ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
W

wolkite exam colletion

сообщение · 2026-05-19 13:50 UTC
A
ለክቡር ዶ/ር ፋሪስ ደሊል የምስጋና መልዕክት እንዲሁም ለአዲሱ ፕሬዚዳንት ዶ/ር አብድልሙህሲን ሀሰን የእንኳን ደህና መጡ መልዕክት እኛ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በሙሉ፣ ለክቡር ዶ/ር ፋሪስ ደሊል በዩኒቨርሲቲያችን ቆይታቸው ዘመን ላደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ፣ ለነበራቸው ቅን አመራር፣ ለተማሪዎች ላሳዩት ክብርና አባታዊ እንክብካቤ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን ልናቀርብ እንወዳለን። በእውነት እርሶ ለእኛ ተማሪዎች ከአስተዳዳሪነት በላይ እንደ አባት፣ እንደ ቤተሰብ አባል ቆመውልናል። በተማሪዎች ችግር ጊዜ አጠገባችን በመሆን፣ በትምህርት እና በግቢ ህይወት ውስጥ ያለንን ተስፋ በማጠናከር እና ለዩኒቨርሲቲያችን እድገት ያደረጉት ጥረት ሁሌም በክብር የምናስታውሰው ይሆናል። ያበረከቱት አስተዋጽኦ በወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ ውስጥ በደማቅ ፅሁፍ የሚታወስ ሲሆን፣ እኛም ተማሪዎች ለእርሶ ያለንን ክብርና ፍቅር በቃላት ብቻ ለመግለጽ የሚከብድ ነው። በቀጣይ የህይወትና የስራ ጉዞዎ ሁሉ የተሻለ ስኬት፣ ጤና፣ ሰላም እና በረከት እንመኛለን። በተጨማሪም አዲሱ የወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ክቡር ዶ/ር አብድልሙህሲን ሀሰን ወደ ዩኒቨርሲቲያችን በመምጣታቸው እንኳን ደህና መጡ ልንላቸው እንወዳለን። እኛ ተማሪዎች በታላቅ ደስታ፣ በክብር እና በፍቅር እንደተቀበልናቸው ለመግለጽ እንፈልጋለን። ዩኒቨርሲቲያችንን ወደ ተሻለ እድገት፣ ጥራት እና ስኬት እንደሚመሩት ትልቅ ተስፋ አለን። በእርሶ አመራር የተማሪዎች ድምፅ የሚሰማበት፣ የእውቀት እና የልማት ማዕከል የሆነ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገነባ እናምናለን። በመጨረሻም፣ ለክቡር ዶ/ር ፋሪስ ደሊል በሰሩት ታላቅ አገልግሎት ከልብ እናመሰግናለን፤ ለክቡር ዶ/ር አብድልሙህሲን ሀሰን ደግሞ መልካም የስራ ዘመን፣ ስኬት እና የተሞላ አመራር እንመኛለን። “መልካም መሪዎች በተማሪዎች ልብ ውስጥ ዘላለም ይኖራሉ!”

All messages on 19 May 2026 · Whole feed · оригинал в Telegram

Open in Telegram Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog