭ ዉስጡ ቁልጭ የሆነ ተቋም ማስመሰል ብቻ😦
11 September 2026
አንድ ትልቅ ተቋም “Best Leadership (ምርጥ አመራር) አለው” የምንለው በመሪዎቹ ስራ አፈጻጸም፣ ባህሪ እና ውጤት ላይ ተመስርቶ ነው። ዋና መለኪያዎቹ፦ ግልጽ ራዕይና አቅጣጫ መኖር ተቋሙ የት መድረስ እንዳለበት ግልጽ ያደርጋሉ። ሰራተኞችን ወደ አንድ ግብ ያሰባስባሉ። ጥሩ ውሳኔ አሰጣጥ በመረጃ ላይ ተመስርተው ይወስናሉ። ችግኝን በፍጥነትና በተገቢው መንገድ ይፈታሉ። ተጠያቂነትና ታማኝነት ለውጤት ኃላፊነት ይወስዳሉ። ፍትሃዊና ግልጽ አሰራር ያስፈጽማሉ። ሰራተኞችን ማሳደግ ሰራተኞችን ያሰለጥናሉ፣ ያበረታታሉ። አዳዲስ መሪዎችን ያፈራሉ። ጥሩ ግንኙነት ሰራተኞችን ያዳምጣሉ። አመራር እና ሰራተኛ መካከል መተማመን ይፈጥራሉ። የላቀ ውጤት ማምጣት ተቋሙ የሚያመርተው ወይም የሚሰጠው አገልግሎት ይሻሻላል። የተቋሙ ስምና ተወዳዳሪነት ይጨምራል። ለለውጥ ዝግጁ መሆን አዳዲስ ሀሳቦችንና ቴክኖሎጂዎችን ይቀበላሉ። በአጭሩ፦ ምርጥ አመራር ያለው ተቋም ሰዎችን የሚያሳድግ፣ ግልጽ አቅጣጫ ያለው፣ በታማኝነት የሚመራ እና ዘላቂ ውጤት የሚያመጣ ተቋም ነው። የአንድ ትልቅ ተቋም (ለምሳሌ ዩኒቨርሲቲ፣ ኩባንያ፣ መንግስታዊ ተቋም) አመራር ብቃት የሚገመገምበት መስፈርቶች፦ 1. ራዕይና ስትራቴጂ አመራር የተቋሙን የወደፊት አቅጣጫ በግልጽ ማሳየት። የረጅም ጊዜ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማስፈጸም። 2. የውጤት አፈጻጸም ዕቅዶችን በተግባር ማሳካት። የተቋሙን ጥራትና ተወዳዳሪነት ማሳደግ። 3. የሰው ኃይል አመራር ብቃት ያላቸውን ሰዎች መምረጥ። ሰራተኞችን ማሳደግ፣ ማበረታታትና ማስተባበር። 4. ግልጽነትና ተጠያቂነት የሚወሰኑ ውሳኔዎች ግልጽ መሆን። ለስራ ውጤት ኃላፊነት መውሰድ። 5. ፈጠራና ለውጥ አመራር አዳዲስ ሀሳቦችን መቀበል። ተቋሙን ከአዳዲስ ፍላጎቶች ጋር ማስማማት። 6. የግንኙነት ብቃት ሰራተኞችን፣ ተጠቃሚዎችንና ባለድርሻዎችን በአግባቡ ማስተናገድ። የመተማመን ሁኔታ መፍጠር። 7. የሀብት አጠቃቀም ገንዘብ፣ ንብረትና ጊዜን በብቃት መጠቀም። ብክነትን መቀነስ። 8. ሥነ-ምግባርና ምሳሌነት በራሱ ተግባር ምሳሌ መሆን። ፍትሃዊነትና ታማኝነትን ማስቀደም። የምርጥ አመራር ዋና መለኪያ: “አመራሩ ከነበረበት ሁኔታ የተሻለ ተቋም ጥሎ መሄድ መቻሉ ነው።”
N
የኛ ተቋም እጅግ ውስብስብ ችግሮች ያሉበት እንደሆነ በርካታ ማሳያዎች አሉ ለዚህም ነው ትላንት የተመሠረቱ ዩኒቨርስቲዎች በተሻለ ስታንዳርድ ላይ ያሉት።
እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ! አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የደስታና የስኬት ዓመት ያድርግልን። አዲስ አመት ስንቀበል ያለፈውን ረስተን የሚመጣውን በአዲስ የምናቅድበት ያድርግልን። እኛም ነገ ከዛሬው የተሻለ ቦታ ሁነን ሠራተኛ ላለማስከፋት ያብቃን።
I
ውድ የአስተዳደር ሠራተኞች በተለይ ዛሬ ባለሙያና ሠራተኛ የሆናችሁ ሠዎች በብዙ መንገድ ደስተኛ ላትሆኑ ትችላላችሁ ነገር ግን ነገ እናንተም ኃላፊዎች ማለቴ አለቃ ትሆናላችሁ ያኔ ማሠብ ያለባችሁ ከእናንተ በታች ያለው ሰራተኛ በምን መልኩ እየኖረ ነው የሚለውን ነው። ለምሳሌ አንዳንድ ተቋሞች ስበብ እየፈጠሩ የተቸገረውን ሠራተኛ ሲጠቅሙ ይታያሉ አንዳንዶች ደግሞ በግልፅ የተቀመጠን ጥቅማጥቅም አንተን ነፍገው የእነሡ ማደጊያ ሊያደርጉት ሲለፉ ታያለህ። አንተ ይህን አይነት ስራ እንዳትሠራ አደራ ምክንያቱም አንተም ነገ እዛ ቦታ ላይ ትቀመጣለህ። ሰራተኞችህ ምን ልብላ እያሉ ያንተን መመቸት እንዳታይ። ሠራተኞችህ እንዴት ልኑር እያሉ የአንተን መኖር እንዳታይ። ሠራተኞችህ እያለቀሡ የአንተን ደስታ እንዳታይ ። የአንተን አስገድደህ ገንዘብ ማገኘት እያወቅ ሠራተኞችህ ገንዘብ እንደማያገኙ እንዳትረሣ።
I
የአስተዳደር ሰራተኛውን ጩኸት እና ስቃይ ልክ እንደ ቁራ ጩኸት ነው የሚቆጥሩት ዝቅ ብሎ ችግርን የሚረዳ አመራር እንዴት ይጠፋል??
16 September 2026
I
በዚህ ተነጋግረን ከጨረስን ሐሙስ ማለትም 7/1/2019 ዓ.ም ጧት ስብሰባ ስላለ ሁሉም መልካም ጥሩ ውጤት ያመጣል ያለውን ሃሳብ ይዞ በጣም መልካም አጋጣሚነው ብዬ አስባለሁ ሚዲያ ብቻ ባይሆን
19 September 2026
D
id 5188928311Файл
ሠላም እዴት ናችሁ የአደረጃጀቱን የመጨረሻውን የስራ ልምድ፤የትምህርት ዝግጅት እና በየስራ ዘርፋ የሚፈልገውን ፎርም መጨረሻ ላይ ልንሞላ ስንል የተለጠፈውን የስራ ዝርዝር እና የሚፈልገውን የሙያ አይነትና መደቡ የሚጠይቀውን የሠው ብዛት የያዘውን ፎርም ፈልጌው ነው ላኩልኝ።።።።።።።። ሠላም ለሁሉም
Архив по месяцам
Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog