English
Open in Telegram
HHalal memory🫀

Halal memory🫀

✅ High trust
@Halal_memory ¡ channel ¡ Education ¡ indexed since 2026-08-26
9 072subscribers
502average post reach
5.5%ER — reach to subscribers
46posts in 30 days
🦋
ምስጋና ለእርሱ .... በውዱእ ውስጥ ወንጀል ማጥራትን ላደረገው ጌታ ፤ በሱጁድ ውስጥ ሀዘንን ማራገፍ ላደረገው አላህ ፤ በልብ ውስጥ ቁርአንን ብርሀን ላደረገው ዐዚዝ ፤ በመስጠት ውስጥ ደስታን ላደረገው ከሪም ፤ ከሀዘን በኋላ ደስታን ላደረገው ረሂም ምስጋና የተገባው ነው
❤2👏1
2 ¡ 347 ¡
🇾
አላህ ሆይ! መጪውን ዕድሜያችንን ካለፈው የተሻለ አድርግልን። ድክመታችንን በእዝነትህ ሸፍንልን። የብልሃታችን ማነስ በምራቻህ ሙላልን። ሰፊ እና በረከት ያለው ሲሳይ ስጠን፤ የተሟላ ደኅንነትንም አድለን። ልጆቻችንን እና ዘሮቻችንንም መልካምና የሰላም ምንጭ አድርግልን። በልቦቻችን ውስጥ መረጋጋትን አውርድ፤ ጭንቀቶቻችንን አስወግድ፤ ደረታችንን አስፋፋልን፤ በእኛ ላይ የተቆጡትንም አስደስት። ስንኖርም ሆነ በመሞቻ ጊዜያችን እዘንልን። አሚን 🤲
❤7
367 ¡
L
ሰው ለሌላው ሰው ማሰቡ ምንኛ ውብ ነው! አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በውስጣቸው የሚያልፉትን ስቃይ ለማንም አይናገሩም። በፈገግታቸው ጀርባ ሀዘን፣ በዝምታቸው ጀርባ ብዙ ሀሳብ ሊኖር ይችላል። ሰዎችን ከመፍረድህ በፊት ሁኔታቸውን ለመረዳት ሞክር። አንድ መልካም ቃልህ የሰውን ልብ ሊያረጋጋ ይችላል። ሌሎችን በችግራቸው ጊዜ አትርሳ፤ አንድ ቀን አንተም የሌላ ሰውን ድጋፍ ልትፈልግ ትችላለህ። 🤲 ለተጨነቁት ዱዓ አድርግ፣ ለተቸገሩት እርዳታ አድርግ፣ ለተሰበሩ ልቦችም የምትችለውን ማጽናኛ ስጥ። አስታውስ! የሰውን ሁሉ ሀዘን ማስወገድ ባትችልም፣ ሀዘኑን ለማቃለል ምክንያት መሆን ትችላለህ። 🌸የሌሎችን ስቃይ የሚረዳ ልብ ይኑረን፤ ሰው ለሰው መድኃኒት እንጂ ቁስል አይሁን።
🍓2
1 ¡ 343 ¡
🦋
ነፍስ ያለው ሁሉ ሞትን ይቀምሳል! ነገር ግን ሁሉ አሟሟት አንድ አይደለም። ሲሞት ምድር ምታለቅስለት ሰው አለ፤ በተቃራኒው ደግሞ ሲሞት ለሰው ልጆች እረፍት የሆነ ሰው አለ።!
😢2💔1
1 ¡ 294 ¡
Photo
🎬 የፍቅር ዋጋ | በ2 ቀናት ውስጥ ይጀምራል! አንድ ፍቅር፣ ሁለት ምርጫዎች፣ የተደበቁ ምስጢሮች… እና የማይቀር ውጤት። 🥀 የመርየም ታሪክ ምን ያህል ይለወጣል? እውነት ሲገለጥ ፍቅር ይቀጥላል ወይስ ያበቃል? 🎬 የፍቅር ዋጋ ⏳ ለመጀመሪያው ክፍል 2 ቀናት ብቻ ቀሩ! ይህን ታሪክ ለመከታተል ዝግጁ ናችሁ? 👀
🍓3
273 ¡
🇾
ሁሉም ሙስሊም ሆኖ ይወለዳል; ሙስሊም ሆነው የሚሞቱት ግን አላህ የመረጣቸው ናቸው!!!!! አላህ ይወፍቀን 🤲🤲🤲🤲🤲
❤8
1 ¡ 243 ¡
🇪
መልካም ምሽት✌️ ለነገ ውሎ ማማር ምሽቱን ወደ አላህ ቀርቦ ማደር . ነገሮች ሁሉ ምላሽና ዉጤት አላቸው። ምሽቱን በወንጀልና ኃጢአት ያሳለፍክ እንደሆነ ጠዋት ላይ ይህ ሊያጋጥምህ ይችላል - .  ለሱብሒ ሶላት እንዳትነሳ የሚጫጫንህ ነገር ይኖራል፣ ኃይለኛ የራስ ምታት ይዘህ ትነሳለህ፣ ሚስትህ አኩርፋ ትጠብቀሃለች፣ ምን እንዳስቆጣት እንኳን ፈልገህ ፈልገህ ልታገኝ አይችልም፣  ልጅህ ከመሬት ተነስቶ  ትምህርት ቤት አልሄድም ይላል፣ ካልሲህን በመፈለግ ብቻ ከግማሽ ሰዓት በላይ ይወስድብሃል፣ ቁርሱ ጨው በዝቶበት አላስበላ ይልሃል፣ መኪናህ አልነሳ ትላለች፣ ዝም ብሎ ያነጫንጭሃል፣ ከቤት ቶሎ አትወጣም፣ ታክሲው ቶሎ አይመጣም ፣ ወያላው ይለክፍሃል፣ ትራፊክ ያለምንም ምክንያት ያስቆምሃል፣ ያለ ጥፋትህ ይከስሃል፣ ቢሮ ስትገባ አለቃህ በቁጣ ይጠብቅሃል፣ ያሳደርከው ሥራ አዲስ ይሆንብሃል፣ ምሳ ልትበላ ስትከፍት ወጥ የለውም፣  ትንሽ ደቂቃ ልተኛ ብለህ ገና ጋደም ብለህ ጣፋጭ እንቅልፍ እየወሰደህ ሳለ የስልክ ጥሪ ይቀሰቅስሃል፣ ዘሁር ከሰገድክ በኋላ ዉዱእ እንዳልነበረህ ትዝ ይልሃል፣ ነገሮች ሁሉ ይሰነካከሉብሃል .... ያኔ ታዲያ አብዝተህ መታገስና ነገሮችን በውዴታ መቀበል ይኖርብሃል። ... ~ ምሽት ለንጋት እርሾ ነው፣ ~ ማለዳ ለዉሎ ጥንስስ ነው፣ ~ ምሽትህን በዒባዳ አሳምር፣ ~ ማለዳህን በሶላት ዚክርና ዱዓ  ጀምር፣ ~ በገዛ እጅህ ቀንህን አሳልፈህ ሠጥተህ ዛሬ ቀኑ የኔ አይደለም አትበል። ኢላሂ ምሽታችን ውብ ይሆን ዘንድ በምናስበው ላይ ሁሉ እርዳን.. @Halal_memory
❤1
215 ¡
L
ዓለም በየቀኑ እየተለወጠች ነው፤ እኛስ? አሁንም በትናንትናው ዕውቀት ብቻ እንቀጥል? 🤔 ትልቅ ስኬት የሚጀምረው በትንሽ ትምህርት፣ በቀላል ጥያቄና በየቀኑ በሚደረግ ጥረት ነው። ዛሬ አንድ አዲስ ነገር ተማር! 🔍 የማታውቀውን ጠይቅ! 🧠 ከስህተትህ ተማር! 💪 ትናንት ከነበርከው የተሻለ ሰው ለመሆን ጥረት አድርግ! ዕውቀት ሀብት ነው፤ መማር ደግሞ ወደ ስኬት የሚወስድ መንገድ ነው! 🕌 አላህ በቁርአን እንዲህ ይላል፦ ﴿وَقُل رَّبِّ زِدْنِي عِلْمًا﴾ «ጌታዬ ሆይ! ዕውቀቴን ጨምርልኝ በል።» (ሱረቱ ጣሃ፣ 20:114) ✨ ዛሬ የምትማረው ነገ የምትደርስበትን ደረጃ ሊወስን ይችላል። ስለዚህ ጊዜህን ተጠቀምበት፣ አእምሮህን አሳድግ፣ ሕልምህንም ወደ እውነት ለመቀየር ዛሬውኑ ጀምር! ━━━━━━━━━━━━━━━ @Halal_memory
❤1
137 ¡
✍ህይወት ማለት ህመም የሌለበት ጉዞ ሳይሆን፣ በህመም ውስጥምተስፋን ሰንቆ መጓዝ ነው። ♻️ እንባ ቢኖርም ፈገግ ማለት፣ስንወድቅም ዳግም ለመነሳት መዘጋጀት ነው። @Halal_memory
🍓1
104 ¡
📚 የኦንላይን ስልጠና እና የዲጂታል ክህሎት ትምህርቶች አሰላሙ አለይኩም ወረህመቱላሂ ወበረካቱህ። የዲጂታል ክህሎትዎን ማዳበር፣ የራስዎን Content መፍጠር እና ቢዝነስዎን በኦንላይን ማስተዋወቅ ይፈልጋሉ? ለጀማሪዎች እና ክህሎታቸውን ማሳደግ ለሚፈልጉ ሰዎች ተግባራዊ የኦንላይን ስልጠናዎችን እዘጋጃለሁ። 📌 የሚሰጡ ስልጠናዎች እና ዋጋቸው 🎬 Content Creation የቆይታ ጊዜ፦ 7 ቀናት 💰 2,500 ብር ✂️ CapCut Video Editing የቆይታ ጊዜ፦ 7 ቀናት 💰 2,000 ብር 📱 Social Media Management የቆይታ ጊዜ፦ 10 ቀናት 💰 3,000 ብር 📈 Digital Marketing የቆይታ ጊዜ፦ 14 ቀናት 💰 4,500 ብር ✍️ Content Writing & Copywriting የቆይታ ጊዜ፦ 5 ቀናት 💰 1,500 ብር 🤖 AI Tools for Content Creators የቆይታ ጊዜ፦ 5 ቀናት 💰 2,000 ብር 🌟 የተቀናጁ የስልጠና ፓኬጆች 🌿 Creator Package Content Creation + Video Editing ⏳ 10 ቀናት | 💰 4,000 ብር 🌳 Business Package Social Media Management + Content Strategy ⏳ 14 ቀናት | 💰 5,000 ብር ⭐ Digital Marketer Package Content Creation + Video Editing + Social Media Management + Digital Marketing ⏳ 21 ቀናት | 💰 7,500 ብር 📖 በስልጠናው የሚያገኙት፦ • ተግባራዊ ትምህርቶችና ልምምዶች • የContent አዘገጃጀት ስልጠና • በራስዎ ቢዝነስ ወይም በስራ ላይ መተግበር የሚችሉ ክህሎቶች • በስልጠናው ወቅት የሚሰጥ መመሪያና ግብረመልስ 📩 ለምዝገባና ለተጨማሪ መረጃ፦ Telegram: @alphabuyyer ክህሎት ይማሩ። በራስዎ ይተማመኑ። አዳዲስ የስራ እድሎችን ይፍጠሩ።
2 ¡ 156 ¡
🇾
Photo
🎬✨ 4 ቀናት ቆጥረን ጨርሰናል! ነገ ይጀምራል! ❤️‍🔥 ፍቅር… ምስጢር… ክህደት… እና የማይቀር ውጤት! 🥀 የመርየም፣ የያሲን እና የካሊድ ታሪክ ከነገ ጀምሮ ይገለጣል። 🎥 የፍቅር ዋጋ 📌 30 ክፍሎች • አንድ የተደበቀ እውነት • አዲስ ጅማሬ @Halal_memory ነገ አያምልጣችሁ! 👀❤️
❤6
229 ¡
L
አንዳንድ ጊዜ በልባችን ውስጥ ያለውን ሀዘን ለማንም መናገር አንችልም። ከፈገግታችን ጀርባ ብዙ የተደበቀ ህመም እንዳለ ማንም አያውቅም። ነገር ግን… ሰዎች ባይሰሙህም፣ አላህ ይሰማሃል። 🤲 ዱዓ ስታደርግ የልብህን ምስጢር ለአላህ ንገረው። ተስፋ ስትቆርጥ የአላህን ምሕረት አስታውስ። መንገዱ ሲከብድህም በሶላትና በዱዓ ወደ አላህ ቅረብ። @Halal_memory
❤4
96 ¡
🇾
የፍቅር ዋጋ ✍️ አሰል ክፍል 1 የመጀመሪያው ቀን ጠዋት ነበር። የከተማዋ ጎዳናዎች በሰዎች እግር እና በመኪና ድምፅ መሞላት ጀምረው ነበር። መርየም ግን በቤቷ መስኮት አጠገብ ቆማ ውጭውን ትመለከት ነበር። ዛሬ አዲስ ሴሚስተር ነበር። አዲስ ትምህርት፣ አዲስ ሰዎች፣ አዲስ ገጠመኞች። መርየም መስታወቱን አይታ ሂጃቧን አስተካከለች። ፊቷ ላይ ትንሽ ፈገግታ ታየ። “ዛሬ ሁሉም ነገር አዲስ ይሆናል።” እሷ ለሰዎች በጣም ብዙ የምትናገር ልጅ አልነበረችም። በጣም ብዙ ምስጢሮች ነበሯት። ከእነዚያ ምስጢሮች አንዱ ደግሞ ለወደፊቷ የምትመኘው ሕይወት ነበር። መርየም ድህነትን አትወድም። በገንዘብ ጭንቀት ውስጥ መኖርን አትፈልግም። ቀኑን ሙሉ ለገንዘብ መሮጥ አትፈልግም። እሷ የምትፈልገው ሌላ ነገር ነበር። ትልቅ ቤት። የተረጋጋ ሕይወት። ጥሩ ልብስ። መጓዝ። በገንዘብ የተረጋጋ ባል። እና በቤቷ ውስጥ በሰላም መኖር። “እኔ የምፈልገው ይሄን ነው።” ይህን ለማንም በግልጽ አትናገርም። ግን በልቧ በጣም ግልጽ ነበር። ቦርሳዋን ይዛ ከቤት ወጣች። ትምህርት ቤቱ ስትደርስ ጓደኛዋ ሳራ ከሩቅ አያት። “መርየም!” መርየም ዞር ብላ ፈገግ አለች። “ሳራ!” ሳራ እየሮጠች መጣችና እጇን ያዘች። “ዛሬ ምን እንደሚሆን ታውቂያለሽ?” “ምን?” “አዲስ ኡስታዝ መጥቷል አሉ።” መርየም ትንሽ ተገረመች። “ኡስታዝ?” “አዎ። አዲስ ነው። ስሙ ያሲን ነው አሉ።” “እና?” “እና ምን እንደሆነ ሰምተሻል?” “አልሰማሁም።” ሳራ በድምፅዋ ዝቅ አድርጋ እንዲህ አለች። “በጣም የተረጋጋ ሰው ነው አሉ። በዲን እውቀቱም ጥሩ ነው አሉ።” መርየም ትከሻዋን አነሳች። “እኔ ትምህርት ብቻ ነው የምፈልገው።” “እሺ እሺ። እንይ እንጂ።” ሁለቱም ወደ ክፍላቸው ገቡ። ተማሪዎቹ በየቦታቸው ተቀምጠዋል። ድምፅ በክፍሉ ውስጥ በዝቶ ነበር። ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በሩ ተከፈተ። የክፍሉ ድምፅ በድንገት ቀነሰ። አንድ ወጣት ኡስታዝ ወደ ውስጥ ገባ። ፊቱ ላይ የተረጋጋ ገጽታ ነበረው። በአካሄዱ ውስጥ ትዕቢት አልነበረም። “አሰላሙ ዓለይኩም።” “ወዓለይኩሙሰላም።” ተማሪዎቹ በአንድ ድምፅ መለሱ። እሱ በቀስታ ወደ ጠረጴዛው ሄደ። “ስሜ ያሲን ነው። ከዛሬ ጀምሮ የዲን ትምህርታችሁን እኔ እሰጣለሁ።” መርየም ዝም ብላ ትመለከተው ነበር። ምንም ልዩ ነገር አልተሰማትም። እስኪጀምር ድረስ። ያሲን መጽሐፉን ከፈተ። “ዛሬ ስለ አንድ ቀላል ነገር እንነጋገራለን። ኒያ።” አንዳንድ ተማሪዎች መጻፍ ጀመሩ። “ሰው አንድ ነገር ሲያደርግ ምክንያቱን ማወቅ አለበት። ምክንያቱ ካልታወቀ ሰው ራሱን እንኳን ሊያጣ ይችላል።” መርየም እጇን ቆም አድርጋ አዳመጠች። ያሲን ቀጠለ። “ለምሳሌ አንድ ሰው ሌላን ሰው ሲወድ ለምን እንደሚወደው ራሱን መጠየቅ አለበት። ለአላህ ብሎ ነው? ለገንዘብ ነው? ለዝና ነው? ወይስ ለራሱ ፍላጎት?” መርየም ወደ መጽሐፏ ተመለከተች። እነዚህ ቃላት በልቧ ውስጥ የሆነ ቦታ ነክተዋት ነበር። እሷ ራሷን ጠየቀች። “እኔ ምን እፈልጋለሁ?” ግን መልሱን ማሰብ አልፈለገችም። ትምህርቱ አለቀ። ተማሪዎቹ መጻሕፍታቸውን መዝጋት ጀመሩ። መርየም ግን አንድ ነገር አስተዋለች። በመጽሐፏ መካከል አንድ ትንሽ ወረቀት ነበር። እሷ ቀስ ብላ አወጣችው። በወረቀቱ ላይ አንድ ጥያቄ ብቻ ተጽፎ ነበር። “መርየም፣ በእውነት ምን ትፈልጊያለሽ?” ልቧ በፍጥነት መምታት ጀመረ። ወረቀቱን በድጋሚ አነበበችው። “ይህን ማን ጻፈው?” ወደ ፊት ተመለከተች። ያሲን ክፍሉን ለቆ ሊወጣ ነበር። “ኡስታዝ!” ያሲን ቆመ። “አ… Read in full →
❤10👍1
4 ¡ 413 ¡
Photo
#🕋🕋 የዘንድሮ የሀጅ ክፍያ 827,000 ብር ሆኗል። የዘንድሮው የሀጅ ምዝገባ ሐሙስ ጥቅምት 12/ 2019 በ33 የማስተባበሪያ ጣቢያዎች መካሄድ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አሳውቋል። አጠቃላይ ክፍያውም 827,000 (ስምት መቶ ሃያ ሰባት ሺህ) ብር እንደሆነ ተገልጿል። የሀጅ ምዝገባው ጥር 10 ቀን 2019 ይጠናቀቃል ተብሏል።
❤1
352 ¡
🇾
ወንጀሎቻችን ከሚያመጡብን ትልቁ መዘዝ ልባችን እና ኢማናችን ለሱ ዋጋ መክፈላቸው ነው ያ አላህ..ወደሱ ቀርበው ከተጠጉ በኋላ ወደኋላ ማለት ምን ያክል እድለቢስነት ነው @Halal_memory
❤2
306 ¡
ራስን መሆን! ራስህን ስትሆን ሰዎች ላይወዱህ ይችላሉ፤ አስቂኙ ነገር....አይነግሩህም እንጂ በውስጣቸው እነሱም እንዳንተ መሆን ይፈልጋሉ። ያ አኺ በምንም አይነት ከባድ ሁኔታ ውስጥ ያመንክበትን ከማድረግና ራስህን ከመሆን ማቆም የለብህም!
👍2
278 ¡
🦋
ነቢዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦ ﴿ما كرهتَ أن يراهُ الناسُ فلا تفعلهُ إذا خلوتَ﴾ “ሰዎች ቢያዩብህ የምትጠላውን ነገር ብቻህን ስትሆን አትስራው።” 📚 ሶሂህ አልጃሚ: 5659
🔥2👍2💔1
1 ¡ 293 ¡
Love what you are doing
ወደ ኋላ ስለቀረህ አትዘን፤ ወደ ፊት መሄድህን አታቋርጥ። ዛሬ የምትዘራው የጥረት ዘር ነገ ፍሬ ሊያፈራ ይችላል! መልካም ቀን
❤5
1 ¡ 255 ¡
የፈለግነውን ሳይሆን የሚበጀንን የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው፤ ምንም ያመለጠን ነገር የለም ያሰብነው ባይሆን የተሰጠንና ያላስተዋልነው ከምናስበው በላይ ሲደምቅ እናያለን። በጌታችን ፍጹም ውሳኔ ሁሌም ልባችን ሙሉ ነው… አልሐምዱሊላህ! 🤍”
❤6
1 ¡ 223 ¡
ዩሱፍን አለይሂ ሰላምን ሲያዩ እጃቸውን የቆረጡት እንስቶች የኔን ሙሀመድ ﷺ ቢያዩ ልባቸውን  በከተፉት ነበር አለች አዒሸቱ❤️‍🔥 አላህ አላህ! ሰሉ አላ ረሡሊላህ ﷺ 🤌 اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى سَيِّدِنَا مُحَمَّدٍ النَّبِيِّ الأُمِّيِّ الْحَبِيبِ الْعَالِي ا لْقَدْرِ الْعَظِيمِ الْجَاهِ وَعَلَى آلِهِ وَصَحْبِهِ وَسَلِّم የኔ ነቢ💚😘 ሰው እንሁን💚
❤3❤‍🔥3
1 ¡ 219 ¡
╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗ 📖 የፍቅር ዋጋ ❤️‍🔥 ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝ ✍️ አሰል ╔════•| ✿ |•════╗ #ክፍል_2️⃣ ╚════•| ✿ |•════╝ صلوا على رسول الله ﷺ 🤍 እሱ የሚያስተምረው ከመጀመሪያው ቀን በኋላ መርየም የያሲንን ጥያቄ ከአእምሮዋ ማውጣት አልቻለችም። “በእውነት ምን ትፈልጊያለሽ?” ይህን ጥያቄ በየቀኑ ለራሷ ትጠይቅ ነበር። መልሱ ግን አንድ ቀን አንድ ነገር፣ በሌላ ቀን ሌላ ነገር ይሆንባት ነበር። አንዳንዴ የምትፈልገው ብዙ ገንዘብ ነበር። አንዳንዴ የምትፈልገው ሰዎች ሲያዩዋት እንዲደነቁባት ነበር። አንዳንዴ ደግሞ ልቧ የሚረጋበት አንድ ሰው ብቻ እንዲኖራት ትመኝ ነበር። ግን ከእነዚህ ሁሉ የትኛው እውነተኛ ፍላጎቷ እንደሆነ እራሷም አታውቅም ነበር። “መርየም! አንቺ ከዛሬ ጀምሮ በአንድ ሰው ላይ ብዙ ማሰብ ጀምረሻል።” ሳራ ከጀርባዋ መጥታ ትከሻዋን ስትነካ መርየም ደነገጠች። “አይ እባክሽ! ማን ነው የማስበው?” “እኔ አላልኩም እኮ ማን እንደሆነ። ራስሽ መለስሽ!” “ሳራ! እባክሽ ተይኝ።” “እሺ እተውሻለሁ። ግን አንድ ነገር ልንገርሽ። ኡስታዝ ያሲን ዛሬ ከክፍል በኋላ አንዳንድ ተማሪዎችን ለልዩ የእውቀት ፕሮግራም ሊመርጥ ነው አሉ።” መርየም ፊቷን አነሳች። “ምን ዓይነት ፕሮግራም?” “የእስልምና እውቀት፣ የግል እድገት፣ የሕይወት ውሳኔዎች እና እንደዚህ ያሉ ነገሮች። ለምን? እንዳትመረጪ ፈርተሻል?” “እኔ እንዳልመረጥ ማን ነገረሽ?” ሳራ ሳቀች። “እኔ የምለው አሁን እንኳን በውስጥሽ ያለውን ነገር አልተረዳሽም። እንዴት ሌላውን ልትረዺ ነው?” “አንቺ ግን ለሁሉም ነገር መልስ አለሽ!” “አዎ፣ ለአንቺ ብቻ ነው የሌለኝ።” ሁለቱም ሳቁ። ⸻ ያን ቀን ክፍሉ ከተጠናቀቀ በኋላ ተማሪዎቹ በቀስታ እየወጡ ነበር። መርየም ደብተሯን ይዛ ልትወጣ ስትል የያሲን ድምፅ ሰማች። “መርየም፣ አንድ ደቂቃ ቆይ።” ልቧ በድንገት ተመታ። ለምን ጠራኝ? ምን አደረግሁ? የትናንቱን ወረቀት አይቶት ይሆን? ወደ እሱ ተመለሰች። “አዎ፣ ኡስታዝ?” ያሲን በእጁ የያዘውን ወረቀት አሳያት። “በፕሮግራሙ ውስጥ ለመሳተፍ ፍላጎት አለሽ?” መርየም በፍጥነት መለሰች። “አዎ፣ አለኝ።” “ለምን?” ይህ ጥያቄ እሷን አስገረማት። “እውቀቴን ለማሳደግ።” ያሲን ትንሽ ፈገግ አለ። “ይህ ጥሩ መልስ ነው። ግን እውቀትሽን ለማሳደግ ብቻ ነው? ወይስ ሰዎች እንዲያዩሽ እና እንዲያደንቁሽ ትፈልጊያለሽ?” መርየም በቃላት መካከል ተያዘች። “ኡስታዝ፣ ሰው እንዲያደንቀው መፈለግ ስህተት ነው?” “ሰው ጥረቱ እንዲታይለት መፈለጉ በራሱ ስህተት አይደለም። ግን ለማን እንደምትሠሪ ማወቅ አለብሽ። ሰዎች ሲያደንቁሽ ብቻ ደስተኛ ከሆንሽ፣ አንድ ቀን ሲተቹሽ ምን ታደርጊያለሽ?” መርየም ዝም አለች። ያሲን ወረቀቱን ሰጣት። “ይህን ሞልተሽ ነገ አምጪ። ለመሳተፍ ከፈለግሽ በእውነት ተሳተፊ። ለሰዎች ለመታየት ብቻ አትሁኚ።” መርየም ወረቀቱን ተቀብላ ከክፍሉ ወጣች። የተናገረው ነገር ቀላል ነበር። ግን ለምን በውስጧ እንደተቀመጠ አልገባትም። ⸻ ምሽት ላይ ቤት ስትደርስ እናቷ በኩሽና ውስጥ እራት እያዘጋጀች ነበር። “መርየም፣ ደረስሽ ልጄ?” “አዎ እማዬ።” “ዛሬ ደክሞሻል?” “ትንሽ።” እናቷ ወደ እሷ ተመለከተች። “ምን ሆነሻል? ከትናንት ጀምሮ ብዙ ታስቢያለሽ።” መርየም ፈገግ አለች። “ምንም አልሆነም እማዬ። ስለ ወደፊት ሕይወቴ እያሰብኩ ነው።” እናቷ እጇን በማድረቅ ወደ እሷ ተዘዋወረች። “ስለ ወደፊት ማሰብ ጥሩ ነው። ግን ልጄ፣ የምትመኚው ሕይወት በገንዘብና በቤት ብቻ እንዳትለኪው።” … Read in full →
❤1
2 ¡ 149 ¡
🇾
ግን አንድ ነገር አልተረዳችም። አንድ ቀን የምትፈልገውን ሕይወት ለማግኘት ስትሮጥ፣ ከራሷ የተደበቀ እውነት ጋር መጋጠሟ አይቀርም። ⸻ በዚያው ምሽት… ያሲን በቤቱ ውስጥ ተቀምጦ የፕሮግራሙን ወረቀቶች እያየ ነበር። አንድ የተለየ ስም በዓይኑ ላይ ቆመ። መርየም። ወረቀቷን አንስቶ መልሷን እንደገና አነበበ። “ግን ለዚያ ሕይወት ስል ምን እንደማልጠፋ ገና አላውቅም።” ያሲን ለራሱ በቀስታ አነበበው። ከዚያ ወረቀቱን አስቀምጦ ወደ መስኮቱ ተመለከተ። “አላህ ሆይ፣ ልቧን ወደ ትክክለኛው መንገድ ምራት።” ስልኩ በድንገት ጮኸ። ያሲን ስልኩን አንስቶ ተመለከተ። ከአንድ የቀድሞ ጓደኛው መልዕክት ነበር። “ያሲን፣ ነገ መገናኘት አለብን። ስለ አንድ ሰው ልነግርህ የምፈልገው ነገር አለ። ይህ ጉዳይ ከቀድሞ ሕይወትህ ጋር ይያያዛል።” ያሲን ፊቱ ተቀየረ። መልዕክቱን ሁለት ጊዜ አነበበው። ከዚያ በስልኩ ላይ ያለውን ስም ተመለከተ። ካሊድ። ያሲን ለጥቂት ጊዜ ዝም አለ። “ካሊድ… ከእኔ ምን ይፈልጋል?” እሱ ገና አላወቀም። ይህ ስም በመርየም ሕይወት ውስጥ የሚኖረውን ትልቅ ቦታ እንደሚይዝ አልገመተም። ክፍል 2 ይቀጥላል… 📌 ለቀጣዩ ክፍል ይጠብቁ። @halal_memory
❤2
1 ¡ 155 ¡
🇾
🇾🇪🇪🇹
╔═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╗ 📖 የፍቅር ዋጋ ❤️‍🔥 ╚═══❖•ೋ° °ೋ•❖═══╝ ✍️ አሰል ╔════•| ✿ |•════╗ #ክፍል_🔟 ╚════•| ✿ |•════╝ صلوا على رسول الله ﷺ 🤍 ወሬው ከየት መጣ? በማግስቱ ጠዋት መርየም ከሳራ ጋር ተገናኘች። ሳራ ከሩቅ እንዳየቻት ፈገግ አለች። “እንዴ! ዛሬ ፊትሽ ላይ ጭንቀት አልታይም። ካሊድ የልብሽን ጥያቄ መለሰልሽ እንዴ?” መርየም ፈገግ አለች። “አንቺ ከማሾፍ ውጭ ሌላ ሥራ የለሽም?” “አለኝ። አንቺን ማስተካከል!” ሁለቱም ሳቁ። ከዚያ መርየም ወደ ጉዳዩ ተመለሰች። “ሳራ፣ ስለ ያሲን የነገርሽኝን ወሬ አሁንም እያሰብኩበት ነው። ግን አንድ ነገር አልገባኝም። ይህን ወሬ ከየት ሰማሽው?” ሳራ ትንሽ ዝም አለች። “ከአንዲት ልጅ ነው። ከሌላ የእውቀት ክፍል ትማራለች። እሷ ከዚህ በፊት ያሲንን እንደምታውቀው ነግራኛለች።” “ስሟ ማን ነው?” “ሊና ትባላለች። ግን መርየም፣ እባክሽ አሁን ሄደሽ አትጠይቂያት። እንደዚያ ነገር አታድርጊ።” መርየም በጥሞና አየቻት። “እኔ ማንንም ልጎዳ አልፈልግም። እውነቱን ብቻ ማወቅ ነው የምፈልገው።” ⸻ በዚያው ቀን ከሰዓት በኋላ ካሊድ ከእናቱ ጋር ስለ መርየም ተነጋገረ። “እናቴ፣ በቅርቡ ወደ ቤተሰቧ ሄደን መነጋገር እፈልጋለሁ።” እናቱ ፈገግ አሉ። “ጥሩ ነው። ግን ልጄ፣ ስለ እሷ በቂ መረጃ አለህ?” “ እያወቅኋት ነው።” “እንግዲያውስ እሷም አንተን እንድታውቅ እድል ስጣት። ትዳር የሚጀምረው በጥሩ ፎቶ ወይም በጥሩ ቤት አይደለም። በመተማመን ነው።” ካሊድ ራሱን ነቀነቀ። “አውቃለሁ፣ እናቴ።” እናቱ ትንሽ ቆይተው ጠየቁት። “አንድ ነገር ግን ልጠይቅህ። ይህችን ልጅ የመረጥካት ስለ ማንነቷ ነው ወይስ በሌላ ምክንያት?” ካሊድ ፈገግ አለ። “እናቴ፣ አንዳንድ ጊዜ አንቺ ከአባቴ የበለጠ ጥያቄ ታበዢያለሽ።” “ስለዚህ ነው እናት የምባለው።” ⸻ ከቀናት በኋላ መርየም በፕሮግራሙ ዝግጅት ላይ ስትሳተፍ ሊናን አየቻት። ሳራ ያቺ እንደሆነች በአይን ምልክት አሳየቻት። ሊና ረጅም ጊዜ ሳትቆይ ወደ መርየም ቀረበች። “ሰላም። አንቺ መርየም ነሽ?” “አዎ። አንቺ ሊና ነሽ?” ሊና ትንሽ ተገረመች። “ስሜን እንዴት አወቅሽ?” መርየም ፈገግ አለች። “ከሳራ ሰምቻለሁ።” ሊና ትንሽ ዝም አለችና እንዲህ አለች። “እንግዲያውስ ስለ ያሲንም ነግራሻለች?” መርየም በቀጥታ መለሰች። “አዎ። ግን እኔ ወሬ ለመስማት አልፈልግም። እውነቱን ካወቅሽ በእርጋታ ንገሪኝ።” ሊና ዙሪያዋን አየች። “እዚህ አይደለም። ከፈለግሽ ከፕሮግራሙ በኋላ እናወራለን።” መርየም ራሷን ነቀነቀች። ⸻ ፕሮግራሙ ካለቀ በኋላ ሁለቱ ልጆች በሌሎች ሰዎች አጠገብ ተቀምጠው ተነጋገሩ። ሊና ጀመረች። “ያሲንን ከዚህ በፊት አውቀዋለሁ። በአንድ ፕሮግራም ላይ ነበርን። በዚያን ጊዜ ከእሱ ጋር የሚቀራረቡ ሴቶች ነበሩ።” መርየም በጥንቃቄ አዳመጠች። “እና እሱ ከእነሱ ጋር ግንኙነት ነበረው?” “አንዳንድ ነገሮችን በግልጽ አላውቅም። ግን ከአንዲት ልጅ ጋር በጣም ተቀራርቦ ነበር። ከዚያ በኋላ ነገሩ ተቋረጠ።” “ስሟ ማን ነው?” ሊና ትንሽ አመነታች። “ሂባ ትባላለች። እሷ ግን አሁን እዚህ አትመጣም።” መርየም በጥሞና ጠየቀቻት። “እነሱ በእውነት ፍቅር ነበራቸው?” “እኔ የማውቀውን ብቻ ነው የነገርኩሽ። ከዚያ በላይ ራሳቸው ያውቃሉ።” መርየም አመሰገነቻትና ተለያዩ። ነገር ግን ከሊና የሰማችው ነገር ከሳራ የሰማችውን ወሬ አላረጋገጠም። የበለጠ ጥያቄ ብቻ ፈጠረባት። ⸻ በዚያው ምሽት ካሊድ ለመርየም መልዕክት ላከ… Read in full →
❤4
1 ¡ 100 ¡
🦋
🦋𝖗𝖎𝖈𝖍🦋
አላህ እንዲህ ይላል፦ 📖 ﴿وَأَقِمِ الصَّلَاةَ لِذِكْرِي﴾ «ለማስታወሴ ሶላትን አቋቁም።» 📚 ሱረቱ ጣሃ 20:14 ሶላት ከአላህ ጋር ያለህን ግንኙነት ከሚያጠናክሩ ታላላቅ የአምልኮ ተግባራት አንዱ ነው ዱንያ በሥራ ሊያጣድፍህ ይችላል ለሶላት ግን ጊዜ ስጥ ሶላትህን አትተው።
7 ¡

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About ¡ FAQ ¡ Index limits ¡ Remove a page ¡ Catalog ¡ Search ¡ How we count