English
Open in Telegram
ቀቀልበን ሰሊም✨

ቀልበን ሰሊም✨

@Heart_ware · channel · Education · indexed since 2026-09-28
379subscribers
85average post reach
22.4%ER — reach to subscribers
3posts in 30 days
ቀልበን ሰሊም✨
✅ ማን አመጣሽ ከእለታት ፩ ቀን የቤታችን በር ተንኳኳ። ጓደኞቼ ነበሩ። አበባይሆሽ አትጨፍሪም አሉኝ። ሃሳቤ አልነበረም ከተኛሁበት ተነስቼ  የምወዳቸውን ጓደኞቼን ተከትዬ ስሄድ ምናልባትም ለመጨረሻ ግዜ ነው። አካባቢያችን ብዙ ካ'ፎች ስለነበሩ በነሱ ስር ነው ያደግነው። የመግሪብ አውራድ ይመስል 1:00pm መሆኑን ምናውቀው በጽናጽልና ደውል በሚጀመረው አባታችን ሆይ ሲሆን(ب ፪ሃረካ መድ አላት) : ሱብሂ መፈጀሩንም የምንረዳው 10:30pm በምንሰማው ቅዳሴ ነው። በተለይ ነገታው ሰንበት ከሆነ ቀደም ብሎ 9:00pm ይጀምራል። እኛ ሰፈር ቀናቶች 44 ይመስሉኛል ፩ወር ፬፬ቀናት። ከልጆች ጋር ስንጫወት 1 እንትና 2..በእናንተ እንትና በኛ..እያልን እንቆጥራለን። ቀናቶቹን ቆጥሮ ጠበል ጻዲቅ ማቅመስ፣ በእንትና ስም ተብሎ የስንዴ ዳቦ መስጠት የተለመደ ነው። በተለይ የአመቱ ከሆነ ይደገሳል። የ*ቀን በ1 ቀኑን ይዘመርና ማታውን በጭፈራል ይቀወጣል, ? የዚህ ቀን የሰፈር ሰው ሁሉ ብር አዋቶ ሰፈሩ በንፍሮ ይታጠናል። ልጅነት የማያነባቸው ብዙ ሺርኪያቶችም ይኖራሉ። በዙሪያችን ፬ ቤ.Christians ነበሩ። ሁሌም ጠዋት school ስሄድ በር ላይ ቆመው ወደ ፈረንሳይ ዞር ይሉና ሚካኤል አንተ ፍረድ የሚሉትን እናት ሳይ እገረማለሁ። ‛በህልሜ ፈረንጅ አየሁ ላላቸው ሰው ሚካኤል ነው’ ይሉት ነበር። ከትምህርት መልስ ለጨዋታ ስንወጣ አባባ ቄሱ..እያሉ መዘመር ቄሱ የቤተሰባችን አባል እስኪመስሉኝ ድረስ ተቀርጾብኛል። ልክ ሰፈራችን ሲመጡ እየተሯሯጥን ሄደን እንሳለማለን። ኋላ ላይ ትንሽዬ ከፍ ስል መሳለሙ ቀርቶ ሳያቸው እየፈራሁ እደበቅ ነበር። ፍራቻውን ምን እንደፈጠረው ባላውቅም ቄስ/የሚለምን ሰው ከመጣ እኔ ሩጫዬ ነው። የሚወስዱኝ ይመስለኛል። ቅዳሜ ቀን ሲደርስ የጠበል ውሃ መድሀኒት ነው እየተባለ እንድናመጣ እንላካለን። የጠበል ሰልፍ ላይ ሂጃብ የለበሰች ሴት ማግኘት የተለመደ ነው። አይሄዱም የተባሉት እንኳ ከጎረቤት 3L ጠበል ተቀብለው ይጠጡታል። እጣው ደርሶብኝ ፩ ቀን ጎረቤቴ ይዛኝ ሄደች። በሩጋ ስንደርስ መሳለምና መስገድ ሲጀምሩ ቀጥ ብዬ ትቻቸው ገባሁ።እውቀቱ ባይኖረኝም ዲን ግን በልቤ ነበር። በግቢው ስፋት እየተደነኩ ሳለ ከውሃው እንድጠጣ ሰጡኝ። ወተት ወተት ይላል። አይ ልጅነት ምናልባትም ወተት እወድ ስለነበር ይሆናል። እቃ ተልኬ የትኛውም ቤት ብገባ ቀድሜ ማየው ደማቅ ቀለማት የሰፈሩበት ስእለ አድኖ ነው። ከዛ ከስራቸው የተጻፈ ገድል። ሁሉንም አነባቸዋለሁ። አንድ በአንድ ስመለከት በ1እጁ ግልገል ይዞ በሌላኛው☝️ብሉ የቆመውን ስእል ሳይ አያቴ: ይኸው ይህኮ 1 አላህን እያስተማረ ነው ያለችው ትዝ ይለኛል። እንደዛሬው እንቁጣጣሽ ከመድረሱ በፊት 5/6 የጳጉሜ ሌሊቶች ይዘመራል፣ ጠዋቱን ደግሞ ሰው ሁሉ ባዙን አውጥቶ ዝናብ ይሻማል። ሄዱ ይዝነብባችሁ መድሃኒት ነው ይሉንና ስንራጭ እንውላለን። ሌሎች በአሎችም ለመስቀልና ቡሄ እንጨት ሰብስበን ዳመራ እንሰራለን፣ አደይ ቀጥፈን መስቀል እናረገዋለን፣ ችቦ ሽጠን ብር ለምነን ceremony እናዘጋጃለን። ዝናብ እንዳይዘንብ እንጸልይና ማታ ችቦ መቃጠል ሲጀምር ሁሌም የሚያስገርሙኝ እነዛ ግጥሞች ይዘመራሉ። እንጨት ሰብሬ ቤት እስክሰራ እንኳን ቤትና የለኝም አጥር እደጅ አድራለሁ ኮኮብ ስቆጥር (እኔ ቤታችን ትዝ ይለኝና...እገረማለሁ) እሳቱ ተፋፍሞ የአደዩ መስቀል ጋር ሲደርስ አውርዱት መስቀሉ እንዳይቃጠል ይባልና ይወርዳል። ሌላም 1 መዝሙር ነበር አላስታውሰውም ብቻ እነሱ እንደ አዝማች * ብለው ሲጠሩ ጓደኛዬ አላህ በይ ይለኝና እነሱ ሳያውቁ አላህ እያልን አብ… Read in full →
4 · 352 ·
ቀ
👆እና በዓል እንዴት አለፈ ..? ኧረ ወገን 🏃 ጁሙዓን ማለቴ ነው !! ሳምንታዊ ..
1 · 198 ·
ቀልበን ሰሊም✨
ማስታወሻ‼️ ~ ለ2019 እስቲ የራሳችሁ Telegram Saved ዉስጥ  ከአላህ ጋር ማሳካት የምትፈልጉት እቅዶችን ፃፉዋቸዉ!! ከዛ pin አርጉት! በየ ሶስት ወሩ እራሳችሁ ፈትሹ! እራሳችሁ ገምግሙ!!አላህ እንዲያሳካላችሁ ዱዓም አርጉ! ~ እኛ እናቅዳለን የሚያሳካዉ አላህ ነዉ! ዝግጁ ናችሁ?አዉ👍 t.me/abukiweb
1 · 190 ·
ቀ
ከሰው አለመጠበቅ ልብን ከክፋት ለማራቅ ሁነኛ መፍትሄ ነው !!
1 · 190 ·
ቀ
ቀልበን ሰሊም✨
Photo
ታገሱ መታገስ ዋጋ አለው !!
226 ·
ቀ
ቀልበን ሰሊም✨
ሹፍ ያሰላም እጅግ የሚገርመው ነገር ሙሳ (ዐ.ሰ) የንግግር ድክመትና በምላሳቸው ላይ  እሰር (ዕንቅፋት) የነበረባቸው ሆኖ ሳለ ያለ መላክተኛ እና ያለ አንዳች ግርዶሽ) #በቀጥታ_ከአላህ_ጋር  ከተነጋገሩት ብቸኛው ነቢይ መሆናቸው ነው። ​ስለዚህ በሰዎች ፊት የሚጎድልብህ ወይም የሚቀንስብህ ነገር ፈጽሞ አያሳስብህ፤ በጌታህ ዘንድ ከፍ የሚያደርግህ የልብ ንጽህናና እውነተኛ  ኢማን ካለህ ያ በቂ ነው። ©
196 ·
ቀልበን ሰሊም✨
እነዛ ወቅቶች ይመጣሉ .. ስኬትን ፍለጋ ልባችን የሚደሙባቸው!! be strong ،،
187 ·
ቀ
Photo
በንጹህ ልብ የተሰጠኝ ውድ ስጦታዬ..🤌 የኔ🌸
214 ·
ቀ
ቀልበን ሰሊም✨
Audio
ሰላም_ለልብሽ_አብዱልሀኪም_ሰፋ.mp3 · 4.0 MB · click to show
እቴ..እድለቢስም ሆነ ዋጋ የሌለሽ አይደለሽም : የፈተናዎችሽና የህመሞችሽ አስቀያሚነት ያንቺ መልክ አይደሉም !! 🌹🌹
1 · 200 ·
ቀልበን ሰሊም✨
ክብር ~ ተሽጦ ፍቅር ~ አይገዛም ። 🤝 ©
1 · 177 ·
ቀ
Photo
እናምልጥ .. ሰዎች በፍቃዳቸው ከሰሩብን ጠባብ ጎጆ፣ ከካቡብን የድንጋይ አጥር፣ ካሰመሩብን የህይወት መስመር እናምልጥ። በራሳችን ነጻ ሃሳብ ፈሰን ካሻን ባህር ጠልቀን እንደውቅያኖስ እንግዘፍ። የደረቱብን አጓጉል የልማድ ድሪቶዎች አቅላችንን ነቅለው ሳያስነቅሉን ቀድመን ከዝቅታቸው እንፈንቅል። ከጫኑብን የጭንቅ ጭነቶች አቧራውን ሳይቀር እናራግፍ። ስንቱ ነቀለ፣ ስንቱ ተሰቀለ። ስንቱ ከእይታ እርቆ አልቆ ቀረ። እንተዋት እቺን ዱንያ፣ ከነ-አጫፋሪዎቾ ፣ ከናወጡላት ህጋቸው፣ ቀደው ከሰፉላት ልኳ ጋር እንተዋትና እንደሰት። በራሳችን ዓለም እንፍሰስ። እናምልጥ ..!! ✍✍
2 · 246 ·
ቀ
ቀልበን ሰሊም✨
Photo
መወደድ ብቻ ሳይሆን መውደድም መሰጠት'ን ይፈልጋል !!
2 · 213 ·
ቀ
ቀልበን ሰሊም✨
ምን ያስቀናሃል ..? በዒባዳ የታለፈ ወጣትነት ،,
2 · 160 ·
ቀልበን ሰሊም✨
ኖሮ መሞት ..؟ ሰው ባልፈለገው ዓለም እየባዘነ፣ ያላሰኘውን እየበላና እየጠጣ፣ ያልወደደውን እየተማረና እየሰራ፣ ያልመረጠውን እያጨና እያገባ፣ ... በውሸት ሳቅ ተሳቆ ጉንጩ እስኪጣበቅ ከሰው ይሉኝታ ተጠንቅቆ እየኖረ ኖርኩ ሲል አያፍርም? ለምን ይፈር ሆ አኗኗሪዎቹም አላፈሩ!! ግድ የለንም ልማድን መጣስ ፋሽን የሚሆንበት ሰአት አልፏል ብዬ አልልም። ሳልኖር ኖርኩ ብዬ አልዋሽም። ሌላው ቢቀር ኖረ..ሞተ ለመባል እራሱ መኖር ያስፈልጋልኮ ሆሆ!! እውነታው አለመኖርን መኖር ነው። ልማድን ለመጣስ ሃይል አለህ?? "ከዲን ዝንባሌ የራቁ ኋላ ቀር ልማዶች!!" እርሶም ቢሆኑ የሚሉትን ይበሉኝ👇👇 @OurFeedback123_bot
1 · 165 ·
ቀ
Voice message
123 KB · click to show
الصلاة على النبي المصطفى صلى الله عليه وسلم 💐
1 · 156 ·
ቀ
ቀልበን ሰሊም✨
ወረቀት ፍቅር ነው : መጻፍ ደግሞ እስትንፋስ., እኛ ደግሞ ያለሁለቱ ነፍስ የማንዘራ ስጋ ለባሽ ፍጡር ህህ!! ✍✍
171 ·
ቀ
ቀልበን ሰሊም✨
በሰዎች ውስጥ ደስታን ፈልግ። ምግብህን አጋራቸው፣ ሸክማቸውን አቅልላቸው፣ ሃሳባቸውን ተካፈላቸው፣ የደስታ ምንጭ ሁንላቸው, ..... ሰው ለሰው መድሃኒቱ ،،
161 ·
ቀልበን ሰሊም✨
ታሞ ነበረ ዳነ፤ አጥቶ ነበረ አገኘ፤ አዝኖ ነበረ ሳቀ! ለመባል አላህ ያብቃችሁ፤ ያብቃን።
93 ·
ቀ
ቀልበን ሰሊም✨
ከቀደምቶች 1 ሰው: 1 ቀን ላንተ ይሆናል 1 ቀን ደግሞ በአንተ ላይ ይሆናል ። ላንተ በሚሆን ቀን አመስግን፣ ባንተ ላይ በሚሆን ጊዜ ታገስ። ቀደር የህይወት ሚዛን ናት👌
2 · 132 ·
ቀ
ቀልበን ሰሊም✨
ሃጥያት እስር ቤት ነው። ነፃ የመውጫው በሩ ተውበት ሲሆን ወደ አላህ መመለስ የደስታ ምንጭ ይሆናል። አላህን በማመጽ ውስጥ የ2 ሃገር ስቃይ ሲኖር እሱን መገዛት ደግሞ ዘላለማዊ ስኬትን ያቀዳጃል።
1 · 123 ·
ቀ
ቀልበን ሰሊም✨
ቀይ መስመር በህይወታችን ማንደራደርባቸው ነጥቦች ሊኖሩ ይገባል። በተለይም ሸሪዓችንን አጥብቀን ልንይዝ በሱም ልንጸና ግድ ይሏል። ወጣ ገባ ማለቱ የኻቲማችንን ነገር አሳሳቢነት ያገዝፈዋልና ጠንቀቅ ብንል ሻል ያለ ነው። በ1 ተራ ስሜት ምክንያት የምናጣው 1ወጣት አይደለም። ይልቁንስ ትውልድ የሚቀይር ጀግና ነው። አንድ ዛፍ ቢወድቅ ስንት ቅርንጫፎች ይሰበራሉ። የስንት አዕዋፋት ቤት ይፈርሳሉ። 1 ሴት አይደለም የምናጣው ከሷ የሚተካውን መልካም ዘር ጭምር ነው። ተስፋዋን ፣ ዓላማዋን ነው። የህልም መሰበር፣ የህይወት መታወክ፣ የዓላማ መሰናከል ምክንያቱ 1 የስልክ ጥሪ ሊሆን ይችላል። 1 እይታ፣ 1 ፈገግታ፣ 1 ሰላምታ ሊሆን ይችላል። የአላህን ድንበር መተላለፍ ቅሉ መግቢያው ቢቀልም መውጫው ግን ከባድ ፈተና ነው።
106 ·
ቀ
ቀልበን ሰሊም✨
Photo
ይሄ ነገር እንዴት ነው ? አያስፈልገንም ትላላችሁ እ ،،
98 ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · Index limits · Remove a page · Catalog · Search · How we count