English
Open in Telegram
ሰሰማያዊ

ሰማያዊ

@Miraa331 · channel · Education · indexed since 2026-09-28
206subscribers
225average post reach
109%ER — reach to subscribers
16posts in 30 days
ሰማያዊ
ሀያዕ ለወንድም ለሴትም አስፈላጊ ነገር ነው ለሴት ልጅ ግን ውሃ ለአሳ የሚያስፈልገውን ያክል ያስፈልጋታል። @miraa331🍀
3 · 276 ·
ሰ
ልዩነት በጀግና ወንድ ጭንቅላት ውስጥ ብዙ ኪታቦችና የአላህ ቃል ቁርዐን ሲኖር በደካማ ወንድ ጭንቅላት ውስጥ ደግሞ ብዙ አይነት ቅርፅና ከለር ያላቸው ሴቶች አሉ! @miraa331🍀
102 ·
ሰማያዊ
''አንድን ሰው እንደምትወደው እንዲያውቅ ንገረው ልቡ እንዲረጋጋም ደጋግምለት'' ነብያችን selelahu aleyhi weselem @miraa331🍀
2 · 107 ·
ሰ
ሰማያዊ
ሳያዩን ወደዱን እኛም ሳናያቸው ወደድናቸው ሳያዩን ናፈቅናቸው እኛም ሳናያቸው እጅጉን ናፈቁን ነብያችን selelahu aleyhi weselem @miraa331🍀
1 · 113 ·
ሰ
ሰማያዊ
​እስቲግፋር ሀብታም ያደርግሃል እስቲግፋር ሰላምን ይሰጥሃል እስቲግፋር በረከትን ያመጣል እስቲግፋር የምህረት በሮችን ይከፍታል እስቲግፋር የአእምሮ ችግሮችን ይፈውሳል እስቲግፋር የማይቻል ነገር ሁሉ ይሰጥሃል ከሁሉም በላይ ደግሞ ከአላህ ጋር ያለህን ግንኙነት ያሻሽላል፡፡ @miraa331🍀
3 · 275 ·
Audio
018_سورة_الكهف_بدر_بن_محمد_التركي_رواية_حفص_.mp3 · 26.0 MB · click to show
113 ·
ሰ
ሰማያዊ
ሴት ልጅ ውድ ናት ነገር ግን ውድ የምትሆነውም የምትረክሰውም በስራዋ ነው!! @miraa331🍀
2 · 217 ·
ሰ
ሰማያዊ
የትኛው መሬት እና የትኛው ውሳኔ ለኛ የተሻለ እንደሆነ አናውቅም ነገር ግን አላህ ለኛ የመረጠው መልካሙን ነው!! @miraa331🍀
3 · 210 ·
ሰ
ሰማያዊ
​🌾ወንጀለኛ ሰው ከስህተቱ ሊመለስ ይችላል አቢድ ሰውም በአንድ ቅፅበት ወንጀል ላይ ሊወድቅ ይችላል። ​ስለዚህ በራስህ መልካም ስራ በጭራሽ አትመካ ተውበትን ፍለጋ እየታገሉ ያሉ ሰዎች ላይ አትሳቅ። አንድ ሰው ታሪኩ እንዴት እንደሚበቃ አታውቅምና ነገ ለአንተ ምን ሊመጣ እንደሚችል አታውቅም። ​ልቦች በአላህ እጅ ላይ ናቸው። እርሱ እንደሚፈልገው ያገለባብጣቸዋል፤ ለዚህም ነው ምርጥ ሰዎች እንኳን ልባቸው ፀንቶ እንዲቆይ አላህን የሚጠይቁት። ​ልብህ ፀንቶ እንዲቆይ አላህን መጠየቅህን፤ ወንጀል ላይ ስትወድቅ ተውበት ማድረግህን ቀጥል አላህን እስክታገኘው ድረስ በዲኑ ላይ እንዲያቆይህ መጠየቅን በጭራሽ አታቁም። ምክንያቱም እውነተኛው ፈተና ዛሬ ያለህበት ሁኔታህ አይደለም፤ እስከ መጨረሻው ድረስ ፀንተህ የምትቆይበት አህዋልህ እንጂ! ​ስለዚህ ይህንን ዱዓ ማድረግን አብዛ፦ ​يَا مُقَلِّبَ الْقُلُوبِ، ثَبِّتْ قَلْبِي عَلَى دِينِكَ ​ልቦችን የምትለዋውጥ ጌታዬ ሆይ፤ ልቤን በዲንህ ላይ አፅናልኝ። ​ነቢዩ ﷺ ራሳቸው ይህንን ዱዓ ያደርጉ ነበረ ስለዚህ እርሳቸው ይህንን ዱዐ ያደርጉ ከነበረ እኛ ስለራሳችን ልብ ሙሉ በሙሉ ደህንነቱ የተጠበቀ ስለመሆኑ ምን ዋስትና አለን? @miraa331🍀
2 · 202 ·
ሰ
ሰማያዊ
ካልተሳኩልን ሃጃዎች ጀርባ አላህ ለኛ የፈለገው ኸይር አለ!! ●صبر @miraa331🍀
1 · 290 ·
ሰ
ሰማያዊ
●​ጠንካራ ከመሆን የምትሰለችበት ጊዜ አለ! ዱዓ ታደርጋለህ፤ ታጋሽ ለመሆን ትሞክራለህ፤ አላህ የተሻለውን እንደሚያውቅ ራስህን ታስታውሳለህ፤ በልብህ ውስጥ ያለውን መናገር ያልቻልከውን ሁሉ እንዲረዳህ ትለምነዋለህ!! ●አበቦችን እንዲሰጥህ አላህን ስትጠይቅ በመጀመሪያ ዝናብ ቢልክብህ አትደንግጥ። ​አንዳንድ ጊዜ የዱዓህ መልስ ባሰብከው መንገድ አይመጣም። አንዳንድ ጊዜ አላህ ወደ አንድ የተሻለ ነገር ከማምጣቱ በፊት በአስቸጋሪ ነገር ውስጥ ያሳልፍሃል። ​ አብኑል ቀይም ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፦ ​"ዛሬ በደረታችን ላይ እንደ ቶን የሚመዝኑት እነዚህ ፈተናዎች፣ አንድ ቀን ከፍ እንደሚያደርጉን ማሰቡ እንዴት ያለ እንግዳ ነገር ነው። አላህን እናመሰግነዋለን። ስለፈተነን ስለወደደን እና ማንም ሊገምተው ከሚችለው በላይ ስላበዛን እናመሰግነዋለን።" ​(አል-ፋዋኢድ 119) @miraa331🍀
4 · 331 ·
ሰማያዊ
​🌾ፅናትን ከ.. ሱመያ ቢንት ኸያጥ رضى الله عنه ​ሱመያ (رضى الله عنه) የእስልምና የመጀመሪያዋ ሰማዕት ነበረች። በሙስሊሞች ላይ ከባድ ስቃይ በሚደርስባቸው ወቅት እስልምናን ተቀብላለች በከባድ ስቃይ ውስጥም ቢሆን ለአላህ ጠንካራ እና ታማኝ ሆና ኖራለች። በእስልምና ውስጥ ያላት ቦታም በጣም ከፍተኛ ነው። ምክንያቱም ህይወቷን ለእውነት አሳልፋ ስለሰጠች ፈተናው ምንም ያህል ከባድ ቢሆን እውነተኛ ጥንካሬ በዲን ላይ ፀንቶ መቆየት መሆኑን ታስተምረናለች። @miraa331🍀
2 · 257 ·
ሰ
إِنَّ الَّذِينَ قَالُوا رَبُّنَا اللَّهُ ثُمَّ اسْتَقَامُوا فَلَا خَوْفٌ عَلَيْهِمْ وَلَا هُمْ يَحْزَنُونَ እነዚያ «ጌታችን አላህ ነው» ያሉ፣ ከዚያም ቀጥ ያሉ በነርሱ ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነርሱም አያዝኑም፡፡ Al Quran 46:13 @miraa331🍀
1 · 32 ·
ሰ
ሰማያዊ
🌾ንፅህናን ከ... መርየም ቢንት ኢምራን (aleyha selam) ​መርየም (aleyha selam) በእስልምና ውስጥ ትልቅ ቦታ ያላቸው ከዓለም ሴቶች ሁሉ የተመረጡና በንፅህናቸው የሚታወቁ ታላቅ ሴት ናቸው። እናታቸው ገና በሆዷ እያለች ለአላህ አገልጋይ እንድትሆን ስለተሳለቻት ከተወለደች ጀምሮ በነቢዩ ዘከሪያ (aleyhi selam) እንክብካቤ በቤተ-መቅደስ ውስጥ በዒባዳ አደገች። አላህም ካልታሰበ ቦታ ሲሳይን ይልክላት ነበር። ​ያለ ምንም ወንድ ንክኪ በአላህ ተአምርና በጂብሪል (aleyhi selam) አማካኝነት ነቢዩ ዒሳን (aleyhi selam) ፀነሰች። ህዝቦቿ በጠረጠሯትና በወቀሷት ጊዜ አላህ በህፃኑ ዒሳ አማካኝነት ንፅህናዋን አረጋገጠላት። በቁርዓን ውስጥ በስሟ ሙሉ ምዕራፍ (ሱረቱል መርየም) የተሰየመላት ብቸኛዋ ሴት ስትሆን ታሪኳ የፅናት፣ የኢማንና ለአላህ ሙሉ በሙሉ የማደር ታላቅ ትምህርት ያስተምረናል። @miraa331🍀
3 · 103 ·
ሰ
ሰማያዊ
ብቻሽን ለመቆም ዝግጁ ሁኚ አንዳንድ ሰዎች በድንገት ይቀየራሉ...ዛሬ ለነሱ ትልቅ ቦታ ይኖርሻል አንድ ቀን ግን ምንም ናቸው! ይህ የህይወት እውነታ ነው። @miraa331🍀
1 · 71 ·
ሰ
ሰማያዊ
መታደል ማለት ምን ማለት ነው' ብለው ከጠየቁሽ ከ1400 እምነቶች መካከል ሙስሊም ሆኖ መወለድ ሙስሊም ሆኖ መኖር ሙስሊም ሆኖ መሞት ነው በያቸው!◦ @miraa331🍀
3 · 220 ·
ሰማያዊ
አልሞላልኝም አልተሳካልኝም ባልከው ነገር ውስጥ አላህ የደበቀልህ መልካም ነገር አለ! @miraa331🍀
49 ·
ሰ
የፈለገውን ያክል ጊዜ ሊወስድ ይችላል ግን inshaallah በመጨረሻ ሁሉም ነገር ውብ ይሆናል! @miraa331🍀
4 · 190 ·
ሰ
ሰማያዊ
🌾​ይህ ለአንድ ሰው ቅጣት ለመሆን በቂ አይደለምን? ​አላህ ሀብት፣ ጤና፣ እና ስፍር ቁጥር የሌላቸውን በረካዎችን የሰጠው፤ ሆኖም በእርሱ ፊት የመቆም ክብር የነፈገው... ​አላህ ለእርሱ የዱንያን በሮች የከፈተለት፤ ሆኖም ለሰላት ጥሪ መልስ መስጠት ያልቻለ.. ​ለሁሉም ነገር እና ለሁሉም ሰው ጊዜ የሚያገኝ፤ ለፈጠረው አንድ አምላክ ሲቀር.. ​በሁሉም ነገር ተባርኮ፤ ሆኖም በአላህ ፊት በሰላት የመቆም እና ለእርሱ የመስገድ ልዩ መብት ተነጥቆ ከመኖር የበለጠ ቅጣት ምን አለ? ​አላህ ﷻ በፊቱ የመቆምን ጣዕምና ፅናት ይወፍቀን..ሰላትን የልቦቻችን ብርሀን ያድርግልን።أمين @miraa331🍀
2 · 91 ·

An open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · Index limits · Remove a page · Catalog · Search · How we count