English
Open in Telegram
ደደግነት በጎ አድራጎት ማኅበር

ደግነት በጎ አድራጎት ማኅበር

@degnitKindness · channel · Education · indexed since 2026-07-12
33 930subscribers
123average post reach
0.4%ER — reach to subscribers
106posts in 30 days
ደ
ደግነት በጎ አድራጎት ማኅበር
Photo
Photo
Photo
🥰2
123 ·
ደግነት በጎ አድራጎት ማኅበር
#ጥቅምት_9 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥቅምት ዘጠኝ በዚህች ዕለት #የአባ_ሊዋርዮስ እና #የአቡነ_አትናስዮስ እረፍታቸው ነው፣ በዲዮቅልጢያኖ ዘመን የመጀመሪያ የሆነው ሰማዕት #ቅዱስ_እስጢፋኖስ_ዘአንጾኪያ በሰማዕትነት አረፈ፤ #ሐዋርያው_ቅዱስ_ቶማስ በሕንድ አገር ድንቅ ተአምር ያደረገበትም ዕለት ነው ዳግመኛም ኢትዮጵያዊው ጻድቁ #አቡነ_መዝገበ_ሥላሴ እረፍታቸው ነው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ሊቀ_ጳጳሳት_ቅዱስ_ሊዋርዮስ በዚች ቀን ቅዱስ አባት የሮሜ አገር ሊቀ ጳጳሳት ሊዋርዮስ አረፈ። ይህም ዕውነተኛ ደግ ንጹሕ የሆነ ሰው በታናሽነቱ መንኲሶ የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት እየተማረ በቤተክርስቲያን ግቢ አደገ። በሮሜ አገርም በሐዋርያት አለቃ በጴጥሮስ ወንበር ላይ ሊቀ ጳጳሳት ሊሆን መርጠው ሾሙት። በጎ መንገድንም በመጓዝ እግዚአብሔርን አገለገለው ሕዝቡን አዘውትሮ ያስተምራቸው ነበርና ከእግዚአብሔርም ሕግና ትእዛዝ የተላለፉትን መክሮ ገሥጾ ወደ እግዚአብሔር ሕግ ይመልሳቸው ነበርና። ታናሹ ቁስጠንጢኖስም በሞተ ጊዜ ከሀ*ዲው ዑልያኖስ ነገሠ እግዚአብሔርም እስከ አጠፋው ድረስ የክርስቲያንን ወገኖች አሠቃያቸው። ይህም ዑልያኖስ ለቈስጠንጢኖስ የአባቱ እኅት ልጅ ነው መንግሥትንም በያዘ ጊዜ የጣዖታትን ቤቶች በመክፈት የክርስቲያንን ወገኖች ሁሉ አሠቃያቸው። ይህ አባት ሊዋርዮስም ከሮሜ አገር ወደ ቂሣርያ መጣ ከቅዱስ ባስልዮስም ጋር ተገናኘ። ከታላቅ ስሕተቱና ከክህ*ደቱ መክረው ይመልሱት ዘንድ ወደ ንጉሥ ዑልያኖስ ለመሔድ ሁለቱ ተስማሙ። እነርሱ ከታናሽነታቸው ጀምረው እየተማሩ ከእርሱ ጋር በአንድነት ያደጉ ናቸውና። ከዚህም በኋላ ተነሥተው ሔዱ ንጉሥ ዑልያኖስም ወዳለበት ደርሰው ከፊቱ ቆሙ ከስሕተቱም በሚመልሱበት ሊናገሩት ወደው ሳለ እርሱ ቀድሞ በጌታችን ላይ በመሣለቅ ክብር ይግባውና የጠራቢውን ልጅ ወዴት ተዋችሁት አላቸው። ቅዱስ ባስልዮስም አንተን በሲኦል ይቀብሩህ ዘንድ ሣጥን ሊሠራልህ ተውነው ብሎ መለሰለት። በዚያንም ጊዜ በእነርሱ ላይ ተቆጥቶ በወህኒ ቤት እንዲያሥሰሯቸው አዘዘ። በዚያም የቅዱስ መርቆሬዎስን ሥዕሉን አግኝተው በፊቱ እያለቀሱ የክርስቶስ ምስክር ሆይ በክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ላይ የዚህን ከሀዲ መሣለቁን አትሰማምን ብለው ጸለዩ ይህንንም ሲጸልዩ ያን ጊዜ አንቀላፉ። አባ ሊዋርዮስም በእንቅልፉ ውስጥ ሳለ ቅዱስ መርቆሬዎስን ሰማይና ምድርን በፈጠረ በሕያው ፈጣሪዬ ላይ እንዲሣለቅ ይህን ከሀዲ በሕይወት አልተወውም ሲል በሕልሙ አየው። ከእንቅልፉ ነቅቶ ያየውን ለቅዱስ ባስልዮስ ነገረው በዚያንም ጊዜ ሥዕሉን ከቦታው አጡት እርሱ ዑልያኖስ ወዳለበት ሒዶአልና በጦርም ወግቶ ገደለው ወደ ቦታውም ተመልሶ ተሰቀለ ከጦሩ አንደበትም ደም ይንጠፈጠፍ ነበር። እሊህ ቅዱሳንም ይህን ድንቅ ሥራ በአዩ ጊዜ መፈራትንና ባለሟልነትን የተመላህ የኢየሱስ ክርስቶስ ምስክር ሆይ ዑልያኖስን ገደልከውን አሉ ። ያን ጊዜ አዎን እንደሚል ሥዕሉ ዘንበል አለ እሊህም ቅዱሳን ሊዋርዮስና ባስልዮስ ደስ አላቸው። ከዚህም በኋላ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያምን ዩማንዮስ ነገሠ እሊህንም ቅዱሳን ከእሥር ቤት አወጣቸውና ወደየቦታቸው ተመለሱ። ይህም አባት ሊዋርዮስ አርዮሳውያንን እጅግ ይጣላቸው ነበር። ከክርስቲያን ወገኖችም ለይቶ ያሳድዳቸዋል። መልካም ጒዞውንም ከፈጸመ በኋላ እግዚአብሔርን አገልግሎ በሰላም አረፈ። የሹመቱም ዘመን ሰባት ዓመት ነው። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ሊቀ_ጳጳሳት_ቅዱስ_አትናስዮስ በዚችም ቀን ዳግመኛ የከበረ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳ… Read in full →
49 ·
ምሥጢር ገለጸላቸው። በዚያን ጊዜ አባ አልመፍርያን ደነገጠ አክሊሉንም ከራሱ ላይ አውልቆ በምድር ላይ ወደቀ ለረጅም ጊዜ እንደ ሞተ ሆነ በተነሣም ጊዜ እንዲህ ብሎ ጮኸ ወንድሞቼ የማደርገውን እስቲ ንገሩኝ ዛሬ እሳት ከሰማይ ወርዶ እንዳያቃጥለኝ ምድርም አፍዋን ከፍታ እንዳትውጠኝ እፈራለሁና ጌታዬ የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት አትናስዮስ ውኃ እየቀዳ የፈረሶችና የበቅሎዎች ጉድፍ እየጠረገ በቤቴ ውስጥ እንደ ባርያ ሊአገለግል አግባብ ነውን ወዮልኝ ወዮልኝ። ጳጳሳቱና የተሰበሰቡት ሁሉ በሰሙ ጊዜ ከእግሩ በታች ወድቀው ሰገዱለት እጆቹንና እግሮቹንም ሳሙ ሊቀ ጳጳሱም ያማሩ የክህነት ልብሶችን ያለብሱት ዘንድ መስቀሎችንና አርዌ ብርቱን ያመጡ ዘንድ በመንበር ላይም ያስቀመጡት ዘንድ አዘዘ። ከዚያም በኋላ ጳጳሳቱ ከመንበሩ ጋር ተሸከሙት ሦስት ጊዜ አክዮስ አክዮስ አክዮስ እያሉ ይህም ይገባዋል ማለት ነው ቤተ ክርስቲያኑን አዙረው ወደ መቅደስ አስገቡት ። ከዚህም በኋላ መቀደሻ ልብስ ለብሶ መሥዋዕቱን አክብሮ ቀድሶ አቈረባቸው እነርሱንም ሀገራቸውንም ባረከ ለዚያችም አገር ምንኛ መጠን የሌለው ደስታ ሆነ ተባለ ። በማግሥቱም አባ እልመፍርያን ተነሥቶ በቅሎ አስመጣ ለጒዞ የሚያሻውን ሁሉ አዘጋጀ አባ አትናስዮስንም በበቅሎ አስቀምጦ እርሱ በእግሩ ተከተለው ጳጳሳቱና ኤጲስቆጶሳቱ ሁሉም ከአባ እልመፍርያን ጋር አጅበዉ ወደ አንጾኪያ አገር ወሰዱት አባት አትናስዮስም አባ እልመፍርያንን አንተም በበቅሎ ላይ ተቀመጥና በአንድነት እንሒድ አለው። አባ እልመፍርያንም ጌታዬ ለእኔ አይገባኝም አንተ በእግርህ ወደ አገሬ እንደመጣህ እንዲሁ እኔም በእግሬ ወደ አገርህ አደርስሃለሁ አለው። የአንጾኪያ አገር ጳጳሳትም የሊቀ ጳጳሳት አትናስዮስን መምጣት በሰሙ ጊዜ ከሕዝብ ሁሉ ጋር ሊቀበሉት ወጡ በታላቅም ክብር ተቀብለው ወደሹመቱ መንበር አስገቡት። ለአባ እልመፍርያንም ሁለተኛ ወንበር አድርገው በክብር አስቀመጡት በዚያችም ቀን ፈጽሞ ደስ አላቸው ተሰናብተውትም ወደ ሀገራቸው በፍቅር አንድነት ተመለሱ። ይህም አባት አትናስዮስ በጎ አኗኗርን ኖረ መንጋውንም በትክክል በእውነት ጠበቀ በጎ ጒዞውንም ፈጽሞ በሰላም አረፈ ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_እስጢፋኖስ_ካልዕ በዚችም ቀን በከሀዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን በአንጾኪያ አገር የሰማዕታት መጀመሪያ ሁኖ ሌላው እስጢፋኖስ በሰማዕትነት አረፈ ። ይህም የፋሲለደስ ወንድም ለሆነ የኒቆምዮስ ልጅ ነው በወገንም የከበረ ነው አባቱም ከአንጾኪያ ታላላቆች ወገን ሁኖ በወርቅ በብር በወንድ ባሮች በሴት ባሮች እጅግ የበለጸገ ነው ክብር ይግባውና ክርስቶስንም እጅግ ይፈራዋል ይወደዋልም ለድኆችና ለችግረኞች አብዝቶ ይመጸውታል በሰው ሁሉ ዘንድ ተወዳጅ ነው ። ይህንንም ቅዱስ እስጢፋኖስን በወለዱት ጊዜ በበጎ ተግሣጽ በምክር አሳደጉት በጀመሪያም የዳዊትን መዝሙር ከዚያም የብሉይና የሐዲስ መጻሕፍትን የመንፈስ ቅዱስ ዕውቀት በላዩ እስቲመላ ድረስ አስተማሩት ። ሁለተኛም ሥጋዊ ጥበብ ፈረስ መጋለብን ጦር መወርወርን በፍላፃ መንደፍን በቅዱስ ፋሲለደስ ቤት ሁኖ ከቅዱሳን ፊቅጦርና ገላውዴዎስ ጋር ተማረ ለፋሲለደስ የወንድሙ ልጅ ነውና ስለዚህም የፋሲለደስ ልጅ ይባላል ። ዘመዶቹም ሁሉ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ናቸው በሕጉ በትእዛዙ በአምልኮቱ ሁሉ የጸኑ ናቸው ። ከውስጣቸውም ክብር ይግባውና ከክርስቶስ የፍቅር ትኲሳት ልቡን የሚያቀዘቅዝ ወደ ቀኝ ቢሆን ወደ ግራም ፈቀቅ የሚል የለም ። ጌታችንም ለእርሱ ያላቸውን የፍቅራቸውን ጽናት በአየ ጊዜ ዓለም ሳይፈጠር ያዘጋጀላቸውን መንግሥቱን ሊአወርሳቸው ወደደ ። ከ… Read in full →
32 ·
ሴቶች ከወለዱአቸው የሚመስለው የሌለ የልዑል ነቢይ የሆነ ጻድቅ ሰውን ሄሮድስ በገደለው ጊዜ ዝሙቱ እንዳይገለጽ ሽቶ ነበር ስለዚህም ተልቶ ተበላሽቶ እስኪሞት ሚስቱንም ምድር እስከ ዋጠቻት ልጅዋም እስከ አበደች ድረስ ጉስቍልና አገኘው የመጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ራስም ዝሙቱን ግልጽ አድርጋ ዘለፈችው። ይህም ጐስቋላ ዲዮቅልጥያኖስ የረከሱ የጣዖታትን አምልኮ ሊገልጥ የማይደበቅ የሕያው እግዚአብሔርን አምልኮ ሊደብቅ ወዶ የቅዱስ እስጢፍኖስን ራስ ቆረጠ የቅዱስ እስጢፍኖስ ራስ ግን ዘለፈችው አማልክቶቹም የርኩሳን አጋንንት ማደሪያዎች እንደ ሆኑ ገለጠች አሳፈረችውም ። በምድርም ውስጥ እንዲደፍኑዋት አዘዘ ። እርሷም በምድር ውስጥ ተደፍና ሳለች ዝም አላለችም ሦስት ቀን ያህል አብዝታ እየተናገረች ትዘልፈው ነበር ሕዝቡም ሁሉ ይሰሟታል እጅግም አፈረ ከእርሳስም ሣጥን ውስጥ እንዲጨምሯትና ሣጥኑን አሽገው ከጥልቅ ባሕር ውስጥ እንዲጥሉት አዘዘ በዚያንም ጊዜ የእግዚአብሔር መልአክ ወረደ ሣጥኑንም ከባሕር አውጥቶ በባሕሩ ዳር አኖረው ። እናቱም ሥጋውን እየፈለገች በእግዚአብሔር ፈቃድ ከዚያ ደረሰች አግኝታውም ዘመን እስቲያልፍ በሥውር ቦታ አኖረችው በፊቱም መብራት አኖረች የመከራውም ወራት ከአለፈ በኋላ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ተሠራችለት ከእርሱም ታላላቅ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ቶማስ_ሐዋርያ በዚችም ቀን በሕንድ አገር ቅዱስ ሐዋርያ ቶማስ ላደረገው ድንቅ ተአምር መታሰቢያ ሆነ ። ይህም እንዲህ ነው ሐዋርያ ቶማስ እንደ ባሪያ ተሽጦ ወደ ሕንድ አገር ከአበኒስ ጋር በገባ ጊዜ አበኒስ ወደ ንጉሥ ጎንዶፎር አቀረበውና ሐናፂ እንደሆነም ለንጉሡ ነገረው ንጉሡም ስለሚችለው ሙያው ሐዋርያውን ጠየቀው ቅዱስ ሐዋርያ ቶማስም እንዲህ ብሎ ለንጉሥ መለሰለት እኔ የጥርብ ሥራን ሁሉ ቀንበሮችን ሚዛኖችን ሠረገላዎችን መርከቦችን በግንብ ሥራም ቤተ መንግሥትን እሠራለሁ ንጉሡም እጅግ ደስ አለው ። ቤተ መንግሥቱንም እንዲሠራለት ከሚሻው ቦታ ወሰደውና በምን ወር ትሠራለህ አለው ሐዋርያውም ከኅዳር መባቻ ጀምሬ በሚያዝያ ወር እጨርሳለሁ አለው ። ንጉሡም አድንቆ ሕንፃ ሁሉ በበጋ ይታነፃል አንተ ግን እንዴት በክረምት ወር ታንፃለህ አለ ሐዋርያም ስለዚህ ነገር ችግር የለም አለ ። ከዚህም በኋላ ንጉሡ ለራሱና ከእርሱ ጋር ለሚሠሩ ሠራተኞች የሚሆን ብዙ ገንዘብን ሰጠው ቅዱስ ሐዋርያ ቶማስም ተቀብሎ ሔደ ። የንጉሥን ለንጉሥ እሰጣለሁ እያለ ለድኆችና ለምስኪኖች መጸወተው ዳግመኛም የቤተ መንግሥቱ ግድግዳው ተፈጽሞ ጣሪያው ቀርቷል ብሎ ወደ ንጉሡ ላከ ። ያን ጊዜም ንጉሥ ብዙ ገንዘብ ላከለት ሐዋርያውም ተቀብሎ እንደ ልማዱ መጸወተው ። ከዚህም በኋላ ንጉሡ በመጣ ጊዜ ስለ ቤተ መንግሥቱ ሕንፃ ጠየቀ ምንም የተሠራ ነገር አላገኘም ነገር ግን ገንዘቡ ለድኆች ምጽዋት ሁኖ እንደተበተነ ሰማ ። እጅግም ተቆጣ በሚገለውም ነገር እስቲመክር ድረስ ሐዋርያ ቶማስን ከአመጣው ከአበኒስ ጋር አሠረው ። በዚያችም ሌሊት የንጉሡ ወንድም ጋዶን በደንገት ታመመና ሞተ መላእክትም ነፍሱን ወስደው ተመሳሳይ የሌለው በወርቅና በዕንቍ የተሠራ ቤተ መንግሥትን አሳዩዋት ። ጋዶንም መላእክትን ይህ ቤተ መንግሥት የማነው አላቸው መላእክትም ለጋዶን ሐዋርያ ቶማስ ለንጉሥ ጎልዶፎር የሠራለት ነው አሉት ከዚህም በኋላ ጋዶን ከሙታን ተለይቶ ተነሣ ያየውንም ሁሉ ለወንድሙ ለንጉሥ ጎልዶፎር ነገረው ። በዚያንም ጊዜ ወደ እሥር ቤት ሮጡ ቅዱስ ሐዋርያ ቶማስንም አበኒስንም ከወህኒ ቤት አወጡአቸው ። ለሐዋርያውም ሰገዱለት የሀገር ሰዎችም ሁሉ ከንጉሥ ጎል… Read in full →
33 ·
በኋላ ብዙ ምሥጢራትን ነገራቸው፡፡ ለመረጣቸው ቅዱሳን እንዲህ መገለጥ ለእግዚአብሔር ልማዱ ነውና ለአባታችን ለአዳም፣ ለሄኖክ፣ ለኖኅ፣ ለአብርሃም በልዩ ልዩ ህብር ተገልጧል፡፡ ኦ.ዘፍ 3፡10፣ 5፡24፣ 6፡13፣ 18፡1 ፡፡ ለሕዝቅኤልም በኮበር ወንዝ፣ ለዳንኤል በሱሳ ግንብ፣ ለኢሳይያስ ሱራፌል እያመሰገኑት ተገልጦላቸዋል፡፡ ሕዝ 1፡1፣ ዳን 8፡1-3፣ ኢሳ 6፡1-3፡፡ አቡነ መዝገበ ሥላሴ በዘመን ደረጃ በኋለኛው ዘመን የተነሡ አባት ይሁኑ እንጂ በሰጡት ሐዋርያዊ አገልግሎትና ገንዘብ ባደረጉት የተጋድሎ ጽናት የከበሩ ቅዱሳን ሐዋርያትን መስለዋቸዋል፡፡ የታዘዘ መልአክ ወደ መንግሥተ ሰማያት ነጥቆ ወስዶ ማደሪያቸውን አሳይቷቸው መልሶ ወደ ምድር ካመጣቸው በኋላ የዕረፍታቸው ጊዜ እንደደረሰ ነገራቸው፡፡ ‹‹በሰኔ ወር ታርፋለህ›› ቢላቸው ‹‹በሰኔማ ልጆቼ ተዝካሬን ማድረግ አይችሉም›› አሉት፡፡ መልአኩም መልሶ ‹‹ዕረፍትህ በሐምሌ ይሁን›› ቢላቸው ጻድቁ አሁንም ‹‹አይሆንም›› ብለው ተከራከሩ፡፡ በነሐሴም እንደዚያው ሆነ፡፡ መልአኩም መስከረምን አሳልፎ በጥቅምት እንደሚያርፉ ነግሯቸው ዐረገ፡፡ ከዚህም በኋላ ለስም አጠራሩ ምስጋና ይግባውና ጌታችን ቅድስት እናቱን፣ መላእክትን፣ ቅዱሳን ጻድቃን ሰማዕታትን ሁሉ አስከትሎ መጥቶ ‹‹አንተ የዓሥራ አንደኛው ሰዓት ቅጥረኛ ወዳጄ ሆይ! (ከቅዱሳን ሁሉ በኋላ የተነሣህ-ማቴ 20፡1-5) የምስራች እነግርህ ዘንድ የድካምህም ዋጋ እሰጥህ ዘንድ መጥቻለሁ፡፡ እነሆ ከጠዋት ጀምሮ ከደከሙት ጋር አንድ አድርጌሃለሁ፡፡ ከአንተም ጋር ቃልኪዳን ገብቻለሁ፣ ስምህን በእምነት የጠራ፣ መታሰቢያህን ያደረገ፣ በጸሎትህም የታመነ እስከ ሰማንያ ሺህ ስድስት መቶ (80,600) ነፍሳት ዓሥራት ይሁኑህ…›› በማለት ቃልኪዳን ከገባላቸው በኋላ ወደ ሰማያት ዐረገ፡፡ በዚያን ጊዜም አቡነ መዝገበ ሥላሴ ፊታቸው እንደፀሐይ አበራና ጥቅምት 9 ቀን ከሌሊቱ በ6 ሰዓት እንደመልካም እንቅልፍ ዐረፉ፡፡ መላ ዘመናቸው 115 ሲሆን የደብረ ገሪዛን ጉንዳጉንዶ ቅድስት ማርያም ገዳም አበምኔት ሆነው ከመሾማቸው በፊት 62 ዓመት፣ ከተሾሙበት ጊዜ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ 53 ዓመት ነው፡፡ መካነ መቃብራቸው እዚያው የደብረ ገሪዛን ጉንዳጉንዶ ቅድስት ማርያም ገዳም ይገኛል፡፡ በጉንዳጉንዶና አዲግራት በሚገኘው ገዳማቸው ውስጥ በስማቸው የፈለቁ ብዙ ፈዋሽ ጠበሎች አሉ፡፡ አዲግራት የሚገኘው ገዳማቸው ውስጥ ያለው ጠበል የትኛውንም በሽታ በአስቸኳይ ፈውስ በመስጠት ይታወቃል፡፡ ተጠማቂው ሰው የማይድንም ከሆነ ቶሎ ይሞታል እንጂ ከ7 ቀን በላይ አይቆይም፡፡ ጻድቁ ብዙ የተጋደሉበት ይህ ገዳም በግራኝ አህመድ ዘመን 44 ጽላቶች ተሰውረውበታል፡፡ ዮዲት ጉዲትም ልታገኘው ያልቻለችው ታላቅ ገዳም ነው፡፡ በአንድ ወቅት ከሃዲያን አሕዛብ ጦረኞች ወደ ገዳሙ ሲወጡ በተአምራት ወደ ፅድ ዛፍነት ተለውጠዋል፡፡ ፅዶቹ አሁንም ድረስ በገዳሙ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ፅዶቹን በእሳት አቃጥለው ከሰል ቢያደርጓቸው ደም ሆነው ይፈሳሉ እንጂ ፈጽሞ ከሰል መሆን አይችሉም። በ ጥቅምት 9 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ 2.ቅዱስ እስጢፋኖስ ካልዕ (ሰማዕት) 3.ቅዱስ አትናስዮስ ብጹዕ 4.ቅዱስ ስምዖን ሰማዕት 5.ቅዱስ ሊዋርዮስ ሊቀ ዻዻሳት 6.ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሣርያ 7.ቅዱስ ቄርሎስ ሊቀ ዻዻሳት 8.አቡነ መዝገበ ሥላሴ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ) 9.አፄ ዳዊት ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ (ግማደ መስቀሉን ያመጡ) በ 09 የሚከበሩ ወርኀዊ የቅዱሳን በዓላት 1.አባ በርሱማ ሶርያዊ (ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት) 2.አቡነ … Read in full →
❤1
58 ·
ደግነት በጎ አድራጎት ማኅበር
Photo
💠የንስሐ ◇የሽብሻቦ ◇ወረብ ◇የቅዱሳን እንዲሁም የመላእክት መዝሙር የምትፈልጉ ከሆነ አሁኑኑ JOIN  በሉት  ይሄ ቻናል ምርጥ ምርጥ መዝሙሮችን በጥራትና በፍጥነት ያሳያል። 𝐉𝐨𝐢𝐧👇👇👇 https://t.me/addlist/sZA2UFcsVPplMjI0
5 ·
ደ
🎙የምስራች አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄ ና መልስ ልንጀምር ነው 1️⃣ ለወጣ 500 ብር ካርድ 2️⃣ ለወጣ  250 ብር ካርድ 3️⃣ ለወጣ  100 ብር ካርድ 👉 ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ
4 ·
ደግነት በጎ አድራጎት ማኅበር
#ጥቅምት_10 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥቅምት ዐሥር በዚህች ቀን የቅዱስ ባኮስ ባልንጀራ የሆነ #ቅዱስ_ሰርጊስ በሰማዕትነት አረፈ፣ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አውማንዮስ አረፈ፣ መስተጋድል የሆነ #ቀሲስ_ዮሐንስ አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ሰርጊስ_ሰማዕት ዳግመኛም በዚችም ቀን ከከሀዲ ንጉሥ መክስምያኖስ ሠራዊት ውስጥ የቅዱስ ባኮስ ባልንጀራ የሆነ ቅዱስ ሰርጊስ በሰማዕትነት አረፈ። ንጉሥ መክስምያኖስም ወደ ሶርያ አገር ወደ አንጥያኮስ በላካቸው ጊዜ ቅዱስ ባኮስን ከውኃ በማስጠም በዚህ ወር በአራተኛ ቀን ገደሉት። ቅዱስ ሰርጊስን ግን አሥሮ በወህኒ ቤት አኖረው። ከዚህም በኋላ በእግሮቹ ውስጥ ረጃጅም የብረት ችንካሮችን ቸንከረው ከፈረሰኞች ጋር ሩጻፋ ወደሚባል አገር እንዲወስዱት መኰንኑ አዘዘ። ሲወስዱትም ያስሮጡት ነበር ደሙም በምድር ላይ እንደ ውኃ ይፈስ ነበር በጐዳናም አንዲት ድንግል ብላቴና አገኘ ከእርሷም ዘንድ ውኃን ጠጣ ሥጋዬን ትወስጂ ዘንድ እስከ ሩጻፋ ተከተይኝ አላት እርሷም ራራችለት ለጒልምስናውም አዘነችለትና ተከተለችው። አንጥያኮስም እንዲህ ብሎ ጽፎአልና ሰርጊስ ትእዛዜን ተቀብሎ ለአማልክት ካልሠዋ ራሱን በሰይፍ ይቁረጡ። እርሱም ለቅዱስ ሰርጊስ ወዳጅ ነበርና ስለርሱም ይችን ሹመት አግኝቷት ነበርና በዚያንም ጊዜ ወታደሩ የቅዱስ ሰርጊስን ራስ ቆረጠው ያቺም ብላቴና ቀርባ ከእርሷ ጋር በነበረ የፀጕር ባዘቶ ከአንገቱ የፈሰሰውን ደሙን ተቀበለች። የስደቱም ወራት እስከ አለፈ ድረስ ሥጋውን ጠበቀች። ከዚህም በኋላ ያማረች ቤተ ክርስቲያን ተሠራችለት ዐሥራ አምስት ኤጲስቆጶሳትም አከበሩዋት የቅዱስ ሰርጊስንም ሥጋ በውስጥዋ አኖሩ ከእርሱም ብዙ ድንቆች ተአምራት ተገለጡ እጅግ ሽታው ጣፋጭ የሆነ በሽተኞችን የሚፈውስ የሽቱ ቅባት ከሥጋው ይፈስ ነበርና። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ሊቀ_ጳጳሳት_ቅዱስ_አውማንዮስ ጥቅምት ዐሥር በዚች ቀን ለአባቶች ሊቃነ ጳጳሳት ሰባተኛ የሆነ የእስክንድርያ አገር ሊቀ ጳጳሳት አውማንዮስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ ንጹሕ ትሑት የሆነ ለዕውነተኛ ሥራ ሁሉ የሚያገለግል ነበር ቅዱስ አብርምዮስም ትሩፋቱን አይቶ ዲቁና ሾመው በዲቁና አገልግሎትም ዐሥር ዓመት ኖረ። ዮስጦስም ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ ትሩፋቱንና የሃይማኖቱን ቅንነት ተመለከተ ምእመናንንም ማስተማር እንደሚችል አውቆ ቅስና ሾመው። ከዚህም በኋላ ቅዱስ ዮስጦስ በአረፈ ጊዜ ይህን አባት አውማንዮስን መርጠው ሊቀ ጵጵስና ሾሙት የአብያተ ክርስቲያናትንም ሥራ ሁሉ ተረከበ። መናፍቃንንም ተከራክሮ የሚረታቸው ሆነ ብዙዎችንም ከስሕተታቸው መለሳቸው ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመለኮቱ ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ትክክል እንደሆነ ግልጽ አድርጎ አስተማራቸው። በሹመቱም ዐሥራ ሦስት ዓመት ከኖረ በኋላ በአንስጣዮስ ሰባተኛ ዘመነ መንግሥት በዚች ቀን አረፈ። በዘመኑም የሶፍያ ሦስቱ ልጆቿ በሰማዕትነት አረፉ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_ዮሐንስ_ቀሲስ ዳግመኛም በዚችም ቀን መስተጋድል የሆነ ቀሲስ ዮሐንስ አረፈ። ይህም ቅዱስ ከተጋድሎው ብዛት የተነሣ ራሱን በሚላጭ ጊዜ በውኃ አያርሰውም ነበር። =>ጥቅምት 10 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት 1.ቅዱሳን ባኮስና ሰርጊስ (ሰማዕታት) 2.ቅዱስ ዮሐንስ መስተጋድል 3.አባ አውማንዮስ ሊቀ ዻዻሳት =>ወርሐዊ በዓላት 1.ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ 2.ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ 3.አቡነ መልክዐ ክርስቶስ 4.ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ (ወልደ እልፍዮስ) 5.ቅድስት … Read in full →
14 ·
Photo
✝✞✝ ቤተ ቅዱስ መስቀል ✝✞✝ =>የአባታችን ቅዱስ ተክለሃይማኖት ክቡር እግርና ከሰማይ የወረደላቸው መስቀል እዚህ ይገኛሉ፡፡ ""ከበረከታቸው አይለየንና፡፡""
19 ·
Photo
✝በዓለ ቅዱስ አባ ኤስድሮስ (ዘገዳመ አስቄጥስ) ✿የታላቁ መቃሪ ደቀ መዝሙር ✿የታላቁ እንጦኒ ወዳጅ ✿የቅዱስ ሙሴ ጸሊም መምህር (የነፍስ አባት) ✝ወበዓለ አቡነ ዮሐንስ ጻድቅ (ኢትዮጵያዊ) ✿የአቡነ ገብረ ናዝናዊ ዘደብረ ኀረይክዋ ወላጅ አባት ✝️ከበረከታቸው ይክፈለን!
🥰2
27 ·
#ጥቅምት_11 አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥቅምት ዐሥራ አንድ በዚችም ቀን ገድለኛዋ #ቅድስት_ጲላግያ እና የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_አባት_ያዕቆብ አረፉ፤ የውቅሮው #አቡነ_ኤልያስ መታሰቢያ በዓላቸው ነው፡፡ ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅድስት_ጲላግያ ጥቅምት ዐሥራ አንድ በዚችም ቀን ገድለኛዋ ቅድስት ጲላግያ አረፈች። ይቺም ከአንጾኪያ አገር የሆነች ናት ወላጆቿም ከሀድያን ናቸው እርሷም አስቀድማ ከረከሰ ሃይማኖቷ ጋር በረከሰ ሥራ ጸንታ መኖርን ገንዘብ አደረገች። እርሷም በመሸታ በጨዋታ ቤት በመዋል ስትሣለቅና ስታመነዝር ስትዘፍንም ትኖራለች። በአንዲት ቀንም የገሀነም እሳትና የዘላለም ሥቃይ እንደሚጠብቃቸው እያሳሰበ ዝንጉዎችንና አመንዝራዎችን ሲገሥጻቸው ኤጲስቆጶስ ጳውሎስን ሰማችው ምክሩም በልቧ አደረ። ከዚህም በኋላ ወደርሱ ሒዳ የሠራችውን ሁሉ ተናዘዘች እርሱም አጽናንቶ የቀናች ሃይማኖትን አስተማራትና አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አጠመቃት። በቀደመው ሥራዋም እየተጸጸተች በጾም በጸሎት በስግደት ሰውነቷን ማድከም ጀመረች ከዚህም በኋላ የወንድ ልብስ ለብሳ ወደ ኢየሩሳሌም ሒዳ በከበሩ ቦታዎች ሁሉ ሰግዳ ሁሉንም ቦታዎች ተሳለመች ወደ ኢየሩሳሌሙ ሊቀ ጳጳሳትም ተመለሰች። እርሱም ከኢየሩሳሌም ከተማ ውጭ ከደናግል ገዳማት ወደ አንዱ ላካት የምንኵስናንም ልብስ ለብሳ በጽኑዕ ገድልም ተጠምዳ ሠላሳ ዓመት ያህል ኖረች እግዚአብሔርንም አገልግላ በሰላም አረፈች። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #ቅዱስ_አባት_ያዕቆብ ዳግመኛም በዚህች ቀን የአንጾኪያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ አባት ያዕቆብ አረፈ። ይህም ቅዱስ ብዙ መከራ ደርሶበታል ስለ ቀናች ሃይማኖቱ አርዮሳውያን አሳደውት በደሴት ብዙ ወራት ኖረ። ከዚህም በኋላ የአንጾኪያ ምእመናን ሰዎች ተሰብስበው መከሩ። መልእክትም ልከው ወደ እነርሱ መልሰውት ጥቂት ቀኖች ኖረ። ከዚህም በኋላ ሁለተኛ አርዮሳውያን ተነሡበት አሳደዱትም በስደትም ውስጥ ሰባት ዓመት ኑሮ በዚያው አረፈ። ✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞✞ #አቡነ_ኤልያስ_ዘውቅሮ ዳግመኛም በዚህች ቀን የውቅሮው አቡነ ኤልያስ መታሰቢያ በዓላቸው ነው፡፡ አቡነ ኤልያስ ዘውቅሮ የትውልድ ሀገራቸው አክሱም ነው፡፡ የአቡነ አረጋዊ 3ኛ የቆብ ልጅ ናቸው፡፡ አባታቸው ውቅሮ የሚገኘው የጥንታዊው የአብርሃ ወአጽብሓ ቤተ መቅደስ አጣኝ ነበሩ፡፡ ይህ ጻድቅ የሚታወቁበት አንድ ትልቅ ገድል አላቸው፡፡ በቀን 548 ጊዜ አቡነ ዘበሰማያትን እየጸለዩ 666 ጊዜ ይሰግዱ ነበር፡፡ ቅዱስ ያሬድ ዓባይ የሀገራችንን አፈርና ዛፉን ሁሉ ጠራርጎ ሲወስድ ቢመለከት ድምጹን ከፍ አድርጎ ኦ አባይ አይቴ ተሐውር ወለመኑ ተሐዲጋ ለኢትዮጵያ ብሎ ሲዘምር ዓባይ ቀጥ ብሎ ቆሟል፡፡ መልአኩም ወዲያው መጥቶ ‹‹ለምን ትደክማለህ? ለምንስ ተፈጥሮን ትከለክላለህ? ሕጉን አታፍርስ›› ሲለው ቅዱስ ያሬድ ደንጎጦ ‹‹አጥፍቻለሁ ዓባይ ሆይ ሂድ የተፈጥሮ ግዴታህን ፈጽም›› ብሎ አሰናብቶታል፡፡ የኢትዮጵያ ብርሃኗ ቅዱስ ያሬድ በዜማው ዓባይን ቀጥ አድርጎ እንዳቆመው ሁሉ አቡነ ኤልያስ ዘውቅሮም በጸሎታቸው ዓባይን ከኢትዮጵያ እንዳይወጣ አድርገውት ነበር፡፡ ታቦተ አብርሃ ወአጽብሓን ይዘው ከኢትዮጵያ ጠረፍ ዳር ኑብያ ሄደው ድንጋይ ከዓባይ ዳር ደርድረው ታቦቱን አስቀምጠው ሥዕለ ማርያምን አድርገው መሥዋዕት ሰውተው ‹‹ዓባይ ከኢትዮጵያ እንዳትወጣ ገዝቼሃለሁ›› ሲሉት ዓባይም ተመልሶ ቆሟል፡፡ ዓባይ ምድረ ኑብያን ሲያጥለቀልቃት መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ተገልጾ ‹‹ለምን የእግዚአብሔርን ስነ ፍጥረት ታስጨንቃለ… Read in full →
61 ·
ደግነት በጎ አድራጎት ማኅበር
Photo
✝ ኦርቶዶክስ ኖት ? ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ። ➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣ ➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣ ➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣ ➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣ ➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣ ➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል። ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው። ◤◢◤◢◤◢◣◥◣◥◣◥ █ 🇯 🇴 🇮 🇳  █ ◣◥◣◥◣◥◤◢◤◢◤◢
4 ·
ደ
💒 ጥያቄ ========= ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስንት ልደት አለው❓️
6 ·
ደ
ደግነት በጎ አድራጎት ማኅበር
Photo
54 ·
ደግነት በጎ አድራጎት ማኅበር
💁‍♂ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል።  ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል ቻናሉን ለመቀላቀል ከስር ክፍት የሚለውን መጫን በቂ ነው።                ክፈት        ክፈት                               ክፈት        ክፈት                                                                    ክፈት        ክፈት        ክፈት        ክፈት ክፈት        ክፈት        ክፈት        ክፈት                                                                                                                                                                                                                                                                                         ክፈት         ክፈት                              ክፈት         ክፈት
2 ·
📕✞ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከሐዋርያቱ ጋር የገሊላ ክፍል በሆነችው በቃና በሰርግ ቤት ተገኝቶ ውሃውን ወይን ጠጅ ያደረገበት የሰርግ ደግሶ የነበረው  ማን ነበር ?      
3 ·
ደ
✅ አሁን online ላላችሁ ብቻ ጥያቄና መልስ ውድድር ልንጀምር ነው❗️ 1️⃣ ለወጣ 100 ብር ካርድ 2️⃣ ለወጣ   50  ብር ካርድ 3️⃣ ለወጣ   25  ብር ካርድ ➡️ ዝግጁ ከሆናችሁ ጀምር የሚለውን ይጫኑ።👇
4 ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · Index limits · Remove a page · Catalog · Search · How we count