አ
267 018subscribers
1 556average post reach
0.6%ER — reach to subscribers
44posts in 30 days
አትሮኖስ
#ተማሪዋ!
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አራት
፡
፡
#ድርሰት_በጥላሁን
፡
፡
"ሄሎ ኤፍዬ ደናነህ? ለቀቀህ?"
"ምኑ ቃልዬ?
" ትራፊኩ ካካካ ፣ ድብርቱ ነዋ"
"ምነው በዚህ ሰአት በሰላም ነው ምን ሆነች ብዬ ደነገጥኩ"
"ሰላም ነኝ ኤፍዬ ምን ሆናለሁ ብለህ ነው፣ ገባህ እንዴ ወደቤት?"
"አዋ እቤት ነኝ ቃልዬ"
"ድብርቱ አለቀቀህም ማለት ነው?"
"ሌላ ግዜ በዚህ ሰአት ስራ ላይ ነህ ብዬ ነዋ"
"አንቺስ እስካሁን እንዴት አልተኛሽም ቃልዬ?"
"እያሰብኩ"
"ስለምንድን ነው የምታስቢው "
"ስላንተ እና ስለኔ"
"ስለኔና ስላንቺ ምን?"
"እስቲ በዛሬዋ ቀን ምን ታስታውሳለህ?"
"በዛሬዋ ቀን ማለት ዛሬ?"
"አይ የዛሬ ስድስት ወር ልክ በዛሬዋ ቀን በሀያ ሰባት"
"ምን ላስታውስ ? ያንቺ ፍቅር ስሜንስ ሳያስረሳኝ ይቃራል ቃልዬ እስቲ አንቺ አስታውሽኝ"
"ልክ የዛሬ ስድስት ወር በዚች ቀን በዚች ሰአት ምሽት ላይ ነበርኮ እዛ ሆቴል በር ላይ የተገናኘነው"
ስትለኝ ልቤ ተረጋጋ።
ስድስት ወር እንደሞላን በደፈናው ባውቅም ቀኗን ለይቼ አላሰብኳትም ነበር። ትኩስ ትንፋሽ በረጁሙ አስወጣሁና።
"ቅድም አብረን እያለን ለምን አልነገርሽኝም ቃልዬ ነው አንቺም ትዝ ያለሽ አሁን ነው?"
"እኔ ነገ ነው የምንገናኘው ስልህ ዛሬ ካልተገናኘን ሞቼ እገኛለሁ ብለህ ስትለኝ ቀኑን አስበህ ነው ብዬ አንተ እንድትነግረኝ ስጠብቅ ነበር አንተ ግን ሌላ አለም ውስጥ ነበርክ ኤፍዬ ምን ብዬ ልንገርህ"
"ይቅርታ ቃልዬ ረበሽኩሽ አይደል?"
"አንተ መረበሽህ ነው የደበረኝ ለማንኛውም ይህን ላስታውስህ ብዬ ነው በቃ ተኛ ኤፍዬ እንደማፈቅርህ እንዳትረሳ እሺ" ቃላቶቿን በጆሮዬ የሰማኋቸው ሳይሆን በደምስሬ በስሪንጅ የወሰድኩ እስኪመስለኝ ድረስ በሁለመናዩ ሲሰራጩ ተሰማኝ።
" እንዳትረሳ ማለት ምን ማለት ነው ቃልዬ?"
"ሆሆሆ ኪኪኪ ይሄ ደሞ ሌላ ምን ማለት ይሆናል ? በቃ እሺ አፈቅርሀለሁ "
አለች። አዎ እንደዛ ነው የሚባለው እንዳትረሳ ስትይ የመጨረሻ የ መለያያ ንግግር አስመሰልሽዋ ታድያ ምን ላድርግ ቃልዬ ልላት አልኩና ካፌ መለስኩት።
"እኔም አፈቅርሻለሁ የኔ ማር"
"ቻው"
"ቻው ደና እደሪልኝ"
ኡፍፍፍፍፍ አልኩና ስልኩን ትራሴ ስር ወትፌ በጀርባዬ ስንጋለል።
አውርተን እስክንጨርስ አንዴ ፈገግ አንዴ ጭፍግግ እያለ ሲሰማን የነበረው ኪያ እኔን ተከትሎ በረጅሙ ተነፈሰና።
"ቆይ ለምንድን ነው ስልኩን ማንሳት የፈራኸው ኤፊ?"
"እኔ እንጃ!"
"አቦ ተወና ኤፊ ደሞ ሀይ በቃ እሺ ስሜትህን ሳልረዳ የማይሆን ነገር ተናግሬ ከሆነ ይቅርታ"
"ተጨማሪ ወሬ ለመስማት ብሎ ይቅርታ የሚጠይቅ ሰው አንተን አየሁ"
"አቦ እኔ ለወሬው ብዬ ነው እንዴ? ወንድሜ አደለህ እንዴ ያንተ ጉዳይ አያስጨንቀኝም ኤፊ"
"ባክህ አንተ ከራስህ ዉጪ ለማንም ተጨንቀህ አታውቅም"
"እሺ ስልኩን ለማንሳት የሸከከህ ለምን እንደሆነ ብቻ ንገረኝ"
"ኧረ ኪያ ልተኛበት ተወኝ ••• በቃ አንደኛ ቃልዬ ሰላም ያልሆነች መሰለኝ ሁለተኛ ቅድም ምን አውርተን ተጦላልበን እንደተለያየን ነግሬህ የለ ስለዛኪ ሌላ ወሬ ሌላ እውነት የምትነግረኝ መስሎኝ ነበር የፈራሁት እኔ ሌላ እሷ ሌላ አለም ውስጥ እንደነበርን ያውቅኩት ግን የደወለችው ልክ የዛሬ ስድስት ወር በዚህ ቀን መገናኘታችንን ልትነግረኝ መሆኑን ስትነግረኝ ነው" አበቃ ይሄው ነው ብዬው ተጠቅልዬ ተኛሁ።
እንቅልፍ አልወስድ ብሎኝ ከአንድ ሰአት በላይ ስገላበጥ ቆየሁ፣ ኪያ እንቅልፍ የወሰደው መስሎኝ ስለነበር ድንገት
" ኤፊ !" በማለት ሲጣራ እየቃዠ መስሎኝ ዝም አልኩት።
" አንተ ኤፍሬም!" በማለት በድጋሚ ተጣራ ።
"አቤት ኪያ ምንድን ነው አል…
Read in full →❤16👍2
2 · 1.2K · "ተወው ስለ ጢባሩ ምናገባን ፣ ጢባሩ ምናምን ትላለህ እንዴ ሲጀመር እኔ ስላንተ ምንም አልነግረውም ዝም ብዬ ቃልኪዳን እና ያ ዛኪ ያልከው ልጅ የእውነት ዘመዳሞች መሆን አለመሆናቸውን ብቻ እንዲያጣራኝ ነው የምነግረው ልጁ ደሞ ፈጣን ነው በርግጠኝነት በዚህም በዛም ብሎ አጣርቶ ይነግረኛል ። ቃል ኪዳን በዚህ አመት መጨረሻ ትመረቃለች አደል?"
"አዎን "
" ምን ዲፖርትመት ነበር የምትማረው?" አለኝ። ነገርኩት።
"ካንተ ጋር ፌስ ቡክ ላይ ፍሬንድ ናችሁ!"
"አዎ ምነው?"
"ፎቶዋን ከዛ ላይ በቀላሉ ማግኘት ይቻላል። በቃ ይሄን ጉዳይ በኔ ጣለው ሳምንት አይፈጅብኝም " አለኝ። በዚህ ተስማምተን ተኛን ። ኪያ በቶማስ በኩል ለማጣራት ያሰበውን ሀሳብ ማታ ተስማምቼ ባድርም ጥዋት ላይ ግን ቀፈፈኝ በቃ በቶማስ በኩል ቃልዬን መከታተል ቀፈፈኝ።
አብረን ኪኪያ ጋር ቁርስ እየበላን ነው።
"ኪያ የማታውን ሀሳብ ትቸዋለሁ አንተም ተወው በቃ ይቅር ባክህ "
"ምኑን?"
"በቶማስ በኩል ያልከውን ለምን እንደሆነ አላውቅም በቃ ደበረኝ ይቅር ተወው በራሴ መንገድ እውነቱን እስካውቅ ድረስ ቃልዬ ያለችኝን ነገር ማመን ነው እምፈልገው እሷን ከጀርባ መከታተሉ ቀፎኛል ይቅር ኪያ ተወው ለሱም ምንም አትበለው
እሺ ኪያ?"
"እሺ ኤፍዬ ከደበረህ ይቀራላ ምን ችግር አለው"
"አዎ ይቅር በቃ አደራ ምንም አትንገረው ለሱም "
"ጣጣ የለውም ኤፊ ቅድም ወደዚህ ለቁርስ እየመጣን ዛሬ እፈልግሀለሁ ሲመችህ ደውልልኝ ብዬ መልክት ልኬለታለሁ ከደወለም የሆነ ነገር ልጠይቅህ ነበር በቃ ሌላ ሰው ነገረኝ ምናምን ብዬ አስቀይሰዋለሁ
"በቃ አዎ እንደዛ በለው " አልኩት ድሮ ለቶማስ እንደዛ ብሎ መልክት መላኩ እየገረመኝ።
ኪኪያ ጋር ተለያይተን ስራ ጀምሬ ትንሽ እንደቆየሁ ከረፋዱ አራት ሰአት አከባቢ ቃልዬ ደወለች።
እንዲሁ ሰላም ልበልህ ብዬ ነው ብላ ትንሽ አወራን። ለስራ ሳይሆን ለቁርስ የወጣሁ እንደመሰላት ባውቅም ምንም አላልኳትም።
ቀን ዘጠኝ ሰአት አከባቢ ደግማ ደወለች። እህቴ ጋር ምሳ በልቼ ለሊቱን ደህና እንቅልፍ ስላልተኛሁ ትንሽ አረፍ ለበል ብዬ ጋደም ብያለሁ።
"አንተ እንቅልፋም እስካሁን ተኝተኻል?" ብላ በመጀመር አሁንም እንዲሁ ልታወራኝ ፈልጋ እንደሆነ ነግራኝ አምስት ደቂቃ ያህል የባጥ የቆጡን ስናወራ ቆየንና ከመሰነባበታችን በፊት•••
"ኤፍሬሜ"
"ወዬ ቃል"
"አፈቅርሀለሁ እሺ "
"እኔም ከምታስቢው በላይ አፈቅርሻለሁ ቃልዬ"
ተባብለን ነበር ስልኩ የተዘጋው።
ቃልዬ እንዲህ ለመሆን ለምን ስድስት ወር እንደፈጀባት ግራ ገባኝ። ስድስቱንም ወር እኔን ፍቅር ከግራ ወደ ቀኝ ከቀኝ ወደ ግራ እያላጋ ሲጫወትብኝ እሷ ግን በመሳቅ ነበር ያሳለፈችው።
ውስጧን ማየት ስሜቷን ማወቅ እስክቸገር ብዙ የማትናገር ፣ እንድታወራ ስወተውታት ፣ ጭቅጭቅ የሚመስላይ ፣ ጨቀጨከኝ ላለመባል መደወል እየፈለኩ ያልደወልኩባቸው ማውራት እየፈለኩ ዝም ያልኩባቸው ቀናቶች ብዙ ናቸው።
እኔ በማውቀው መንግስትም ሆን የግል ድርጅት አንድን ሰራተኛ በቋሚነት ለመቅጠር የሙከራ ግዜ የሚባለው የስራ ቆይታ አርባ
አምስት ቀን ነው።
ቃልዬ ስድስት ወር በሞላን ማግስት ያልተመደ ለውጥ ያሳየችኝ እኔን በቋሚነት ለመቀበል እና አሁን እንደምትደውለው ቶሎ ቶሎ ለመደወና ፍቅሯን በግልፅ ለመናገር ስድስት ወር ሙሉ የቆየችው ስድስት ወሩ የሙከራ ግዜ ነበር ማለት ነው?
በቃ ይህ የቃልዬ ሁኔታ ለኔ አዲስ ነው ፣ ቃልዬ እና እኔ የምንገናኝበትን ቦታ ለመቀጣጠር የት ደረሽ የት ደረስክ ለመባባል ካልሆነ በስተቀር በስልክ ብዙ አናወራም ብናወራም እኔ በቃ ናፈቅሽኝ ድም…
Read in full →❤14👍3
1.1K · አ
"እሺ ኤፍዬ ካልተመቸህ ችግር የለውም" አለችኝ። ይህን ሶስት ቀን ቃልዬ ላይ የነፈሰው የተባረከ ንፋስ ከየት በኩል ነው የመጣው በፈጣሪ ፣ አቦ ቃልዬ ሁሌም እንዲህ በሆነች ብዬ ከልቤ እየተመኘሁ ዘመቻዬን ቀጠልኩ።
ስጦዝ ውዬ ቀን ዘጠኝ ሰአት የኮንትራት ደንበኛዬ የሆነው ሱማሌው አብዱራህማን ሲደውል•••
"ዋውው አቦ ይመችህ በቃ የቃልዩ ቀሚስ ተገዛ እያልኩ ስልኩን አነሳሁ"
"ወርያ የት ነው ያለው እኔ አንተን ጫት ተራ መላክ ይፈልጋል" አለኝ።
"መጣሁ መጣሁ አብዱዬ ቅርብ ነኝ" አልኩትና በረርኩ ወደሱ።
ምርጥ ከፋዬች ከሚባሉት ደንበኞቼ ተርታ የሚመደብ ነው።
እንደጠበኩት የቀሚሷን ዋጋ ለመሙላት የሱ መልክት ብቻ በቂ ሆነ። ተጨማሪ ትንሽ ሰራሁና ወደ ፑቲኳ በረርኩ።
እንደደረስኩ ባጃጄን ጥግ አስይዤ እያቆምኩ ኬት ተክለፍልፎ እንደመጣ እንጃ •••"ቀሚሷ ተሽጣ ቢሆንስ?" የሚል ጥያቄ ሹክ ሲለኝ። ኧረ አይሸጥም በዛ ዋግ ማን ይገዛል ? ቢሸጥስ አንድ ብቻ ነው እንዴ የለው ከለለም የገባበት ገብቶ ያመጣል እንጂ ሌላ ቀሚስ አልገዛ " እያልኩ ዘው ብዬ ስገባ እዛው ቦታዋ ላይ ተሰቅላለች። ቃልዬ ቀሚሷ ውስጥ ሆና ፈገግ ስትል ታየችኝ።
ቀንስልኝ እንኳን እንዳላልኩት ትዝ ያለኝ ብሩን ከፍዬ በስጦታ መጠቅለያ አስጠቅልዬ ወደነ ቃልዬ ግቢ መብረር ከጀመርኩ በኋላ ነበር።
ምን ሆኜ ነው ግን ትናንት በጠራበት ዋጋ ከፍዬው የወጣሀት? አይ መጣደፍ እያልኩ ባጃጇን ከአቅሟ በላይ እያጣደፍኩ ግቢ አከባቢ እንደደረስኩ ቆምኩ።
ስልኬን ከኪሴ አውጥቼ ለቃልዬ ከመደወሌ በፉት ድንገት ቀና ብዬ ፉት ለፉት ወዳሉ ተማሪዎች አየት ሳሳደርግ
ከግቢ ወደከተማ የሚወጡ፣ ከከተማ ወደግቢ የሚገቡ እንዲሁም እዛው በሩ አከባቢ ለወሬ አልያም ታክሲ ጥበቃ ከቆሙ የተማሪዎች ግርግር መሀል ቆሞ እኔ ባጃጅ ላይ እንዳፈጠጠ አየሁት ። አጠገቡ ያለችው
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose❤17👍2
1 · 1.3K · አትሮኖስ
#ተማሪዋ!
፡
፡
#ክፍል_አስራ_አምስት
፡
፡
#ድርሰት_በጥላሁን
፡
፡
ስልኬን ከኪሴ አውጥቼ ለቃልዬ ከመደወሌ በፉት ድንገት ቀና ብዬ ፊት ለፊት ወዳሉ ተማሪዎች አየት ሳሳደርግ
ከግቢ ወደከተማ የሚወጡ፣ ከከተማ ወደግቢ የሚገቡ እንዲሁም እዛው በሩ አከባቢ ለወሬ አልያም ታክሲ ጥበቃ ከቆሙ የተማሪዎች ግርግር መሀል ቆሞ እኔ ባጃጅ ላይ እንዳፈጠጠ አየሁት ። አጠገቡ ያለችው ሴት በከፊል ጀርባዋ ነው የሚታየኝ።
ሲያፈጥብኝ ኪያ የቃልኪዳንን እና የዛኪን ግኑኝነት እንዲያጣራ ልላከው ሲለኝ ይቅር ያልኩትን ልጅ ቶማስ መሆኑን ለመለየት አድጎ በተንጨፈረረው ፀጉሩ ምክንያት ተቸግሬ ነበር።
ቶማስ መሆኑን እንዳወቅኩኝ ፀጉሩን እየነካካ ትክ ብሎ ወደኔ ባጃጅ ሲመለከት የፀሀይ መከላከያውን አውርጄ ወደተቃራኒ አቅጣጫ ፊቴን በማዞር ማዶ ማዶውን ማየት ጀመርኩ።
ከሰከንዶች ቆይታ በኃላ አየት ሳደርገው አሁንም አይኑ ወደኔ አቅጣጫ ነው ።
ካጠገቡ አንዲት ቀጭን ሴት ፊቷን ከሱ ጀርባ ወዳለች ሌላ ሴት አዙራ እያወራች ቆየችና ልጅቷ እንደሄደች ከቶማስ ጋር ማውራት ጀመሩ።
ይለየኝ አይለየኝ ባላውቅም አጠገቡ ካለችው ልጅ ጋርም እያወራ አይኑ ግን እኔ ባጃጅ ላይ ነው።
ምናልባት ወደከተማ መሄድ ፈልገው ወደጊቢ ሰው ይዞ በሚመጣ ባጃጅ ለመሄድ እየጠበቁ ሳይሆን አይቀርም።
ቶማስ እነቃልዬ ግቢ ቢማርም እስከዛሬ ድረስ ለብዙ ግዜ ወደዚህ ግቢ ስመላለስ አንድም ግዜ አይቼው አላውቅም።
ከኪያ ጋር ስለሱ ካወራን ሳምንት እንኳን ሳይሞላ ሳየው ገረመኝ።
አንዲት ደብተር ጠቅልሎ እንደያዘ የጎፈረ ፀጉሩን እየጠቀለልና ከልጅቷ ጋር እያወራ ካሁን ካሁን ተጠጋ አልተጠጋ ብሎ እየጠበቀኝ ነው መሰል ወደኔ ባጃጅ አማትሮ ማየቱን ቀጥሏል።
ከሱ ጋር ሰላም መባባልም መተያየትም ስላልፈለኩ ባጃጄን አስነስቼ ከነሱ በተቃራኒው ሽቅብ ትንሽ ጠጋ አልኩና በኔና በነሱ መካከል ያለውን ርቀት አስፍቼ በማለፍ ጠጋ ብዬ ቆምኩ።
በጎን መስታወት አየት ሳደርግ ጭራሽ ልጅቷም ተጨምራ ሁለቱም አይናቸው እኔ ባጃጅ ላይ ነው። እሱ ያወራል ልጅቷ ወደኔ እያየች ትስቃለች ።
" ምን እያወራላት ነው የምትስቀው? ኪያ ችክ ካለ አይመለስ አትንገረው ይቅር እያልኩት ስለኔና ስለቃልዬ ነግሮት ይሆን እንዴ ? ኪያ አያደርገውም አይባልም ፣ ድሮም ተው ሲሉት ይብስበታል ።
ብቻ ነግሮት ይሁንና እኔና ኪያ ተጋደልን" እያልኩ እነሱ እስኪሄዱ ቃልዬ ጋር ሳልደውል ቆየሁ።
ፎርስ በመባል የሚታወቀው ከፍ ያለ ባጃጅ መጥቶ ቶማስን እና ልጅቷን ጨምሮ አጠገባቸው የቆሙትን ጠራርጎ እንደወሰደልኝ ቃልዬ ጋር ደውዬ በር ላይ መሆኔን ነገርኳት።
ከመምጣቷ በፊት የገዛሁላትን ስጦታ ብር በማስቀምጥበት የባጃጇ ዳሽቦርድ ውስጥ አስገብቼ ቆለፍኩበት።
ቃልዬ ከግቢ እየወጣች ከሩቅ እንዳየኋት ልቤ መዝለል ጀመረች።
የናፈቀችው እናቱ ከገበያ ስትመጣ አሻግሮ እንዳያት ህፃን ልጅ ሮጠህ ተጠምጠምባት ተጠምጠምባት የሚለኝ ነገር መቼ እንደሚቆም እያሰብኩ ፈገግ አልኩ።
በቃልዬ ምርጫ ከድሬ ሆቴሎች ወደ አንዱ አመራን።
ሆቴሉ በር ላይ እንደደረስን
" ቃልዬ ሂጂ ግቢ መጣሁ በዛ በኩል ላቁማት እዚህ ጋር መንገድ ዘጋለሁ " ስላት።
"እንብየው ብቻዩን አልገባም እዚሁ ጋር ልጠብቅህ ሂድ አቁማትና ና " አለችኝ።
ጠጋ ብዬ አቆምኩና ስጦታዋን ከጀርባዬ ደብቄ ተያይዘን ገባን።
እሷ ቁጭ ስትል እኔ ዝም ብዬ ከፊት ለፉቷ በመቆም ስመለከታት ቀና ብላ እያየችኝ•••
"እህህህ ምን ሆነህ ነው እንደዚህ የምታየኝ ኤፊዬ ቁጭ አትልም እንዴ ?" አለችኝ።
ስጦታውን ከጀርባዬ አውጥቼ ሰጠሁዋት ።
"ምንድን ነው ኤፊዬ?"
"ከፍ…
Read in full →❤13👍2
1 · 1K · "አዎ አውርተን አናውቅም ግን የሆነ ቀን እንደምንሄድ እያሰብኩ ልብሱን ገዝተህ ስጦታ ሰጠኸኝ ከዛ ። በቃ ያኔውኑ ከኤፍዬ ጋር ሀረር ስንሄድ ነው የምለብሳት ብዬ ነው ያስቀመጥኳት ?" ስትለኝ ሀረር የመሄዳችን ጉዳይ እውን ሊሆን መሆኑ ታወቀኝና የደስታ ስካር አዝሮ ሊደፋኝ ደረሰ።
መልሳ ደሞ "አሁን ግን ሀሳቤን ቀየርኩ" ስትለኝ
"ሀሳቤን ቀየርኩ ማለት?" አልኳት የመሄድ ሀሳቧን የቀየረች ስለመሰለኝ በጋለው የደስታ ስሜቴ ላይ ቀዝቃዛ ውሃ የደፉበት ያህል ቅዝቅዝ ብዬ።
"፣በቃ ሀሳቤን ቀየርኳ ይቺን ነው ለብሼ መሄድ የምፈልገው፣ መች እንሂድ ኤፍዬ በዚህ ሳምንት ቅዳሜ ወይ እሁድ ብንሄድስ ይመችሀል?" ስትለኝ ውስጤ በደስታ ጎርፍ ተጥለቀለቀ።
ግማሽ ፊቷን የሸፈነውን ፀጉሯን ወደ ጀርቧዋ ብትን አድርጌ ግንባሯን ሳም አደኳትና " እንኳን ቀጣይ ቅዳሜ አሁን በዚህ ምሽት እንሂድ ብትይኝ ትራንስፖርት ብናጣ እንኳን ተሸክሜሽ እሄዳለሁ እንጂ አይ በቃ መሽቷል ትራንፖርትም የለም የምልሽ ይመስልሻል ቃልዬ?" ስላት ረጅም ሳቅ ሳቀች።
"በቃ ቅዳሜ እንሄዳለን ሃሳብሽን አትቀይሪም አደል ቃል?"
"ኤፍዬ ሙት እንሄዳለን ምነው ድንገት አሁን የወሰንኩ መሰለህ እንዴ ? ሳስብበት ነበርኮ" ስትለኝ የተሰማኝ የደስታ ስሜት ቃልዬን ካገኘኃትም፣ ከዛ በፉትም፣ በቃ ከተወለድኩ ጀምሮ ተስምቶኝ የማያውቅ ልዩ ስሜት ነበረው።
በቃልዬ ትንሽ ስከፋ በዚህ ምድር ላይ አንድ የከፋው ሰው ቢፈልግ እኔ ብቻ የምገኝ የሚመስለኝን ያህል በቃልዬ ደስ ሲለኝም እንዲሁ በአለም ላይ የኔን ያህል ደስተኛ የሆነ ያለም አይመስለኝ።
ደስ የሚል ምሽት አሳለፍን። ሸኝቻት ስመለስ ቀን ቆጠራ ጀመርኩ። እስከቅዳሜ ድረስ ስንት ቀን ነው ያለው? ዛሬ ማክሰኞ ፣ እእ ማክሰኞ እማ አይቆጠርም በቃ ነጋኮ እሮብ ሀሙስ አርብ ሶስት ቀን አለ ገና ብዙ ነው ። ሶስት ቀኑ የሶስት ወር ያህል ረዝሞ ታየኝ። ሀረር ከሄድን በትንሹ አንድ ቀን ሳንድር እንደማንመለስ እርግጠኛ ነበርኩ።
አብረን ካደርን ደግሞ ••••አልኩኖ ሳልጨርሰው ኪያ ትዝ አለኝ። እሱን ብሎ አማካሪ ፣ አቦ ካሁን በሁዋላ ስለቃዬ ከኪያ ጋር በጭራሽ ማውራትም የለብኝም ። ጭራሽ ትንፍሽ አልልለትም። እዛው ገራጅ የተበላሸ መኪኖ እያስጎተቱ ከሚመጡ ሹፌሮች ጋር ይመካከር። ድሮስ እሱ ስለመኪና እንጂ ስለፍቅር የት ያውቃል። ቢያቅም የሚያውቀው በፍቅረኛሞች ፀብ ማሀል ገብቶ የራሱን ማብሰል እንጂ ሌላ ምን ያውቃል ? ምንም አያውቅም እያልኩ ጓደኛዬን ብቻዬን እያማሁት ሰፈር ደረስኩ።
ገብቼ ከሰላምታ ዉጪ ከኪያ ጋር ምንም ሳላወራ ተጠቅልዬ ለሽ አልኩ ።
አይደርስ ነገር የለ ቅርፍፍ እያሉ እልሔን ያስጨረሱኝ ሶስት ቀኖች አልቀው ቅዳሜ ደረሰ። ትናንት ማለትም አርብ ማታ ከቃልዬ ጋር ተደዋውለን ከአራት ተኩል እስከ አምስት ሰአት ባለው ግዜ ውስጥ ተገናኝተን ለመሄድ ቀጠሮ አስረናል። ፀጉሬን መስተካከል ብቻ ነው በኔ በኩል የቀረኝ ስራ ። ማታ ዘወትር የሚቆርጠኝ ልጅጋ ፀጉሬን ልስተካከል ብሄድም ወረፋ ስለነበር ጥዋት ሁለት ሰአት ቀጠሮኛል።
ከእንቅልፌ የነቃሁት አስራሁት ሰአት ላይ ቢሆንም እዛው እየተገላበጥኩ እንደምንም አንድ ሰአት ተኩል ሆነ።
ተነሳሁ።ለወትሮው ከአንድ ሰአት በፉት ስራ የሚሄደው ኪያ ተጋድሟል።
ከላይ የለበሰውን ጎተት ሳደርገው ተገላብጦ መልሶ ተኛ። ወዝወዝ አደረኩት።
"እ ምንድን ነው?" አለኝ እጅና እግሩን ወደላይ እና ወደታች እየወጣጠረ ።
"ስራ አትሄድም እንዴ ረፍዷል እኮ ?"
"ደና አደርክ ኤፊ ስራ ገባለሁ ግን ትንሽ አርፍጄ ነው የምገባው ብዬ ነው የተኛሁት እራሴን አሞኛል ባክህ አንተ ልትሄ…
Read in full →❤10👍2
957 · አ
"አይ አትሂድ ይቅርብህ ኤፊ ብትደውልም አያነሳም ብታንኳኳም አይከፍትልህም ልብስ ለመቀየር ከሆነ የምትገባው ይቅርብህ ፣ ትርፉ መቃቃር ነው" እያለ እንዳልገባ ሲሞግተኝ ጤነኛ መስሎ አልታይህ አለኝ።
"ማነው ውስጥ ያለው ኪያ አይደል እንዴ? ማለቴ ከማንም ጋር ይሁን ግን ኪያ ነው ውስጥ ያለው አይደል?"
"አዎ እሱማ ኪያ ነው ሌላ ማን ይሆናል"
"እና ታድያ ምን እያልከኝ ነው ለምንድን ነው የማይከፍትልኝ ልብስና ጫማዬን በር ላይ ሆኜ እንዲያቀብለኝ መንገር እንጂ መግባት አልፈልግ"
" በሩን ከፍቶ እንደማያቀብልህ እርግጠኛ ስለሆንኩ ነው" ብሎኝ እርፍ ። ብልጭ አለብኝ።
"ቆይ ውስጥ ከማን ጋር ነው ያለው?"
"ከሴት ጋር"
"እና ከሴት ጋር ቢሆንስ ታድያ ቆይ ማነች ሴቷ እኔ አውቃታለሁ?" ስለው ለኔ መልስ ሳይሰጠኝ ልንገረው አልንገረው በሚል ዳይለማ ውስጥ በገባ ስሜት እንዴ እኔን አንዴ ከሳቋ ጋር የምትታገለውን ገነትን ሲመለከት ኪያ ከማን ጋር እንደሆነ ገባኝ።
"ተወው አትንገረኝ ከማን ጋር እንዳለ ገብቶኛል ፣ ከመክሊት ጋር ነው አይደል?"
"አዎ ኤፊ " አለኝ ፈራ ተባ እያለ።
"እንኳን መክሊትን ዘር ማንዘሮቿን ይዞ ቢጋደም ለደንታው ነው እኔ ገብቼ ልብሴን ወስዳለሁ ሳንኳኳ አይክፈትና እንትያያለን እንግዲህ!" ብዬ ልሄድ ስት ክንዴን ያዝ አድርጎ
"ኤፍሬምና ኪያ በሴት ተጣሉ ሲባል አይደብርም ኤፊ ፣ ልብስ መቀየሩ ይቅርብህ አትግባ"
" ሀ••••ይ አቦ ልቀቀኛ እንግዲህ አታበሳጨኝ ከመክሊት ጋር ስለሆነ ነው ከሱ ጋር የምጣላው ዝም ብለህ በማታውቀው ነገር ውስጥ ገብተህ አትንቦጫረቅ ልቀቀኝ አቦ"
ስለው ጭራሽ ወገቤ ላይ ተጠምጥሞ " ኤፊ ኤፊ የለበስከው እኮ አፖስቶ ነው በቃ ዛሬ ቅዴ ቢሆንም በዚሁ ልብስ ብትውል ብዙ አያሳጣም ልጅቷም ኪያም ከሚደብራቸው"
ሲለኝ ከኪያ በላይ በማያገባው ገብቶ የሚንዛዛብኝ ጓደኛው ደሜን አፈላው።
"ተስፋዬ የምሬን ነው ከኪያ ጋር ሳይሆን ካንተ ጋር ልጣላ ነው ፣ ሰአቴን አትግደልብኝ ፣ አሁን ትለቀኛለህ አትለቀኝም?"
"አለቅህም ኤፊ" ሲለኝ ።
ትግስቴ ተንጠፍጥፋ አለቀች።
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose❤12😱5
1.1K · አትሮኖስ
#ተማሪዋ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስድስት
፡
፡
#ድርሰት_ቀጥላሁን
፡
፡
በዚህ መሀል ባለስቋ ገነት ከሱቅ ወጥታ መሀላችን ገባች።
"ኤፊዬ በሱም አትፍረድ እንዳትጣሉ ብሎ እኮ ነው ፣ አንተ ደሞ እላዩ ላይ እንደባብ ተጠምጥመህ ነው እንዴ እንዳይገባ የምታደርገው ኧረ ትገርማለህ" እያለች አላቀቀችኝ።
"ኤፍዬ እንደድሮው በረባ ባረባው በየሜዳው መጣላት እንደተውክ አውቃለሁ ፣ ብትሄድም እንደማትጣላው እርግጠኛ ነኝ ግን ኤፍዬ የግድ አሁን ገብተህ ልብስህን መቀየር አለብህ?"
"አዎ ገኒ ዛሬ ስራ አልሰራልም ሌላ ፕሮግራም አለኝ አሁኑኑ ልብሴን ቀይሬ መሄድ አለብኝ " አልኳት ሰአት እያየሁ አራት ሰአት ከሀያአምስት ሆኗል።
"ከልጅቷ ጋር ስለሆነ አልተናደድክም አይደል ኤፍዬ?
"ኧረ ገኒ ምናገባኝ እና ነው የምናደደው? ዛሬ ነው እንዴ ኪያ ከመክሊት ጋር የጀመረው ቆየኮ፣ የዚህ ድርቅ ማለት ነው እንጂ የገረመኝ እኔ ስወጣ ትገባለህ ኤፍሬም እንዳይመጣብን ጠብቅልን ብሎሃል እንዴ? ወዳ ከተደፋች እንኳን አንተና ኪያ ስትፈልጉ የገራዥን ወንዶችን በመሉ አስለፋችሁ አስገቡላት አይመለከተኝም ፣ ያንተ ግግም ማለት ግን ያስጠላል እሺ"
ስለው ዝም አለ።
"በቃ ኤፍዬ እራሱ ተስፋዬ ሄዶ ልብስና ጫማህን ያምጣልህ አንተም እርግጠኛ ነኝ ባታየቸው ነው የምትመርጠው ፣ ሂድ እራስህ ይዘኽለት ና ፣ ንገረው ኤፍዬ እንዲያመጣልህ የምትፈልገውን ልብስና ጫማ!" አለችኝ።
"አሪፍ መላ ነው ገንዬ እንዴት እንደዚህ አይነት ሀሳብ እስካሁን እንዳልመጣልኝ ይገርማል " አለ ተስፋዬ።
"ይገርማል አደል የምትገርመው እማ አንተ ነህ። አንተ እንድታመጣልኝ አልፈልግም እራሴ ሄጄ ነው የምወስደው "
ስለው " ውይ ኤፍዬ እልሁን ተወዋ በቃ ይልቅ ንገረው ሄዶ ያምጣልህ ሄደህ ክፈት አልከፍትም ስትጨቃጨቅ አከራዬቹም ሊደብራቸው ይችላል" አለችኝ ገነት። ነገርኩት ።
ሊያመጣልኝ እንደሄደ " በቃ ይዞ ይምጣና እዚሁ እኛ ቤት ቀያይረህ ትሄዳለህ " አለችኝ።
ከአስር ደቂቃ በኋላ ይዞልኝ መጣ።
"ምናልህ?" አለችው ገነት።
" አይ ምንም አላለም ምን ይላል ብለሽ ነው?" አላት።
"አንተ ግን የእውነት ጓደኛው ከሆንክ ምከረው ፣ ቆይ እሱ እድሜ ልኩን እንደወህኒ ቤት እስረኛ ሌላው ካልቀመሰለት አይበላም እንዴ? ሀይ ሁሌ ጓደኞቹ የጀማመሯቸው ሴቶች እያፈላለገ መጨረስ ነው ስራው ?" ስትለው ሳቄን አመጣችው።
"ገኒ ደሞ ጥፋቱ የሱ ብቻ ነው እንዴ ሴቶቹ ባይፈልጉ በግድ አያመጣቸው" አለ የኪያ ጠበቃ ተስፋዬ።
"ስማ ተስፋዬ አንተ ለኪያ የምትከራከረውን ያህል እሱ እራሱ ለራሱ እንዲህ ሲከራከር አይቼም ሰምቼም አላውቅም ትገርማለህ አቦ" ስለው እኔን እንዳልሰማ አልፎኝ ከገነት ጋር የጀመረውን ክርክር ቀጠለ።
እነሱ ሲከራከሩ እኔ ከሱቁ ጀርባ ወዳለው የነገነት ቤት ገባሁና ተጣጥቤ ልብሴን በመቀየር እኔና ቃልዬ ወደተቀጣጠርንበት መናሀሪያ ሄድኩ።
ቀድሚያት ነው የደረስኩት። ደወልኩላት ። እየደረስኩ ነው አለችኝ። ከአምስት ደቂቃ በኋላ ቃሌ ከመጣችበት ባጃጅ ወርዳ ወደኔ ስትመጣ አየሁዋት።
አምሮባታል። አጠገቤ እስክትደርስ አላስችል ብሎኝ ወደሷው ሄድኩና እቅፍ አድርጌ
"እንዴት እንዳማረብሽ የኔ ቆንጆ''
"አመሰግናለሁ አንተም አምሮብሃል ኤፍዬ"
ወደ ሀረር ጉዞ ተጀመረ። እኔና ቃልዬ እያወራን አምስት ደቂቃ ያህል የተጓዝን ሳይመስለን ነበር ሀረር የደረስነው።
"አሁን ወዴት ነን ኤፍዬ?" አለችኝ እንደወረድን።
"መጀመሪያ ምሳ እንብላ ከዛ ማየት የምትፈልጊውን ሄደን እናያለን።
ቃልዬ በዋናነት ማየት የምትፈልገው አምስቱን የጀጎል ግንብ በሮች እና የሀረርጌን ለማዳ ጅቦች ነው።
…
Read in full →❤10👍2
1 · 985 · አ
ቃልዬ ስለፈራች ጅቦቹን በሩቁ አይተን ከመመለስ በቀር አልተጠጋንም።
ፀጥ ረጭ ያለ የመኝታ አገልግሎት ብቻ የሚሰጥ ቤት አልጋ ያዝንና እራት ለመብላትና በዛውም ትንሽ ዘና ለማለት ወጣ አልን ።እኔም ቃልዬ ፉት ላይ ያለው ደስታ ልዩ ነው።
መጠጣት ብፈልግም ቃልዬ ብዙ እንድጠጣ ስላልፈለገች በስሱ ጠጥተን ወጣን።
በሀረር ጎዳናዎች ላይ በከተማው እኔና ቃልዬ ብቻ ያለን እስኪመስለኝ ድረስ እየተቃቀፍን ፣ ደሞ እየተላቀቅን፣ እየተላፋንና እየተሳሳቅን አልጋ ወደያዝንበት አመራን ።
ልክ ወደግቢው ስንቃረብ ግን የሁለታችንም አንደበት ተዘጋ። ተመካክረን በቃ ዝም እንበል የተባባልን ያህል አልጋ ወደያዝንበት ግቢ ልንደርስ ትንሽ እርምጃዋች ሲቀሩን በመካከላችን ፀጥታ ሰፈነ።
እንደተቃቀፍን በፀጥታ እራሳችንን ማዳመጥ ጀመርን። የልብ ትርታዬ ከእጥፍም በላይ ሳይሆን አይቀርም ምናልባት የቃልዬም እንደዛው ሆኖባት እሱን እያዳመጠች ይሆናል ዝም ያለችው። ምነው ዝም አልክ ምነው ዝም አልሽ እንኳን ለመባባል አልፈለግንም። ለምን ዝም ፀጥ ረጭ እንዳልን ሁለታችንም ገብቶናል ። የግቢውን በር አንኳኳሁ በሩ ስር ያለው ጥበቃ ወድያው ከፈተ። አሁንም በፀጥታ ወደ ክፍላችን አመራን።
የክፉሉን በር ከፍተን እንደገባን በውስጥ በኩል በሩ ላይ አስደግፌ አየኋት የቃልዬ አይኖች ተስለመለሙ ከንፈር ለከንፈር ተናነቅን።
ቃልዬ የላይኛውንም የስረኛውንም ከንፈሯን ገጥማ አፌ ውስጥ ስትሞጅረው አየር ማስወጣት የለ አየር ማስገባት መንገዱ ተዘጋ።ትንፋሽ አጠረን።
ከንፈሮቻችን ሳይላቀቁ እንደተጣበቁ እጄን ወደ ፁጉሯ ልኬ ፀጉሯ ላይ የተሻጠውን የፀጉር ማስያዣ መዘዝኩት ። ፀጉሯ እኔም እሷም ፊት ላይ ተነሰነሰ። ሳንላቀቅ ወዳልጋው እየተጠጋን የአንድ እጄ ጣቶች ፀጉሯ መሀል እየተርመሰመሱ የሌላኛው እጄ ጣቶች ወደጀርባዋ አምርተው የቀሚሷን ዚብ ከላይ ከትከሻዋ ጀምሬ እስከ ቀጭኑ ወገቧ ድረስ ተረተርኩት። ቀሚሷ እየተንሸራተተች ወርዳ ቀጭን ወገቧን ተሻግራ ዳሌዋ ላይ ጉዞዋ ተገታና እንደጉርድ ቀሚስ ተንጠለጠለች።
የቀሚሷን መሄድ ተከትለው ጡቶቿ ከጡት ማሳይዣዋ አፈትልከው ለመውጣት አመፅ ላይ ያሉ ይመስል እንደተወጣጠሩ ሳያቸው ልቤ ዝቅ አለች።
ከንፍሯ ከከንፈሬ አፍንጫዋ ከአፍንጫዬ እንደተያያዙ የፍቅርን ረቂቅ ጣእም በትንፋሽ እና በፈሳሽ መልክ እየማጉ በቃልዬም በኔም ሰውነት ውስጥ ሲያሰራጩ የፈጠሩት ሙቀት መንደድ ጀመረ።
ምላሷ ላይ የሚንከባለለውን ምላሴን ከምላሷ እያፋታሁ ዝቅ ብዬ አንገቷን ከፍ ብዬ ጆሮዋን ስስማት መላ አካላቷ በንዝረት ሲርገፈገፍ ይታወቀኛል።በፍቅር ሲቃ እየቃተተች የምታወጣው ድምፅ አቅሌን አሳጣኝ ።
በስሜት ማእበል እየቀዘፉ ወደ ጀርባዋ ያመሩት እጆቼ የጡት ማስያዣዋን ፈትተው ለቀቁት። በከፊል ብቅ ያሉት ጡቶቿ ነፃነታቸውን አውጀው ከደረቴ ጋር ለመፋለም የተቀባበሉ ይመስል ወደ ፊት ተቀሰሩ።
ወደጀርባዬ ገፋ አድርጋኝ ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ከላይ የለበስኩትን ነጭ ሸሚዝ ቁልፎች ስትከፍት ፊት ለፍት እያየኋት ዋጣት ዋጣት የሚል ስሜት የፈነቀለው ልዩ ግፊት ሁለመናዬን ናጠው።
ሸሚዜን አውልቃ አሽቀንጥራ ጣለችውና ከደረቴ ጀምራ በከንፈር በምላሷ እያራሰች በአንገቴ በኩል ወደላይ ተሻግራ ከንፈሬን ስትጎርሰው የጋለው ሰውነቴ እንደኤርታሌ እስተ ጎመራ ፈንድቶ መፍለቅለቅ ጀመረ ።
ብድግ አድርጌ አልጋው ላይ በጀርባዋ አንጋለልኳት። እግርና እጆቿን ግራ ቀኝ ከፋፍታ፣ የተቀሰሩት ጡቶቿ በትንፋሿ ልክ እላይ ታች እያሉ ፣ አይኗን ከደን ከፈት እያደረገች ወደላይ ስትመለከተኝ አልጋው ጠርዝ ላይ ቆሜ እየተመለከትኳት የፍቅር አውሎንፋስ ከቆምኩበት ወደላ…
Read in full →❤17👍2🤔1
1 · 1K · አትሮኖስ
#ተማሪዋ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ሰባት
፡
፡
#ድርሰት_በጥላሁን
፡
፡
በአልጋው ሜዳ ላይ የፍቅር ፍልሚያው ተጀመረ። ከዚህ በኋላ በያንዳንዷ ሰከንድ የተፈጠርው ነገር ለኔም የማልቋቋመው ተዓምር ሆነብኝ•••
ድንግልናዋ የለም። ነገር ግን አይደለም ድንግል አይደለሽም እንዴ ብዬ የምጠይቅበት አንደበት ለትንፋሽ የሚሆን ግዜ ስታሳጣኝ ድንግል ለምኔ የሚል አዲስ ነጠላ ዜማ መዝፈን ጀመርኩ።
የሷን ድንግል ልወስድ ቋምጬ እኔ እራሴ እስከዛሬ ምንም የማላውቅ ድንግል እንደነበርኩ ያሳመነችኝ የፍቅር ድብድቡ በተጀመረ በአራት ደቂቃ ውስጥ ነበር።
ከአራት ደቂቃ ቡሃላ አጠቃላይ እንቅስቃሴያችንን በበላይነት የተቆጣጠረችው ቃልዬ ነች።
የሚሰበር ነገሬን ሁሉ ሰባብራ እና ከጥቅም ውጪ አድርጋ ለመዘረር ዘጠኝ ደቂቃዎች ያህል ካልጋው ጫፍ እስከጫፍ ስታሽከረክረኝ እንደዚህም አይነት ሴት አለች ለካ እያልኩ በሷ መደመም ብቻ ሳይሆን ከዚህ ቀደም አንቀላፍተው እንቅልፌን የሚያመጡብኝን ሁለት ሴቶች ጭምር አስረገመችኝ።
በተለያየ አጋጣሚ ሁለቴ ከሞሞካከር በስተቀር እኔ በዚህ ዙርያ ብዙ ልምዱ እንዳልነበረኝ ባልክድም ያ ሙከራ እንጂ ትግበራ ለመባል እንኳን የማይበቃ መተሻሸት እንደነበረ ያመንኩት አሁን ነው።
ቃልዬ እያገለበጠች ስታንገላታኝ በተለይ አንደኛዋ ከዚህ ቀደም ያጋጠመችኝ ሴት ትዝ አለችኝ ። ምን ሆና ነው ግን እንደዛ አይኗን ጨፍና የተጋደመችው? ማደንዘዣ መርፌ ተወግታ ነው እንዴ የመጣችው? አልኩ።
ቃልዬ ትለያለች ። ወንድ ነኝ እኔ መብለጥ ነበረብኝ እንዴት እበለጣለሁ ብዬ በአጉል ትእቢት ደስታዬን መቀነስ አልፈለኩም።
ሁልግዜ ወንድ መብለጥ አለበት የሚል ነገር በአንዳንዶቻችን ወንዶች ጭንቅላት ውስጥ ያለ ኩፈሳ እንጂ ከተግባሩ ጋር ሲነፃፀር እውነቱ ሌላ የሚሆንበት አጋጣሚ እንዳለ እንደቃልዬ አይነት ተውረግራጊ የአልጋ ንግስቶች ያጋጠሟቸው ወንዶች መች ይክዳሉ።
እኔም መበለጤን አምኜ ስታጋድመኝ ስጋደም ፣ ስታስቀምጠኝ ስቀመጥ፣ ስታስቆመኝ ስቆም ፣ ስትንጠለጠልብኝ ስሸከም፣ ስትጨፍርብኝ ሳስጨፍር ወገቤ ተንቀጠቀጠ፣ ጉልበቴም ተብረከረከብኝ።
ሁለት እጄን ወደላይ ሰቅዬ •••
" ቃልዬ ገደልሽኝኮ የዕረፍት ሰአት የለም እንዴ ?"ልል ትንሽ ነበር የቀረኝ። እየተሽከረከረችና እያሽከረከረች ልኬን ስታሳየኝ እኔም እሷም ውስጥ የነበረው የደስታ ሲቃ ልዩ ነው።
እና እኔ ነኝ ቃልዬን ለምን ልጃገረድ አልሆንሽም ብዬ ለመደንፋት ሞራል ያለኝ?። ከድንግልናዋ ምን ጉዳይ አለኝ። ኧረ ምንም ። ብራንባር ቅብርጥሴ ኧረ የታባቱ ። ደሞ እሱ ኖረ አልኖረ ብዬ ልጨነቅ እንዴ። ጥንቅር ይበል ።
ብር አንባር ድሮስ ምን ያደርጋል ?እንደዉም ድንግልናኮ የወንዶች ባላንጣ ነው፣ የምሬን ነው ድንግልና ምቀኛ ነገር ነው።
እንደአመፀኛ ሚዜ በር ዘግቶ አላስገባም ሰርገኛ አርፈህ ተኛ እያለ ከመከላከል በቀር ምን ስራ አለው? ምንም።
እና እባክህ አሳልፈኝ በሞቴ ልግባ አልግባ እያልኩ ከሱ ጋር ግብግብ መግጠም ምን ያደርግልኛል? ምንም።
ኧረ እንኳንም አልኖረ ፣ ድንግል ሆና ዝም ብላ በጀርባዋ ተንጋላ በል ከቻልክ ግባ ካልቻልክ ስራህ ያውጣህ ብትለኝና ነገር አለሙን ሁሉ ለኔ ብትተወው ምን ይውጠኛል?እንደዛች ማደዘዣ መርፌ የተወጋች እንደምትመስለው ልጅ ሳትገላበጥ ሰትላወስ አይኗን ጨፍና በመጋደም ኧረ አሳመምከኝ ቀስ በል እንጂ ኤፊ አመመኝ እኮ እያለች የአልጋ ላይ ትራፊክ ሆና ብታሳቅቀኝ መሳቀቅ እንጂ ምን አተርፋለሁ?።
ልጃገረድ ብትሆን ለሷ ትልቅ ነገር ሊሆን ይችላል። ለኔ ግን ከሱ ጋር ትግል ገጥሜ ላቤን ከማንቆርቆር በስተቀር ምንም እንደማይሰራልኝ ያሳመነ…
Read in full →❤9👍3
742 · አልጋውን ማለቴ መድረኩን አጠቃቀምሽ ልዩ ነበር፣ ያልጨፈርሽበትን የአልጋ ክፍል ማግኘት ይከብዳል።በተለይ መሀል አከባቢ እሱ ቁጭ እንዳለ አንቺ እሱ ላይ ተቀምጠሽ ያሳየሽን እንቅስቃሴ ገራሚ ነው።
እንደዛው እንደተቀመጥሽ ወደላይ ወደላይ እያልሽ የአፋሮችን ባህላዊ ውዝዋዜ ስትስትጫወቺው ያየ የሰው ልጅ ቁጭ ብሎም መዝለል ይችላል እንዴ? ማለቱ የማይቀር ነው።ወድያው ከአፋርኛ ወደ ሸጎዬ ቢት ቀይረሽ ግራ ቀኝ ዘንበል ቀና ስትይ ልዩ ትእይንት ነበር ።
እሱን አይተን ሳንጠግበው እንቅጥቅጥን ታስነኪው ጀመር፣ እዛ ላይ እንደተመሰጥን ወደ ጀርባሽ ድንገት ዝንጥፍ ብለሽ ስትታጠፊ እኔ በእውነት ወገብሽ ቅንጥስ ያለ ሁላ መስሎኝ ልጮህ ነበር።
ቃልዬ ሳቋን መቆጣጠር እያቃታት እያቃረጠች ብታስቸግረኝም ስቃ ጋብ እስክትል እያረፍኩ የዳኛውን ማብራሪያ ቀጠልኩ•••
አንድ ሳልነግርሽ ማለፍ የማልፈልገው ድንቅ እንቅስቃሴ መጨረሻ አከባቢ አንቺ ከስር ሆነሽ እሱን ከላይ ካደረግሽው በኋላ እግሮችሽን ወገቡ ላይ አጠላልፈሽ ያሳየሽው አለም ነው ።
እሱን አላላውስ ቢለውም ድንቅ ፍትወቶግራፊ የታየበት የዳኞቹን እና የ ተመልካቾችን ስሜት ሰቅዞ የሚይዝ ድንቅ ፐርፎርማንስ ነበር።
በዚሁ ቀጥይ ነገ ትልቅ ቦታ እንደምትደርሺ አልጠራጠርም ።
ይልና ባንዴ ፊቱን ዘፍዝፎት ወደኔ ይዞራል ከዛ እንዲህ ይለኛል •••
" ወዳንተ ስመጣ በጥቅሉ የሷ እንቅስቃሴና ፍጥነት ከጠበቅከው ውጪ የሆነብህና ግራ የተጋባህ መሆኑን ነው ያስተዋልኩት።
ለዚህ ማሳያው ዙሩ እየከረረ እና እየተጋጋለ ሲመጣ አንተም እንደኛው በሷ ሁኔታ የተገረምክ በሚመስል ሁኔታ ሙሉ በሙሉ የእንቅስቃሴያችሁን ቁጥጥር አንቺ እንዳሻሽ እንደፈቀድሽ አድርጊኝ ብለህ ለሷ በመተው ለመሳተፍ ሳይሆን እንደኛው ለመዳኘት የመጣህ ይመስል በአድናቆት ስትመለከታት ማየቱ በቂ ነው" ይለኛል ።
ከዛ የድምፅ ዳኛው ማይኩን ይቀበልና
ማነሽ ቃልኪዳን እኔ ላንቺ አድናቆቴን የምገልፅበት ቃል የለኝም።
በጥቅሉ ስታሰሚን የነበረው በስሜት የበለፀገ ድምፅ እንደ እንቅስቃሴው የሚፈጥን እና የሚረግብ ሪትሙ ልክክ ያለ ፣ ቴምፖው የተመጠነ ለጆሮ የሚጥም ድምፅ ነበር።
ወደ ኤፍሬም ጋር ስመጣ እእእ ኤፍሬም አንተ ጋር የነበረው ነገር በጣም ግራ የሚያጋባ ግራ የገባው ድምፅ ነው ።
እኔ የምታወጣው ድምፅ ማጓራት ይሁን ማቅራራት በፍፁም ሊገባኝ አልቻለም። እንቅስቃሴው ትንሽ ከበድ ብሎህ ስለነበር ድምፅህን አዛብቶታል።
ላንተ ያለኝ ምክር ሰፈራችሁ ጫካ አልያም ተራራ ካለ ባይኖርም ከከተማ ወጣ ብለህ ሰው ወደማይኖርበት ጫካ በመሄድ ጮክ ብልህ የድምፅ (ቮካል ) ልምምድ በመስራት ይህንን አባጣ ጎርባጣ ድምፅህን ልትሞርደው ይገባል " ይለኛል።
"ካካካካ አባጣ ጎርባጣ ድምፅ ግን ምን አይነት ነው ቃልዬ?" ስላት ቃልዬ እየሳቀች ስለነበር መልስ አልሰጠችኝም።
"ከዛ ሶስተኛው ዳኛ ደሞ•••" ብዬ ልቀጥል ስል•••
"ኧረ ኤፍዬ በቃህ መሳቅ ደከመኝ ኪኪኪኪ በእውነት ሆዴን አመመኝ በቃህ" አለችኝ።
ከወንበሬ ላይ ተነስቼ ወደ አልጋው በመሄድ ቃልዬን አቅፊያት ተኛሁ።
እሁድ አመሻሹ ላይ ወደ ድሬ ተሳፈርን። የሚኒባሱ የመጨረሻ ወንበር ላይ ያለነው እኔና ቃልዬ ብቻ ነን።
ሚኒባሱ ገና አልሞላም ከመናሀሪያ ቢወጣም ከመንገድ ላይ ለሞሙላት
"የሞላ የሞላ አወዳይ፣ ሀሮማያ ፣ደንገጎ ፣ ድሬ ዳዋ ሁለት ሰው" እያለ ይጣራል።
ውስጤ እርብሽብሽ አለብኝ ። ከቃልዬ ጋር ድሬ ስንደርስ መለያየታችን ግድ መሆኑን ሳስበው አስጠላኝ።
"ቃልዬ ተነሽ እንውረድ !" አልኳት እጇን ያዝ አድርጌ እየተነሳሁ።
"ምነው ኤፍዬ ምን ረስተህ ወጣህ " እያለች ተ…
Read in full →❤8👍2😱1
700 · አ
"ኪኪኪ ምንድን ነው ደሞ አቅም ግንባታ ?"
"አሁን ከዚህ ስንወጣ የሀረርን ሰንጋ ጥሬ ስጋ ነው የምበላው ከዛ ወንዱና ሴቱ ይለያል እንግዲህ"
ስላት ጥበቃው " አቤት ጠራችሁኝ እንዴ ልጆች?" ብሎ ክፍላችን ድረስ እስኪመጣ ነበር ሳቋን ጥበቃው ቤት ድረስ እስኪሰማ የለቀቀችው።
ጥበቃውን ነገሩ ወዲህ ብዬ በሩን ዘግቼ ስመለስም እየሳቀች ነው።
"ኪኪኪ አይ ኤፍዬ •••ኤፍዬ ሙት ጫወታህ እኮ አይጠገብም ።
" የምን ጫወታ ? አዎ ላንቺ ጫወታ ነው ዛሬ ልክሽን ካላሳየሁሽ ወንድ ያባቱ ልጅ አይደለሁማ"
"በ. ም. ን በ ጥሬ. ስጋ ?" እያለች በሳቅ ስትንከተከት እኔም አብሩያት ስንተከተክ ቆየሁና•••
ቃልዬ ሙች ትናንትም እኮ መብላት የፈለኩት ጥሬ ስጋ ነበር ግን ያንቺ ምርጫ ስላልነበር ነው የተውኩት"
"እና ዛሬም የኔ ምርጫ ጥሬ ስጋ መብላት ባይሆንስ?"
"ብቻሽን ትበያታለሻ ቀልድ የለም ፣ ከጥሬ ስጋ ውጪ ወይፍንክች ብያለሁ ወይ ፍንክች"
"ቆይ ቆይ ጥሬ ስጋ ወንድ ያደርጋል እንዴ?"
"ይሄኔ ነው መሸሽ ማለት ያለበት አሁን ነው መሻሻ! እንዴ ቃልዬ እንደቀልድ እያዋዛሽ ሞራሌ ላይ ታንክ መንዳት ጀመርሽ አደል?"
"እንዴ እንዴት ስለምን ታንክ ነው የምታወራው?"
"ከዚህ በላይ የሰውን ሞራል በታንክ መደፍጠጥ አለ እንዴ የምን ታንክ ትያለሽ እንዴ ደሞ? ጥሬ ስጋ ወንድ ያደርጋል እንዴ ? ማለትሽ ትናንትና ወንድ አልነበርክም ዛሬ ጥሬ ስጋ በልተህ ወንድ ልትሆን ነው ወይ? ማለትሽ አይደል እንዴ?
"
"ጫ. ን. ያ. ለ. ው መጣ" አለች ቃልዬ ጋደም ካለችበት ቀና እያለች።
"ማን ነው ጫንያለው? የጥበቃው ስም ጫን ያለው ነው እንዴ?" አልኳት ወደ በሩን አየት አድርጌ።
"ኤፍዬ ሙት አንዳንዴ እየቀለድክ ይሁን እያመረርክ ይምታታብኛልኮ ለማንኛውም ኤፍዬ እኔ እንደዛ ለማለት ፈልጌ አይደለም ወንድማ ወንድ ነህ ሊያውም መለሎ ቁመት፣ ጠይም ፊት ፣ ያልወፈረ ቀጭን የማይባልም ተክለሰውነት ያለው ፣ ፊቱ ላይ ያለው የደስደስ ወደሌላው የሚጋባ ደስ የሚል የሀበሻ ወንድ!" አለችኝ።
የሰውነቴ ሙቀት በአንድ ግዜ እጥፍ ሲሆን ተሰማኝ። የድሬ ከተማ ህዝብ በሙሉ ተሰብስቦ ቃልዬ አሁን ያለችኝን ቢለኝ እንካን ይህን ያህል ሙቀቴ የሚጨምር አይመስለኝም...
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose❤16👍4
831 · አትሮኖስ
#ተማሪዋ!
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ስምንት
፡
፡
#ድርሰት_በጥላሁን
፡
፡
"ኤፍዬ ሙት አንዳንዴ እየቀለድክ ይሁን እያመረርክ ይምታታብኛልኮ ለማንኛውም ኤፍዬ እኔ እንደዛ ለማለት ፈልጌ አይደለም ወንድማ ወንድ ነህ ሊያውም መለሎ ቁመት፣ ጠይም ፊት ፣ ያልወፈረ ቀጭን የማይባልም ተክለሰውነት ያለው ፣ ፊቱ ላይ ያለው የደስደስ ወደሌላው የሚጋባ ደስ የሚል የሀበሻ ወንድ!" አለችኝ።
የሰውነቴ ሙቀት በአንድ ግዜ እጥፍ ሲሆን ተሰማኝ። የድሬ ከተማ ህዝብ በሙሉ ተሰብስቦ ቃልዬ አሁን ያለችኝን ቢለኝ እንኳን ይህን ያህል ሙቀቴ የሚጨምር አይመስለኝም።
••••
በሚያፈቅሩት ሰው መሞካሸት የሚፈጥረው የደስታ ስሜት ልዩ ነው።
"አመሰግናለሁ ቃልዬ!" አልኳት። ከሰከንዶች ዝምታ በኃላ•••
"ኤፍዬ "
"ወዬ ቃል"
"አመረርክ እንዴ ትናንት እኮ እኔን ለማሳቅ ብለህ እኔን አሸናፊ አንተን ተሸናፊ አድርገህ እንደቀለድክ እንጂ ከልብህ እንዳልሆነ ነበር ያሰብኩት፣ ኤፊዬ ሙት እኔ ትናንት በነበረው ነገር በጣም ደስተኛ ነኝ፣ ምንም ያጎደልክብኝ ነገር የለም ተመችቶኛል"
"ገሎ ማንሳት፣ ጠብሶ ማሸት የሚባል ነገር ታውቂያለሽ"
"ገሎ ማንሳት አላውቅም ጠብሶ ማሸት ግን ለበቆሎም ሊሆን ይችላል ለሰውም ይሆናል ያው ጠብሰክ እያሸኸኝ አይደል እንዴ ኤፊዬ?"
"ካካካ አንቺ ነሻ ገለሽ የምታነሽው ጥሬ ስጋ ወንድ ያደርጋል እንዴ ብለሽ ከገደለሽኝ በሁዋላ አይደለም በሽንገላ በክሪክ አልነሳም።
ያለው አማራጭ ወንድነቴን ማሳየትና ማስመከር ብቻ ነው"
"ክሪክ ምንድን ነው ኤፊ ?"
"የተሽከርካሪ ጎማ ለመቀየር ለሌላም ጉዳይ ብቻ መኪናው ከፍ የምናደርግበት ነዋ " አልኳት በቃ ወሬህ ዞሮ ዞሮ ከትራፊክ ህግና ከተሽከርካሪ አይወጣም አይደል እንዳትለኝ ውስጥ ውስጡን እየተሳቀቅኩ።
"እኔ እንግዲህ ወንድነትህን አይቼዋለሁ ሌላ የምታሳየኝ አዲስ ነገር አለ?"
'አዎ አለ"
"እና አሳየኛ "
"አሁን አይደለም ስንመለስ " ብዬ እጇን ይዤ በመጎተት ከአልጋው ላይ አነሳኋትና ይዣት ወጣሁ።
እየሄድን መንገድ ላይም "አይ ኤፊ" እያለችና ዝም ብላ እያየችኝ ትስቃለች።
"ለምንድን ነው የምትስቂው ቃልዬ?"
" ኤፊዬ ግልፅነትህ በጣም ደስስስስስ እንደሚለኝ ታውቃለህ ግን?"
"አላውቅም ነበር ይሄው አሁን ነገርሽኝ። እና ግልፅነቴ ብቻ ነው ደስ የሚልሽ?"
"ሌላውን ሌላ ግዜ እነግርሀለሁ"
"በጣም የሚገርመኝ ባህሪሽ የሆነ ነገር ለማውራት ቀጠሮ የምትይዥው ነገር ነው"
"ሁሉም ነገር እኮ ባንድ ግዜ አይወራም ኤፍዬ"አለችኝ ወገቤን አቀፍ አድርጋ ወደሷ በመጎተት በዳሌዋ ገጨት እያደረገችኝ።
ተንገዳግጄ ልወድቅ ነበር ። የሴት ቀጭን የለውም አለች አያቴ። ቃልዬ በርግጥ የሰማዩ ንጉስ ክብሩ ይስፋና ከወገቧ ቀጠን ከዳሌዋ ሰፋ አድርጎ ስላስዋባት በዛ ዳሌ ተገጭቼ ብንገዳገድ በኔ አይፈረድም። ቃልዬ
" ና በደንብ ልግጭህና ውደቃ በቃ ነካ ሳረግህ ተንገዳገድክኮ መውደቅ አምሮህ ነው" እያለች ድጋሚ ልገጨኝ ስትሞክር አንገቷን አቅፌ ተረፍኩ።
ለጥሬ ስጋ እስከዚህም ብትሆንም አንተ የበላኸውን ነው የምበላው ሌላ ምግብ አላዝም ብላ አብራኝ በላች።
በልተን እንደጨረስን እዛው በስሱ ማወራረጃውን እየተጎነጨን ቆየን። እንደትናንትናው ከዚህ በላይ እንዳትጠጣ በቃህ አላለችኝም። እኔም በነፃነት በላይ በላይ እልፈው ጀመር።
ነገር ግን ቃልዬም እንደስከዛሬው ከሁለት በላይ አልጠጣም የምትለውን ረስታው ይሁን ትታው ደገም ደገም ስታደርግ ኦኦ ሁለታችንም ከሰከርን ማን ማንን ሊጠብቅ ነው ? አልኩና የኔን መጠጣት ገታ ማድረግ እንዳለብኝ ወሰንኩ።
ጭራሽ " ጠጣ እን…
Read in full →❤7👏2
1 · 457 · "ኪኪኪ ምንድን ነው ደሞ አቅም ግንባታ ?"
"አሁን ከዚህ ስንወጣ የሀረርን ሰንጋ ጥሬ ስጋ ነው የምበላው ከዛ ወንዱና ሴቱ ይለያል እንግዲህ"
ስላት ጥበቃው " አቤት ጠራችሁኝ እንዴ ልጆች?" ብሎ ክፍላችን ድረስ እስኪመጣ ነበር ሳቋን ጥበቃው ቤት ድረስ እስኪሰማ የለቀቀችው።
ጥበቃውን ነገሩ ወዲህ ብዬ በሩን ዘግቼ ስመለስም እየሳቀች ነው።
"ኪኪኪ አይ ኤፍዬ •••ኤፍዬ ሙት ጫወታህ እኮ አይጠገብም ።
" የምን ጫወታ ? አዎ ላንቺ ጫወታ ነው ዛሬ ልክሽን ካላሳየሁሽ ወንድ ያባቱ ልጅ አይደለሁማ"
"በ. ም. ን በ ጥሬ. ስጋ ?" እያለች በሳቅ ስትንከተከት እኔም አብሩያት ስንተከተክ ቆየሁና•••
ቃልዬ ሙች ትናንትም እኮ መብላት የፈለኩት ጥሬ ስጋ ነበር ግን ያንቺ ምርጫ ስላልነበር ነው የተውኩት"
"እና ዛሬም የኔ ምርጫ ጥሬ ስጋ መብላት ባይሆንስ?"
"ብቻሽን ትበያታለሻ ቀልድ የለም ፣ ከጥሬ ስጋ ውጪ ወይፍንክች ብያለሁ ወይ ፍንክች"
"ቆይ ቆይ ጥሬ ስጋ ወንድ ያደርጋል እንዴ?"
"ይሄኔ ነው መሸሽ ማለት ያለበት አሁን ነው መሻሻ! እንዴ ቃልዬ እንደቀልድ እያዋዛሽ ሞራሌ ላይ ታንክ መንዳት ጀመርሽ አደል?"
"እንዴ እንዴት ስለምን ታንክ ነው የምታወራው?"
"ከዚህ በላይ የሰውን ሞራል በታንክ መደፍጠጥ አለ እንዴ የምን ታንክ ትያለሽ እንዴ ደሞ? ጥሬ ስጋ ወንድ ያደርጋል እንዴ ? ማለትሽ ትናንትና ወንድ አልነበርክም ዛሬ ጥሬ ስጋ በልተህ ወንድ ልትሆን ነው ወይ? ማለትሽ አይደል እንዴ?
"
"ጫ. ን. ያ. ለ. ው መጣ" አለች ቃልዬ ጋደም ካለችበት ቀና እያለች።
"ማን ነው ጫንያለው? የጥበቃው ስም ጫን ያለው ነው እንዴ?" አልኳት ወደ በሩን አየት አድርጌ።
"ኤፍዬ ሙት አንዳንዴ እየቀለድክ ይሁን እያመረርክ ይምታታብኛልኮ ለማንኛውም ኤፍዬ እኔ እንደዛ ለማለት ፈልጌ አይደለም ወንድማ ወንድ ነህ ሊያውም መለሎ ቁመት፣ ጠይም ፊት ፣ ያልወፈረ ቀጭን የማይባልም ተክለሰውነት ያለው ፣ ፊቱ ላይ ያለው የደስደስ ወደሌላው የሚጋባ ደስ የሚል የሀበሻ ወንድ!" አለችኝ።
የሰውነቴ ሙቀት በአንድ ግዜ እጥፍ ሲሆን ተሰማኝ። የድሬ ከተማ ህዝብ በሙሉ ተሰብስቦ ቃልዬ አሁን ያለችኝን ቢለኝ እንካን ይህን ያህል ሙቀቴ የሚጨምር አይመስለኝም...
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose👎4❤3👍2
1 · 479 · 🏴 | ታላቁ ማንችስተር ዩናይትድ በዚህ በውድቀቱም ሰአት ቢሆን የሚደግፍ ትክክለኛ ዩናይትዳዊ ለሆነ ብቻ JOIN ይበል ❤️
ከእሁድ እስከ እሁድ መረጃዎችን በጥራት ይኮምኩሙ👇
138 · A
🟡• ቤቲንግ ይጫወታሉ መበላትስ ሰልችቶታል እንግዲያውንሱ በነፃ ያለምንም ክፍያ በቀን ከ 50-150 odd የሚለቀቅበት ቻናል ልጠቁማቹ ትጠቀሙበታላችሁ🔥
ቻናሉን ከስር JOIN ሚለውን በመንካት ቶሎ ይቀላቀላሉ👇
174 · አትሮኖስ
#ተማሪዋ
፡
፡
#ክፍል_አስራ_ዘጠኝ
፡
፡
#ድርሰት_በጥላሁን
፡
፡
ወደ ማሳረጊው አከባቢ ቃልዬ ስሜት ውስጥ ሆና የተናገረችው ነገር በሚሳኤል የተመታሁ ያህል ጆሮ ግንዴን አደባየው።
ቃልዬ ድክም በለ ድምፀት በስሱ "ዛኪዬ የኔ ፍቅር አልቻልኩም" የሚሉ ቃላቶች ብትናገርም ወደ ጆሮዬ ሲደርሱ ግን ጩኸታቸው የመብረቅ ያህል አስደንጋጭ ነበር።
ጆሮዬን ማመን ተሳነኝ። ከባልቦላው ያጠፋችኝ ያህል ውስጤ ድርግምግም አለ። ከነበርኩበት ጣፋጭ የፍቅር ትኩሳት ወርጄ በረዶ ሆንኩ።
ተወርውሬ ደብዘዝ ያለውን መብራት ቦግ ሳደርገው ከስሬ የተንጋለለችው ቃል አይኗን ከሀይለኛው ብርሀን ለመከላከል በክንዷ እንደመጋረድ እያለች "ምነው ኤፍዬ?" ስትለኝ በዝምታ አፈጠጥኩባት።
"ምነው ኤፊ ለምን አበራኸው?" አለችኝ ደግማ ክንዷን ገለጥ አድርጋ እየተመለከተችኝ።
"አአአአ •••አሁን ምንድን ነው ያልሽው ቃል?" አልኳት
"ለምን አበራኸው ነዋ ያልኩህ አይሰማህም እንዴ ኤፍዬ"
"አይ ከዛ በፊት"
"ከዛ በፊት ማለት?"
"ከማብራቴ በፊት ምንድን ነው ያልሽው?" ••••
•••••••
"ኪኪኪ እንዴ እሱንም እማ አልደግመውም "
"ለምን ? ለምንድን ነው እማትደግሚው?"
"እህ በፍቅር እና በስሜት ውስጥ ሆነህ ያወራኸውን ነገር እኮ ሲደገም ይለዛል ለዛው ይጠፋል ደስ አይልም"
"ግድ የለም እኔ መስማት ስለምፈልግ ድገሚው"
"መስማት ስለፈለክ ነው ወይስ ደግመህ መስማት ስለፈለክ"
"ደግሜ መስማት ስለፈለኩ ?" አልኳት እሷ በፈገግታ ውስጥ ሆና እያወራችኝ ስለነበር ደግማልኝ እስክሰማው መደንገጤም መለወጤም እንዳይታወቅብኝ እየሞከርኩ።
"በናትህ መብራቱን እንደቅድሙ አድርገው ኤፍዬ?"
"ንገሪኛ መጀመሪያ"
"እንዴ ካልደገምኩልህ አታጠፋውም እኔ አጠፋዋለሁዋ ምነው ማሽከርከር የሚያቅተኝ መሰለህ እንዴ ብላ ቀና አለችና ማብሪያ ማጥፉያውን ወደ ግራ ዘውራ አደበዘዘችው።
" እና አትነግሪኝም "
"አልነግርህም "
"ቃልዬ እባክሽ "
"እንዴ••••የምርህን ነው አንጣ ወረቀትና እስክርቢቶ ያልኩትን ልፃፍልህና ሌላ ግዜ አልተሸነፍኩም ብዬ ብክድ እንኳን ማስረጃ ይሆንሃል ከፈለክም ደጋግመህ ታነበዋለህ ኪኪኪኪ"
ቃልዬ ምን እያለች እንደሆነ ሊገባኝ አልቻለም።በዚህ ሰአት ወረቀትና እስክርቢቶ ኬት ያመጣል ብላ ነው አደል የምትጫወትብኝ አልኩና ስልኬን አንስቼ ከስልኬ ላይ የማስታወሻ መፃፊያውን መተግበሪያ ከፍቼ
"ይሄው መጨረሻ ላይ ያልሽኝን እዚህ ላይ ፃፉልኝ ወረቀት ምናምን ኬት ይመጣል በዚህ ሰአት "
"አይ ኤፍዬ!" እያለች ሞባይሉ ላይ ፃፈችና ሰጠችኝ።
ፅሁፉን ሳነበው ሽምቅቅ ብዬ አንድ ፍሬ አከልኩ ። ቃልዬ ሞባይሌ ላይ ፅፋ የሰጠችኝ •••" ዛልኩልህ የኔ ፍቅር ይላል።
ጆሮዬ እና አይኔ መስማማት አቃታቸው። ማንን እንደምረግም ግራ ገባኝ ። ጆሮዬን ልርገም ሀሳቤን? ። ውስጤ ያ ሀሳብ ያ ጥርጣሬ ባይኖር ጆርዮ ኬት አምጥቶ "ዛልኩልህ የኔ ፍቅር " የሚለውን ንግግር ዛኪዬ የኔ ፍቅር ብሎ ይሰማል።
ጥርጣሬ የፍቅር ሰንኮፍ የደስታ ጭንጋፍ ነው ። እኔ የምፈልገው ከቃልዬ ጋር በደስታ እና በፍቅር መቀጠል ነው። ስለዛ ልጅ ማሰብ ካላቆምኩ ደግሞ ያንን ማጣጣም አልችልም። ለአንዴና ለመጨረሻ ግዜ ከአይምሮዬ ላወጣው ምንም ሳይፈጠር ምንም የተጨበጠ ነገር ሳይኖር ዝም ብዬ ስለሱ ላላስብ ላልጨነቅ ቃልዬንም ላላስጨንቅ ለራሴ ቃል ገባሁ።
"አንተ ጨቅጫቃ ሴቭ አድርገውና ሁሌ አንበበው እሺ መሸነፏን ትክዳለች ብለህ ነው አደል ካልደገምሽው ብለህ እርርይ ያልከው ኪኪኪ ሆሆ በቃ አሸንፈኻል ተሳክቶልሀል እሺ ኤፍዬ እሁንስ ደስ አለህ? " አለችኝ። አቅፋኝ እየ…
Read in full →❤17👍3
1 · 728 · "እሺ አልጨርሰውም" ብያት ዝም አልኩ ከንቺ የሚለየኝ ሞት ብቻ ነው ልላት ነበር እውነትም የሚረብሽ ነገር አለው አልኩ ለራሴ ።
" አይ ኤፍዬ የሆነ ሌላ አገር የምሄድና የምንራራቅ አስመሰልከው እኮ ሁለታችንም የተለያየ ቦታ እንሁን እንጂ ከድሬ አልወጣን ዛሬ ብንለያይ መገናኘት በፈለግን ሰአት በደቂቃዎች ውስጥ መገናኘት እንችል የለ እንዴ የሆነ አየር መንገድ አድርሰኸኝ የምትመለስና ወደ ሌላ ቦታ የምበር መሰለህ እንዴ?"
"ልክ ነሽ መገናኘቱንማ ማን ይከለክለናል" አልኳትና አሁንም ዝም አልኩ። ንግግሯ በድጋሚ አቃጨለብኝ።
ለካ እሱም አለ። ያንን ስሜትማ መቋቋምም አልችል። አያምጣው ነው እንጂ አያድርስ አለች ዘፋኟ።
እስከግቢ ሸኝቻት ስመለስ ወደዛ ቤት መግባት ቢያስጠላኝም ግድ ነው እና ገባሁ። ፍራሼ ላይ ጋደም እንዳልኩ ምን ግዜ እንቅልፍ እንደጣለኝ አላውቅም ብንን ስል መሽቷል ።
ተነስቼ ከቃልዬ ጋር በስልክ አወራሁና ወጣ ብዬ ገኒ ሱቅ ሄጄ በሩ ላይ ቁጭ እንዳልኩ ገኒ ሳላዛት ቀዝቀዝ ያለ ቢራ ይዛ መጥታ ከፍታ ሰጠችኝና እዛው አጠገቤ ቁጭ አለች።
"እንዴት ነበር የሄድክበት ፕሮግራም ኤፍዬ መች መጣህ ?"
"አሪፍ ነበር ገንዬ በጥዋት ነው የመጣሁት ገብቼ ተኛሁ"
"ኪያ ክከትናንት ወዲያ መጥተህ መሄድህን ሲያውቅ ቆሌው ነው የተገፈፈው ••••" ብላ ልትቀጥል ስትል
"እንኳን ቆሌው ቆዳውም ይገፈፍ አይመለከተኝም በናትሽ ገንዬ በዚህ ርእስ ላይ የማውራት ፍላጎቱ የለኝም ሌላ ነገር እናውራ ከይቅርታ ጋር" አልኳት።
"ውይ እንደዚህማ አታምርር ኤፍዬ ደሞ ቀሽት ያዱገነት ችክ መያዝህን ነግሮኛል" እያለችኝ ሌላ ሰው ለማስተናገድ ተነስታ ሄደች ። መልስ አልሰጠኋትም።
ትንሽ ቆይቶ ኪያ እራሱ መጣ ሱቁ በር አከባቢ እስኪደርስ መኖሬን ስላላስተዋለ እንዳየኝ እንደመደንገጥ አለና
"አማን ነው ኤፏ የት ሄደህ ነው እህትህ ትናንት ካንድም ሁለቴ መጥታ አጣችህ ስልክህን ዘግተህ የት ጠፍተህ ነው?"
"የትም" አልኩት። ዝም አለ ።
ለህቴ ሳልነግራት መሄዴ ልክ እንዳልነበር እያሰብኩ አሁን ብሄድ ባለቤቷ እቤት ስለሚሆን እሱ ደሞ ለኔ ካለው ጥሩ አመለካካት የተነሳ እንድትናገረኝ ስለማይፈልግ እሱ ፊት ብዙ አትበሳጫጭብኝም አሁኑኑ ሄጄ ብገላገል ይሻላል አልኩና ተነስቼ ወደ እህቴ ቤት ሄድኩ።
ስገባ ባሌቤቷ እቤት የለም።
"ቁጭ በል" አለችኝ ። ቁጭ አልኩ። የታላቅነቷን ትንሽ ቆጣ ቆጣ አለችና ወድያው ቀዝቀዝ ብላ እራት እንድበላ እያቀረበችልኝ
"ኤፍዬ እቁቡን ችላ አትበለው እንጂ፣ ቆይ ባጃጅ ሹፌር ሆነህ መቅረት የምትፈልገው? እስካሁን ስምንት ወር ጥለኻል የቀረህ አራት ወር ብቻ ነው። እኔ እቁብ ጥለህ ባጃጁ የተገዛበትን ሂሳብ ለኔ ትመልሳለህ ያልኩህ ሆን ብዬ ነው። ላንተው መሻሻል ነው ጭንቀቴ እንደምንም ብለህ ጨርስ። ከዛ ሀሀረር ያለውን የአያቶቻችንን ቤት •••"
ስትል አቋረጥኳት።
"እታለም እንሸጠዋለን ልትይኝ ባላሆነ ? ተይ መሸጥ በሚባል ነገር እኔ አልስማማም እንዲሁ እየተከራየ ቢቆይ ይሻላል ። መሻሻል ካለብኝም በራሴ ደክሜ በማመጣው እንጂ በመሸጥ መሆን የለበትም"
"እስቲ መጀመሪያ እኔን አስጨርሰኝ እኔም ሙሉ በሙሉ ቤቱን እንሽጠው አላልኩም ። ግቢው ሰፊ ነው አምስት መቶ ካሬ ሜትር ስለሆነ ሁለት መቶ ሀምሳውን ከፍለን ባዶ መሬቱን ብቻ በመሸጥ ከእቁቡ ጋር ቀላቅለን የሚበቃ ከሆነ ሚኒባስ ገዝተህ ሀረር ድሬ መስመር እንድትሰራ ነው ያሰብኩት። ካልበቃ እኔ እጨምርልሀለሁ የሚተርፍህ ከሆነ ደግሞ ጎሮ አነስ ያለች ቦታ ገዝተህ ቀስ በቀስ ጎጆህን ትቀልሳለህ" አለችኝ። በእህቴ ሀሳብ በጣም ደስ አለኝ። ከሀረር መልስ የ…
Read in full →❤10👍7
2 · 763 · አ
"ጭራሽ ብሶበት እየተንቀለቀለ ነው"ስለው አስቀያሚ ፈገግታ ከንፈሩን ወደ ጎን ለጥጦ ፈገግ ይልና፡
" ለማንኛውም በረድ ቀዝቀዝ ማለቱ ጥሩ ነው የተንቀለቀለን ነገር በቀላሉ ማጥፋት ከባድ ነው"ይላል። ዝም ብለውም ሲደጋገም
"ሁሌም እንዲህ ትላለህ ኪያ ቆይ ምን ልትለኝ እየሞከርክ ነው?••••
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose👍10❤3
862 · Mitiku 👁
🚂 ሁሉም ሰው የራሱ ታሪክ አለው! ❤️
📖 አንድ አስተማሪ ታሪክ...
አንድ የ24 ዓመት ወጣት ከአባቱ ጋር በባቡር እየተጓዘ ነበር ከመስኮቱ ወደ ውጭ እየተመለከተ በታላቅ ደስታ ጮኸ
🗣️ «አባባ! ተመልከት! ዛፎቹ ወደ ኋላ እየሮጡ ነው!»
አባቱም በፍቅር ፈገግ አለ።
በአጠገባቸው የተቀመጡ አንድ ወጣት ባልና ሚስት ግን ይህን ሲመለከቱ በመገረም ተያዩ። የ24 ዓመት ወጣት እንደ ትንሽ ልጅ መደሰቱ እንግዳ መሰላቸው።
ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወጣቱ እንደገና በደስታ ጮኸ
🗣️ «አባባ! ተመልከት! ደመናዎቹም ከእኛ ጋር አብረው እየሮጡ ነው!» ☁️
ባልና ሚስቱ መታገስ አቃታቸው። ወደ አዛውንቱ አባት ቀርበው
«ለምን ልጅዎን ጥሩ ዶክተር ጋር አይወስዱትም? እንደዚህ ያለ ባህሪ ለምን ያሳያል?» ብለው ጠየቁት
አዛውንቱ አባት በረጋ መንፈስ ፈገግ አሉና እንዲህ አሏቸው
💔«ዶክተር ጋር ወስጄው እኮ አሁን ነው የምንመጣው ልጄ ከተወለደ ጀምሮ ዓይነ ስውር ነበር። ዛሬ ግን ማየት የሚያስችሉትን ዓይኖች አግኝቷል»
😢 እነዚያ ባልና ሚስት የወጣቱን ባህሪ ከመፍረዳቸው በፊት ማወቅ የነበረባቸው ታሪክ ይህ ነበር!
📌 የሕይወት ትምህርት ❤️
በዚህች ዓለም ላይ የምታየው ሁሉ እውነት ሙሉ ምስል አይደለም።
እያንዳንዱ ሰው የራሱ የሆነ ታሪክ የማናውቀው ሕመም የማንረዳው ትግልና የማይታይ ስሜት አለው
❌ ከማወቅህ በፊት አትፍረድ!
❌ ከመረዳትህ በፊት አትተች!
❌ የሰውን ሁኔታ በላይ ላዩ ብቻ አይተህ የሕይወቱን ታሪክ እንደምታውቅ አታስብ!
✅ በምትችለው መጠን ሌሎችን ለመረዳት ጥረት አድርግ።
✅ በፍርድ ፈንታ ርኅራኄን፣ በትችት ፈንታ ደግነትን ምረጥ።
ምክንያቱም አንተ/ቺ የምታየው የሰውን ባህሪ ብቻ ነው፤ እሱ ግን የራሱን ታሪክ በሙሉ ያውቃል!
🔄ይህን መልዕክት ለወዳጅ ዘመደዎ ያጋሩ!
@atronosee👍1👏1
22 · #ባለ_ጭንብሉ
፡
፡
#ክፍል_አምስት
፡
፡
ሲፈን የዶክተሩን በር አንኳክታ ገባች ሰላም ብሎ እንድትቀመጥ ጋበዛት ሲፈን ተቀመጠች እና ዶክተሩን ምን ይሻላል በሚል አይነት ታስተውለው ጀመር
"ሲፈን ያው በቃ እንደነገርኩሽ ነው ምን ያህል እንደተጎዳ እኔም አንቺም እንዲሁ በግልፅ አይተናል ከሞት ለማትረፍ የተቻለንን ጥረት አድርገን እንዳየሺው ተሳክቶልን ሙሉ በሙሉ ጤንነቱን መልሰነዋል ነገር ግን በደብደባው ከባድነት የተነሳ የማስታወስ ችሎታውን ለጊዜው አቷል ምን አልባት ወደፊት የሚፈጠረው አይታወቅም ለጊዜው ግን ይሄንን ነው ያየነው አይዞሽ አትጨነቂ የሚፈጠረው አይታወቅም!"አለ ዶክተሩ
"ዶክተር በጣም ይከብዳል ብዙ የማታውቀው ነገረ አለ!"ብላ ደንገጥ አለች ለዶክተሩ የነገረችው በጣም ጓደኞች እንደሆኑና ምንም አይነት ቤተሰብ እንደሌለው ነው እሱም ብዙ አልተጫናትም
"ምንድነው የማላውቀው ሲፈን?"አለ ዶክተሩ
"አይ ማማለቴ እኔ በጣም እወደዋለው ሊረሳኝ አይገባም ፡"አለች
"ሲፈን ካጠገቡ ሳትርቂ ሁሌም ካገኘሽ ይላመድሻል "
"ግን "አለች ሲፈን ተወችው
"ይልቅ አሁን ሙሉ በሙሉ ስለነቃ ነይ ሄደን አብረን እንየው" ብሎ አስነስቷት አብረው ወደ ባለጭንብሉ ወጣት የተኛበት ክፍል ሄዱ ከክፍሉ ሲደርሱ ወጣቱ አዳም አልጋው ጫፍ ላይ ግራ በመጋባት ተቀምጧል፡
ዶክተሩ እንዳየው
"አሃ ነቅተሃል እንዴ?" አለው ለሰላምታ እጁን እየዘረጋለት
"አዎ ግን ምንድነው !ምን ሆኜ ነው እኔ ምንም ማስታወስ አልቻልኩም ፡ምንም ምንም !"አለ በጭንቀት ተወጥሮ
ሲፈን ጨነቃት ግራ ግብት አላት እኔ ነኝ የማውቀው ጓደኛው ብላለች ነገር ግን ስሙን እንኳ በጭራሽ አታውቀውም፡ የምታውቀውንስ እንዴት ብላ ትንገረው፡አንተ እቤታችን በውድቅት ለሊት ለመዝረፍ መጥተህ እኔንም የመድፈር ሙከራ አድርገህብኝ ነበር ከዛ ቤተሰቦቼ ያዙህ ከዛ አባቴ መጋዘን ውስጥ ቆልፎብህ ሲያስደበድብህ የማስታወስ ችሎታህን አጣህ፡ እያልኩ ነው የማቀውን የምነግረው ኧረ የማይሆነውን አለች
"አይዞህ ተረጋጋ የሆኑ ሰዎች የድብደባ ጥቃት አድርሰውብህ እሷ ናት ይዛህ የመጣችው "
"አሃ ማናቸው እና አልተያዙም በጭራሽ ምንም አላስታውስም ምንድነው ያረጉኝ ፡ "አለ አዳም በጭንቀት
"ያው ማጅራት መቺ ይሆናሉ ምንም አይነት መረጃ ከኪስህ ውስጥ አላገኘንም እንግዲ ሌቦች ቢሆኑ ነው ምንም ሳያስቀሩ የወሰዱብህ እንግዲ እሷ ስታገኝህ በደም ተጨማልቀህ እራስህን ስተህ ነበር ያው ባጋጣሚ የሁለታችሁም ጓደኛ የሆነ ሰው ነው እዛው ሰፈር አካባቢ ጠርቷት ያገኘችህና ይዛህ የመጣችው፡!!"
አለው ዶክተሩ ሲፈን የነገረችውን እያስታወሰ፡ ባለ ጭንብሉ ግራ ቢገባውም ይህችን የመሰለች ጓደኛ ስላለው አመሰገነ በቃ እሷ ስለኔ ካወቀች ቤቴ ትወስደኛለች ብሎ አሰበ መልሶ በውስጡ እንዴ ቤቴን አውቀዋለው አለ የቤቱ ስህል መጣለትና መልሶ ጠፋበት ወደ ሲፈን ተመለከተ በጣም ቆንጆ ናት የት ነው የማውቃት ጓደኝነታችን እስከምን ድረስ ይሆን፡ምንም ትዝ ሊለኝ አልቻለም
"ሲፈን ነው ስምሽ ?"
"አዎ ሲፈን ይፍሩ"
"እሺ ሲፈን ግን የት ነው የማውቅሽ?"
"ያው እንደ ማንኛውም ትውውቅ ነው የመጀመሪያ ትውውቃችን"አለች ሲፈን በገዛ እጇ አጣብቂኝ ውስጥ ገባች፡
"ማለት ?"
"ማለት ያው አንተ ነህ መተህ የተዋወከኝ ካፌ ውስጥ ቁጭ ብዬ"አለች እንደመጣላት
ባለጭንብሉ አዳም ግራ ተጋባ ስለዚህም ትውስታውን ማምጣት አቃተው በጭራሽ አላስታወሰም በጣም ተናደደ አንዴት አንድ ነገር እንኳ አያስታውስም
"ዶክተር እባክህ በደንብ አክመኝ እና ከውጥረት ገላግለኝ !"አለ
"ስም…
Read in full → 43 · "ሰላም ነው ሲፈኔ በስራ ጉዳይ የማወራው ሰው አለ ወደዚያው ነኝ!"ብለው ፈጠን ብለው ሄዱ ሲፈን በረንዳው ላይ እንደቆመች፡ከግቢ እስኪወጡ ሸኘች እና ወደሳሎን ተመለሰች በውስጧ ብዙ ብዙ ነገር አመላለሰች የአባቷን ስራ የክንዴን ስራ የባለ ጭንብሉ ሁኔታ፡ሁሉም ነገር እንደ ትርሂት አይምሮዋ ውስጥ ተመላለሰ ምን ሆኖ ይሆን ሆስፒታል ውስጥ ግራ በመጋባት ተጨንቆ ተኝቶ ይሆን ፡የእክምናውን ወጪ ብከፍልም፡አንዳች ሳንቲም አልተውኩለትም ከሐኪም ቤት ቢያስወጡት ምን ይበላል ምንአይነት ሰው ነኝ ግን ምን አገባኝ ቅጣቱ ነው እንደውም እረድቼዋለው አይመለከተኝም እንዴዴዴዴ ትላለች በውስጧ ከራሷ ጋር እየተሟገተች፡
አቶ ይፍሩ ጓደኛቸው ይርጋን ቤታቸው ድረስ በመሄድ አገኟቸው በጣም ተናደዋል ብስጭታቸውን እንደደረሱ ነበር የዘረገፉት
"እንዴ ሰማህልኝ እኔ ሰሞኑን ሁሉ እንዴት ብለው ነው ልጁም ክንዴም ከመጋዘኑ የወጡት ምን አልባት ልጁን የላከው ሰው ይሆናል ይዞአቸው የተሰወረው እላለው፡ለካንስ እራሱ ክንዴ ነው ልጁን ይዞ ያመለጠው ይሄ ውሻ!"አሉ አዲሱ ዘበኛ የነገራቸውን አስታውሰው
"ማነገረህ ደሞ!"አሉ ይርጋ ግራ ተጋብተው
"ዘበኛው ሲሳይ!"
"ቆይ ቆይ እንዴት እንዴት ነው ነገሩ እስከዛሬ አልነገረህም ነው?!"አሉ ይርጋ በጥርጣሬ
"እህ ዝምብዬ ሳባብለው ነዋ በርግጥ አይቻለው በጓሮ በኩል ሲወጡ ነገር ግን ስለዛ በር የማውቀው ነገር አልነበረም የኛ ቤት አካል መሆኑን እንኳ ያወኩት ጊዜው ካለፈ በዋላነው ነገርግን አንድሰው ሌላውን ሰው ደግፎት ሲወጣ አይቻለውአለኝ!"
"አይገርምም እኔ አዲሱን ዘበኛ ጠርጥሬዋለው አባሪ እንዳይሆን!"አሉ ይርጋ
"እሺ አሁን ወደዋናው ጉዳይ ግባ የሱፍ እጁ አለበት ነበር ያልከኝ ምንድነው አልገባኝም ልታስደንቀኝ ነው ወይስ የሱፍ ከምር ከድቶናል ነው የምትል?!"
"አዎ አልኩህ ልጁ ባለጭንብሉ የአብዲ ጓደኛነው አሉ አይለኛ ለያዥ ያስቸገረ ዱርዬ በስርቆት የሚተዳደር እና ዘረፋውን እንዲ ያካይድ በየሱፍና በአብዲ ነው የተመረጠው ሰሞኑን የራሴን ሰው የሱፍን እንዲከታተሉ መድቤ ነበር እናም እውነቱ ይህ መሆኑን ደረሱበት!"አሉ ይርጋ በውስጣቸው ያሴሩትን አቶ የሱፍን የመጣል ተንኮላቸውን እያደሩ አቶ የሱፍ በየዋህነት የነገሯቸውን የልጄ ስራ ነው ያባለጭንብል ልጅ ያን ያህል ሰው የሚጎዳ አይደለም ገንዘብ ስላስፈለገው ብቻ ነው እንደው ለይፍሩ እንዴት እንደማስረዳው አላውቅም እስኪ አንተ አግዘኝ ብለው አማክረዋቸው ነበር አቶ የሱፍ ነገር ግን አቶ ይርጋ በዚህ አጋጣሚ አንዱን በአንዱ የመጣል ምኞታቸውን ለማሳካት ይፍሩን በየሱፍ ላይ አስነሱ አቶ ይፍሩ የበለጠ አበዱ በየሱፍ ላይም ዛቱ ብዙ ብዙ መከሩ ካቶ ይርጋ ጋር የሱፍን ለማጥፋት እገድለዋለው ይሄ ከሃዲ ..ሞት ባቶ የሱፍ ቤት ማንጃበብ ጀመረ..
======
አዳም ከቤቱ ወቶ ከቀረ አንድ ወር ሆነው እትዬ ፅጌ በልጃቸው አለመመለስ ምክንያት እንባቸው ፈሶ ፈሶ ያለቀ ይመስል በእንባቸው ፈንታ ብቻቸውን እያወሩ ወዲያ ወዲ ማለቱን ጀምረዋል በጠዋት ተነስተው የት እንደሚሄዱ ሳይናገሩ ወደ አመሻሹ ላይ ግርጥት ጉስቁል እንዳሉ ደካክመው ይመለሳሉ የቤቱን ስራ ኤዶም ሆኗል የሚሰራው አባትም በጠዋት ተነስተው፡ቤተክርስቲያን በመሄድ ልጃቸው እንዲመለስላቸው ለፈጣሪያቸው፡ልመናና ፀሎታቸውን አድርሰው፡ወደስራቸው ይሄዳሉ ኤዶም በተስፋ የወንድሙን መገኘት ያልማል ከዛም በላይ ደሞ የእናቱ ሁኔታ አሳስቦታል ወይኔ እማማ ሁሌም በኛ ምክንያት እንደ ፈንዲሻ ፍክት እንዳለች ነበር አሁን ግን ፊቷ የቀይ ጥቁር ሆኗል ሲቆይ ከዚም በላይ መሆንዋም አይቀር ይላል በጣም ፈርቷል ስለ እናቱ እማ ይበቃል…
Read in full → 43 · አ
፡እንዴት ክንዴ ልጁን ለማስመለጥ ሲል ከይፍሩ ጋር ይጣላል እንጃ ብቻ ይፍሩ የደበቀን ነገር ሳይኖር አይቀርም!"አሉ በማነሳሳት አቶይርጋ፡የሱፍ ጨነቃቸው አይደረግም የሰውን ልጅ አይን እያየ መግደል ኧረ አይደረግም፡ ይፍሩ ወይ እስካሁን እንደያዘው ይሆናል እንጂ መግደል አያደርገውም እንዴት ሰው በሰው ላይ ሊጨክን ይቻለዋል ሌላውስ ሌላ ነው ነብስ ማጥፋት ኧረ ኧረ...... !
✨ይቀጥላል✨
#Share #like and #subscribe እያደረጋቹ።
👇Sebscribe
YouTube link👇
https://www.youtube.com/@atronose👏1
32 · አትሮኖስ
📝 የኮሌጁ አስተማሪ
አንድ ቀን ምሽት አራት የኮሌጅ ተማሪዎች ሌሊቱን ሙሉ ሲጨፍሩና ሲዝናኑ አደሩ። በማግስቱ የሚወስዱትን ከባድ ፈተና ግምት ውስጥ ሳያስገቡ ምንም ሳይማሩ ቀሩ። ጠዋት ላይ ከፈተናው ለማምለጥ አንድ እቅድ አወጡ።
ገላቸውንና ልብሳቸውን በጭቃና በቆሻሻ አቆሸሹና ቀጥታ ወደ አሰማሪያቸው ቢሮ ሄዱ። አስተማሪውን አግኝተው "ጌታዬ፣ ትናንት ማታ ወደ አንድ ሰርግ ሄደን ስንመለስ የመኪናችን ጎማ ተንፍሶብን መኪናውን እስከ ግቢ ድረስ እየገፋን ስንመጣ ነው እንዲህ የቆሸሸነው፤ ለፈተናው አልተዘጋጀንም" አሉት።
አስተማሪውም ታሪካቸውን በጥንቃቄ ካዳመጠ በኋላ አሰበበት። ከዚያም ከሶስት ቀናት በኋላ ልዩ የድጋሚ ፈተና እንደሚሰጣቸው ቃል ገባላቸው። ተማሪዎቹም በጣም ደስ ብሏቸው አመስግነውት ወጡ። በነዚህ ሶስት ቀናት ውስጥ በደንብ አጥንተው ተዘጋጁ።
በፈተናው ቀን ወደ አስተማሪው ቢሮ መጡ። አስተማሪው ግን አራቱንም ተማሪዎች በተለያዩ አራት ክፍሎች ውስጥ ለየብቻቸው አስቀመጣቸው። ተማሪዎቹ በደንብ ስላጠኑ በዚህ አልተደናገጡም ነበር። ነገር ግን ፈተናውን ሲያዩት ደነገጡ። ፈተናው የያዘው ሁለት ጥያቄዎችን ብቻ ነበር፦
1- ያንተ ስም፡ ___ (1 ነጥብ)
2- ትናንት ማታ የፈነዳው የትኛው የመኪና ጎማ ነው? __ (99 ነጥብ)
አማራጮች፦
(ሀ) የፊት የግራ
(ለ) የፊት የቀኝ
(ሐ) የኋላ የግራ
(መ) የኋላ የቀኝ
📌 የሕይወት ስንቅ
ሁልጊዜ ለድርጊትህ ተጠያቂ ሁን፤ ውሸት ለአጭር ጊዜ ሊያስመልጥህ ቢችልም በመጨረሻ ግን ያጋልጥሃል።
🔄ለወዳጅ ዘመድዎ ያጋሩ
@atronosee👍2
32 · #ባለ_ጭንብሉ
፡
፡
#ክፍል_ስድስት
፡
፡
አዳም የዶክተሩ ቤት መኖር ከጀመረ ሳምንት አለፈው ግራ እንደተጋባ ከግቢው አልፎ ሳይወጣ እራሱን ለማግኘት ደጋግሞ ወደ ውስጡ ወደ አእምሮው ፍተሻ ያደርጋል የሆነ ነገር ብልጭ ይልለትና ድርግም ይልበታል በተለይ ደግሞ ስለራሴ እንዳውቅ ትረዳኛለች ብሎ ተስፋ የጣለባት ሲፈን ወደቤትህ እወስድሃለው መጣው ብላው ስሙን እንኳ ሳትነግረው ጥላው መጥፋቷ የበለጠ አስገርሞታልም፡እንዲጠራጠራትም አድርጎታል ስለድብደባው፡በደንብ ታውቅ ይሆናል ያለምክንያትማ ትታኝ አትሄድም ነበር እያለ ያስባል ዶክተሩንም ያስቸገረ እየመሰለው ተሳቋል እስከመቼ ነው ደክተሩን የሙጥኝ ብዬ የምኖረው፡ ምን ይሻላል ይላል
"አሃ ጓደኛዬ እዚ ነህ እንዴ?"
.. "አዎ ዶክተር መስፍን ጨረስክ እንዳልረብሽህ ብዬ ነው!"..
"ኧረ ምን ትረብሸኛለህ መፀሐፍ አታነብም ነበር እንዳይደብርህ?"...
"እስኪ እሞክራለው ትኩረቴን አንድ ቦታ መሰብሰብ ስላቃተኝ እኮ ነው፡ እኔ የምልህ ዶክተር ልጅቷ አሁንም ስልክ አታነሳም?"
"አዎ ባክህ ስልኳ በመጥራቱ እንዲያ እንዳልተደሰትኩ አለመነሳቱ ደሞ በጣም እያናደደኝ ነው ያው እንግዲ በዚው ከቀጠለች ፍለጋ እንወጣለን፡ አይመስልህም?!"
"መሆን አለበት፡የእውነት ጓደኛዬ ከሆነች ጭካኔዋ ያሳዝነኛል በሌላ በኩል እኔን የደበደብኝ ሰዎች ወስደዋትም እንዳይሆን እፈራለው !"አለ አዳም ባለጭንብሉ ተጨንቆ
"አይዞ ጓደኛዬ መምጣቷ አይቀርም፡አንድ የምትደብቀው ነገር እንዳላት ግን እኔም ጠርጥሬያለው ግን እሱን ጊዜ ይፈታዋል፡ "አለ ዶክተሩ የልጁ ሁኔታ እያሳሰበው፡ የሆነ ሰአት ላይ እንደሚያስታውስ ያውቃል ግን መቼ....
ልጅቷስ ...ሲፈንስ ...ምን አጠፋት...?
===
ሊያ የሲፈን ታናሽ እህት ናት ትንሽ አስቸጋሪ ልጅ ናት አቶ ይፍሩ በስተመጨረሻ ቀበጥ ልጅ ሰጠሺኝ ይሏቸዋል ሁልጊዜ ሊያ ስታጠፋ ባለቤታቸውን ሊያ አጥፍታ ትስቃለች ሲቆጧት እንዲሁ የተቆጪዋን እንቅስቃሴ በማየት ብቻ ትስቃለች እህቶቿ ሊያ ድክሞ ይሏታል ምክንያቱም ሰው ማድከም ነው ስራዋ ትንሽ የሲፈን ኀይለኝነት ብቻ ነው ሊያን የሚያሳስባት በተረፈ ማንም ገፍቶ እንደማይጨክንባት ታውቃለች ዛሬም በርቀት የሲፈንን መኪና ስታያት ይሸኛት የነበረውን ጎረምሳ ልጅ፡
"በቃ ቻው፡ባላየ ዝም ብለህ ንካው፡ቻዎ ቻዎ!"ብላው ወደ ግቢው በር በፍጥነት ተጠጋች፡
ልጁ ምንድነው ችግሩ አንሳምም እንዴ ቢያንስ የሽኝት ክፍያ !"ብሎ እነደመሳቅ እያለ ተጠጋት"አፈር ብላ ዳኒ ሲስተር መጣች ሂድ፡!"አለችው ልጁ እየገረመው ገልመጥ ገልመጥ እያለ ወደፊት ሄደ በዚ መሃል ሲፈን ደረሰች፡ሊያ ለዘበኛው ሲሳይ በር እንዲከፍት ነግራው፡ወደ ቤት ገባች ሳሎን ሁለቱ እህቶቿ እና እናቷ ተቀምጠው እያወሩ ደረሰች እናቷን ቅብጥብጥ እንደማለት ብላ ስማ አጠገባቸው ተቀመጠች ተከትላ ሲፈን ገባች ሁሉንም ሰላም ብላ ቁጭ ካለች በዋላ ወደ ሊያ እያየች ቆየች
"ምንድነው ሲፍ ሊያ ናፍቃሽ ነው፡ወይስ ያደረገችው ነገር አለ ቸክለሽ አጠናሻት እኮ "?!አለች ራሔል
እንደመቀለድም እንደመጠየቅም ብላ...
"አይ እንግዲ ይሄን ንትርክ እንዳጀምሩኝ!"አሉ እናት...
"አይ እማ !አይ በማለት ነገሮች የሚቆሙ ቢሆን እንዴት ጥሩ ነበር !"ብላ እሮዛ እንደመሳቅ አለች.... "እንዴ እዚቤት ሁልጊዜ የግጥማቹ እርህስ የምታደርጉኝ ለምንድነው ኧረ ላሽ አንዳንዴ ከኔ ላይ!"አለች ሊያ እጇን በቄንጥ እያወናጨፈች ሲፈን ብልጭ አለባት
"አንቺ ክፍት አፍ ስነስርሃት ይኑርሽ ጨምላቃ ነይ እንደውም የምትነግሪኝ ነገር አለ ብቻችንን ተነሽ!…
Read in full →👍1
47 · አ
ሲፈን በጠዋት ተነስታ ሳሎን ውስጥ ከወዲያ ወዲ እያለች ትንጎራደዳለች፡ለባለጭንብሉ ፡እንዴት፡አድርጋ በማይጎዳው መልኩ ማንነቱን እንደምትነግረው እያሰበች ነው፡ ሲሰማስ ምን ይል ይሆን፡ጨርሶ ውሸት ነው ብሎ ይከራከር ይሆን ወይስ በራሱ አፍሮ ብር ብሎ ይጠፋ ይሆን እንጃ
"ሲፍ ልትወጪ ነው?" ሮዛ ነበረች መሀል ላይ ቆማ ስታያት
"አዎ ምነው?"አለች ሲፈን
"አይ የሆነ የምደርስበት ቦታ ነበረኝ ከወጣሽ እግረመንገድሽን እንድትሸኚኝ ብዬ ነው ከተመቸሽ?!"
"ይቻላል ግን መኪናሽስ ?ወደሱቅስ አቴጅም?"
"መኪናዬ ገራጅ ናት አጉል ፀባይ አምጥታለች ሱቅ እገባለው ቅድሚያ ጉዳይ አለኝ፡ይመችሻል?"
"እሺ የዚቤት ጉዳይ አያልቅ፡መቼም ሁሉም ሰው ሚስጢር አለው!"ብላ ሲፈን ቦርሳዋን አንስታ ወጣች
"እንዴ ፍጥነት ቆይ ጠብቂኝ ማሚን ደናዋይ ልበላት እንዴ!"አለች እሮዛ
"ሞተር እስከማሞቅ ነው ደግመሽ ተኝተሽ ልትነሺ ነው?!" አለቺ ሲፈን ደረጃውን እየወረደች
"አይይይ እዚቤት ታላቅ ታናሽ የለ የት ሄጄ ልከበር !"እያለች እያሾፈች ወደናቷ ክፍል ገበች እናም እናቷን ትንሽ አውርታ መልካም ቀን ብላቸው፡ወደሲፈን ተመለሰች
==============
ኤዶም በእናቱ ዝምታ ተጨንቋል፡አንድ ነገር ብትናገር ነው የሚሻለው ከዝምታዋስ ምስኪን እናቴ አዳም በጣም እንደሚናፍቃት አውቃለው ግን ምን ማድረግ እችላለው እኔ በመልክ ብመስለውም የሱን ያህል በጭራሽ ልሆንላት እንደማልችል ከድሮም አውቀዋለው፡እማ ፈጣሪ፡ይርዳሽ፡እንጂ ፡ምን ይባላል !ይላል እናቱን በስስት እያየ ፡እናት ከተቀመጡበት፡ ሆነው ሲቆዝሙ ቆዩና ድንገት ተነስተው ቆሙ ኤዶም አብሮ ብድግ አለ
"ኤዶሜ የኔ ዓለም አይዞ አትጨነቅ ቤተክርስቲያን ሄጄ ተሳልሜ ልመጣ ፈልጌ ነው ነጠላዬን አቀብለኝ!?"አሉ የኤዶምን ጉንጭ እየነካኩ
"እሺ እማ ጥሩ ነው እኔም ልምጣ?"
"አይ አይ አንተ በኋላ ትሄዳለህ እዚው ሁን ምን እንደሚፈጠር አይታወቅም !"አሉ እትዬ ፅጌ ነጠላቸውን እየለበሱ
"እሺ ካልሽ እናቴ እራስሽን ጠብቂ !"ብሎ ጉንጫቸውን ሳም እቅፍ አደረጋቸው እማ አንቺ አንድ ነገር ከሆንሽ ምን እንደምሆን አላውቅም እንጃ አለ በውስጡ ኤዶም ስለ እናቱ...
======
አቶ ይፍሩ ከአቶ ይርጋ ጋር ምክር ይዘዋል የከዳቸውን እና ሊጎዳቸው ያሴረውን ሰው ለመበቀል ቋምጠዋል የእንዴት ተደፈርኩ ቁጭት አንገብግቧቸዋል እንዴት ባጎረስኩ ተካፍለን እንብላ ባልኩ ስንት ነገሬን በግልፅ ባሳየው እንደ እራሴ ቤተሰብ ባየወሸ፡ጓዳ ጎድጓዳዬን ባስጎበኘው እኔ ላይ እኔ ላይ ወንበዴ መላክ ቱ !እኔ ይፍሩ አደለውም ከቅዳሜ በዋላ እቺን አየር ከተነፈስክ አላወከኝም፡የቆረትኩ ለት ምንም እንደማይመልሰኝ!እያሉ ምንም በማያውቁት አቶ የሱፍ ላይ አምርረው ይዝታሉ በተቀመጡበት ሆነው አልፎ አልፎ ጠረቤዛውን ይመታሉ አቶ ይርጋ የሸረቡት ሴራ ግቡን እንደመታ ስላወቁ ውስጥ ውስጡን ተደስተዋል፡የሱፍ ድሮም ፡ከኛጋር ስራ የሚሰራም ሰው አልነበረም እንዳው ያገኘነውን ውሰድብን ብሎ ከመጥራት በስተቀር ምን የሚፈይደው ነገር አለ አጉል የጓደኝነት ስምምነት ይዞን እንጂ እሱ ጋር ያን ሁሉ እቃ እያመጣን ስናስገባ የተለየ አድርጎ እራሱን መቁጠር ጀመረ ከፈለግን እንደሱ አይነት መጋዘን ማዘጋጀት ለኛ ቀላል ነው እንካ በእንካ ነው ጨዋታው ይሄ መች ከብዶ!እያሉ ላቶ ይፍሩ ተጨማሪ፡ተንኮል እየነገሩ ማነሳሳቱን፡ገፍተውበታል።
"አሁን እኔ የምልህ ሰዎችህን አዘጋጅተሃል፡?"አሉ ይፍሩ ኮስተር እንዳሉ
"አዎ ሁሉም ተዘጋጅተዋል!"
" ይርጋ፡ምን ማለት ነው ሁሉም?ለአንድ ኮስማና አንድ ባታሊዮን ጦር ልትመድብ ነው እንዴ?!"አሉ በመገረም
" አይ …
Read in full →👍1
51 ·
An open public feed from the search index
ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled.
Times are UTC.
Public content only, official Telegram API.
About ·
FAQ ·
Index limits ·
Remove a page ·
Catalog ·
Search ·
How we count