English
Open in Telegram
☾☾⋆ 𝐇𝐚𝐥𝐚𝐥 𝐕𝐢𝐛𝐞𝐬 𓇢𓆸

☾⋆ 𝐇𝐚𝐥𝐚𝐥 𝐕𝐢𝐛𝐞𝐬 𓇢𓆸

@Muslima122 ¡ channel ¡ indexed since 2026-07-25
227subscribers
68average post reach
30%ER — reach to subscribers
72posts in 30 days
🦋𝕣𝕒𝕙𝕒𝕥🦋
ቁርኣን የልቦች ብርሃን 🌟 ... የህይወት መሪ እና የነፍስ እረፍት ነው። በቀን ውስጥ እንኳን ጥቂት አንቀጾችን ማንበብ 📖 ... ትርጉሙን ማስተንተን እና በህይወታችን ላይ መተግበር የውስጥ ሰላምን እና የአላህን እዝነት ያጎናጽፋል። @Muslima122
54 ¡
🦋
መድረሻ አልባ ክፍል ስድስት 6 'መድረሻ አልባ ደብዳቤዎች 4' አሰላሙ ዋአለይኩም ወራህመቱላህ! ካሊድ ምን እንደምልህ አላውቅም በጣም እንዳዘንክ አቃለሁ በዳኒ ሞት አላህ ሰብር ይስጥህ!እኔም በጣም ነው ያዘንኩት………...ግን ካሊድዬ የዳኒ ሞት አንተን የመከረህ ይመስለኛል ዝምተኛው መካሪም አይደል!(ለምን አልኩ?) ከዳኒ ቤተሰቦች ቤት ስንወጣ መፅሐፍ ጠየከኝ እናም መለወጥ እፈልጋለሁ አልከኝ።እውነት ኾኖ ከተቀየርክ አልሐምዱሊላህ! አላህ ልመናዬን ተቀብሎኛል ማለት ነው።የዳኒ ሞት መክሮሃል ሰበብ ሆኖሃል ያልኩት ለዚ ነው። እውነትም ዝምተኛው መካሪ! ከሞት በላይ ምን መካሪ አለ! ደሞ እንዴት እሱን መፅሐፍ ሠለሀዲን ጋ አጣኸው?ግን እንኳንም አጣኸው ካንተ ጋ በደንብ ለመቀራረብ ምክንያት ይሆነኛል እናም በአንድ መፅሐፍ እንዳንለያይ ሌላ መፅሐፎችንም እጨምርልሃለሁ ኢንሻአላህ! አንተንም አላህ ይምራህ! ያፅናህ! 'መድረሻ አልባ ደብዳቤዎች 5 "ሲኦል ምንድነው ብትሉኝ፤ማፍቀር ካለመቻል የሚመጣ ስቃይ ነው እላችኋለሁ።” (ፊዮዶር ዶስትዮቭስኪ) “ፍቅር!መስዋዕትነት ነው።ፍቅር ማለት መስጠት እንጂ መቀበል አይደለም፤ማሰብ እንጂ መታሰብ አይደለም፤ፍቅር ማለት ለማስደሰት መቻል ነው" (የሺጥላ ኮከብ) 'እስካሁኗ ደቂቃ ድረስ የፍቅርን ውስጠ ምስጢር የሚተነትን ፅሁፍ ለማዘጋጀት ድፍረቱን አላገኘሁም።ሲመስለኝ ያለን እውቀት ሁሉ ፍቅርን አሟልቶ ለመተንተን በቂ አይደለም.......አሁንም ስለ ፍቅር የምናውቀው በጣም ጥቂቱን ነው”(ሲግመንድ ፍሩድ) (ባለፈው በዚ እጀምርልሃለሁ ብዬ ነበር) አልሐምዱሊላህ! አሁን የምፈልገውን ካሊድ እየሆንክ ነው(በዚህ ያስቀጥልህ) ት/ቤትም መስጂድ ስትሄድ አይቼሃለሁ።ደስ ብሎኛል አባዬም ደስ ብሎታል።አዎ አባዬ ግራ ሊገባህ ይችላል፤ከአባቴ ምንም የምደብቀው ነገር የለኝም አንተን ካየሁህ ቀን ጀምሮ የተሰማኝን እና የሆነውን ኹሉ እየነገርኩት ነው።የሰጠሁህን መፅሐፎች ብዙዎቹን እሱ ነው እያመጣ ይኼን ስጪው እያለኝ የነበረው።ላንተ የተሰማኝን ስሜት ስነግረው'ሰዐዳዬ አንቺ ወደ ሐራም ነገር እንደማትሄጂ እርግጠኛ ነኝ።ኢንሻአላህ አላህ ካለ ትምህርታችሁን ስትጨርሱ ከእናትሽ እና ከወንድምሽ ጋ ተመካክረን እሱንም አናግረነው መልካም ፍቃዱን ካገኘን ኒካህ ታስሩና ትምህርታችሁን (University ) ትቀጥላላችሁ።አሁን ግን ትምህርትሽ ላይ ትኩረት አርጊ" አለኝ። ካሊድዬ ግን አንተ ትወደኝ ይኾን? 'መድረሻ አልባ ደብዳቤዎች 6' አሠላሙ ዋአለይኩም ወራህመቱላህ! ካሊድ(ዬ) እንዴት ነህልኝ?እኔ አልሐምዱሊላህ! አሁን እኮ ከእናትህ ጋርም ተዋወኩ።እንዴት ደስ የምትል እናት ነው ያለህ!ከሷ ጋ ማውራት እንዴት ያስደስታል! እና አልሐምዱሊላህ ተስተካክለሃል ደሞም በዚሁ ከቀጠልክ ከኤልያስ ትበልጣለህ(ማነው ኤልያስ?ትለኝ ይኾናል) ትናንት አንብቤ የጨረስኩት መፅሐፍ ላይ ያለ ልጅ ነው።እዛ መፅሐፍ ላይ የተስተካከለችው ሲሃም ስትሆን እዚህ ደሞ አንተ(የኔ ካሊድ)! ታሪካቸው እንዴት ደስስ እንደሚል እነ ሙኽታር፣ኸውለት፣ራህማ...... በቃ የበለጠ መፅሐፉን እሰጥህና ታነበዋለህ።እነዚህን ደብዳቤዎቼንም እሰጥሃለሁ እናም መድረሻ አልባ የነበሩት ፅሁፎቼም በአላህ ፍቃድ መድረሻ አግኝተዋል!! አልሐምዱሊላህ!!!!!! አንብቦ ጨረሰ።ሁሉንም እንደነበረ አጣጥፎ መፅሐፉ ውስጥ አስቀመጠ።ለሱ እየተሰማው የነበረው ስሜት እሱ ጋ ብቻ ባለመቅረቱ ደስ አለው። -ጠዋት ላይ ቁርስ ሰርቶ ከእናቱ ጋ ከበሉ በኋላ እሳቸውን እየጠየቀ ቡና አጥቦ፣ቆልቶ፣ፈጭቶ አፍልቶላቸው ቁጭ ብለው እያወሩ "እማ! አንድ ነገር ልነግርሽ ነበር" አላቸ… Read in full →
73 ¡
🦋𝕣𝕒𝕙𝕒𝕥🦋
Btw ትክክለኛው ሰው ማለት  🤝 ፍፁም  የሆነ ወይም ስህተት የማይሰራ አይደለም I there's a person ከባድ ጊዜያት ውስጥ ስትሆን no matter what  happens እጅህን የማይልቅ 🙌 ፣ judge ሳያደርግህ ህመምህን የሚጋራ and ከጎንህ የሚቆም ሰው ማለት ነው። 💪 @Muslima122
65 ¡
ታገስ 🙏 ሁልጊዜም በህይወት መነሻህና መድረሻህ ስታስበው ቀላል ነው፤ መሀሉ ግን አይነገርም! ⚠️ አየህ ፈተናው፣ ተስፋ መቁረጡና ከባዱ ጊዜ ያለው መሀሉ ላይ ነው። ይሄን ወሳኝ ጊዜ በጥበብ ልታልፍ የምትችለው በአንድ ነገር ብቻ ነው 'በትዕግስት!' 💪 ወዳጄ ታገስ አለበለዚያ ምንም ብትለፋ ህይወትህን አትቀይርም! @Muslima122
59 ¡
🦋
መድረሻ አልባ ክፍል ሰባት -የፈተና ጊዜያቸው እየቀረበ ነው ሁለት ሳምንት የማይሞላ ጊዜ ነው የቀራቸው።እነ ካሊድም በደንብ እየተዘጋጁ ነው።ሐሙስ ማታ ካሊድ ኢሻ ሰግዶ ቤት ገብቶ እራት በልቶ ከእናቱ ጋ ካወሩ በኋላ ክፍሏ አስገብቶ አስተኝቷት ግንባሯን ስሞ ወደ ክፍሉ ኼደ። ጁምዐ ጠዋት መስጂድ ሄዶ ሱብሂ ሰግዶ ተመልሶ መጣ።እስካሁን እናቱ አልተነሳችም "እማ!" እየተጣራ ክፍሏ ገባ።አልመለሰችም፡፡"እማ አመመሽ እንዴ?" ብሎ ሄዶ ሲያያት ትንፋሿ የለም፡፡"እማ! እማዬ!" አትመልስም፡፡ ወደማይቀረው ጉዞ(ሞት)ሄዳለች፡፡ ካሊድ ደነገጠ ራሱን ስቶ ወደቀ።ከሰአታት በኋላ ካሊድ ስልክ አላነሳም ሲለው ሰለሀዲን ቤታቸው መጣ፥በሩ ክፍት ነው፡፡ገባ፡፡ "ካሊድ" "እማ* የሚመልስ የለም የመኝታ ቤቱ በርክፍት መሆኑን አየና ወደዛ ሄደ።የካሊድ እናት ተኝተዋል ካሊድ መሬት ላይ ወድቋል።እየሮጠ ሄዶ "እማ" አትመልስም፡፡ መሞቷን አወቀ ማልቀስ ጀመረ''ኢንና ሊላሂ ወኢንና ኢለይሂ ራጂዑን " እያለ ካሊድን ይጠራዋል፡፡ እሱም አይመልስም። ውሃ ፊቱ ላይ ረጨበት። ካሊድ ነቃ "እማዬስ? ለምን አትመልስም? እእ... ተኝታ ነው?" አለ። ሰለሀዲን ሳይመልስለት ወጣና ሰዐዳ ጋ ደወለ።ብዙ ሳይቆዩ ከአባቷ ጋ መጡ፡፡ካሊድ የእናቱን እጅ እየነካ ያለቅሳል።ሰዐዳም "ትናንት እኮ ሰዐዳዬ ልጄን አደራሽን እኔ ከሞትኩ ማንም ዘመድ የለውም ስትለኝ ነበር” ብላ ማልቀስ ጀመረች። የሰዐዳ አባት ካሊድና ሰለሀዲን ተጋግዘው መኪና ውስጥ አስገቧት።በፒያሳ በሰባራ ባቡር ፓስተር ዊንጌትን አልፈው አወሊያ ጀናዛ ማጠቢያ ወሰዷት።ከጁምዐ በኋላ ሰላተል-ጀናዛ ተሰግዶባቸው ወደ ኮልፌ ኢስላም መቃብርተወሰዱ።ተቀበሩ፤አፈር ተጫነባቸው።የሰዐዳ አባት ለሳቸው ሰደቃ እንዲሆን ቴምር ገዝተው ጀናዛውን ለቀበሩት ከሰለሀዲን ጋ ሆነው እየሰጡ ነው።ካሊድ አንድ ጥግ ላይ ቁጭ ብሎ የ'ናቱን ቀብር እያየ እያለቀሰ ነው፡፡ሰዐዳና እናቷ ከያስሚን ጋ ሆነው ቤቱን አስተካክለው ለሰደቃ የታረደውን ስጋ እየሰሩ ነው፡፡ሰለሀዲን ካሊድን አቅፎ ደግፎ ይዞት መኪና ውስጥ ገብተው ወደ ቤት መሄድ ጀመሩ። መኪና ውስጥ ይኽ ነሺዳ ተከፍቷል፦ ''የጀሊሉን ፍርጃ፣ በአሚን ተቀብዬ፣ ሸኝቼ ተመለስኩ፣ አደራህን ብዬ፣ የአዝራኢልን ኮቴ፣ ፍርዱ ሲያመጣው፣ የኔ ያልኩትን ሰው፣ ቀብሬው መጣሁ። (ሙንሺድ ሰለሀዲን ዘይኑ ግጥም ፈይሠል አሚን) ቤት ሲደርሱ ካሊድ" አሁን እማ የለችማ?መጣህ ልጄ? ለምን ቆየህ? አትለኝማ? እማ ዛሬ ከፍቶኛል ብዬ የምነግራት የምመክራት እናቴ የለችማ?'' ብሎ ማልቀስ ጀመረ።ሁሉም አለቀሱ። -የካሊድ እናት ጓደኞች፣የካሊድ ጓደኞች እነ አህመድና ሌሎችም ሰዎች መጥተው በልተው ወጡ።የሰዐዳ አባት አድራለሁ ብሎ የነበረ ቢሆንም አህመድና ሰለሀዲን እኛ አለን ብለው ከለከሉት፡፡ከሰዐዳ ከእናቷ እና ያስሚን ጋ ሆነው ተመልሰዋል።ካሊድ ከማልቀስ ውጭ ምንም አይናገርም፤ሰለሀዲንና አህመድም ሳይነጋገሩ ቁጭ ብለዋል፡፡ካሊድ ምንም አልበላም ሰላት ሰዐት ሲደርስ ብቻ ይሰግዳል።አራት ሰዐት ካለፈ በኋላ በተቀመጠበት ተኛ ሰለሀዲንም ተነስቶ አለበሰው፡፡ሁሉም ተኙ። ።።።ሰአዳና ያስሚን በጠዋት ከአባቷ ጋ ሆነው መጡ።ቁርስ አቀራርበው ጠሯቸው ካሊድ እንቢ ቢልም የሰዐዳ አባት ተቆጥቶት ትንሽ በላ።የሰዐዳ አባት ስራ ስላለበት ቁርስ በልቶ ወጣ።ካሊድ አሁንም ሲያለቅስ "ካሊዶ በቃ አታልቅስ ዱአ አርግላቸው ያንተ ዱአንጂ ለቅሶህ ምንም አይፈይዳቸውም" አለ ሰለሀዲን፡፡ካሊድም ተነስቶ "እናቴ እኮ ናት! የሞተችው እናቴ ለኔ ከእናትም በላይ ነበረች! ምን ያህል እንደተጎዳው ታቃለህ? አታቅም ምክንያቱም ባንተ አልደረሰም! በ… Read in full →
55 ¡
🦋𝕣𝕒𝕙𝕒𝕥🦋
✴🧡 ይድረስ ሲስቁ ለሚማቱ ጀለሶቻችን😁😂 አንድ ቀን 𝐫𝐢𝐩🫠
50 ¡
«ጌታዬ ሆይ! 🙏 ሰዎች የውጩን መልካም ማንነቴን ያያሉ፤ አንተ ግን የውስጤን ስህተት በደንብ ታውቃለህ። በቸርነትህ የሸፈንከውን ጉድለቴን አታጋልጥብኝ፤ ከአንተ በቀር መጠጊያ የለኝምና በምህረትህ ሰውረኝ። 💖» @Muslima122
47 ¡
🦋𝕣𝕒𝕙𝕒𝕥🦋
መድረሻ አልባ ክፍል ስምንት .. "ዋእለይኪ ሰላም" አላት አንድ ወረቀት ሰጠችውና ወደ ወንበሯ ኼደች። አነበበው። ''የሆነ ጊዜ በሰጠኸኝ መፅሐፍ ላይ 'ሃሰን ኢብን አሊይ ቢን አቢጣሊብ(ረ.ዐ) እጅግ ከሚወደው ጓደኛው ሙሀመድ ቢን አሕነፍ ጋርተጣልተው ለሶስት ቀናት ተኮራረፉ። ጉዳዩ ያስጨነቀው ሐሰን(ረ.ዐ) ለሙሀመድ ቢን አህነፍ ደብዳቤ ፃፈለት።የደብዳቤውም መልዕክት እንዲህ ይላል ለሙስሊሞች ከሶስት ቀናት በላይ መኮራረፍ አይፈቀድላቸውም።የእኔና ያንተ ኩርፊያ ደግሞ ከሶስት ቀን በላይ ሆኗል።ነብያችን (ሰ.ዐ.ወ) ከሙስሊሞች በላጩ በሰላምታ የጀመረው ነው' ብለዋልና አንተ ደግሞ ከኔ ትበልጣለህና እባክህን የሰላምታውን እድል ላንተ ልተውልህና ሰላም ብለኸኝ ታርቀን ወደነበርንበት እንመለስ"በማለት ነበርየላከለት።እናም ሳላ አንተም ከኔ ትበልጣለህና በሰላምታ ጀምረህ እንታረቅ-ፈተና ሲያልቅ በሩ ጋ እጠብቅሃለሁ (ወይም ጠብቀኝ)።" ይላል። ፈተና ላይ የሚመጣ አልመሰለውም ነበር።የፈተናው ቀን ከመድረሱ በፊት የሰዐዳ አባት'' ልጄ! ሀዘን ላይ እንደሆንክ አውቃለሁ እናትህን ነው ያጣኸው አላህ ጀነተል ፊርደውስን ይወፍቃት።ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) 'አንድ ሰው ጀነት ውስጥ ደረጃው ከፍ ብሎ ይመለከታል።ይህ ለኔ ነው? ሲል ይጠይቃል።'ልጅህ ላንተ በሚጠይቅልህ ምህረት(ዱዐ) ነው ይባላል።"ብለዋል እናም አንተ ማልቀስ ትተህ ሁልጊዜ ዱአ አርግላት።ልነግርህ የፈለኩት ሰቐ ፈተና ናችሁና እስከዛሬ የለፋህበትን ትምህርት የመጨረሻ ፈተና የምትወስድበት ቀን ነው እንደማትቀር አስባለሁ።" አለ። "እናቴ ይህን ሁሉ ጊዜ የለፋችልኝ ተምሬ ተለውጬ ትልቅ ደረጃ እንድደርስላት ነው እናም እኔ አልቀርም-እፈተናለሁ።" ሰለሀዲን የሰዐዳ አባትም ደስ ብሎት ግንባሩን ሳመው።ፈተናውን ጨርሶ ሲወጣ ካሊድና ሰዐዳ ቆመው እየጠበቁት ነበር።'አሰላሙ ዋአለይኩም አላቸው። "ዋአለይኩም ሰላም" መለሱ። "ለአላህ ብለህ አውፍ በለኝ " አለ ካሊድ ምንም ሳይለው አቀፈው።ተቃቀፉ። → ፈተና ከጨረሱ ሁለት ወራት በኋላ የሰዐዳ አባት ሰለሀዲንና ካሊድን ቤቱ ምሳ ጠርቷቸዋል።እነሱም ዝሁር ሰግደው በሰኣቱ ተገኝተዋል።ምሳ ከበሉ በኋላ የሰዐዳ አባት፦ " ዛሬ ላናግራችሁ የፈለኩት ስለ ሰዐዳና ስለ ካሊድ ነው።ሰዐዳ ትምህርት ከጀመራችሁ ጊዜ አንስቶ ስ'ላንተ ትነግረኝ ነበር።እናም አንድ ቀን ወድጄዋለሁ አለቺኝ።እኔም አሁን ትምህርትሽ ላይ ትኩረት አድርጊ አልኳት።ምክንያቱም ግንኙነታችሁ የሀራም ይሆን ነበር።ሀራም የሆነው ፍቅር ሳይሆን ግንኙነቱ ነው።ፍቅር ተፈጥሯዊ ፀጋ ነው።በሀላል ሲሆን ደግሞ የበለጠ ፍሬያማ ይሆናል።ኢብኑል ቀይም(ረ.ሂ)'በፍቅር መውደቅ በሽታ ነው፤ያፈቀሩትን ማግባት መድሃኒቱ ነው።" ብለዋል።አንድ ታሪክልንገራችሁ 'የረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ልጅ ዘይነብ ለትዳር እድሜዋ ሲደርስ ከአጎቷ ልጅ አል-አስ ኢብን ራቢ ጋር ትዳር መሰረተች።በጣም ደስተኛ ነበሩ።ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) ነብይ ሆነው ሲላኩ አል-አስ እስልምናን አልቀበልም አለ።ሚስቱ ዘይነብም'ወደ እውነቱ እስከምትደርስ ድረስ ምን ጊዜም ከጎንህ ሆኜ በምትፈልገው ሁሉ ድጋፌን እሰጥሃለሁ' አለችው።በበድር ጦርነት አል-አስ ከካፊሮች ወገን ኾኖ ረሱልን(ሰ.ዐ.ወ) ተዋጋ።ምርኮኛ ተደርጎም ተወሰደ።ዘይነብ ይህን ስትሰማ ገንዘብ ስላልነበራት የእናቷ ስጦታ የሆነውን ሐብል ለክፍያ አቀረበችው።ረሱልም (ሰ.ዐ.ወ) ክፍያ እየተቀበሉ ምርኮኞችን ሲያስለቅቁ የውድ ባለቤታቸው ንብረት እጃቸው ላይ ሲያርፍ ደነገጡ።'ይኽ ክፍያ የማን ነው?" አሉ የአል-አስ መሆኑ ተነገራቸው።ረሱልም(ሰ.ዐ.ወ) 'ይህ የአንገት ጌጥ የኸዲጃ ነው።እናንተ ሰዎች ሆይ! ይህ ሰው የልጄ ባ… Read in full →
❤5👍3
65 ¡
🦋
አላህን ማዉሳት አብዙ ፣ አላህን በማዉሳት ላይ የሚያበረታታችሁንም ሰዉ ወዳጅ አድርጋችሁ ያዙ፡፡ @Muslima122
👍1
55 ¡
🦋𝕣𝕒𝕙𝕒𝕥🦋
Photo
ጉዳዬንም ሁሉ ወደ አንተ አስጠግቻለው 🥰
❤1
51 ¡
ከልጄ ጋር ወክ እያደረግን በቤተክርስቲያን አቅራቢያ በተሰቀለ የእየሱስ ክርስቶስ ምስል አጠገብ አለፍን 🏛️ "ባባ ባባ ይህ ማነው?" በማለት ጠየቀኝ 🤔 "እርሱ የእግዚአብሔር ልጅ አምላካችን ነው" አልኩት። ልጅ ግራ በመጋባት መንፈስ እያየኝ "ለምን ሰውነቱ ቆሰለ ለምንስ ተሰቀለ?" በማለት ዳግም ጠየቀኝ። እጁን ጠበቅ አድርጌ ያዝኩትና "በእርሱ የማያምኑ አመፀኞች ናቸው የሰቀሉት" አልኩት "ጠንካራ ጌታ አይደል? ለምን ራሱን አላዳነም? አባቱስ ለምን አልተከላከለለትም?!" ሲለኝ "የልጁን ስቅለት ተቀብሎ ስቅለቱ ለእኛ የተከፈለ መስዋዕትና የኃጢአታችን ማስተሰሪያ እንዲሆን እግዚአብሔር ይህን መንገድ መረጠ" አልኩት። ወደ ሐውልቱ ትኩር ብሎ እየተመለከተ "አባቴ ሆይ! ልትከላከልልኝ እየቻልክ ለሌሎች ሲባል እኔ እንድሰቃይና እንድሰቀል ትፈቅዳለህን?" "አልፈቅድም ይህማ አይሆንም" አልኩት ቀበል አደረገና "ታዲያ በልጁ ስቅላት እግዚአብሔር እንዴት ደስ ይሰኛል?! ልጁን ሳያሰቃይና ሳይቀጣ ኃጢአታችንን ይቅር ማለት አይችልምን?!" ከልጁ አንደበት የተወረወሩት ጥያቄዎች አባት እስልምናን እንዲቀበል ሰበብ ሆኑት 🩶🩶🩶 𝕤𝕦𝕓𝕙𝕒𝕟𝕖𝕜 አሏህ ያጠመመውን ማንም አያቃናውም @muslima122 አሏህ ያቃናውን ማንም አያጠመውም
👍4👏1
1 ¡ 68 ¡
በብዙ ነገር ልታዝን ትችላለህ ግን You have finished your internet Package እንደሚል text ልብ የሚነካ ነገር የለም😖😫😤 @Muslima122
😭5
61 ¡
🦋
ያረብ 🌙 እባክህ አስችለን ✨ በምንንጋደድበት ጊዜ ደግፈን ተስፋ ስንቆርጥ ተስፋ ስጠን ሲያመን አሽረን ከአንተ ስንሸሽ አቅርበን አላህዬ አውቃለው ትወደናለህ ፈተናዎችህን እንድናልፍ ጠንካራ አድርገን 🤲 @Muslima122
👍4
58 ¡
🦋𝕣𝕒𝕙𝕒𝕥🦋
ጌታዬ አምላኬ ባንተ 🙏 ፍቅር የወደቁ ልቦች ግን ታድለው ❤️ ሁል ጊዜ ሰላም ሁል ጊዜ ደስታ 🕊️ መረጋጋት መስከን መርጋት እፎይታ ተድላ 😊 አህህህ አምላኬ ባንተ ፍቅር የወደቁት እኮ ሌላ አለም ውስጥ ናቸው ✨ በእዝነትህ ይከበባሉ በቁጣህ ይንቀጠቀጣሉ ጀነትህን ይከጅላሉ አህህህ 🌳 ጀሀነምን ይሸሻሉ አምላኬ አላሁመ ኢነከ አፉዉን ቱሂቡል አፍወ ፈአፉ አና ያ ከሪም 🤲 @Muslima122
🥰3
53 ¡
ከስር ያለውን ፅሁፍ Copy የሚለውን ተጭናችሁ ለ Chat Gpt ስጡት የሚላችሁን እዩ፤ ከፈለጋችሁ ያላችሁን Copy አድርጋችሁ በጥቂቱ በ Comment ፃፉልን 😂 ℹ️ Based on everything you know about me, roast me and do not hold back, use Amharic language.
😁1
1 ¡ 57 ¡
✨ᴅᴀɪʟʏ ʜᴀᴅɪᴛʜ✨ ❴Part 7❵ #hadith329 "ዓኢሻ (ረ.ዐ) እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፦ "አንዲት ሴት ከርሳቸው (ከዓኢሻ) ዘንድ እያለች ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ይገባሉ። "ይህች ማን ናት?" አሉ። "ይህቺ እገሌ ናት ስለ ሰላቷና አምልኮዋ ብዛትእያጫዋተችኝ ነው"። አሉ ዓኢሻ። ".....የምትችሉትን ብቻፈፅሙ በአላህ እምላለው! እናንተ (ከዒባዳ) እስካልሰለቻችሁ ድረስ አላህ (ምንዳ ከመለገስ) አይታክትም። ከአላህ ዘንድ ተወዳጅ የዒባዳ ክንውን ሰውየው ዘውትር የሚፈፅመው ነው።" (ቡኻሪና ሙስሊም) @Muslima122
🥰2
59 ¡
🦋
أكثِروا من الصَّلاة على النبي ﷺ اللَّهمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ، وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ، اللَّهمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ، كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ، إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيدٌ». @Muslima122
👍2
56 ¡
🦋𝕣𝕒𝕙𝕒𝕥🦋
መድረሻ አልባ ክፍል ዘጠኝ ተሰናብቶት ወጣ።ወደ ቤት እየሄደ ሠለሀዲን ደወለለት። "አሰላሙ ዋአለይኩም ሙሽራው ወንድሜ" " ዋአለይኩም ሰላም Proffesor" "የት ነህ?"... "ወደ ቤት እየሄድኩ "ዛሬ አንተ ጋ መጥቼ ማደር እችላለሁ?" "አዎ!የምን ማስፈቀድ ነው'' "እሺ በቃ እመጣለሁ" ከኢሻ በኋላ መጣ።ካሊድ እየፃፈ ነው። "ምን እየፃፍክ ነው?" ''የሆነ ታሪክ ነው" "ለእመ ብከ ጥበብ ፀሐፍ ይላሉ ወልደህይወት እንፍራንዛዊ" "ምን ማለት ነው'' "ጥበብ ካለህ ፃፍ! ርዕሱ ምን ይላል?" "ርዕሱ ...ለምን ነው" "ስለ ምንድነው?!! "እሱን ልጨርስና ታየዋለህ” አለው። እራት በልተው ወደ መኝታቸው ሄዱ።ለሊት ላይ ሰለሀዲን ከእንቅልፉ ሲነቃ ካሊድ ሱጁድ ላይ ሆኖ በጣም ሲያለቅስ አየው።እስኪጨርስ ጠበቀውና"ለምን ይኽን ያክል ታለቅሳለህ?' አለው። "ላላ....... ትናንት የሰጠኸኝ መፅሐፍ ላይ የባለ ኩኪሱን ልጅ ታሪክ አላነበብክም?እኔ ስንት ወንጀል አለብኝ!ለሱ ማልቀስ የለብኝም!? ደግሞም በዚህ ሰዐት እናቴ ቀብር ውስጥ ናት ለሷስ ዱአ ማድረግ የለብኝም?" አለውና ተነስቶ መስገዱን ቀጠለ።ሰግዶ ጨርሶ ድጋሚ ሊቆም ሲል "እሺ ዕረፍት አታደርገም?' አለ "ረቢዕ ኢብን ኸይሠም አምልኮ በማብዛታቸው ምክንያት ሰዎች 'ራስህን አሳርፋት' አሉት። እርሱም'የምደክመው የነፍሴን እረፍት ፈልጌ ነው'አላቸው።" አለና ሰላቱን ጀመረ። -ካሊድና ሰዐዳ ኒካህ ሊያስሩ አንድ ሳምንት ቀርቷቸዋል።ዛሬ ለፕሮግራሙ (ለኒካህ)ልብስ ሊገዙ ከሰለሀዲንና አህመድ ጋ ተቀጣጥረዋል።ካሊድ ዝሁር ሰግዶ እየወጣ ሰለሀዲን ደወለ።"አሰላሙ ዋአለይኩም "ዋአለይኩም ሠላም" "አትመጣም'ንዴ እየጠበኩህ ነው" "አሁን ነው ከመስጂድ የወጣሁት።አህመድ መቷል?" "አይ እየመጣሁ ነው ብሎኛል" "በቃ እኔም እየመጣሁ ነው" ከአህመድ ቀድሞ ካሊድ ደረሰና አህመድን ሊጠብቁ ወደ ካፌ ገቡ። ካሊድ፦'ቅድም ከመስጂድ ወጥቼ ሽቶ ልገዛ ስል አንድ ሀዲስ ትዝ አለኝ" "ምን የሚለው?" አለው ሰለሀዲን ''ጥሩ ጓደኛ ማለት ምሳሌው ልክ እንደ ሚስክ ነው።ካለህ ትገዛዋለህ ካልሆነም ከሽቶው መልካም መአዛ ታገኛለህ።" የሚለውን አለና 'አንተ ማለት ለኔ እንደዛ ነህ' ብሎ አቀፈው። ካፌ ገብተው ምግብ ካዘዙ በኋላ ሰለሀዲን ባለፈው እየፃፍክ የነበረው የት ደረሰ?'' አለ "ቆይ" አለውና ይዞት ከነበረው መፅሐፍ መሀል ወረቀቱን አውጥቶ ሰጠው።ሰለሀዲንም ማንበብ ጀመረ። ፀሐዩዋ ቦታዋን ለጨለማው አስረክባ ከሄደች ሰአታት ተቆጠሩ።በሰማዩ ላይ አልፎ አልፎ ኮከቦች የሚታዩ ሲሆን ጨረቃዋም በግማሽ ፈገግታ በጥቁሩ ሰማይ ላይ ትታያለች።በአካባቢው የውሾች ጩኸትና የሌሊት ወፍ ድምፅ ብቻ ይሠማል። ፅጌሬዳ የፅድ ዛፍ እና በተለያዩ ውብና ለልብ ሀሴትን የሚሰጡ አበቦች የተሞላው ጊቢ ውስጥ በረንዳው ላይ በስስ ቲሸርትና ቱታ አንገቱን ጉልበቱ ውስጥ ቀብሮ መሬት ላይ የተቀመጠ ሰው ይታያል። ለቅሶና እንቅልፍ ማጣት ተባብረው አይኑን አሳብጠው በርበሬ አስመስለውታል። እዚህ ቦታ ላይ ከተቀመጠ 24 ሰአት ሊሞላው ነው፣ምግብም ሆነ መጠጥ አልቀመሠም።ውስጡ መጎዳቱን ፊቱን አይቶ መረዳት ይቻላል። ከጠዋት ጀምሮ ጓደኛው እየደወለለት ያለ ቢሆንም አላነሳለትም። "ምነው ጌታዬ! እኔ ክፉው፣ለማንም የማልጠቅም ሠው እያለሁ ለምን እሷን?" ይላል ደጋግሞ፣ ትናንት በዚህ ሰአት አብራው የነበረችውን፤በህይወት የነበረችውን እናቱን አስታውሶ። ያለ አጋዥ ብቻዋን ሆና ብቸኛውን ልጇን እናትም አባትም፣ ወንድምም እህትም፣መካሪ ጓደኛ ሆና ነበርያሳደገችው። በምድር ላይ ማንንም ከሱ እኩል እታደርግም፣ከቤት … Read in full →
👍5
55 ¡
🦋
አላህ በልብህ ውስጥ ምኞትን በከንቱ አያኖርም፤ በልብህ ውስጥ ቁጭትና ሐዘን ተቀምጦ እንዲቀር ብሎ የሆነን ነገር እንድትመኝ አያደርግህም ከጊዜ በኋላም ቢሆን ሊሰጥህና ሊያጎናጽፍህ እንጂ። ​ልብህ መለመንንና መጸለይን እስካልሰለቸ ድረስ አላህ ይሰጥሃል፤ የአላህ ቸርነትና ልግስና ከሕሊናህ (ከምናብህ) በላይ ሰፊ፣ ከፍላጎትህ በላይ ታላቅ፣ እንዲሁም ከምኞቶችህ ሁሉ በላይ እጅግ የበዛ ነው ።»
🥰3
1 ¡ 51 ¡
🦋𝕣𝕒𝕙𝕒𝕥🦋
✍ትልቅነት በእድሜ ላይ ሳይሆን ባስተሳሰብ ትልቅ መሆን ነው ሂወት ላይ ለውጥ ማምጣት የሚችለው። 👌በእድሜ ስለበለጧቹ ሰዎች ሳይሆን በአስተሳሰብ በበለጧቹ ሰዎች ተሞክሮ ውሰዱ🌺
👍2
38 ¡
  ከሰዎች ሁሉ ክፉው ማን ነው? ሲሉት;   መጥፎ ጥርጣሬ ስላለው ማንም የማያምንና    መጥፎ ባህሪ ስላለው ማንም የማያምነው ሰው ነው አለ። @muslima122
💯2❤1
38 ¡
🦋
በጊዜ ሂደት ሁሉም ነገር ይረሳል ⏳✨
👍2
37 ¡
🦋
🦋𝕣𝕒𝕙𝕒𝕥🦋
ሙሳ ከባህር መካከል ወጣ 🌊 ዩሱፍም ከጨለማ እስር ቤት ወጣ 🌙 ኢብራሂምም ከእሳት ልብ ውስጥ ወጣ 🔥 ዩኑስም ከአሳ ነባሪ ሆድ ውስጥ ወጣ 🐋 በአላህ ሀይል እኛም ከእያንዳንዱ መከራ እንወጣለን ✨ አላህ ሆይ ከሁሉም ጭንቀትና መከራ አውጣን 🤲 ሰፊ ወደሆነው መንገድ የአዛኞች ሁሉ አዛኝ የሆንከው ሆይ ❤️‍🩹 @Muslima122
👍1
10 ¡

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About ¡ FAQ ¡ Index limits ¡ Remove a page ¡ Catalog ¡ Search ¡ How we count