Web appOpen in Telegram
የየነቃ ትውልድ Tube

የነቃ ትውልድ Tube

@ReformationNeeded · channel · Fun · indexed since 2026-08-26
15 229subscribers−68 in a week
421average post reach
2.8%ER — reach to subscribers
42posts in 30 days
F
🟩 አምላካችን:- "እርሱ ብቻ የማይሞት ነው፤..." ። 1ኛ ጢሞቴዎስ 6:16
577 ·
F
🫶በወጣቱ ላይ ላያቸው ሚናፍቃቸው ባህሪያት ራሴን ጨምሮ:- ♦️ፍቅር 🔹ትህትና 🔹ቸርነት ♦️ሪህራሄ 🔹ተስፋ ♦️እምነት 🔹ሰላም 👌በፍጹም ላያቸው ማልፈልጋቸው ♦️ትዕቢት ♦️ራስ ወዳድነት 🔹ቅንዓት 🔹ኢፍትሐዊነት ♦️ፍርሃት
565 ·
F
🤦‍♀ከራስ ጋር ትግል🤦‍♀ 📖 ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ 📖 ምዕራፍ=አንድ   ክፍል=3 ብን ብዬ ስነሳ አባቴ "Good morning" አለኝ እኔም ቶሎ ብዬ እጁን ሳየው በጆግ ውሀ ይዟል በሚያሳዝን ሁኔታ አይኖቼን እያሻሻሁ "አባ ግን አላሳዝንህም?" አልኩት እሱም "የኔ ቆንጆ ልጅ ስለምታሳዝኚኝ እኮ ነው ቸርች እንድንሄድ የቀሰቀስኩሽ" አለኝ በሁኔታዬ በጣም እየሳቀብኝ እኔም ቀስ ብዬ እየተነሳሁ ሶሲን ዞሮ ብዬ ሳያት ተሸክመው ቢወስዷትም አትሰማ ከዛ ከአባቴ ጋር ተያየንና ቆይ ባንሰራላት!! ተባብለን ኮቴዬን አጥፍቼ አባ የያዘውን የጆግ ውሀ ተቀበልኩት እናም "በእየሱስ ክርስቶስም የእንቅልፍ መንፈስ" እያልኩ በእጄ እረጨኋት ከዛ ሶሲ ከእኔ በባሰ ሁኔታ ብን ብላ ተነሳች እኔም አጠገቧ ብሆን እንደማትለቀኝ ስለማውቅ ሮጬ ከአባቴ ጀርባ ተደበኩ "እረ ኡኡኡኡ ብላ በጩኸት አቀለጠችው በጣም አናድጃት ነበር እንደው ግን አለቅሽም" ብላ ነጠላ ጫማ አነሳችብኝ እሷ ከተናደደች ማንም አይመልሳት አባቴም አያይዟን አይቶ "የለሁበትም!!" አለና በችኮላ ከክፍላችን ወጣ ክው ብዬ ብቻዬን ስቀር "እማማማማ!!" እያልኩ ብን ብዬ ሮጥኩ እማም "ደግሞ ነጋላችሁ" አለችን ቡና እየቆላች "ከልጆቹ የአባትየው" ብላ አባቴን ማንቆር ጀመረች አባም እኛን ረስቶ ከእማ ጋር ነቆራ ጀመሩ ሶሲም ንዴቷ ሲበርድላት  ""እኔ እንዳንቺ አይደለሁም ብላ ትታኝ በሰላም  አልጋችንን አነጣጥፈን ፊታችንንም ተጣጥበን ቁርስ አቀረብን እናም ሶሲ አመስግናልን  በላን እኔና ሶሲም የበላንበትን አነሳሳን እናም ልብሳችንን ለመቀየር ወደ ክፍላችን  ገባን እኔም እስቲ ልብስ ምረጪልኝ እያልኳት ልብሴን እንዳለ አወጣሁት ንዴቷ ብዙም አለቀቃት"ቸርች ነው ፓሪ የምትሄጂው?" አለችኝ እንደረሳ ልትሆን እንጂ ትናንት በተነጋገርነው መሰረት ዛሬ ኳይር ፕሮግራም አለን ሙድ መያዝሽ ነው አልኳት እንደ ማኩረፍ እየሰራኝ ብቻ ትንሽ ተጨቃጭቀን ለባብሰን ቀድመን መሄድ ስላለብን ወጣን እንደተለመደው ሶሲ ሰው ስትጠራ ሲጠሯት እኔ ሳልፍ "ሜሪ ያዝልቅልሽ!!" እያሉኝ መንገዳችንን ቀጠልን በሰላም እየሄድን ልንደርስ ስንል እኛ ቸርች አጠገብ ያለ የወጣቶች ሆቴል ጋር የሶሲን ጓደኛ ማህሌትን አገኘናት እናም ሰላም አልናት እና  "ሶሲ ፍቅር ኑ እንግባ" አለችን አብዛኛው ወጣቶች እዚህ ነው ውሎ አዳራቸው በተለይም የHigh school ተማሪዎች እኔም  "ምን ልናደርግ" አልኳት  ኮስተር ብዬ ማህሌትም "ልንማር!! ሜሪ ደግሞ አንዳንዴ ምታካብጂው ነገር አለ" ብላ አላገጠችብኝ እውነት ለመናገር ምንም አትመቸኝ ትንሽ ወጣ ያለች ነች ሶሲ ግን ልቧ እስኪጠፋ ትወዳታለች ስለሷ ብዙ ግዜ ስነግራት  አንቺ ብዙ ማታውቂው ነገር አለ ትለኛለች ግን ብቻ የሷ ነገር ግራ ያጋባኛል ጭልጥ ብዬ በሀሳብ ሄድኩ ማህሌትም እጇን እያወላወለች "ሜሪ ነግቷል እንዳተኚ" አለችኝ ከት ብላ እየሳቀችብኝ አሁንም ግራ ገብቶኛል ምንም መልስ ሳልሰጣት ወደ ሶሲ ጠጋ ብዬ "ነይ አታስረፍጂኝ እንሂድ" አልኳት "እረ በጌታ እሺ ብያት እረ ይደብራታል አንድ አፍታ ገብተን እንውጣ በጌታ እምቢ እንዳትይ" አለችኝ እኔም ብቻዋን ትቻት መሄድ ስላልፈለኩ "እሺ ግን ቶሎ እንወጣለን" ብዬ ገባን እሺ ስንል የማህሌት ፊት አበራ አይገልፀውም እንዳለችው ወደ ውስጥ ገባን ልክ እንደገባን    . . .  ይቀጥላል. . . . @abit9 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 https://t.me/ReformationNeeded https://t.me/ReformationNeeded https://t.me/ReformationNeeded sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
1 · 582 ·
F
ወሲብ የደም ቃል ኪዳን ነው። #ክፍል1 ሰላም ለእናንተ ይሁን የአባቴ ብሩካን የአምላክ ፈቃድ ከሆነ ከዛሬ ጀምሮ በሶስት ክፍል የተያዘ ብዙ ወጣቶችን እየጨረሰ ስላለው የዝሙት ልምምድ እንማማራለን ለሌሎችም ሼር ማድረግ አይረሳ🙏 ስማ ወንድም ወሲብ ደስታ የሚሰጥ ብቻ አይደለም። ወሲብ "መዝናኛ "( fun) ወይም እንደ "Normal " ነው ብለህ የምታስብ ከሆነ ተበልተሀል ። 📌 ወንድም ወሲብ ቃል ኪዳን ነው (Sex is a blood covenant) ድንግልና የደም ጉዳይ አይደለም #የኪዳን እንጂ! ብሉይ ኪዳን በእንስሳት #ደም የጸና ነበር(ዘጸ 24:8)፡፡ አዲስ ኪዳን ደግሞ በኢየሱስ #ደም የጸና ነው(ማቴ 26:28)፡፡ ኪዳን በደም ይጸናል(ዘካ 9 :11)፡፡ ደም ሳይፈስ ኪዳን የለም(ዕብ 9:20) ኪዳኑ በአንተ ሰውነት እና መንፈስ አልፎ ወደ ቀጣይ ትውልድህ የሚደርስ አደገኛ ውጤት (consequence)አለው። እግዚአብሔር የወሲብ ግንኙነትን የተቀደሰ እንዲሆን አድርጎ ነው የፈጠረው።  እግዚአብሄር የፆታን ግንኙነት የፈጠረበት ዓላማ አለው። ስለዚህ ነው እግዚአብሄር የሴት ልጅን አካል መጀመሪያ ላይ ደምን ያስቀመጠው ። ያ ደም አጋጣሚ አይደለም ። የቃል ኪዳን ምልክት ነው። ስታፈርሱት ወደ አስገዳጅ መንፈሳዊ ውል ትገባላችሁ። 📌 ስለ ወሲብ ልታውቁት የሚገባው #እውነት ፦ 1.ወሲብ አካላዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊም ነው። ከሴት ጋር በተኛህ ቁጥር መንፈስህ  ከእርሷ ጋር  ይታሰራል ።  ከአንዲት ሴት ጋራ አልጋ ስትጋራ ። የምትጋራው አልጋ ብቻ ሳይሆን ። ወሲብ በማድረግህ እሱን ተከትሎ የሚመጡ መንፈሳዊ እስራትን፥ የተወሳሰቡ ችግሮችን ፥ የእጣ ፈንታህን ገዳዮችን (destiny killers ) በሙሉ ትጋራለህ። የወሲብ አደገኛነት እዚህ ላይ ነው። 1ኛ ቆሮ 6:16 2. በወሲብ ምክንያት መንፈሳዊ በሽታዎች ይተላለፋሉ ። 📌 በወሲብ የማታዩትን መናፍስትን ትወርሳላችሁ ። ፍቅር ለመስራት enjoy ለማድረግ ብለህ ያደረከው sex የማይታዩ መናፍስት ተሸካሚ ያደርግሀል። በወሲብ ደስታ ብቻ አይደለም የሚተላለፈው ። ከጋለሞታ ጋር ከተኛህ መንፈሷን ትወርሳለህ። ከተሰበረች ተስፋ ከቆረጠች  አላማ የሌላት ሴት ጋር ከተኛህ ዋጋ ቢስነት ይተላለፍብሀል። ከሰው ሚስት ጋር ከተኛህ እርግማን ትወርሳለህ። የዝሙት መንፈስ ካለባት ሴት ጋር ወሲብ ካደረክ ዘመንህን በአንድ ሴት የማይረጋጋ ዘማዊነት ይተላፍብሀል። ወሲብ ተላላፊ ነው። ከአንተ ወደ እርሷ ከእርሷ ወደ አንተ ። ስኬት የራቃት በጭንገፋ የተመታች ቡኩን ሴት ጋር ከተኛህ ገንዘብ አገኛለሁ የት እንደሚገባ አላውቅም ማለት ትጀምራለህ። አጋንንት በረከትህን የሚበላበት በር በዝሙት ትከፍታለህ። ስኬት የራቀው ሆነው አንተ ሰርተህ ሌላው ይበላል ። ከጋብቻ ውጭ ካገኘሀት ሴት ጋር ስትተባበር ግራ መጋባትን፣ እርግማንን እና የተሰባበረ ዕድል ፈንታ ትወርሳለህ። 3. ቀጣይ ዘረ ማንዘርህ ከባድ ዋጋ ይከፍላሉ ። እግዚአብሔር ኃጢአት እስከ ሦስተኛውና ለአራተኛው ትውልድ ድረስ ተላልፎ የሀጢያት ሸክም እንደሚያመጣ ተናግሯል ። ዘዳግም 5:9-10 በወሲብ ምክንያት ለልጅ ልጆችህ እርግማን ታወርሳለህ ። " ከአያት ቅድመ አያት የመጣ እርግማን ነው የነሱ ሀጢያት ነው " ይላሉ የልጅ ልጆችህ ። ከአያታችን የመጣ በረከት ነው መባል አትፈልግም  ወዳጄ ? 4. ከጋብቻ ውጪ የሚደረግ ወሲብ ራስን ማጥፋት ነው። ከጋብቻ ውጭ ወሲብ በአባላዘር በሽታዎች መያዝ ፣ ያልታቀደ ህፃን መውለድ በዚህ ምክንያት ውርደት ፥ ሀፍረት ፥ ከጓደኛ በታች መሆን ፣የትምህርት መቋረጥ ፥ ቤት መፍረስ ፥ በአይን የማይታይ ጥ
15 · 574 ·
F
🤦‍♀ከራስ ጋር ትግል🤦‍♀ 📖ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ 📖   ምዕራፍ=አንድ    ክፍል=4 ልክ እንደገባን ማህሌት ሶሲን "ሶሲ ባለፈው ያልኩሽ ጓደኞቼ ናቸው ተዋወቂያቸው ሜሪ ተዋወቁ" አለችን እሺ ብለን ሶሲ " Hey ጀለስኮች" ብላ እንደመሳቅ አደረጋት ቀለል አድርጋ በደስታ ቁጭ አለች እኔም"ሰላም" አልኳቸው "hiii" አሉኝ እጃቸውን ወደኔ እያውለበለቡ በውስጤ የማህሌት አልበቃ ሲል ጭራሽ ተደራጅተው መጡብኝ አልኩ እኔ ዝም ብዬ ቁጭ አልኩ እነ ሶሲ አለማቸውን ረስተው ያወራሉ በወሬ መሀል ሶሲ"ቆይ ከአዲስ አበባ ነዋ የመጣቹት" አለቻቸው "Yap!!" አለች ከመካከላቸው አንዷ በጣም በሚያስጠላ ሁኔታ ቀጠል አድርጎ ሌላኛው ደግሞ "ግን 11 ክፍልን እዚህ ልንማር ነው የመጣነው" ሲል ልቤ ልትወጣ ደረሰች ሳላስበው "እርፍፍፍፍ" አልኩ ግን ዞር ዞር ብዬ ሳይ ማንም አልሰማኝ አሰብኩት ማህሌት የሶሲ የልብ ጓደኛ ነች በዛ ላይ አይለያዩም አሁን የእነዚህም ጓደኛ ልትሆን ነው እኔስ ምን ተስፋ አለኝ ብዬ በሀሳብ ተዋጥኩ ከመሀከላቸው አንዱ ዮናስ የሚባለው "ሜሪ የት ሄድሽ" እያለ ልክ እንደ ማህሌት እጁን ያውለበልብ ጀመር "ልመደው ሜሪ እኮ 12 እንደወለደ በተቀመጠችበት ትሄዳለች" አለች ማህሌት ነበረች እውነቷን ነው ሁልጊዜ ከእሷ ጋር ስሆን የማይለየኝ ነገር ትካዜ ነው እኔ ጓደኛ ሳልፈልግ ወይም ሳልወድ ቀርቼ ሳይሆን የልጆቹ ሁኔታ ጭራሽ ደስ አይልም ነበር እኔ ሶስት ጓደኞች ነው ያሉኝ ከእነርሱ ሌላ ጓደኛ ልለምድ አልችልም በዚያ ላይ እንደዚህ ቀበጦች ሆ ብዬ አሁንም ሌላ ሀሳብ ውስጥ ገባሁ ሶሲና ልጆቹ ተጣጥመዋል እየተሳሳቁ ነው "ሜሪዬ ፈታ በይ"" አለችኝ ከመካከላቸው አንዷ ምን ክላስ ነሽ ስትለኝ "B" አልኳት ""ውይይይ አንድ ክላስ አይደለንማ እኛ C  ነን"" አለችኝ ሁላችሁም አልኳት (ጮክ ብዬ በደስተኝነት መልኩ) ""አዎ አያናድድም"" አለች የቅብጠት ቁዘማ እየቆዘመች አሁን ይሄ ምን ያናድዳል ብዬ ለራሴ ተገረምኩ ወዲያውም ሶሲ ቀበል ብላ ታድያ ምን ችግር አለው ዋናው አንድ level መሆናችሁ ነው ሜሪ ፀደቅንብሽ  ይኸው አዲስ ጓደኞች አስተዋወቅንሽ"" አለችኝ እኔም በአባባሏ ክው ብዬ ቀረሁ በጣም አናደደችኝ ግን ሌሎቹ ወሬያቸው ጦፏል ምንም ደስ ስላላለኝ  በአይኔ እንደመጥቀስ እያደረኩ ኮስተር እያልኩ ሶሲን አየኋት "እንሄዳለን እስቲ ተረጋጊ" አለችኝ ጮክ ብላ አሁንም አባባሏ አስደነገጠኝ በውስጤም ብቻ በሰላም ልውጣ ማደርገውን አውቃለሁ እያልኩ እና እሺ አልኳት ትንሽ ቆይተው እራሳቸው "guys በቃ እንውጣ" አሉ እኔም "አዎ ይሻላል" አልኩ እና ተነሳን ማህሌት እና ሶሲ ከፊት እኔና ዮናስ የሚባለው ከኋላ ሆነን ወጣን ልክ ስንወጣ ዮናስ ወደ እኔ እያየ "እና እንሸኛቹ አ" አለ "አይ አያስፈልግም እናመሰግናለን" አልኩት በዚያ ሰአት ጓደኞቼ ቢያዪኝ "ሜሪ እንዲህ ትኮሳተሪያለሽ ??ነው ወይስ ሜሪ አይደለሽም??" ነበር ሚሉት ከዚያም"" ስለተዋወኩሽ ደስ ብሎኛል የኔ ማር" ብላ አቀፈችኝ እኔም እያቀፍኳት እኔም አልኳት(ሁኔታው ምንም አልጣመኝም በሶሲ ግን ተናድጄባታለሁ ሁሉንም ተሰናብተናቸው እኔና ሶሲ ወደ ቸርች መሄድ ጀመርን ልክ "እና ሜሪ ብላ ልትቀጥል ስትል "ሶሲ Please ዝም ብለሽ እንሂድ አልኳት እና ዝም ብላ በሰላም መሄድ ጀመርን ልክ ቸርች ስንደርስ .  . .    . . . . ይቀጥላል. . . . . @abit9 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 https://t.me/ReformationNeeded https://t.me/ReformationNeeded https://t.me/ReformationNeeded sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ለአንድ
479 ·
F
ወሲብ የደም ቃል ኪዳን ነው ። #ክፍል-2 ⚠️ “Sex is a transaction ” ማለት በቀላሉ ሲተረጉም፦ ግብይት  ማለት ነው። ለምሳሌ ፦ ሱቅ ገብተህ ገንዘብ ትከፍላለህ የሆነ የፈለከውን ዕቃ ትወስዳለህ ። Sex ማለት እንደዚህ ነው። የምትወስደውም የምትሰጠውም  መንፈሳዊ ነገሮች አሉት ። 1ኛ ቆሮንቶስ 6:16 ወሲብ የምትለዋወጠው ነገር ነው። “Sex is an exchange”  አንተ ወይም አንቺ የእግዚአብሔር በረከቶች አሉህ ። Sex ስታደርግ በረከቶችህ በሙሉ ይወሰዳሉ አንተ ወይም አንቺ ከዛኛው ሰው ባዶነት፥ ድህነት ፥ ስኬት ማጣት ፥ ወድቀት ትወስዳለህ ። በበረከት በሞገስ ስትኖር የነበረው ሰው ህይወትህ miserable  ይሆናል ። የሆነ ወቅት በጣም ሀብታም የነበሩ ሰዎች ወርደው ባዶ የሚሆኑበት አንዱ ምክንያት በዝሙት Case የሸመቱት ውድቀት ነው። “ወግታ የጣለቻቸው ብዙ ናቸውና፤ እርስዋም የገደለቻቸው እጅግ ብዙ ናቸው።”   — ምሳሌ 7፥26 አንድ ጥያቄ ልጠይቃችሁ ? በጣም በሰው ላይ የምትጠላው ባህሪ በአንተ ላይ መገለጥ ሲጀምር ከየት እንደመጣ ታውቃለህ ? በዝሙት Sex ምክንያት የተላለፈብህ ባህሪይ ነው። ወሲብ ተላላፊ ነው። ከአንተ ወደ እርሷ ከእርሷ ወደ አንተ የሚተላለፍ በሽታዎች አሉ። ከየት እንደመጣ አታውቅም፦ ትበሳጫለህ ትቆጣለህ ትጨነቃለህ ለምን እንደዚህ እንደሆንክ አታውቅም። ትሁት ፥ ሰው አክባሪ፥ ትዕግስተኛ ፥ ደስተኛ ነበርክ አሁን ግን አይደለህም። ወንድሜ ከሌላው ሰው የተላለፈብህ በሀጢያት ምክንያት የመጣ መጥፎ ባህሪ ነው። በወጣትነት ዕድሜ ትልቁ ፈተና ወሲባዊ ፈተናዎች ናቸው ። በአንተ እና በበረከቶችህ በስኬትህ መካከል የወሲብ ገደል አለ ወደ ህልምህ ለመድረስ የግዴታ ገደሉን መዝለል አለብህ ። ካልዘለልክ ጉድጓድ ውስጥ ወድቀህ ከአላማህ ቀርተህ ከጓደኞችህ በታች ትሆናለህ ። ዝለል !! አንተ ከወሰንክ እግዚአብሔር ሊረዳህ ዝግጁ ነው ። “ለራሳችሁ ተጠንቀቁ ” ጥንቃቄ ይጠብቅሀል ግድ የለሽነት ይገልሀል።   — ሉቃስ 17፥3 #መፍትሔ ፦የእግዚአብሔር ፈቃድ ከዝሙት ርቃችሁ እንድትቀደሱ ነው፤  ደግሞም እያንዳንዱ የገዛ ሰውነቱን በቅድስናና በክብር መያዝ እንዳለበት እንዲያውቅ ነው፤  ይህም እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወተ ሥጋ ምኞት አይሁን። 1 ተሰሎንቄ 4:3-5 የእግዚአብሔርን ቃል ታዘዙ ። በመታዘዝ ራስህን እና ትውልድህን ትታደጋለህ !! ... ይቀጥላል .... ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ🧔 .     #እወዳችኋለሁ❤   ለማማከር አገልግሎት እኔን ለማገኘት  👉  @abit9                        🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 https://t.me/ReformationNeeded https://t.me/ReformationNeeded https://t.me/ReformationNeeded sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
7 · 537 ·
F
🤦‍♀ከራስ ጋር ትግል🤦‍♀ 📖ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ 📖 ምዕራፍ=አንድ ክፍል=5   ልክ ቸርች ስንደርስ በጣም አርፍደን ነበር ስንገባ ፀሎት ተጀምሯል ከቤት የወጣነው ግን ቀደም ብለን ኳይሮች ለመገናኘት ነበር እግዚያብሄር ሲረዳን የኳይራችን አሰልጣኝ ሆኖ የማያውቀውን ትንሽ ችግር አጋጥሞኝ ነው ብላ አርፍዳ ነበር ወደ ውስጥ በሚያስገባ መንገድ የኳይሮች ክፍል አለ አሻግረን ስናይ ሁሉም ተሰባስበዋል ልብስ እየቀየሩ ደረስን ቀስ ብለን ሰላምታም ሳንሰጣቸው ኮቴያችንን አጥፍተን ገባንና ቁጭ አልን  እኛም በተራችን ልብሳችንን ቀያየርን እና በህብረት ፀልየን ስለ ፕሮግራሙም አመስግነን ተረጋግተን የምንዘምረውን መዝሙር አንዴ ደግመን ተለማምደነው  ወደ ጉባኤው ገባን ፕሮግራሙን የመራው ወንድማችን የቀጣዩን ፕሮግራም አስተዋውቆልን እኛን ወደ መድረክ ጋበዘን ወደ መድረኩም ከወጣንባት ጊዜ ጀምሮ እስክንጨርስ ከእኛ ልምምድ ይልቅ መንፈስ ቅዱስ ይበልጥ ፕሮግራሙን አስደሳች አደረገልን ማለዳ ማለዳ አዲስ የሆነው ጌታ ጉባኤውን ባረከ እንደወትሮ መቆም ሳይሆን በምንዘምረው መዝሙር በምናወጣቸው ቃላቶች መንፈስ ቅዱስ ህዝቡን ተናገረ ባረከ ፈወሰ በጣም ደስ እያለን የእኛን ፕሮግራም ጨርሰን ወረድን ጌታንም አመሰገንን ህዝቡም ባረከን እንዲህ እንዲህ ብሎ ፕሮግራሙ በጣም ደስ በሚል ሁኔታ አለቀ ስንጨርስ በህብረታችን ሆነን ፀለይን እና ሰላም ተባብለን ተቃቀፍን በመሀል ዳኒ የሚባል  ጓደኛችን  ቀስ ብሎ ወደኔ እንደማቀፍ ብሎ"ይቺን የቅድሟን ጉዳቹንማ. . .  አላስጨረስኩትም ""በጌታ"" አልኩት ቶሎ ብሎ ራቅ አለኝ እና ከመሪያችን ጀርባ ሆኖ በአይኑ እያየኝ ሲያሳቅቀኝ "እኔ ላንተ እንዲህ ነኝ?" አልኩት እንደማያደርገው ስለማውቅ እየተሳሳቅን እንደተለመደው በህብረት ወጣን ዳኒ እና ኤልሻዳይ "ቅድም እኮ ጋሽ ሰሌ ሲሉ በድንጋጤ ሶሲ አላስጨረሰቻቸውም "ስለኛ ጠየቃችሁ? አለችው "ምን ያለበት ምን አይችሉም" አሉ ኤልሹ ነበረች እኛ አሁንም ድንጋጤ ላይ ነን "ምን አላችሁሁሁ"? አልናቸው "ይገርማችኋል በታንክ ነው ምረሽናቸው ላግኛቸው!! ብቻ ብሏል"አለችን "ውይ ልጆቹን አታስደንግጫቸው ምንም አላለ መጥቶ ልምምድ ላይ ከሆናችሁ አልረብሻችሁ ብሎን ሄደ አላስተዋለም"ሲል እንደዛ አትሉም ምን ዙሪያ ጥምጥም አስኬዳችሁ አልኳቸው  ኤልሹ ሳቅ በተሞላ መልኩ እያየችኝ "የት እንደነበርሽማ አዳሜ ታብራሪያታለሽ" አለች ቶሎ ብሎ ዳኒ "ይህንማ መንገድ ላይ አይደለም ቁጭ አድርጌ ነው ማናዝዝሽ" ብሎን በሉ ቻው ብሎን ቻው ተባብለን ሄደ ኤልሹም ልክ ዲኒ እንደሄደ ስለ ሁኔታው ጠየቀችን በጣም ስታስጨንቀን ሁሉንም ነገር ነገርናት እና "ውይ ለዚሁ ነው እንዴ"" ብላ በግርምት አየችን ኤልሹዬ በጣም ቀለል ያለች ልጅ ናት በዛው ልክ ሲበዛ አስተዋይና መንፈሳዊም ነች ""እንዴ ኤልሹ ምን ነካሽ በናትሽ አሁን ቸርች እየሄድን እንዲህ ማድረግ አለብን?" አልኳት ሀሳቤ ሶሲን እንድትመክርልኝ ነበር የባሰ እሷ እኔኑ አስወጋችኝ😊"ሜሪዬ ያለ ነው""(ብላ ፈገግ አለች) ትንሽ እንደሄድንም ተሰናብታን ""በሉ በቃ ቀጣይም አርፍዱ እና እንዳሁኑ የምትታለፉ መስሏችኋል"" ብላን ተለያየን እኔና ሶሲ መንገዳችንን ቀጠልን እየሄድን እያለ ድንገት ስልኬ ጠራ . . . . . . . . . . ይቀጥላል 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 https://t.me/ReformationNeeded https://t.me/ReformationNeeded https://t.me/ReformationNeeded sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
1 · 468 ·
F
📌መሞት እስካልቀረ ድረስ በጌታ በኢየሱስ ስም አምኖ መሞት እንዴት መታደል ነው።
1 · 392 ·
F
ወሲብ የደም ቃል ኪዳን ነው። #ክፍል-3 (የመጨረሻ ክፍል) እግዚአብሔር በሴት ብልት  ላይ "ሀይሜን"  ያስቀመጠው በምክንያት ነው። ኪዳን ነው ። ለዚህ ነው የመጀመሪያውን ወንድ የማይረሱት። ውድ ልባም ሴት ድንግልናዋን የምትሰጠው በህይወት ዘመኗ አብሯት ለሚኖረው ለባሏ ነው። ድንግልና የሚሰጠው ለባል ነው !! ድንግልና ክብር ነው። ድንግልናን ያስቀመጠው እግዚአብሔር ነው። ከጋብቻ ውጭ ወሲብ መፈጸም የሚያመጣው ችግሮች ፦ 1. ተራ የሆነ የግብረ ሥጋ ግንኙነት ባርያ ያደርግሃል። የምትተኛቸው ሴቶች ጥንካሬህን( strength )እና energy ይወስዳሉ።ከቃል ኪዳን ውጪ የምታደርገው ወሲብ በጎነትን፣ መክሊትን እና ስኬትህን ያሳጣሀል። ለዚያም ነው ብዙ ወንዶች ወድቀው መነሳት የማይችሉት ። ጉልበታቸው ባልተፈቀደ የነሱ ባልሆነ አልጋ ላይ ተሰባብሯል። 2. በወሲብ አጋንንት ይተላለፋል ከመጀመሪያው ጀምሮ ጠላት መጠቀሚያ ያደረገው ሴትን ነው። 2ኛ ቆሮንቶስ 11:3 አሁንም የተለወጠ ነገር የለም። አንዳንድ ሴቶችን ዲያብሎስ ይጠቀማል። በአጋንንት እስራት ውስጥ ካለች ሴት ጋር sex ካደረክ አጋንንት በቀጥታ ይገባብሀል ። ደካማ ወንዶች አዕምሮ የጎደላቸው ለክፉ መንፈስ ተጋላጭ ናቸው ። ማስተዋል የጐደለውን ወጣት፣ ብስለት ከሌላቸው መካከል አየሁት፤ ከጎልማሶችም መካከል ለየሁት። ምሳሌ 7:7 3. በኮንዶም መካላከል አትችልም። አንዳንድ ወጣቶች በኮንዶም በመጠቀም መርገም የሚከላከሉ ይመስላቸዋል ። ወንድሜ ፦ አጋንንት መንፈስ ነው በኮንዶም መካላከል አይቻልም ። መከላከል የሚቻለው ንፅህናን በመጠበቅ ብቻ ነው። መከላከል የሚቻለው ዝሙትን "በመሸሽ" ብቻ ነው። በወጣትነት ዕድሜ ላይ የነበረው ዮሴፍ የቀረበለትን የወሲብ ግብዣ " እንቢ " በማለት ነው የተከላከለው።ዘፍጥረት 39:7 4. ወሲብ የሰልፍ ህይወት ውስጥ ያስገባል። የአንድ ቀን የ “አዝናኝ” ምሽት ለህይወት ከምትዋጋቸው ጦርነቶች ጋር ሊያቆራኝ ይችላል። የአንድ ቀን ወሲብ ዘመንህን ሰልፍ የሞላበት ያደርገዋል ። የአንድ ቀን ስህተት ህልሞችህን damage ያደርጋል ። ሀያላን በወሲብ ወድቀዋል ።  ወጣት ባለራዕይ በወሲብ ራዕይቻው ተበላሽቷል ። የተቀቡ አገልጋዮች አገልግሎታቸው በዝሙት ምክንያት ተበላሽቷል። ቤተክርስቲያን ተዘግቷል ። ሳምሶን የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት ታላቅ ሰው ነው ነገር ግን የሞተው በዝሙት ነው።  መሳፍንት 16:1 አንተ ከሳምሶን ትበልጣለህ ? 5. ከጋብቻ ውጭ sex ለበሽታዎች እና ላልታቀደ  ለእርግዝና ይዳርጋል። በዝሙት ምክንያት እነዚህ በሽታዎች ይተላፍብሀል ። ልብ በል sex ተላላፊ ነው የሚባለው ለዚህ ነው። HIV/AIDS  ፥ HPV ፥Gonorrhea Herpes simplex ፥ Chlamydia Hepatitis B – የጉበት በሽታ Syphilis በወጣትነት( ተማሪነት) ዕድሜ ወሲብ ማድረግ ለፅንስ ማስወረድ ፥ ለደም መፍሰስ ፥ መካንነት ይዳርጋል ። ከዚህም አልፎ በዕርግዝና ምክንያት ለስነ ልቦና ጉዳት ፥ ትምህርት ማቋረጥ፥ ውርደት፥ ሀፍረት ፥ ከቤተሰብ መጣላት ፥ ከአላማ መቅረት ፥ ከጓደኞች በታች መሆንን ያስከትላል ። ዋናው ደግሞ ከእግዚአብሔር ጋር ያለን ህብረት ያበላሻል ። መንፈሳዊ ህይወትን ይጎዳል። ቁልፍ ጉዳይ ፦  መንፈሳዊ ንፅህናን ጠብቅ !! ንፅህና ሃይል ነው ያለ ቅድስና እግዚአብሔርን ማየት አይቻልም ። “ለርኵሰት ሳይሆን እግዚአብሔር በቅድስና ጠርቶናልና።”   — 1ኛ ተሰሎንቄ 4፥7 ሰውነቱን የሚጠብቅ ሰው የወደፊት ህይወቱን ይጠብቃል። ቃል ኪዳንን የሚያከብር ሰው እጣ ፈንታውን ይጠብቃል። እራሳችሁን
2 · 396 ·
F
👌በዚህ ዘመን ከሚያስፈልጉ ነገሮች የመጀመሪያው ተሃድሶ ነው። 🔹በግል ተሃድሶ ♦️በቤተሰብ ተሃድሶ ♦️ለቤተ ክርስቲያን ተሃድሶ 🔹እንደ ሀገር ተሃድሶ። ለተሃድሶ ተግተን እንጸልይ።
1 · 333 ·
F
🤦‍♀ከራስ ጋር ትግል🤦‍♀ 📖 ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ📖         ምዕራፍ=አንድ          ክፍል=6       ስልኬ ጠራ ሳየው ቢኒ ነበር"ውይ ቢኒዬ ልደውልልህ ስል" ስለው በዚያ በሚያምር እና ልቤን ሀሴት በሚያሰማት ድምፁ "ምነው ሜሪዬ እንዴት ሳትመጣ ልትይኝ ነዋ?" አለኝ "እ እኮ እንዴት ቀረህ? አልኩት "ዛሬ እኮ ቃለህይወት እኔ እያሰለጠንኳቸው ያሉት ወጣቶች ፕሮግራም ነበረባቸው እና አብሬያቸው መሆኑ ግድ ስለሆነብኝ ነው" አለኝ "አይ እንደዛ ከሆነ አሪፍ ነው እኛም ዛሬ አገለገልን ብታይ በጣም ደስ ይል ነበር" አልኩት "ድሮስ የሙሉ ወንጌል ተማሪዎች ቀውጢ አይደለን!!""  ብሎ ቀለደብኝ ""እና ሜሪዬ ወደ አጀንዳዬ ስገባ የዛሬው ቀጠሯችን እንደተጠበቀ ነዋ?" አለኝ እውነት ለመናገር እንገናኛለን እንዳልኩት እርስት አድርጌው ነበር "እህ ለካ እሱም አለ በቃ በኋላ ቤት ኑና አብረን እንወጣለን" አልኩት "እሺ ሜሪዬ" አለኝ እና ቻው ተባባልን። አሁንም በእኔና ሶሲ መሀል ፀጥታ ሰፍኗል ሁለታችንም ዝም ተባብለናል በነገራችን ላይ ሶሲ ትፈራኛለች ግን  ተኳርፈን መቆየት አንችልም እኔም መታረቃችን ላይቀር ነገር ብዬ "አንቺ ፍቅር" አልኳት በእጄ ነካ አድርጌአት 'ወይዬ እማ" አለችኝ ፍክት ብላ"ስሚኝ እኔ እኮ ያናደደኝ አንደኛ ቸርች እየሄድን እንዲህ ማድረግ የለብንም! ሁለተኛ ደሞ ልጆቹ ምንድነው እንዲህ የሚሆኑት ብቻ የሆነ ነገራቸው ይጨንቃል ምንም ደስ አላሉኝ. .  ኸረ ሊያ ያላችሁኝሽ የት ነው ምታውቀኝ??" አልኳት ሁኔታዋ ግርም ስላለኝ ሶሲም "ልክ እኮ ነሽ ግን ማህሌት ስታጨናንቀኝ እኮ ነው ደሞ ብታይ ሁሌ ነው አስተዋውቅሻለሁ ምትለኝ የነበረው ሊያ ደሞ ፍቅር የሆነች ልጅ ነች ማለት ሰው ትወዳለች አንቺ ደግሞ ብትቀርቢያት እና የበለጠ ብታውቂያት እንዲህ አትይኝም ነበር" አለችኝ እኔም ነገሩ ባይዋጥልኝም ""እስቲ እናያለን" ብያት ተቃቅፈን እንደተለመደው የእብደት ጉዟችንን ቀጠልን መንገድ መንገዱን ስንቆም የሚቀረን ሰው የለም የማናውቀውንም ጭምር ሰላም ስንል ሱቅ እየገባን ላንገዛው እቃ ስንጠይቅ እንዲህ እንዲህ እያልን  ቤት ደረስን ስንደርስ እማ ብቻ ነበረች አባቴ ገና አልገባም "እማ የኛ አለም" ብለን ተጠመጠምንባት "እናንት ጉደኞች የዛሬው ፕሮግራም በእውነት አስገራሚ ነበር" አለችን ስራዋን ቆም አድርጋ ደስ እንዳላት በሚያሳብቅ አይኖቿ እያየችን እኔም ወሬ ሳጋግል (ኮሌታዬን ነካ ነካ እያደረኩ እንደ መጎረር እየሰራኝ)"well እንግዲህ ከልጆቹ ነው" አልኳት እማ እና ሶሲ ተያይተው ከት ብለው ሳቁ ከዛም ""በይ የኔ ጉረኛ ልብስሽን ቀይሪና ስኒ አቀራርቢ"" አለችኝ "እንዴ እማ ትንሽ ቆይቼ ወጣለሁ አልቀይርም" አልኳት "እኔ ምን ጨነቀኝ ዋናው መስራትሽ ነው" ብላኝ ምሳ ማቀራረብ ጀመረች እንዳለችኝ ስኒዬን አቀራርቤ ቄጤማም ጎዘጎዝኩና ወደ ጓዲያ ገብቼ እማን ማገዝ ጀመርኩ  ሶሲ ደግሞ ቡና መቁላት ጀመረች በመሀል ""ልጆቼ ቆሎ ፈጆቼ!!! የፈጆቼ እናት ውዷ ባልተቤቴ"  እያለ አባቴ መጣ እኛም በአባባሉ እየሳቅን እማ "ሶል ከማን ጋር ነበርክ? እንዲህ አሸምድደው የላኩብን!"" ብላው ሳቀችበት እኔም በእጆቼ ሳህኖች እንደያዝኩ "አባ Welcome!!" ብዬው በአባባሉ እሱም እየሳቀ ገባ ""ጥሩ ሰአት መጣሁ አይደል?" አለን እና "የኔ ኩስኩሱ" አላት ወደ ሶሲ ጠጋ ብሎ እኔም የእጅ ውሀ ይዤለት እየመጣሁ ሲል ሰማሁት እና እንደማኩረፍ እያደረገኝ  "እረ ነው ጥሩ እኔም እናቴ አለችልኝ እሷ ታቆለማምጠኛለች" አልኩት እያስታጠብኩት እሱም በእጁ ውሀ እየረጨኝ "የኔ ቀበጥ!!!" አለኝ ሶሲ ቀና ብላ አይታኝ "የባስ አታ
1 · 394 ·
F
🔴ፖርኖግራፊ እና ክርስቲያን🔴 በዓይነቱ ለየት ያለ ተከታታይ መንፈሳዊ ትምህርት፦ #ፖርኖግራፊምንድነው? #ራስን በራስ መድፈር? #ከሰውነት ወደ እንስሳነት🚷 #ፖርን ያቆሰለው አእምሮ ምን ይመስላል? #ያልተነገሩ የመውጫ መንገድ ተግዳሮቶች ዊዝድሮዋል ሲምፕተምስ እና ሌሎችም በ https://t.me/ReformationNeeded ለሌሎችም ሼር በማድረግ ያድርሱ
1 · 324 ·
F
🔴ፖርኖግራፊ እና ክርስቲያን🔴                  #ክፍል1 ውድ የነቃ ትውልድ ቤተሰቦች የኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም እና ፀጋ ለእናንተ ይሁን! ከዚህ ቀጥሎ በሚኖሩን ጥቂት ጊዜያት “#ፖርኖግራፊ እና ክርስቲያን ” በሚል ርዕስ የሚቀርቡ አጫጭር እና ተከታታይ መንፈሳዊ ግንዛቤን የሚያስጨብጡ ትምህርቶች አቀርባለሁ። ለዛሬ እንደ መግቢያ የመረጥኩት #የፖርኖግራፊ ትርጓሜው ምንድነው? #ፖርኖግራፊ ናቸው ብለንስ የምንፈርጃቸው ነገሮች ምን ምን ናቸው? ድንበራቸውስ የት ድረስ ነው? የምለውን እንድናይ ነው። አብዛኛው ክርስቲያን የፖርኖግራፊን ትርጓሜ በተለምዶ፦ “የብልግና ተንቀሳቃሽ ምስሎች እና እርቃን ምስሎች” በሚል አጭርና የተዛባ ትርጓሜ ስለገደበው ሌሎች ተያያዥ እና አደገኛ ወሲባዊ ልምምዶች እንደ ጤናማ የሕይወት እንቅስቃሴ ተቆጥረው በብዙ ክርስቲያን ወጣቶች ዘንድ ያለከልካይ ሲተገበሩ ይስተዋላል። ፖርኖግራፊ “ፖርኔ” እና “ግራፋይን” ከሚሉ የግሪክ ቃላት የመጣ ነው። “ፖርኔ” ጋለሞታ ሴት ማለት ሲሆን “ግራፋይን” ደግሞ መመዝገብ ወይንም መፃፍ ነው። በጊዜውም ባለው ጥንታዊ ትርጉም፦ የአንዲትን ጋለሞታ ሴት ወሲባዊ ሕይወት መዝግቦ በፅሁፍ እና በስዕል በማቅረብ ሰዎችን ባልተገባ እና ኃጢያት በሆነ መልኩ ለዝሙት እና ወሲባዊ ምኞት የሚያነሳሳ ድርሰት ነው። ይሄው ወሲባዊ ኃጢያትን የመጻፍ፣የመሳል እንዲሁም  የመድረስ ሴጣናዊ አባዜ በየዘመኑ እየሰፋ እና እያደገ መጥቶ አሁን ካለንበት ዘመን ደርሷል። ይሄም መጽሐፍ ቅዱስ በሮሜ1፥24-28 (ይነበብ) ላይ እደሚያስረዳን ሰዎች እግዚአብሄርን ለማወቅ እና ለመታዘዝ ባልወደዱ መጠን የወደቁት ከባድ የኃጢአትና የሥነ-ምግባር ዝቅጠት የሚያሳይ ነው ። በሰዎች መሃል ከሚደረግ ዝሙት አንስቶ እስከ ሰው ከእንስሳ ግንኙነት ከግብረሰዶማዊነት አንስቶ እስከ በስጋ ዘመዶች መሃል የሚደርግ እርኩሰት ያሉ ድርጊቶችን በቪድዮ ቀርፆ በምስል አንስቶ በመጽሐፍ ደርሶ ኢንተርኔት በሚባል መረብ ሊያጠምድ የእህቶቻችንና እና የወንድሞቻችንን እንዲሁም የታዳጊ ህጻናትን ደጅ በስልኮቻቸው ፣በታብሌቶቻቸው እንዲሁም በኮምፒውተር በኩል ደጆቻቸውን ያንኳኳል። አሁን ባለውና ተቀባይነት ባገኘው ትርጉሙ፦     ፖርኖግራፊ ማለት ማንኛዉም የታተመ እና የተጻፈ ምስል፣ድምጽ እና ቪዲዮ በውስጡም ማንኛዉንም ዓይነት ጾታዊ ግንኙነት የሚመስል(መሳሳም እና ያልተገባ አካላዊ ንኪኪን ይጨምራል) የያዘ ወይንም ወሲባዊ ድርጊቶችን፣እርቃንነትን እና ወሲባዊ ንግግሮችን ያካተተ ነገር ነው(sex_chat)። ስለዚህ ክርስቲያን ሆነ የቆምክበትን ቦታ ታውቃለህ❓ የምታያቸውን፣የምትሰማቸው እና የምታነባቸዉን ነገሮች ታስተውላለህ❓ የሀገራችን ወጣቶች አዘውትረው የሚያዳምጡት የምዕራባዊያኑ ሙዚቃ ፖርን ሰለመሆኑ ከዚህ በላይ ማስረጃ የለም። እያንዳንዱ የሴትና የወንድ ፆታዊ የአካል ክፍል እየተነሳ የሚሞገስበት፣እርቃንነት የሚወደስበት እናም በትዳር ላይ መባለግ እንደ ጀብዱ የሚጨፈርበት ሙዚቃ ከዚህ ሌላ ትርጉም ሊሰጠው አይችልም።ዝሙት ነውና ሌላው ደግሞ ፊልም በሚባል መዝናኛ በሚመስል ማር በመርዝ ተቀምመው የሚቀርቡ የፍቅር ታሪኮች ውስጥ ያሉ ከጋብቻ በፊት የሚደረጉ መሳሳም፣ አካላዊ ንኪኪ አልፎም ወሲባዊ ድርጊቶች እና ሌሎችም በእውነታ ላይ ያልተመሰረቱ የፍቅር ፈንጠዝያዎች የወጣቱን ቀልብ ገዝተው ባሳደሩት ተጸዕኖ እንደ ጤናማ ድርጊት ያለ ዕፍረት በየአደባባዩ ይተገበራሉ። በዚህ አጋጣሚ በዚህ ልምምድ ያላችሁ ወጣቶች ከየትኛውም ፊልም ራሳችሁን አርቁ። ስለዚህ አንባቢ ሆይ አሁን ትርጉሙንም ድንበር የለሽነቱንም አይተናል። እናስተውል እራሳችንንም
6 · 322 ·
F
🤦‍♀ከራስ ጋር ትግል🤦‍♀  📖 ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ📖          ምዕራፍ=አንድ           ክፍል=7         ከዛም የተለመደው ቦታ እንድናከብርለት ተስማማን ቢኒ "እና በቃ ሜሪ እና ሊዱ ሄዳቹ ጠረዼዛ አስተካክሉ እኔና ናሆሜ ኬክ ይዘን እንምጣ" አለን "እሺ ግን እንዳትቆዩ!" አልኳቸው ናሆሜም "አንቆይም ሜሪዬ በቃ እንዳይደብራችሁ እሺ!" አለን እና ስመውን ሄዱ እኛም በሀሳቡ ተስማምተን እኔና ሊዱ ሆቴል ሄድን ቢኒ ዝም ብሎ እንጂ ምንም ሚስተካከል ነገር አልነበረም ከሊዱ ጋር ወደ ሆቴሉ ገባን የተለመደች ቦታ አለችን እናም ወደዛው አመራን የምናውቃቸውንም ሰዎች ሰላም ብለን ቁጭ አልን እና ሊዱ "አብረን ብንሄድ ይሻለን ነበር እዚህ ከሚደብረን" አለችኝ እኔም ጠረጴዛው ላይ እጄን ተመርኩዤ ጋደም እያልኩ "እህህህህ!! (ትንፋሼን በሀይለኛው እያስወጣሁ) አዎ ይሻለን ነበር" አልኳት ሊዱም ""ኸረ በቃ ተነሽ! ነግቷል እኮ" አለችኝ እኔም ዝም ብያት መተኛቴን ቀጠልኩ "ሜር እውነት እንዳይደብርሽ ተነሺ እ ደሞ ፀሀዩም ነው እንዲህ ያደካከመሽ" አለችኝ ስስት ብላ እያየችኝ እኔም ቀና ብዬ አየኋት ዝም ብዬ ስለሰለቸኝ ነበር ጋደም ያልኩት እሷ ግን ከእኔ በላይ ስለኔ ታስባለች ፀሀይ አቃጠለኝ ስላት እሷን እየለበለባት ለኔ ሸሚዟን አውልቃ የምትሰጠኝ ዝናብ ሲሆን ብርድ ይመታሻል እያለች. . . ስለ ሊዱ ስንቱን ላውራው የቱን ልናገረው ቆይ ሊዱ ምኔ ነች? እህቴ? ጓደኛዬ? እናቴ? እ ምኔ ነች በቃ ሊዱዬን እነዚህ ቃላቶች ያንሱባታል  ቁም ነገረኛ ሆና አይደለም የምወዳት ግን ለደቂቃ ጠረኗ ይናፍቀኛል እኛ ቤት ሁላችንም ሊዱን በምክንያት ነው የምንጠራት እማም ቡቻዬ የምትላት የራሷ ምክንያት አላት ያኔ እማ እኔን ከወለደች በኋላ የሶስት አመት ከምናምን ህፃን እንዳለሁ የደም መርጋት አጋጥሞሻል ተብላ ሆስፒታል ለሆስፒታል ስትንከራተት፣ ቤት እየመጡ የእማ ህብረቶች ሲፀልዩላት. .  በዚሁ ሁሉ መሀል ጌታ ክእኛ ይልቅ መፅናኛ እንድትሆናት ሊዱዬን ሰጣት አንድ ቀን: የመዘምራን ህብረቶች በሙሉ ተሰባስበው እማን ከበው እጃቸውን ጭነው ሲፀልዩላት በዚያ ግርግር መሀል ተሽሎክሉካ መጥታ በጣፋጭ ማር አንደበቶቿ በስስ እጆቿ የእማን ፀጉር እየነካካች "አይዞሽ እሺ እማይዬ አሜን አሜን አለ" አለቻት እማ እስካሁን ድረስ ይሄ ነገር ሲነሳ እምባዋ ልክ የለውም ሁልጊዜ ሊዱዬን ባየቻት ቁጥር ይሄ ነገር ትዝ ይላታል በእርግጥ ሊዱ ይሄ ህይወት አይገባትም ነበር ሁልጊዜ ሊዱ "ቆይ እናቴ ምን ያህል ብትጠላኝ ነው?? እኔን ማየት የማትፈልገው ትላለች ከልጅነታችን ጀምሮ የወደፊት ራዕያችሁን ፃፉ ስንባል የክፍሉ ልጆች ዶክተር፣ ኢንጅነር፣ፓይለት. . ስንል ሊዱዬ ግን "እናቴን ማግኘት" ነበር የምትለው በሌላ ቀን ደግሞ የእናትና አባታችሁን ስም ፃፉ ሲባል ሊዱዬ የእማ እና የአባትዬን ስም ትፅፍ እና ልታሳርም ስትሄድ አስተማሪዎቻችን "አይይ የአባትሽን ስም ተሳስተሻል ነገ ቤተሰቦችሽን ጠይቂና ነይ ያኔ አርምልሻለሁ"" ይሏት ነበር እና እኔም ሊዱ- ዬ የምላት ኪያዬ (የኔ) እንደማለት ነው ""ሜሪ ሜሪ ሜሪዬ. ."" የሚል ድምፅ ሰምቼ ብን ብዬ ከሄድኩበት የሀሳብ አለም ስነቃ ሊዱ አጠገቤ መጥታ እጄን ይዛኝ እየጠራችኝ ነው እኔም የኔ መመሰጥ ገርሞኝ ዞር ብዬ "ሊዱዬ" አልኳት "ምነው ሜሪ እኔን ቁጭ አድርገሽ በሀሳብ ትሄጄለሽ?" አለችኝ "ስላንቺ እያሰብኩ ነበርኮ" አልኳት ፈገግ ብዬ መቼስ ጉራ ከኔ ተምራለች ትከሻዋን እያሻሸች "አዎ አዎ አውቃለሁ ያው እኔ እኮ ምገርም ሰው ነኝ" አለችኝ ቆፍጠን ብላ ቁጭ እያለች እኔም ከት ብዬ ሳኩባት እና ስልኳን አውጥታ
252 ·
F
ፖርኖግራፊ እና ክርስትና ክፍል2 ማስተርቤሽን እንደ አስገድዶ መድፈር 📖ማስተርቤሽን፦ ፃታዊ የአካል ክፍልን በመነካካት ወሲባዊ እርካታን ማግኘት ሰላም የነቃ ትውልድ ቲዩብ ቤተሰቦች የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ለእናንተ ይሁን! በክፍል ሁለት ደግሞ ማስተርቤሽን ምንድነው የሚለውን እናያለን፦ የፖርንና የፍትወት መገባደጃው ማስተርቤሽን ነው። በተለምዶም "ራስን በራስ ማርካት"  ወይም ግለ ወሲብ የሚል ትርጓሜ አለው። ነገር ግን ይሄ ትርጉም ትክክል አይደለም በ3 መሰረታዊ ምክንያቶች: ✅1ኛ እግዚአብሄር የወሲብን ስጦታ የሰጠው በትዳር ዉስጥ ላሉ ባልና ሚስት ብቻ ነው። ስለዚህ ወሲብ በባህሪው የሁለትዮሽ ትስስር እንጂ የአንድዮሽ ተግባር አይደለም። ሊሆንም አይችልም። ✅2ኛ በትዳርም እንኳን ቢሆን ወሲብ ፍቅርን ጥልቅ በሆነ መንገድ የመግለጫ ስጦታ ነው። ይሄም በ1ኛ ቆሮ 7÷3-5 እንደተጻፈ አንዳቸው አንዳቸውን ከራሳቸው አብልጠው ለማስደስት በሚያደርጉት ጥረት የጋራ እርካታን የሚያገኙበት እንጂ የራስን ፍላጎት እና ስሜት ብቻ ለማርካት የሚኬድበት ጉዞ አይደለም ✅3ኛ ወሲብ አካላዊ ስሜትን ከማርካት በላይ መንፈሳዊ ትርጉም አለው ይሄውም በትዳር መሃል የሚፈጠርን አድነት የሚያመጣ ከመሆኑም በላይ የእግዚአብሄር ስጦታ የሆኑት ልጆች የሚገኙበት መንገድ ነው። ስለዚህ ወሲብ ከዚህ ሁሉ ኃላፊነት ጋር የተሰጠ ጋብቻዊ ጸጋ ነው ይሄም ጉዳይ ራስን በራስ የማርካት ጉዳይ ሳይሆን ሌላ ሁለተኛ አካል የሚፈልግ የሁለትዮሽ ትስስር ነው። ከነዚህ ዋና ዋና የወሲብ መገለጫዎች ተነስተን ማስተርቤት የሚያደርግ ሰው በተለያየ መንገድ ለምሳሌ በምስል፣በድምፅ ወይንም ደግሞ በቪዲዮ ሌላ ወንድን ወይንም ሴትን አምጥቶ/ታ ነው። ወይም በምናቡ ስሎ/ላ ነው ከሚል ግልጽ ከሆነ ድምዳሜ ላይ እንደርሳለን። ይሄ ደግም መሰረታዊ እና የማይነጣጠሉ የኃጢያት ልምምዶችን ይዞ ይመጣል እነዚህም ምኞትን የራስ ባል ወይም ሚስት ያልሆነን ሰው ለዝሙት መመኘትን፣ምኞትም ደግሞ በማቴ5፥28 እንደተፃፈ ማመንዘርን ይወልዳል። ይሄም ወሲብን ከተፈቀደበት መንገድ ውጪ ለገዛ ስጋዊ ምቾት ማዋልን ያመጣል በዚህም በ1ኛ ቆሮንቶስ 6፥18 እንደተጻፈ በገዛ ስጋ ላይ ኃጢያትን መስራትን ያስከትላል።  ስለዚህ የማስተርቤሽን ገላጭ ትርጉም ምን ይሁን? በፒውሪቲ ዙርያ የሚሰሩ አንድ ዶ/ር ስዩም አንቶንዮ የተባሉ ሰው በአንድ ወቅት ሲናገሩ፦ “📌ማስተርቤሽን ማለት ራስን በራስ መድፈር ነው!” የሚል ትርጉም ሰተውታል። በእርግጥም ይሄ ትርጉም አቻ ቃሉ ባይሆንም ከኃጢያትነቱ እና ከሚያስከትለው የአእምሮ ቀውስ አንፃር የሚመጥነው ትርጓሜ ነው። 1ኛ ቆሮ 6 ላይ እንደተፃፈ ስጋ ለጌታ እንጂ ለዝሙት አይደለም። እዛውም ክፍል ላይ ቀጥሎ በዋጋ ስለተገዛን የራሳችን አለመሆናችንን ያመለክተናል ታዲያ ለዚህ ለጌታ በሆነው ማንነታችን ላይ ይህን ኃጢያት መፈጸም እና ማዋረድ አልፎም ጌታን ብቻ እንድናከብርበት የተጠራንበትን መጠራት በፍትወት ማቆሸሽ የራስን ንፅህና በራስ መድፈር ነው እንጂ ሌላ ምንም ሊባል ይችላል? በእርግጥ አንዳንድ ሰዎች ፖርኖግራፊ እና ማስተርቤሽን በቀጥታ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ስላልተጠቀሰ ኃጢያት አይደለም ሲሉ ይደመጣል። የእነዚህን ሰዎች ስንኩል አመክንዮ ለመረዳት አንድ ምሳሌ ማየት ጠቃሚ ይመስለኛል፦ በአንድ ወቅት አንድ በባልንጀራው ላይ የሚቀና ሰው ነበር ይሄም ሰው የባልንጀራውን ንብረት ሁሉ የራሱ ለማድረግ ምኞት ነበርው። ይሄንንም ድብቅ ፍላጎቱን የምታውቀው ሚስቱ ስትመክረው ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ዘጸ 20 ላይ “....የባልንጀራህን ሚስት ሎሌዉንም ገረዱንም በሬዉ
5 · 306 ·
F
ክርስቶስን ያመነ ሁለቴ ይወለዳል አንዴ ይሞታል። ያላመነ ግን አንዴ ይወለዳል ሁለቴ ይሞታል። ምርጫው በእጃችን ነው። ክርስቶስን መምረጥ or not. ዛሬ ወስነን ክርስቶስን እንከተል። ኢየሱስ ክርስቶስ እንደሞተና እንደተቀበረ፣ ከሞትም በሦስተኛው ቀን እንደተነሳ በልባችን እንመን። ኢየሱስ ጌታ ነው ብለን እንመስክር። ምክንያቱም ሌላ የመዳኛ መንገድ የለምና። እባካችሁ ከክርስቶስ ጋር ሳትተዋወቁ አትሙቱ። ምንም ማንም ይቅርባችሁ ልባችሁን ወሰናችሁ ለክርስቶስ ስጡ። ዳግመኛ ተወለዱ። ኢየሱስ ይወዳቿል❤️❤️ 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 @ReformationNeeded @ReformationNeeded @ReformationNeeded sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ◈sʜᴀʀᴇ ለአንድ ጓደኛችሁ ሼር አድርጉለት
184 ·
F
🤦‍♀ከራስ ጋር ትግል🤦‍♀ 📖ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ📖        ምዕራፍ=አንድ         ክፍል=8 "ተይ ስለ ሰው ሳታዉቂ አታውሪ" አለችኝ ሀይለኛ ኩስታሬና ግልምጫ በተሞላ መልኩ እኔ እንኳን እንዲህ ተኮሳትራብኝ እንዲሁም ቶሎ ይከፋኛል ትክዝ ብዬ ስለ ነገሩ ማሰብ ጀመርኩ ይህ ነገር ብዙ ጊዜ ተደጋግሟል ሶሲ ከእኔ ይልቅ ለጓደኞቿ ትልቅ አክብሮት ያላት መሰለኝ ከእኔ ይልቅ እነሱን ያስበለጠች መሰለኝ ልቤ ፈራ የማጣት መሰለኝ አይኖቼ ዕምባ አቀረሩ በዚህ መሀል አባቴ መጣ "ልጆች!! ልጆች" እያለ እየተጣራ ገባ እኔም በጣም ከፍቶኝ ከሶሲ ክፍል ወጥቼ ወደ ክፍሌ ስገባ አየኝ "እንዴ! ሜሪ ስንት ሰአት መጣሽ?" አለኝ ኮቱን እያወለቀ እኔም ድብር እንዳለኝ "ቆየሁ" አልኩት አባ ቶሎ ይረዳኛል "አይንሽ ደግሞ ልክ አይደለም አሞሽ ነው ወይስ አልቅሰሽ?" አለኝ  ቀስ ብሎ ፊቴን እያሻሸኝ እኔም "አይ አባ ምንም አልሆንኩ" ብዬው ወደ ክፍሌ ገባሁ ሶሲ በዚህ መሀል ምን ሆንሽ ልትለኝ እንኳን አልመጣችም በቃ ስለ ጓደኞቿ ሲነሳ ትቀያየራለች የዋኋ ሶሲ ትቀየርና ሌላ የሆነ በቃ መንፈስ ነው የምትመስለኝ የክፍሌን በር ቆለፍኩትና ልብሴን ቀያይሬ ተጠቅልዬ ተኛሁ በዚህ ሁሉ መሀል የኔ ምስኪኗ እናት "ልጄ ውሻዬ ምን ሆናብኝ ነው እማ!! እማይዬ" እያለች በሚያምር እና ችግሬን በሚያስረሳኝ ድምጷ መጣራት ጀመረች እኔም ላስጨንቃት ስላልፈለኩ ተነስቼ በሩን ከፈትኩላት ልክ እንዳየችኝም "ምነው ልጄ ከእነ ናሆሜ ጋር ሰላም አይደለም??" አለችኝ አልጋ ላይ ቁጭ ብለን ፀጉሬን እያሻሸችኝ "እረ እማ አይደለም ትንሽ ደክሞኝ ነው" አልኳት "በቃ የምን ድካም ዉጊው እንጂ" ብላኝ ሀዘኔን በሚያስጠፋው ሳቋ ከት ብላ ሳቀች እኔም አብሬያት ፈገግ አልኩ በቃ ቤቱን ላሟሙቅ ብላ ቡና አቀራረበችና ማፍላት ጀመረች ብቸኝነቱ ቀጥሏል እኔም ሶሲም ክፍላችን ነን ብዙውን ጊዜ እኔና ሶሲ ሊዱ ከሌለች ተለያይተን አንቀመጥም ከሁለት አንዳችን ክፍል ስናነብም ስንተኛም አንለያይም ነበር እማ እና አባ "ሜሪ! ሶሲ! ኸረ ምንድነው ኑ!" አሉን እኔም ከአልጋዬ ተነስቼ በሬን ከፍቼ ስወጣ ከሶሲ ጋር ተገጣጠምን እናም ሶሲ ፈገግ ብላ "Hii ሜሪ" አለችኝ በግርምት መልኩ "ኢኢኢ" አልኳት ህፃን ሆነን ስንጣላ እና ጓደኞቻችን ሲያስቀይሙን እንደምንሆነው እየሆንኩ ሶሲም ጠጋ አለችኝ እና "አይደለም እኮ ጌታን አንቺ ስለ ማሂ በጣም ብዙ የማታውቂው ነገር አለ" አለችኝ እኔም ምን ሊኖር ይችላል?? የሚል ጥያቄ ወደ አዕምሮዬ ቢመጣም እሺታዬን አንገቴን በመነቅነቅ ገለፅኩላት እሷም ደስ አላት እና ሳመችኝ በቃ ይሄው ነው ኩርፊያችን እናም የተለመደው እብደት ጀመረን እየተጯጯህን ወደ ሳሎን ገባን አባ ቶሎ ብሎ "እህ እህ ገባኝ ቅድም ተጣልታቹ ነው አይደል?" አለኝ ፋታ አልሰጡንም እማም ቀጥላ "እኔ ደግሞ ስንቱን አሳሰብሽኝ  ፍቅራቹም ፀባቹም አይቻል" አለች ሶሲም በአባብላቸው  ፈገግ አለችና "በቃ ራት ላቀራርብ" ብላ ወደ ጓዲያ ገባች እጃቸውን አስታጥቤ ራት በላል የበላንበትን እያነሳሳሁ ስለ ዛሬው ፕሮግራም ነገርኳቸው ደስ እያለንም ቡናችንን ጠጥተን ነገ ክላስ ስላለን ቶሎ መተኛት አለብን ተባብለን እና ደብተራችንን አስተካክለን ተኛን አይነጋ የለ ነጋ እኔም ጠዋት ከሶሲ ቀድሜ ተነሳሁ በእንቅልፍ መንፈስ ሆኜ አይኖቼን እያሻሸሁ ወደ ሶሲ ዞር ብዬ ሳይ ጧ ብላ ተኝታለች "ተበላሽ ገለቴ!" ብዬ በቀስታ ሳኩባት እና በጥሩ መንፈስ ተነቃቅቼ አባቴ ጋር ሄድኩ እና "እንዴት አደሩ? ጋሽ ሰሌ" አልኩት በሹክሹክታ እና ኮቴዬን አጥፍቼ እየገባሁ እንደዛ ሳደርግ የነበረው ሶሲ እንዳትነሳ ነበር ግን ሳይ
205 ·
F
🔴ፖርኖግራፊ እና ክርስትና #ክፍል3 ክርስቲያን ፖርን ስታሮች በሳይበር መስኮት የሳይበር ወሲብ ማለት፦ ማንኛውንም ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂን ለምሳሌ ስልክ፣ታብሌት፣ላፕቶፕ እና የመሳሰሉትን በመጠቀም በኢንተርኔት ወይም በሌሎችም አገልግሎት አቅራቢ ኔቶርኮች አማካኝነት የሚደረግ ቅጥ አምባሩ የጠፋ ወሲብ ነው። ሰላም የነቃ ትውልድ ቲዩብ ቤተሰቦች የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ እና ሰላም ለእናንተ ይሁን! ለዛሬ ከዚህ ትልቅ የሳይበር የወሲብ ባህር ውስጥ የምናተኩረው በሁለት ዓሣዎች ላይ ነው። እነዚህም ዓሣዎች በተለምዶ ፦ live cam(ቪዲዮ ሴክስ) እና ቻት ሴክስ በመባል ይታወቃሉ። ይሄንን የ#ክፍል3 ጽሁፍ ከስር መሰረቱ ለመረዳት አንባቢ 👉🏿#ክፍል1 እና #ክፍል2 ን በሚገባ መረዳት አለበት።ከክፍሎቹም ተያያዥነት አንፃር አንዱ ክፍል ብቻውን ሙሉ ሃሳብ የሚያስተላልፍ ሳይሆን በቀደሙት ክፍሎች ላይ ተንሰላስሎ የሚገባ ሰንሰለት ነው። ወጣት ክርስቲያኖች አንዴ በ ቪዲዮ እና ቻት ሴክስ ኃጢያት ተፅዕኖ ውስጥ ከወድቁ በኋላ የሚያደርጉትን ባለማስተዋል እንደ እንስሳ በስሜታቸው እየተመሩ በሬ ለመታረድ እንደሚነዳ እንዲሁ እራሳቸውን ለፖርኖጋራፊ ጣዖት መስዋዕት ያደርጋሉ። መጽሐፍ ቅዱስ በሮሜ6፥13 ...ብልቶቻችሁን የዓመፃ የጦር እቃ አድርጋችሁ ለኃጢያት አታቅርቡ... ይላል። በተቃራኒው እነዚህ ወጣቶች በቪደዮ እና በምስል የራሳቸውን እርቃን በአማላይ ድምጽ እና ጹሁፍ ቀምመው ከሚያውቁት ወይም ደግሞ ምንም ትውውቅ ከሌላቸው ሰው ጋር በመመለዋወጥ ስሜታችውን ለማርካት ይጓዛሉ። ኢንተርኔቱም ሲፈልጉ ከሚያውቋቸው ጓደኞቻቸው ጋር ሳይፈልጉ ምንም ከማያቁት ሰው ጋር የሚገናኙበትን ምስጢራዊ የዝሙት ድግስ ደግሶ ኑ ይላቸዋል። እነሱም ከቤታቸው ሳይወጡ ከፈለጉበት ሆነው ጥቂት የስልክ ወይም የ ኮምፒውተር ቁልፎችን በመጫን ይሄን ልቅ ድግስ ይታደማሉ።ድግሱን ለመታደም የሚያስፈልገው መስፈርት ቅለት እና ምስጢራዊነቱ ለወጣቶቹ ጊዜያዊ መደበቂያን እና ምቾትን በመፍጠር የበለጠ ከሱሱ ጋር እንዲላተሙ ያደርጋቸዋል። ያልተረዱት አንድ እውነት ግን ምናልባት ከሰው ምስጢር ማድረግ ይቻል ይሆናል ሁሉን ከሚያይ አምላክ አይኖች ስር ግን የት መደበቅ ይቻላል?? ሰማይ ዙፋኑ ምድርም የእግሩ መረገጫ ናት!... “በሕያው እግዚአብሔር እጅ መውደቅ የሚያስፈራ ነው።” ዕብ 10፥31 #ሳይበር ሴክስ አስከትሎቱ ምንድነው❓ ✅1ኛ ሳይበር ሴክስን የሚያደርጉ ሁሉ የፖርኖግራፊ(ክፍል 1 ይመልከቱ) መሪ ተዋናዮች በተለምዶም ፖርን ስታርስ ናቸው። ነገር ግን ይሄን እውነታ እንዳያዩ ዓይናቸው ይታወራል። ወሲባዊ ስሜቱን በጽሁፍ እርቃኑን ደግሞ በምስል አድርጎ ለአድንም ይሁን ለብዙ ሰው የሚያጋራ ግለሰብ ፖርን የሚተውን ተዋናይ እንጂ ሌላ ምን ይባላል? ✅2ኛ, በዚህ ልቅ ድግስ ላይ የሚሳተፍ ወንድም ይሁን ሴት ጋለሞታነትን ይለማመዳል።በግልፅ አነጋገር ወንደኛ ወይም ሴተኛ አዳሪ ይሆናል። ለጊዜያዊ ደስታ እርቃናቸውን የሚቸረችሩ፣ንፁህ ጓደኞቻቸውን የሚያስነውሩ፣የማያውቃቸው ሰው ለጥቂት ደቂቃ ቻት ሴክስ የሚገዛቸው ጋለሞታዎች ይሆናሉ። ስለዚህ አንባቢያን ሆይ “ሥጋችሁ የክርስቶስ ብልቶች እንደሆነ አታውቁምን?እንግዲህ የክርስቶስን ብልቶች ወስጄ የጋለሞታ ብልቶች ላድርጋቸውን❓ አይገባም።ወይስ ከጋለሞታ ጋር የሚተባበር አንድ ሥጋ እንዲሆን አታውቁምን❓1ኛ ቆሮ6÷15-16 👨ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ👨 .          #እወዳችኋለሁ❤ በዚህ ግንኙነት ውስጥ ያላችሁ እኔን ለማገኘት 👉 @abit9 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 @ReformationNeeded @ReformationNeeded @Re
2 · 180 ·
የ
የነቃ ትውልድ Tube
Photo
click to show
. ክርስቲያናዊ ጋብቻ ➡️ለወጣቶች፦ የወደፊት ትዳራቸውን በክርስቲያናዊ ምሳሌነትና በጌታ ፈቃድ ለመመስረት ለሚዘጋጁ ➡️ለእጮኛሞች፦ በፍቅርና በቅድስና ላይ የተመሠረተ ክርስቲያናዊ እጮኝነትን ለመምራት ለሚፈልጉ ➡️ለባለትዳሮች፦ የጋብቻ ህይወታቸውን በክርስቶስ ፍቅርና በመጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ማደስ ለሚፈልጉ ባለትዳሮች ​እና ወጣቶች የተዘጋጀ መፅሐፍ ነው ከታች የሚገኘውን ሊንክ በመንካት በ250 ብር ብቻ መግዛት ይችላሉ። ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን በቀላሉ መጽሐፉን ያውርዱ👇👇👇👇 https://ye-buna.com/samiyy?ref=product_detail&product=6abca0f06ad01_samiyy መጽሐፉን ከከፈሉ በኋላ "showlife" በሚል Sms text ይደርስዎታል እዚያ ላይ የመጽሐፉ የ pdf ሊንክ አለ
86 ·
F
Photo
click to show
#ይሄ_መልዕክቴ_ከማያምን_ሰው_ጋ_የፍቅር_ግንኙነት_ለጀመሩ_ይድረስልኝ አንዳንድ ክርስቲያኖች አማኝ ካልሆነ ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነትን ለመጀመር ሲያስቡ 🙍‍♀" ምናልባት ወደ ጌታ ብስበውስ ማን ያውቃል !" 🙎‍♂ " ጌታ እኔን ተጠቅሞ ወደ ቤቱ ቢያመጣትስ ! " ይላሉ ። 🚫 የኔ ወንድም ከላይ እንደሚታየው የክሬን መኪና ከጥፋት አወጣለሁ ብሎ ወደ ጥፋት መግባት አለ አስብ/ህ! 💎ልብ ብላችሁ እላይ ያለውን የክሬን መኪናን ተመልከቱ ውሃ ውስጥ የገባውን መኪና አወጣለሁ ብሎ እራሱ ውሃ ውስጥ ገብቷል። ይሄን ከራሳችሁ ሕይወት ጋ አመዛዝኑ መጀመሪያ ላይ ከዓለም እያወጣሽው እና ወደ ጌታ እየመለስሽው ሊመስልሽ ይችላል ፤ እውነቱ ግን መፅሀፍ ቀዱስ እንደሚናገረው አብ ካልሳበው በቀር ወደ ጌታ የሚመጣ አለመኖሩ ነው ። (ዩሐ 6፥44) ወንጌልን በአፍ እና በተግባር መናገር የእኛ ስራ ነው ። ሰውን ወደ ጌታ ማምጣት ግን የእኛ ስራ አይደለም ። 👉 ሰው ወደ ጌታ መምጣት ያለበት ለመዳን ከጌታ ውጭ ሌላ መንገድ እንደሌለ ተረድቶ እንጂ ያፈቀረውን ሰው ደስ ለማሰኘት ከሆነ ሀይማኖት ቀየረ እንጂ አላመነም አልዳነም ። ስለዚህም ዛሬ ነገ ሳትሉ ግንኙነታችሁን አቁሙ አይ ከላችሁ በሕይወታችሁ ቀይ መብራት እያበራ ነው። " ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?" (2ኛ ቆሮ 6:14) 👨ወንድማችሁ ፍሬ ነኝ👨 .          #እወዳችኋለሁ❤ በዚህ ግንኙነት ውስጥ ያላችሁ እኔን ለማገኘት 👉 @abit9 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 @ReformationNeeded @ReformationNeeded @ReformationNeeded     ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ   sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯   
118 ·
F
🤦‍♀ከራስ ጋር ትግል🤦‍♀   📖ተከታታይ መንፈሳዊ ልብወለድ📖   ምዕራፍ=አንድ   ክፍል=9 ዞር ስል ዮናስ እና መጡ የተባሉት የማህሌት ጓደኞች እራሷ ማህሌት  እና ሶሲ ናቸው ከምንም በላይ ሶሲን ሳያት  በጣም ተናደድኩ ""ሜሪዬ!!" ብላ ሊያ የምትባለው አቀፈችኝ  የሷ አልበቃ ብሎ ወዲያው ዮናስ "ኸረ ለኛም አስተርፊልን" ብሎ ተጠመጠመብኝ አኳኋኑ ገርሞኝ ድንግጥ እንዳልኩ ዞር ስል ሶሲ ከሊዱ ጋር የጦፈ ወሬ ይዛለች ናሆሜ እና ቢኒ በጣም ደብሯቸው ቁጭ ብለዋል ቀና ብዬ ማህሌትን ሳያት አይን ለአይን ተያየን እና ሼም ይዞኝ ሰላም ብዬ አቀፍኳት ከጎኗም አንድ ቆንጆ በሚባል ደረጃ ያለ ልጅ ቆሞ ነበር እሱንም ሰላም አልኩት በዚህ መሀል የደውል ድምፅ ሰማን እና እነ ማህሌት እየተጣደፉ "byyy" አሉን ሶሲም እየተቻኮለች ሊዱን ሳመቻት እና እነ ቢኒን "እንገናኛለን!!" ብላቸው ሄደች እኔም ተገላገልኩ ብዬ ወደእነ ቢኒ ዞር ስል ደብሯቸዋል ወደ ክላስም ስንሄድ ዘግተውኛል ሊዱ ብቻ ነበር ስታወራኝ የነበረው በሁኔታቸውም ተገርሜ አንተ ቢኒ አልኩት እሱም ወደ እኔ ዞር አለና "አቤት" አለኝ ኮስተር ብሎ (እረ ሩጡ እንጂ!!) የትምህርት ቤታችን ዳይሬክተር ነበር ሁላችንም እየሮጥን ክላስ ገባን ከእኛ እኩል መምህሩም ገባ ደብተር እያወጣጣን ለምን ይሆን የዘጉኝ?? ሊያን ሰላም ማለቴ ይሆን ያናደዳቸው?? እ ወይስ ዮናስን? የሚል ጥያቄ ወደ አዕምሮዬ ይመላለስ ጀመር ወደ ሊዱ ዞር አልኩና "ሊዱዬ ቆይ የሚያናድድ ነገር አደረኩ እንዴ??" አልኳትኝ በሚያሳዝን አይን እያየኋት "እረ እንጃ ሜሪ እኔ ምንም አልታየኝም ግን ምን ሊደብራቸው ይችላል ብላ ጥያቄዬን በጥያቄ መለሰችልኝ ወዲያውም "ሜሪ ደብተርሽን ስጪኝ እስቲ note ወደ ኋላ ነኝ" አለኝ ናሆሜ ነበር ሰጠሁትና "ኡፍፍፍ ቢያንስ እሱን አላስደበርኩትም"" አልኳት ቀስ ብዬ ሰረቅ እያደረኩ ቢኒን እያየሁት ወይኔ ምን ሆኖ ይሆን?? ብዬ ለብቻዬ ማሰብ ጀመርኩ። ደብተሬን ከናሆሜ ተቀበልኩና Note መፃፍ ጀመርኩ እየፃፍኩኝ ድንገት ዞር ብዬ ቢኒን ሳየው ምላሱን እያወጣብኝ ድምፅ በማያሰማ መልኩ "ሰራሁልሽ" አለኝ በጣም ደስ አለኝ መሳቅ ጀመርኩ ሊዱና ናሆሜ እያዩኝ "በሉ አስፈጁና" እያሉ መገረም ጀመሩ እኔና ቢኒ መሳቃችንን አላቆምንም መምህሩ ወደኛ ዞር ሲል ከኛ ውጪ ኮስታራ የለም ሲያየን ኩስትር ብለናል ልክ እሱ መፃፍ ሲጀምር እነ ሊዱም በተራቸው ሁኔታው አስቋቸው ከእኛ በባሰ ሁኔታ ሲስቁ ተማሪዎቹ እየተዟዟሩ እያዩን ግማሹ "ውይይይ ደስ ሲሉ እኮ!" ይላሉ በጣም የሚግባቡን ደግሞ በሹክሹክታ "በቃ አበዳችሁ? ምን ይባላል አንድዬ ይከተላችሁ" ይሉናል በእነሱ አኳኋን በመምህሩ ሁኔታ በእኛ መሳቅ ማቆም አለመቻል ተገርሜ  "እውነትም እብዶች" አልኩኝ ወደ ናሆሜ ዞር ብዬ እያየሁት እሱም "ይቺ ነገር ቅኔ ነች?!! ከእኔ ካንቺ ማነው እብድ? ሆ" አለኝ እስኪብርቶውን ዴስክ ላይ ቁጭ እያደረገ "እንዴ አትሳሳት እሷ እብደቷን Master አድርጋለች Master የሚለው ማዕረግ ይቀርሀል" እያለ የባሰ ቢኒ አጋጋለ መምህሩ ኖቱን ጨርሶ ቁጭ አለ እኛ ገና ስንጀምር ሰዉ ጨርሷል መምህራችንም በደንብ አስረድቶን እኛም በአንድ ልብ ተረድተነው ወጣ ትምህርቱ እንዲህ እንዲህ እያለ በጣም ደስ በሚል ሁኔታ አለቀ እኛም እየተቻኮልን ስንወጣ "እረ ጠብቁኝ" አለ ናሆሜ ነበር "እየሄድን እንጠብቅሀለን" ብዬው ልሄድ ስል ቢኒ ቦርሳዬን ጎተት አድርጎ "ነይይይ ምን አሮጠሽ" አለኝ "ሀይሌን አግኝቼው ሚስጥር ነግሮኝ" ብዬ ዝገትን በዝገት መለስኩለትና ቀስ እያልን መራመድ ጀመርን ናሆሜና ሊዱ ገና ከክፍል እየወጡ ነበር "ግን ቅድ
47 ·
የ
የነቃ ትውልድ Tube
Photo
click to show
. ክርስቲያናዊ ጋብቻ ➡️ለወጣቶች፦ የወደፊት ትዳራቸውን በክርስቲያናዊ ምሳሌነትና በጌታ ፈቃድ ለመመስረት ለሚዘጋጁ ➡️ለእጮኛሞች፦ በፍቅርና በቅድስና ላይ የተመሠረተ ክርስቲያናዊ እጮኝነትን ለመምራት ለሚፈልጉ ➡️ለባለትዳሮች፦ የጋብቻ ህይወታቸውን በክርስቶስ ፍቅርና በመጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ማደስ ለሚፈልጉ ባለትዳሮች ​እና ወጣቶች የተዘጋጀ መፅሐፍ ነው ከታች የሚገኘውን ሊንክ በመንካት በ250 ብር ብቻ መግዛት ይችላሉ። ከስር ያለውን ሊንክ በመጫን በቀላሉ መጽሐፉን ያውርዱ👇👇👇👇 https://ye-buna.com/samiyy?ref=product_detail&product=6abca0f06ad01_samiyy መጽሐፉን ከከፈሉ በኋላ "showlife" በሚል Sms text ይደርስዎታል እዚያ ላይ የመጽሐፉ የ pdf ሊንክ አለ
39 ·
G
Photo
click to show
ክርስቲያን የሆነ ሁሉ መቀላቀል ያለበት  ተወዳጅ መንፈሳዊ ቻነል 👇👇👇👇👇 🈴JOIN🈴 ያድርጉ Wave @seer_lewi
79 ·
F
📛 በወሲባዊ ሀጢያት ልምምድ ውስጥ ያለ ማንኛውም ሰው እነዚህ አራት ወሳኝ ነገሮች ያጣል ፡፡ 1 ) ራዕይን ማጣት የጊዜ ጉዳይ እንጂ በወሲባዊ ሃጢያት የፀና ሰው ራዕዩን ማጣቱ አይቀሬ ነው ፡፡ ያለ ምንም ዓላማ በጭፍን የመረረ ህይወት መኖር ይጀምራል 2) ተፈጥሮአዊ እውቀትን ማጣት ማንም ሰው ሊረዳው የሚችለውን ቀላል ነገር እንኳን እንዳይረዳ ያደርገዋል ፡፡ በመፅሐፍ ቅዱስ የሶምሶንን ታሪክ ስናነብ አራት ጊዜ የሃይልህን ምንጭ ተናገር ብላው በፍልስጤማውያን ልታስይዘው ሞክራ ትክክለኛውን የሃይሉን ምንጭ ስላልነገራት አራቱንም ጊዜ ከእጃቸው አምልጦ እንኳን ደሊላ ለምን እነደቀረበችው አልገባውም ነበር ፡፡ ምክንያቱም ተፈጥሮአዊ እውቀቱ ( common sense ) ተወስዶበታል ፡፡ 3) ፍርሃትን ማጣት እየሄደበት ያለው ጎዳና     👉 ከእግዚአብሔር እንደሚለየው     👉 መጨረሻው ሞት እንደሆነ     👉 አካላዊ ጉዳት እንደሚያደርስበት #እያወቀ ፍሬኑን ከመርገጥ ይልቅ ነዳጅ መስጫውን እንዲረግጥ ወደ ሞት እንዲፈጥን ያደርገዋል ፡፡ ፍርሃቱን ይቀማዋል ! 4) የእግዚአብሔርን ውለታ ያጣል በህይወታችን ያለ ስኬትና ክንውን የእግዚአብሔር ውለታ እንጂ የእኛ የስራ ውጤት ብቻ አይደለም ፡፡ ወሲባዊ ሃጢያት የእግዚአብሔርን ውለታ ፣ ፀጋና ሞገስ ከሰው ያርቀዋል ፡፡ ሶምሶን  ከደሊላ ጋር በመተኛቱ የእግዚአብሔር ክብር ያለበትን ፀጉሩን ሲያጣ እናያለን ፡፡    .          #እወዳችኋለሁ❤ 👉 @abit9 🔹🔸🔹Join Us🔹🔸🔹 @ReformationNeeded @ReformationNeeded @ReformationNeeded     ሼር በማድረግ ለወዳጆ ያካፍሉ   sʜᴀʀᴇ💯 sʜᴀʀᴇ 💯 sʜᴀʀᴇ💯   
❤4🥰2
1 · 107 ·
G
🤩ምን አይነት ትምህርት ይፈልጋሉ አሁን በዳምጣው የምትሉትን መርጣው "Join" ያድርጉ 🙏🙏
8 ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog · Search · How we count