Web appOpen in Telegram
TTech+Ethiopia

Tech+Ethiopia

✅ High trust
@techpluset · channel · Tech · indexed since 2026-07-19
31 321subscribers
3 163average post reach
10.1%ER — reach to subscribers
48posts in 30 days
▒ marekegn ▒
Photo
click to show
​🌐 DNS ምንድን ነው? 🆕 ኢንተርኔትንስ እንዴት ፈጣን ያደርገዋል? ​ዲ ኤን ኤስ (Domain Name System) ልክ እንደ ኢንተርኔት ስልክ ማውጫ (Phonebook) ነው። ​አሰራሩ፦ እኛ ብራውዘር ላይ google.com ብለን ስንጽፍ ኮምፒውተሮች አይረዱትም። DNS ይህንን ስም ወደ ኮምፒውተሮች መለያ ቁጥር (IP Address: ለምሳሌ 142.250.190.46) ይቀይረዋል። ​ፈጣን እና ደህንነቱ የተጠበቀ DNS፦ የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪዎች የሚሰጡት ዲኤንኤስ አዝጋሚ ሊሆን ይችላል። ​የሚመከሩ አማራጮች፦ የ Cloudflare (1.1.1.1) ወይም የ Google (8.8.8.8) DNS በስልክዎ ወይም ራውተርዎ ላይ በመቀየር ፈጣን እና ደህንነቱ የተጠበቀ ብራውዚንግ ማግኘት ይችላሉ። ​#Networking #DNS #InternetTips #ITBasics
3 · 2.3K ·
Photo
click to show
🎣 Phishing (የማታለያ ሊንክ) ጥቃትን እንዴት በቀላሉ መለየት ይቻላል? ​ሀከሮች የይለፍ ቃልዎን እና የባንክ መረጃዎን ለመስረቅ ትክክለኛውን ድረ-ገጽ አስመስለው የውሸት ሊንክ ይልካሉ። ​የድረ-ገጹን አድራሻ (URL) በትክክል ይመልከቱ፦ ከመንካትዎ በፊት ስሙን አስተውሉ። ለምሳሌ ከtelegram.org ይልቅ telegraam.org ወይም tlgrm-security.com ብለው ሊያሳስቱ ይችላሉ። ​የአስቸኳይ ስሜት የሚፈጥሩ ጽሑፎች፦ "አካውንትዎ በ24 ሰዓት ውስጥ ይዘጋል" ወይም "ገንዘብ ተሸልመዋል አሁኑኑ ይክፈቱ" የሚሉ መልዕክቶች አብዛኛውን ጊዜ ወጥመዶች ናቸው። ​መረጃ ከመሙላትዎ በፊት ማረጋገጥ፦ ሊንክ ተጭነው በሚከፈተው ገጽ ላይ በፍጹም ፓስወርድ፣ OTP ወይም የባንክ ሚስጥር ቁጥር አያስገቡ። ​#CyberSecurity #Phishing #OnlineSafety #InfoSec
2.5K ·
Photo
click to show
💾 የ SSD እና HDD ልዩነቶች፦ የትኛው ይመረጣል? የኮምፒውተር ፍጥነትን ለመጨመር ተገቢውን የማከማቻ አይነት ለመለየት ማወቅ ወሳኝ ነው። HDD (Traditional Hard Drive)፦ በውስጡ በሚሽከረከር ማግኔቲክ ዲስክ ይሰራል፤ ዋጋው ርካሽ ሲሆን ለትላልቅ ፋይሎች ማከማቻ ጥሩ ቢሆንም ፍጥነቱ ግን በጣም አዝጋሚ ነው። SSD (Solid State Drive)፦ ምንም አይነት ተንቀሳቃሽ አካል የለውም፤ ልክ እንደ ፍላሽ ሜሞሪ በቺፕ ይሰራል፤ ከ HDD በ5 እጥፍ እስከ 10 እጥፍ ድረስ ፈጣን ነው። ምርጫው፦ ኮምፒውተሩ በሰከንዶች ውስጥ እንዲበራ እና አፖች በፍጥነት እንዲከፈቱ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙ (C: Drive) በ SSD ላይ መጫን አለበት። #Hardware #SSDvsHDD #TechTips #ComputerHardware
1 · 2.3K ·
▒
Photo
click to show
📶 የWi-Fi ፍጥነት ሲቀንስ መፍትሄ የሚሆኑ 3 ነገሮች የኢንተርኔት ፓኬጅ ኖሯችሁ ዋይፋይ የሚዘገይ ከሆነ ምክንያቱ የራውተሩ አቀማመጥ ሊሆን ይችላል። ራውተርን መሃል እና ከፍ ያለ ቦታ ያስቀምጡ፦ ራውተርን መሬት ላይ ወይም ኮርነር ውስጥ ከማስቀመጥ ሳሎን መሃል እና ከፍ ባለ ጠረጴዛ ላይ ማድረግ ሞገዱ በደንብ እንዲዳረስ ይረዳል። ከግድግዳ እና ከብረት ማራቅ፦ ወፍራም የኮንክሪት ግድግዳ፣ ማይክሮዌቭ እና የብረት እቃዎች የWi-Fi ሞገድን ይቀንሳሉ። 5GHz Band ይጠቀሙ፦ ራውተራችሁ ድርብ (Dual Band) ከሆነ ከ 2.4GHz ይልቅ 5GHz የሚለውን ስም ምረጡ፤ በጣም ፈጣን እና የሌሎች እቃዎች ጣልቃ ገብነት የሌለበት ነው። #Networking #WiFiTips #TechHacks #InternetSpeed
7 · 2.2K ·
▒ marekegn ▒
Photo
click to show
📲 Two-Factor Authentication (2FA) ለምን አስፈለገ? ​ፓስወርድ ብቻውን አካውንትን ከስርቆት ለመጠበቅ በቂ አይደለም፤ 2FA ሁለተኛ የመከላከያ አጥር ይፈጥራል። ​አሰራሩ፦ ትክክለኛውን ፓስወርድ ቢያስገቡም እንኳ ወደ ስልክዎ የሚላክ ሚስጥር ኮድ (SMS ወይም Authenticator App) ሳያስገቡ ማንም ሰው መግባት አይችልም። ​ዋና ጥቅሙ፦ ሀከሮች ፓስወርድዎን ቢያውቁትም የእርስዎ ስልክ በእጃቸው ከሌለ አካውንቱን መክፈት አይችሉም። ​የት መጠቀም አለብዎት?፦ በቴሌግራም፣ በፌስቡክ፣ በኢሜይል እና በሁሉም የባንክ አፖች ላይ አሁኑኑ Settings ውስጥ ገብተው ያብሩት። ​#CyberSecurity #2FA #AccountSecurity #OnlineSafety
2 · 1.8K ·
Photo
click to show
​🌐 Frontend እና Backend ልዩነታቸው በአጭሩ ​አንድ ድረ-ገጽ ወይም አፕ ሲሰራ ለሁለት ተከፍሎ ነው የሚዘጋጀው። ​Frontend (የሚታየው ክፍል)፦ ተጠቃሚው በአይኑ የሚያየው፣ የሚነካው እና የሚጠቀምበት ንድፍ (UI) ነው። የሚሰራውም በ HTML, CSS, JavaScript እና እንደ React ባሉ ፍሬምዎርኮች ነው። ​Backend (ከጀርባ የሚሰራው)፦ ተጠቃሚው የማያየው ነገር ግን አፑ በትክክል እንዲሰራ ዳታዎችን የሚመዘግብ፣ ሎጂኩን የሚቆጣጠር እና ሰርቨር የሚያስተዳድር ክፍል ነው። በ Python, Node.js, PHP እና ዳታቤዞች ይሰራል (ለምሳሌ MySQL)። ​በቀላል ምሳሌ፦ መኪና ውስጥ ስቲሪንግ እና መቀመጫው Frontend ሲሆን፣ ሞተሩ እና ማርሹ ደግሞ Backend ናቸው። ​#Programming #WebDevelopment #Frontend #Backend
1 · 1.6K ·
Photo
click to show
​🧹 የኮምፒውተርን C: Drive ለማጽዳት ቀላሉ መንገድ ​ድራይቭዎ ቀይ አብርቶ ከሞላ እና ኮምፒውተሩን ካንቀራፈፈው አላስፈላጊ ጊዜያዊ ፋይሎችን (Temp Files) ያጽዱ። ​Temp ፋይሎችን ማጥፋት፦ የኪቦርዱን Windows + R ተጭነው በሚመጣው ሳጥን ውስጥ %temp% ብለው ይጻፉና Enter ይበሉ፤ የሚመጡትን ፋይሎች በሙሉ Select አድርገው አጥፏቸው (Delete)። ​Prefetch ማጽዳት፦ በድጋሚ Windows + R ተጭነው prefetch ብለው በመጻፍ የሚመጡትን ፋይሎች ያጥፉ። ​Storage Sense ማብራት፦ Settings > System > Storage ገብተው Storage Sense ቢያበሩ ኮምፒውተሩ በራሱ ጊዜያዊ ፋይሎችን ያጸዳል። ​#PCMaintenance #TechTips #WindowsHacks #CleanDrive
6 · 1.7K ·
Photo
click to show
በ me pass ግን ስንቶቹ ገንዘብ እየሰራቹ ነው? ያልጀመራቹ ንገሩኝ አብራርቼ ነግሪያቹ ትጀምራላችሁ token ያላቹ ደሞ 💡💰MEC (Mepass Token) Seller 💵💵 0.1 MEC💎 = 110 Birr 💵 0.5 MEC💎= 600 Birr 💵 1 MEC💎= 1,200 Birr💵 2 MEC💎= 2,500 Birr💵 5 MEC 💎= 6,500 Birr💵 10 MEC💎 = 13,100 Birr💵 ✈️BIG RATE Limited Time Only⚡️✅ ✉️DM NOW💬➡️  @marekegn 💙 @marekegn  ✅ @marekegn ✅
1.8K ·
▒
Video
mark.mp4 · 10.4 MB · click to show
ይሄን App ከ Google Playstore ያውርዱ👇 ለ Android ተጠቃሚዎች👇 https://play.google.com/store/apps/details?id=com.xd.metapass ለ Iphone ተጠቃሚዎች 👇 https://apps.apple.com/us/app/me-pass-meta-earth-pass/id6475705957 Invitation code ስትነኩት Copy ይሆናል 👉 9xnqa66y በተጨማሪም ጥያቄ ካላቹ መጠየቅ ትችላላቹ አካውንት Create አርጋቹ ከላይ ባስቀመጥኩላቹ Invitation Code Verify አርጋቹ ስትጨርሱ 100 ብር 🤑 Reward ታገኛላቹ ከዛ በተጨማሪ ለያንዳንዱ Invite ለምታረጉት ሰው በኛ invitation code Verify አርጎ ሲጨርስ 100 ብር የምታገኙ ይሆናል🙌🤑 አከፋፈቱን ከላይ ባለው Video መሰረት መክፈት ትችላላቹ 🤝 📱📱ምንም አይነት ጥያቄ ካላቹ @marekegn 📱📱
5 · 1.9K ·
▒ marekegn ▒
Photo
click to show
​💻 ኮምፒውተር ላይ Restart እና Shut Down ልዩነታቸው ​ኮምፒውተር ችግር ሲፈጥር "Shut down አድርገህ አብራው" ከማለት "Restart አድርገው" የሚባለው ለምንድን ነው? ​Shut Down፦ በዊንዶውስ ውስጥ Fast Startup የሚባል አሰራር ስላለ ኮምፒውተሩ ሙሉ ለሙሉ አይጠፋም፤ በሚቀጥለው ጊዜ በፍጥነት እንዲበራ ሲስተሙን በከፊል አስቀምጦት (Hibernate አድርጎት) ነው የሚተኛው። ​Restart፦ ዊንዶውስን፣ ራምን እና ሁሉንም የጀርባ ፕሮግራሞች ሙሉ በሙሉ ዘግቶ ከዜሮ አዲስ አድርጎ ይቀሰቅሳቸዋል። ​መፍትሄ፦ ኮምፒውተርዎ ሲጨናነቅ ወይም የሆነ ነገር መስራት ሲያቆም Shut down ከማድረግ ይልቅ Restart ማድረግ ችግሩን በደንብ ይፈታል። ​#WindowsTips #TechHacks #PCTips #ComputerBasics
1 · 1.5K ·
Photo
click to show
​✈️ ስልክን ቻርጅ ሲያደርጉ Airplane Mode ማብራት ምን ይጠቅማል? ​ስልክዎን በፍጥነት ቻርጅ ማድረግ ከፈለጉ ይህን ቀላል ዘዴ ይሞክሩ። ​ምክንያቱ፦ ስልካችን ሁልጊዜ የኔትወርክ መስመር፣ ዋይፋይ እና ብሉቱዝ ለመፈለግ ከበስተጀርባ ብዙ ኃይል ይበላል። ​ውጤቱ፦ Airplane Mode ሲያበሩ እነዚህ ግንኙነቶች በሙሉ ስለሚቋረጡ ባትሪው ኃይል ማባከን ያቆማል፤ ቻርጅ የሚወስደው ፍጥነትም በእጅጉ ይጨምራል። ​ተጨማሪ ጥቅም፦ ቻርጅ በሚያደርግበት ወቅት የሚፈጠረውን ሙቀትም ይቀንሳል። ​#MobileTips #BatteryHacks #SmartphoneTips #TechHacks
2 · 1.2K ·
Photo
click to show
🕶️ የብራውዘር Incognito (Private) Mode በትክክል ምን ይሰራል? ​ብዙ ሰው ኢንኮግኒቶ ከከፈተ ማንም አያየኝም ብሎ ያስባል፤ እውነታው ግን የተለየ ነው። ​የሚሰራው፦ የእርስዎን የፍለጋ ታሪክ (Search History)፣ ኩኪስ (Cookies) እና ያስገቧቸውን ፎርሞች እርስዎ ከተጠቀሙበት ስልክ ወይም ኮምፒውተር ላይ እንዳይቀመጡ ያደርጋል። ​የማይሰራው፦ ከዋይፋይ ባለቤቱ፣ ከኢንተርኔት አቅራቢው (Ethio Telecom) ወይም ከከፈቱት ድረ-ገጽ ባለቤት ማንነትዎን አይደብቅም። ​ጥቅሙ፦ በሰው ስልክ ወይም ኮምፒውተር ላይ የራስዎን አካውንት ከፍተው ለመጠቀም በጣም አሪፍ ነው። ብራውዘሩን ሲዘጉት ወዲያው ሎግ አውት (Log out) ያደርጋል። ​#TechFacts #IncognitoMode #TechTips #CyberSafety
1.2K ·
Photo
click to show
Photo
click to show
​🔒 የድረ-ገጽ አድራሻ ላይ HTTPS እና HTTP ልዩነታቸው ​አንድ ድረ-ገጽ ስንከፍት ከላይ አድራሻው ጋ ቁልፍ ምልክት የሚኖረው ለምንድን ነው? ​HTTP (ያልተጠበቀ)፦ የሚልኩት መረጃ (ፓስወርድ ወይም የካርድ ቁጥር) ልክ እንደ ግልጽ ደብዳቤ ክፍት ሆኖ ይጓዛል፤ በመሃል ያለ ማንኛውም ሰው በቀላሉ ሊያየው ይችላል። ​HTTPS (የተጠበቀ)፦ መረጃው ከመላኩ በፊት ስለሚመሰጠር (Encrypted ስለሚሆን) በመሃል ማንም ሰው ሊሰርቀው ወይም ሊያነበው አይችልም። ​ጥንቃቄ፦ የቁልፍ ምልክት የሌለው (HTTP) ድረ-ገጽ ላይ በፍጹም ፓስወርድም ሆነ የባንክ መረጃ እንዳያስገቡ። ​#WebSecurity #HTTPS #InternetBasics #OnlineSafety
1.3K ·
Video
21.0 MB · click to show
👉New apk ⭐️TANVEXO⭐️ 👉ZAPERO & MELKAM EDEL ከሰራችሁ ቀላል ነው! 👉ስራውን ለማታቁ ደግሞ...just ቪዲዮው ላይ እንዳለው የ WhatsApp task መስራት ነው። 👉በምትፈልጉት አካውንት ታስክ እንዳትስሩ spam አለፍ ካለም ban ልትደረጉ ትችላላችሁ...ስለዚህ አዲስ አካውንት ተጠቀሙ! 👉ገና አፕ እንዳወረዳችሁ : ⭐️Sign-up bonus 50 birr ⭐️task ሰርታችሁ የቀረውን መሙላት ነው ⭐️Withdraw ከ 100 ብር ጀምሮ ነው ⭐️የክፍያ አማራጭ telebirr add አድርጉ ሃሳቡን ከተረዳችሁት 8 ደቂቃ ማየት አያስፈልግም 👉 ለመጀመር ይሄን ይጫኑ https://www.tanvexoapp.com/home?invite_code=280367 👉Any question comment አርጉ Withdrawal confimred✅✅
2 · 1.4K ·
Telegram bot🤖 Website ✈️ Application 📱 Social media manager 🔤 ማሰራት የምትፈልጉ DM @marekegn 📱📱📱📱📱
1 · 1.1K ·
Photo
click to show
🔋 ስልክን ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ ላይ ሰክቶ ማደር ባትሪ ያበላሻል? ​ብዙ ሰው ስልኬን ሌሊቱን ሙሉ ቻርጅ ላይ ትቼው ባድር ባትሪው ያብጣል ወይም ይፈነዳል ብሎ ይጨነቃል። ​እውነታው፦ ዘመናዊ ስልኮች ስማርት ቺፕ ስላላቸው ባትሪው 100% ሲሞላ በራሳቸው የኤሌክትሪክ ፍሰቱን ያቆማሉ፤ ከመጠን በላይ አይሞሉም (Overcharge አያደርጉም)። ​ትክክለኛው አደጋ፦ ዋናው ጠላት ሙቀት ነው! ስልኩ ከነሽፋኑ (Cover) ትራስ ስር ወይም ፍራሽ ላይ ከተቀመጠ ሙቀቱ መውጫ አጥቶ የባትሪውን እድሜ ያሳጥረዋል። ​ምክሩ፦ ሌሊት ቻርጅ የሚያደርጉ ከሆነ ሽፋኑን አውልቀው ጠፍጣፋ ጠረጴዛ ላይ አስቀምጠው ይተኙ። ​#MobileTips #BatteryLife #TechFacts #SmartphoneHacks
1.1K ·
Photo
click to show
​📶 የሞባይል ዳታ ቶሎ ቶሎ የሚያልቅብዎት ምክንያት እና መፍትሄው ​ምንም ሳያዩ የኢንተርኔት ፓኬጅዎ በአጭር ጊዜ ውስጥ እያለቀ ከተቸገሩ እነዚህን 2 ነገሮች ይፈትሹ፦ ​Play Store Auto-Update፦ አፕሊኬሽኖች በሞባይል ዳታ በራሳቸው Update እንዳይሆኑ ፕሌይ ስቶር ውስጥ ገብተው Settings > Network Preferences > Auto-update apps የሚለውን "Over Wi-Fi only" ያድርጉት። ​Background Data ያጥፉ፦ የማይጠቀሙባቸው አፖች ከጀርባ ዳታ እንዳይበሉ የስልክዎ Settings > Data Usage ውስጥ በመግባት የፌስቡክ እና የቲክቶክን Background data ይዝጉት። ​#DataSaving #EthioTelecom #MobileHacks #TechTips
2 · 968 ·
Photo
click to show
​🧹 የቴሌግራም ማከማቻ (Storage) ሞልቶ ስልክዎ ተጨናንቋል? ​ቴሌግራም የምናያቸውን ቪዲዮዎች እና ፎቶዎች በሙሉ ስልካችን ውስጥ (Cache) አስቀምጦ የማከማቻ ቦታ ይጨርሳል። ​መፍትሄው፦ የቴሌግራም Settings > Data and Storage > Storage Usage ውስጥ ይግቡ። ​Clear Cache ያድርጉ፦ ይህንን ሲጫኑ ቴሌግራም ያጠራቀመውን አላስፈላጊ ጊጋባይት ያጸዳል፤ ዋናው መልዕክትዎ ወይም ፎቶዎ አይጠፋም (ድጋሚ ዳውንሎድ ማድረግ ይቻላል)። ​Auto-Download ያጥፉ፦ ቴሌግራም ቪዲዮዎችን በራሱ እንዳያወርድ Automatic media download የሚለውን በማጥፋት የስልክዎን ሜሞሪ እና ኢንተርኔት ፓኬጅ ይቆጥቡ። ​#TelegramTips #StorageHacks #AndroidTips #TechBasics
919 ·
Photo
click to show
የኮምፒውተር ፍላሽ USB ያለ 'Eject' መንቀል የሚያስከትለው አደጋ ፋይል ገልብጠን ስንጨርስ ፍላሹን በቀጥታ ነቅለን የምናወጣ ከሆነ ትልቅ ስህተት እየሰራን ነው። ​ምክንያቱ፦ ኮምፒውተሩ ፋይሉ አልቋል ብሎ ቢያሳይም፣ ከጀርባ የመጨረሻዎቹን ዳታዎች እየጻፈ ወይም እያደራጀ ሊሆን ይችላል። ​አደጋው፦ ሳያረጋግጡ በቀጥታ ሲነቅሉት ፋይሉ ሊበላሽ (Corrupt ሊሆን) ይችላል፤ አልፎ ተርፎም ፍላሹ ሙሉ በሙሉ "Format" ካልተደረገ አልከፍትም ሊል ይችላል። ​ትክክለኛው መንገድ፦ ሁልጊዜ ፍላሹ ላይ Right Click አድርገው Eject የሚለውን ተጭነው ኮምፒውተሩ "Safe to Remove" እስኪል መጠበቅ አለብዎት። ​#ComputerTips #USBDrive #TechSafety #WindowsHacks
2 · 905 ·
አንድ college recommended ላድርጋቹ በደንብ የማቀው college ነው
401 ·
▒
Photo
click to show
Photo
click to show
#የዕድል_ጥቆማ📣 🚀 ለኢትዮጵያውያን ወጣቶች የተዘጋጀ ነፃ የኤሌክትሮኒክስ እና አይቲ (IT) ሥልጠና 🚀 ✨ በኤሌክትሮኒክስ ወይም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ፍላጎት ኖሯችሁ የወደፊት ሕይወታችሁን የሚቀይር ተግባራዊ ሙያ መቅሰም ትፈልጋላችሁ? ኤል ጂ-ኮይካ ተስፋ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ (LG-KOICA Hope TVET College) በገበያው ተፈላጊ በሆኑ ሁለት ዋና ዋና የሙያ መስኮች ሙሉ በሙሉ ነፃ ሥልጠና ይሰጣል። የሥልጠና መስኮች፦ 📌 ኤሌክትሮኒክስ፦ የኤሌክትሪካል እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገና (ደረጃ 2 እና 4) 📌 ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፦ የሃርድዌር እና ኔትወርክ ጥገና (ደረጃ 3 እና 4) ሥልጠናውን ልዩ የሚያደርገው፦ 🔹 ሙሉ በሙሉ በተግባር የተደገፈ ጥራት ያለው ሥልጠና 🔹 የእንግሊዝኛ እና የኮሪያ ቋንቋ ትምህርት 🔹 በቂ ልምድ ባላቸው አሰልጣኞች እና በተመጠነ የተማሪዎች ቁጥር የሚሰጥ ትምህርት 🔹 የቴክኖሎጂ ክበባት እና የተለያዩ ተጨማሪ እንቅስቃሴዎች 🔹 ደረጃቸውን የጠበቁ ቤተ-መጻሕፍት እና የኢ-ላይብረሪ (e-library) ግብዓቶች 🔹 በአገር ውስጥና በውጭ አገር የሥራ ዕድል የማግኘት ዕድሎች 🔹 ትምህርታዊ የጉብኝት ፕሮግራሞች ማን ማመልከት ይችላል? 🔸 የ9ኛ እና 10ኛ ወይም የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል የትምህርት ዝግጅት ያላቸው 🔸 በኤሌክትሮኒክስ ወይም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘርፍ ፍላጎት ያላቸው 🔸 ከሰኞ እስከ አርብ ሙሉ ቀን ለመማር ፈቃደኛ የሆኑ 🔸 የእንግሊዝኛ፣ የሂሳብ እና የፊዚክስ የመግቢያ ፈተና ለመውሰድ ዝግጁ የሆኑ 🔸 *ኮሌጁ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ቤተሰቦች፣ ሴቶችን እና አካል ጉዳተኞችን በልዩ ሁኔታ ያበረታታል* ✍️ የሥልጠናው ሁኔታ፦ መደበኛ (ሙሉ ቀን)፣ በግንባር 💵 ክፍያ፦ ሙሉ በሙሉ ነፃ 📍 አድራሻ፦ አዲስ አበባ፣ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ፣ ሰሚት ኮንዶሚኒየም፣ ወረዳ 05 🔗 የማመልከቻ ቦታ፦ ሰሚት ኮንዶሚኒየም በሚገኘው የኮሌጁ ቅጥር ግቢ በአካል በመገኘት ማመልከት ይቻላል። የሚያስፈልጉ ሰነዶች፦ 📌 የ9ኛ-10ኛ ወይም የ11ኛ-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት — ዋናውና ፎቶ ኮፒ 📌 የ10ኛ ወይም የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ካርድ — ዋናውና ፎቶ ኮፒ 📌 የተማሪው 2 የፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ 📌 የወላጅ/የአሳዳጊ 1 የፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ 📞 ስልክ ቁጥር፦ 011 66 77 564 / 011 6 66 18 29 "ለእርስዎ ካልሆነ እባክዎን ፍላጎቱ ላላቸው ሌሎች በማጋራት (Share) ያድርሱ። 🙏 ተጨማሪ ዕድሎችን ለማግኘት ይከተሉን🫴 @LGKHTCOLLEGE_BOT @LGKHTCOLLEGE_BOT https://www.tiktok.com/@lgkoicahope?is_from_webapp=1&sender_device=pc
421 ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog · Search · How we count