English
Open in Telegram
ግግጥም ብቻ 📘

ግጥም ብቻ 📘

✅ High trust
@getem · channel · Fun · indexed since 2026-06-12
62 884subscribers
5 622average post reach
8.9%ER — reach to subscribers
13posts in 30 days
P
Papi
ግዜ ደጉ . . . ልክ ለመሆን ላለመሳሳት ወርቅ ዘመኔን መፈተን በ'ሳት በፍጡር ይዘት በሰው ትከሻ ፍፁም ካልሆንኩ ይሉት ንክሻ ገጥሜ ትግል ውድቀት ሳላምጥ ሰው እንኳን መሆን ሲያቅተኝ በቅጥ... ጊዜ ደግ አይደል...? ካጓጉል ቅዠት ነክቶ ያባንናል ወደቀ ያሉት በድሜ ይቃናል ነብር ነኝ ባዩም ግልገል ይሆናል ከሆዴ አራግፎ የጅል ኩራቴን ፆም አስገድፎ ሰጠኝ እራቴን የውስጤን ርሀብ በጉርሻ ዋጀው አልጋ ትራሴን ከ'ረፍት አበጀው ተመስገን አልኩ ልቤን ሳሳርፍ መንፏቀቅ ትቼ  በተሳቢ ረድፍ መቆም ስጀምር ታየኝ መንገዱም ለካስ ጉዞ ነው መንገዳገዱም By Tadios Alemayehu @getem @getem @paappii
52 · 10.2K ·
Henock
A  SPARKLER Even if that sun never rises, I'm already bright with your lights. The night becomes darker and darker, but can't destroy your smile, a sparkler. No way! The black fog centered me like a core? oh, I'm safer than ever before. And if it's not going to end, I'll choose to stay dead. smelling your fragrance instead. If this night finally decides to go away, I still won't  miss the sun anyway! [ዓለም] @mypoems396 @getem @getem @getem
13 · 9.9K ·
P
ያመሻሽ ስንኞች (በእውቀቱ ስዩም) በቀዝቃዛ ጎጆ፤ በደብዛዛ ኩራዝ እንባ እያጣቀስኩኝ ፤ በምገልጠው ጥራዝ፤ ኑሮየን ባጠናው፤ ፍቺው አይገለጥ ሊቅ ሆኘ ተፈጠርሁ፤ በቂል ለመበለጥ፤ “”””” እሳቴን አንድጄ ጭራሮ ማግጄ ሰታቴየን ጥጄ ሺ ጊዜ ባማስል፣ ራት አላበሰልሁ እኔ ከማገዶው፤ ቀድሜ እየከሰልሁ፤ By Bewketu seyoum @getem @getem @paappii
58 · 11.3K ·
Papi
"ስለበላች ፣ ከማርህ" የሙጫህ ወለላ ፣ የግንድህ ወዘና ማርኮኛል ውዴ ፣ ሕይወቴ ነውና መቆረጤን ፣ ደምቶ አክሟልና ጦር ባያፈሰው ፣ የጎንህን ደም ውሃ ነፍሴ በተራበች ፣ ሆና ወይራ በኦና በረሃ ግና ተመስገን ፣ ትፈልቃለች እንደ ጮራ ስለበላች ፣ ከ "መ" ማርህ ጠግባለች ፣ በማስማርህ ወደሃት ፣ አልፈህ ከሚስማርህ ክድን አይኗ ፣ የታወረ ረሃቧ ፣ ሆድ የሞረሞረ መዛሏ ፣ ጥልፍ የተጣመረ ግና ደምተህላት አንዴ ጠገበችብህ ውዴ አለችህም መንገዴ በማጉረስህ ፣ ደም ስጋ የዘላለምን ፣ ሕያው ጸጋ ረጋች ካንተ ፣ በርትታ ላትሰጋ እያየችህ አለች ፣ዘወትር በቀኝህ ለመዳኗ ሁሌ ፣ ስታመካኝህ "አቅምሽ?" ሲሉ ፣ አንተን ስታስቃኝህ By #ናትናኤል_አበበ (Hiyaw_Kidan) @getem @getem @getem
4 · 8.5K ·
P
አልገባህም እንጂ የነገርኩህ ሁሉ ታድነኝ ነበረ ‘ራስህ በቀላሉ በመታየት ብቻ በተራ ሰላምታ በትንሽ ንግግር በቁጥብ ፈገግታ ባታስተውል እንጂ እየጠፋች ያለች ቀስ በቀስ ከምድር ደጅህ በቅላ ነበር ‘ምታሳዝን ፍቅር አላሳዝንህም? By Meleti Kiros @getem @getem @paappii
65 · 9.5K ·
P
Papi
የሰይጣን ጆሮን ማን ደፈነልኝ? አይነ ጥላዬን ማን ገፈፈልኝ? የማን ተማፅኖ ጎሁን ቀደደው? በማን ተማልዶ እግዜር ፈቀደው? አይገባም አንዱም ከሰውጋር ውለው ምን ቢላመዱም በመውደድ ብቻ በመኖር ብቻ - ከቆንጆ አይወልዱም እናም ይሄ ዘር ከምን በቀለ? ከማንጋር አድሮ እሸት ደቀለ? በሚል ጥያቄ ግርምቱን ታጥቆ ስልቻ ልቡን ደስታ ጠቅጥቆ ካለልማዱ ሸክም ቢከብደው ከትዝታው ላይ ህመም ህመሙን - መርጦ ይካደው? አዎ ይካደው! ከሀዲ መባል ስምን ቢያውክም ሰባራ ቅስምን ደባብሶ ሚያክም ፀበል አፍልቆ ጅኒ 'ሚያዳክም ፈውስ አግኝቶ ሰው - ደዌ አያመልክም እኔም እንዲሁ ቀኔን በብርሀን መዳፉ ዳብሶት ፊቴን የደስታ ፀዳል አልብሶት እንደ ቁም ነገር ቸገረኝ ብሶት ደስታዬም ሰፍቶ አይመስልም ልኬ ማኩረፍ ከበደኝ ሳቅ ሆነ መልኬ መልመድ አቃተኝ ላንድቀ'ንንኳ? ለካስ ችግር ነው ህልምም ሲሳካ? By Tadios Alemayehu @getem @getem @paappii
33 · 6.3K ·
P
Papi
ዛሬ ተፀፅተሽ በእንባ እንደነገርሺኝ፣ ሰይጣን አሳስቶሽ ከሆነ የተውሺኝ እኔን እንድትከጂ ላሳሳተሽ ሰይጣን፣ ለውለታው ምላሽ ላጭስለት እጣን። By endelibu @getem @getem @paappii
63 · 5.1K ·
P
Papi
በቀን ብርሀን ባገኘኋት ከአንድዬ ‎በሚያወራጭ እልፍ ውጥረት በድካሜ ተከልዬ ‎ ‎ደቂቅ ተስፋን ስንቅ አድርጌ ‎አንዳንዴ ሳንስ ለንጀራዬ ላንዴ ስል ከፍ ለማዕረጌ ‎ ‎ዝም ባለ ሁነት አንዳንዱን በር ሳልፍ ‎በህገኛ ቃላት ህገኛም ባልሆኑ ውዬ ስለፋለፍ ‎ ‎የኔ አምላክ የኔ እፎይታ ‎የማይረሳኝ ውድ ጌታ ‎ ‎በተፈጥሮ ህግጋቱ ለጎኔ እረፍት ‎ጣፋጭ እንቅልፍ ቢያበጅለት ‎ ‎ጭር ባለው ለሊት ህልም ተከሽኖ ‎ያደረኩት የሰማሁት ቅዠት ሆኖ ‎ ‎አይኔን ከድኖ ልቤ ቢያየው ‎ያንን ገሃድ ውስጤ ፈራው ‎ ‎ለካ እውነት ነው የአያቴ ቃል ‎አይን እያየ ልብ ይፈርዳል ‎ by Behailu Firde @getem @getem @getem
10 · 4.9K ·
Henock
Photo
እንዳልኩት.. እኔ በዚ ቤት፡ አላውቅም ስቄ ጮኼበት፣ የለውም የቤት እመቤት ማን ጠርቶኝ?¡ አላልኩም አቤት፨ ፤ መራመድ መሄድ አይደለም        ሚያሸክክ የሰውን ጉልበት፣ ለካንስ ክብድብድ ይላል መቃናት ዝቅ ካሉበት ፡ ፡ (ማጎንበስ ከተቃኑበት!) ፤ ይደክማል መተንፈስ' ባ'ቅሙ      ተሻግሮ ከቅፅበት ቅፅበት፡ ያሰኛል አንዴ በሳቡት ዘላለም ችሎ መሰንበት ፡ ፡ (ሁሉንም የሰለቹ ለት!) ፤ ስጋዬን ከጥንብ አንሳ ጋር        ተባብሮ ሊቋደስ ሚሻ፡ ክፉ ቀን ቢመጣም እንኳ       አልባክን ለጠብ ንክሻ! (ደሞንስ ምን ሊረባው ነው ለሞተ ገላ ሚንጫጫ?) ያሰኘኝ ብቸኛ ነገር ከሕይወት 'ራሴን ማንጫ! 𝓯𝓻𝓸𝓶:book=(𝑡𝑟𝑖 𝑤𝑒𝑑𝑒𝑚𝑜𝑡) @mypoems396 @getem @getem @getem
12 · 4K ·
ሰውነት ነበረ በአይን የሚያግባባን ፣ መሀላችን ገብቶ በቁስ ሰላም አጣን። ከአፍ የገባ ሁሉ በውድድር አለም፣ ተይው አትመዝኝው ሁሉ አይመዘንም። ትንሽ ነው ስንባል ስላመንን አይደል፣ የያዝነውን ጥለን ላልያዝነው ስንዋልል። የመከራ ዋጋ በቅናሽ ገዝተነው፣ የያዝነውን አጥተን ከሰው አገኘነው። ሁሉ አይመዘንም ሁሉም አይገዛም፣ ምክር ያለቦታው ህመምን አይገፋም። የተሰበረ ልብ ረክሷል ቀንሷል፣ ያገኘውን ሲሰብር ጥርስ ማየት ለምዷል፣ ሲሰድብ ይሳቃል፣ ሲጎዳ ይሳቃል፣ ሲያሳንስ ይሳቃል። ሚዛን ያጋደለ ቀን የዘመመ ዕለት፣ የሳቀለት ሁሉ የሚሳለቅበት ። ከቶ አንዴም አይመስለው ዛሬውን ያምነዋል፣ ዛሬ ሁሉም ረክሷል። ስንት ነው ሰውነት? ስንት ገባ እውነት? መሳቅ ያሸልማል ባዘመመ ሰው ቤት። እንደሰው ሞኝ አለ ትላንት ያላቀናው፣ ታሪክና ስህተት ልቡን ያላነቃው። እንደሰው ሞኝ አለ? እስኪ እንደው ንገሩኝ፣ ሰውነት ነበረ እውነት ይሆን አውሩኝ። ትላንትና የተፋው ለዛሬ የተረፈ፣ እስኪ እንደው ንገሩኝ አንድ ሰው ካለፈ። ሙዝየም እናስገባው ብዬ ነው @abela_black @getem @getem @getem
17 · 5K ·
P
ፊደል እንደ ንፍሮ ዘግኖ ቅሟል ስንል በአንሶላ ፈንታ ደርቦ እያደረ ፣ የብራና ጥቅል ፤ (ጠብቀነው ነበር) “ምን ያወራል? “ ብለን እሱ ግን ዘግይቶ “እግዜር የለም” አለን። : (ይኸው ግራ ገባን እኛ መኃይማን) : እሱ እንዴት ተገኘ? በየትኛው እስትንፉስ ቀለማት ላይ ናኘ? : እንዴት ፊደል ቃመ ዘግኖት እንደ ንፍሮ? : እንዴት መረመረ እንዴት ተናገረ ሀሳቡን ቀምሮ ? (የለም እኮ አይልም) የለም ባለው ጌታ ባይፈጠር ኖሮ? by ሚካኤል አ @getem @getem @paappii
16 · 5K ·
H
Henock
#አንዲት_ቃል ስጋር ሆኖ ሳለ          የሌት ተቀን ውሎ አምላክም ይሰጣል           ማረፊያ እንካ ብሎ ለቅዱስ ሚካኤል አማላጅን ብልክ ጠይቄ ስለሷ ሶስት ወር  አስቆጥሮ                  ተዋኀደኝ ነብሷ ፀሎት ሰመረና ሽምጥ ያጋለብኩት የህይወት ዘመኔ ባንዲት ቃል አበቃ አንቺን ሰጦ ለኔ አንቺ ጋ ስቀመጥ ለእልፍ አእላፉ የሚለፈልፈው ተዘጋ ምላሴ ብክን ክን ክን ሚለው ተረጋጋ ነብሴ እውክታ የሞላው ኑሮዬ እና ቀኔን እረሳሁት ታግዬ ታግዬ ውሎዬን አረፍኩት እ ር ፍ ዮኒ      ኣታን @yonatoz @getem @getem @getem
11 · 2.7K ·
ያ ጊዜ የምንለው መስከር'ም በቃኝ ሲል ጥቅምት ሲገባ እናያለን ሁሌም ህዳር የሚያፈራ ሌላ ውብ አበባ የእኔ ጥያቄ ግን? ሰላም የሀገሬን ጡት                 መቼ ነው የሚጠባ? By ይክበር ፀጋዬ @getem @getem @paappii
❤48👍10😁4
14 · 6.9K ·
P
ይለቀሳል በሐዘን ፥ ባይኖርም አባባይ ዕንባም አይገደውም ፥ ይወርዳል እንደ አባይ ደስታ ግን ሰው ይሻል አብሮ የሚያሳስቀው ፥ አጃቢ ተከታይ ሲዳር ሚዜ ሚሆን ፥  ሲዘፍን ተቀባይ ። ሰው በደስታ ድሎት ቦታ አልበቃ ብሎት ሲሆን ሐሴት ባሴት ከአጀብ ተነጥሎ ፥ ተደብቆ በሌት መች ያቅታል ማዘን ፥ በሲቃ ማቃሰት ? ይልቅ የሚከብደው ፥ ለብቻ መደሰት ። By Habtamu Hadera @getem @getem @paappii
❤67😢12🔥6
40 · 7.1K ·
H
Henock
እንዴት መተው አቅቶን፡             ራሱ ገመድ ያስረናል? የሸሸነውን ጭለማ፡             ዳግም መጋፈጥ ያምረናል?! እንዲህ ሆኗል ሰዉ ሁሉ፣ አይጥልም ጥሎም ላ'መሉ። በጣር በምጥ ያመለጠውን፡           ያን አበሳ ያን አዘቅቱን፣ ይከፍትና አስገብቶ፡           ያለምደዋል አዲስ ቤቱን! እንዲህ ሆኗል አለሙ፣ ቀይሮም ያው ነው ቀለሙ። ድባቴ የሚባል ደባል ያመጣል ከየትም ስቦ ያሞቀው ነገር ይመስል ደስታ ላይ ሃዘን ደርቦ! እንዲህ ሆኗል ብስለት ልኩ፣ ደረቅ ቁስል እያከኩ። (ለመሆኑ ምን ማለት ነው?) ካለበት መጣራት : መልሶ መላልሶ፣ የረሱትን እምባ : የረሱትን ለቅሶ??! @mypoems396 @getem @getem @getem
❤34🔥21👍4😢2
19 · 7.3K ·
Papi
❞ማህሌተ-ሸማ❝ በቀጭን ጥልፍ ፣              ላይ ታች ተጣመረ ቀይ በርኖስ ዘምዝሞ ፣             ደም መንፈስ ደመረ ፈታይ በፈተለው ፣             በእንዝርት ቁጭት ጥጥ ነዳፊ በደቦ ፣             ባጠረቃው ለወጭት አንዛሪ ደዋሪ ፣           በተሳተፉበት ሸማኔ እርካቡን ፣           ባፈራረቀበት ማህሌተ-ሸማ ፣           ይኸው ድር ከማጉ ለገላየ ሽፋን ፣           አይመስልም ህዳጉ ፈፅሞ ያልተፃፈበት ፣             ቀለም በሀረጉ በህዳግ የተሞላ ፣             ጥለት ስጉ ጥጉ ግና ይናገራል... ዘርፍ ተሸልሞ ፣             በላዩ እንደ ቅጠል ሲል ያዘም'ራል አባትህ አዳም ፣             ይሄን ለብሶ ነበር። ቡልኮ ያጎነጸፈኝ ፣              የፅንፌ ፅንፈኛ ደጉ ሳምራዊ              ንስ ወደረኛ #ናትናኤል_አበበ @getem @getem @getem
❤22👍5🔥1
6 · 5.2K ·
ህይወትህ በሙሉ እሾህ ቢበዛበት፣ ወጥመድ ብቻ ቢሆን አንተ ያለፍክበት። እንደትሞኝ መቼም ተስፋ አትቁራጥ ደርሶ፣ ስኬት ከቶ አይቀርም ጠፍቶ ሀዘን ለቅሶ። እንኳንስ የሰው ልጅ ባለብዙ ጣጣ፣ ጌታም አልተመቸው ምድራችን ሲመጣ። @getem @getem @paappii
❤55👍7😁5🔥2
28 · 5.1K ·
C
መስቃ (በእውቀቱ ስዩም) ተፈጥረን በጎግ ማጎግ ምድር በሰላም ተኝተን አናድር፤ ሀውልታችችን የቃየን ድንጋይ ስማችን ሽብሩ፤ ኢጄታ ፣ ገላጋይ ነፍስ ሳናውቅ፤ ከነፍሰ ገዳይ ተዋውቀን ከመርባታችን ተላልቀን በጥይት ተገበያይተን በፈንጅ ወረዳ፤ ሰኞ ማክሰኞ ተጫውተን፤ ጎልማሳው ከሚስቱ ፅዋ ፣ ተጎንጭቶ ሳይረካ ከጫጉላ ወደ ጫካ የወጣቱ፤ ለጋ ጣቱ፤ ከቃታ ጋር ተጣብቆ የብር ቀለበት የት አውቆ፤ የጅራፋችን ድምጽ፤ በጥይት ድምጽ ተለውጦ ሞፈራችን ተፈልጦ ካረስነው ትልም በላይ፤ የቆፈርነው ምሽግ በልጦ በሙሉ ልብ ለመሞት ፤ በግማሽ ልብ አኖራለን ፤ ደረት መትተን ጥለን፣ ገድለን፤ ደረት ደቅተን እንቀብራለን፤ ጎረቤቶቻችን ሁሉ፤ ያምባ ጉዋሮ ቤት ሆነው መኖራችንን ተቀናቅነው፤ ቤት ለእምቦሳ ብንላቸው፤ ወይፈን ሆነው እያደሩ ወደ ስስ ብልታችን ፣ ቀንዳቸውን እየወደሩ፤ እሳት አንጫጫር ብለው ገልና ፍም ተውሰው በየለቱ ሲጋብዙን፤ እሳተ ጎመራ ጠንስሰው፤ የመላእክት ጭምብል ለብሰው እንኩዋን ከሰው ካውሬ ብሰው፤ @getem @getem @getem
❤51👍4
12 · 5.3K ·
C
C-ራክ
. . . የደጄ ፈረስ ፥ ሀሙስ ሚመጣው ጊዜ እንደሚቀር ፥ ከወደ ኋላው ልክ እንደጭራው የክረምት ወዳጅ ፥ በጋ እንደሚያብል ባረጀ ሰሞን ፥ ወጥቶ እንደሚጣል ያወቀ አይመስለም ፥ ቀን አኳኋኑ በሌት ዘፈኑ ያሳዝነኛል ፥ እኔ ከአሁኑ ©ሲራክ ወንድሙ @getem @getem @getem
🔥15❤6😢1
4 · 4.8K ·
H
በጭንቋ ቀን ምጧ ደርሶ   ላብ አጥምቋት ፊቷ ርሶ          ማርያም ማርያም እያለች....... ስሟን ስትጠራ እርሷን ስትማፀን  ትገላግላት ዘንድ በእንባ ስትለምን    በልደቷ ቀን መታሰቢያ.....      ሰምታ ጸሎት ስለቷን ማርያም ማረቻት እናቴን በዛች ቅፅበት ስሟን ሰማሁ ደጋግሜ ምስሏን አየሁ             እንዴት ዉብ ናት .....❤ ✨✨✨✨✨✨ ✍️ዔደን ታደሰ 01/02/19 @ediwub @getem @getem  
❤102👎4🔥4
12 · 4.2K ·
Papi
ውልብታ (በእውቀቱ ስዩም) በደራው ጎዳና፤ ብቅ ብትይ ደንገት ተበደርኩኝና የሎጥን ሚስት አንገት ዞሬ ባስተውልሽ ፤ ድፍርስ አይኔ ጠራ፤ ማየት ፍዳን ሳይሆን፤ ጽድቅን እየጠራ፤ ፈገግታሽ አንደ ህልም የሁዋሊት ያስኬዳል፤ በዚህ መጠን ማማር፤ በህግ ይፈቀዳል ? @getem @getem @paappii
❤41🔥13👍8👎2
21 · 2.8K ·
H
መቅደስ ===== የሳምኩሽ ለት ያረከስኩሽ መስሎ ተሰማኝ፣ ሀጢያቴን አይቶ አምላክ አንቺን እንዳይቀማኝ። ካገኘው ሴት ሁሉ ከንፈሬ እያረፈ፣ በስሜት ስብጥር ስንቴ እንዳላደፈ፣ አንቺ ላይ ሲያርፍ ግን ራሱን ተፀየፈ። ነብስሽ የተዋበች የዋህ ውብ የሆነች፣ አንደበትሽ ጣፋጭ ከማር የጣፈጠች። እርጋታ ፈገግታሽ ልብን የሚማርክ፣ የንዴትን እሳት ማርኮ የሚያንበረክክ። አካላትሽ ሲያዩት እጅጉን ያሳሳል፣ ከጥጥ ከደመና እልፍ ይለሰልሳል። የነካሽም እጄ እንዴት ያረክስሻል፣ የሀጥ ሰው ጥሪ ገነት መች ያስገባል፣ ያለንስሃ ግን የኔ እግር ተገኝቷል። ከገነት ደጃፉ፣ ከነጭ ወተት ጎርፉ። ከምንጭ ውሀ መርካት፣ ከመና ቁርስ እራት። ሁሉን ከምትሆኚ ተገኘሁ ካንቺ ቤት፣ ገላዬን ልታጠብ ይለቀኝ እንደሆን፣ መፅሀፈ ህይወት መቅደስ ናቹ ብሎን። እንዴትስ ሳልነፃ ልግባ ወደልብሽ፣ የኔ የማደፍ ወግ አያደርስ ከደጅሽ። ይህንን እያሰብኩ ጎትታ ብታቅፈኝ፣ በማይፀየፍ ልብ አቅፋ ብትስመኝ፣ ያለፍርድ ኩነኔ በፍቅሯ ተያዝኩኝ፣ ጫማዬን ሳላወልቅ ከልቧ አደርኩኝ፣ ገባሁኝ። @abela_black @getem @getem @getem
❤36👍4
25 · 2.3K ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · Index limits · Remove a page · Catalog · Search · How we count