ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

ETHIO ≈ SCHOOL

2 542 members
19 July 2026
Фотография
click to show
#ጥቆማ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት (AAU-MCS) በማቋቋም በ2019 ዓ.ም ከ1ኛ-7ኛ ክፍል ለማስተማር ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል። በመሆኑም ልጆቻችሁን በሚከፈተው የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት ማስመዝገብ የምትፈልጉ ወላጆች የሚከተሉትን መረጃዎች ልታውቁ ይገባል፦ የምዝገባ ጊዜ ከሐምሌ 14-21/2018 ዓ.ም የምዝገባ ቦታ 5 ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂና ቢዩልት ኢንቫይሮንመንት ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር E04 ትምህርት ቤቱ የሚገኝበት ቦታ፦ 5 ኪሎ (በቀድሞው የድኅረ ምረቃ/ፋርማሲ ትምህርት ቤት ግቢ) የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 1,000 ሲሆን፤ በቀጣይ ወርሃዊ የክፍያ መጠን ይገለጻል ተብሏል። የሚያስፈልጉ ሰነዶች ● የተመዝጋቢ ልጆች የልደት ካርድ ● ከቀድሞ ትምህርት ቤት ያጠናቀቁበት ሰርተፊኬት ● ሁለት የወላጅ እና አራት የልጅ ፎቶግራፍ ● ወላጆች ህጋዊ አሳዳጊ መሆናቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ ● የክፍያ ደረሰኝ እና የመመዝገቢያ ክላሰር ትምህርት ቤቱ ቅድሚያ ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ልጆች ዕድል የሚሰጥ ቢሆንም፣ ባለው ክፍት ቦታ መሠረት ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ውጭ ላሉ ተማሪዎች በውድድር ተደራሽ የሚሆን መሆኑ ተገልጿል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
117 ·
F
Фотография
click to show
#ጥቆማ አዲስ ሠልጣኞችን ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁን የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክ አካዳሚ አሳውቋል። በኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ (ESL) ስር የሚገኘው የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክስ አካዳሚ፣ አዳዲስ ሠልጣኞችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያስችለውን የትምህርት እና የመሠረተ ልማት ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቁን ገልጿል። አካዳሚው ዘመናዊ የማስተማሪያ መሠረተ ልማት፣ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ ካሪኩለሞች እና ብቁ የማስተማር አቅም በማሟላት ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ዝግጁ መሆኑን የአካዳሚው ዲን ሲራጅ አብዱላሂ ገልፀዋል። ሲሙሌተሮች በመጠቀም እና በባቦጋያ ሐይቅ ላይ በሚካሄዱ የተግባር ስልጠናዎች በከፍተኛ የደህንነት እና የጥራት ደረጃ ለማከናወን ምቹ ሁኔታ መፍጠሩንም ጠቁመዋል። አካዳሚው ከመሠረታዊ የባህር ላይ ደህንነት ስልጠናዎች ጀምሮ እስከ የመርከብ መኮንንነት ፕሮግራሞች በዓለም አቀፉ የባህር ድርጅት (IMO) መስፈርቶች መሰረት የተዘጋጁ ስልጠናዎችን ለመስጠት መዘጋጀቱን አረጋግጠዋል። #ESL ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
145 ·
21 July 2026
Фотография
click to show
Фотография
click to show
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል። በክልሉ በ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 85,531 ተማሪዎች መካከል 83,342 ተማሪዎች ወደ 9ኛ ክፍል የሚያሸጋግራቸውን ውጤት አምጥተዋል፡፡ ዘንድሮ ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች 97.4% የሚሆኑት ያለፉ ሲሆን፤ ይህም በክልሉ ባለፉት ዓመታት ከተመዘገበው ከፍተኛው ውጤት መሆኑን የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አንተነህ ፈቃዱ ገልፀዋል፡፡ የማለፊያ ነጥብ ለመደበኛ ተፈታኞች 50% እና ከዚያ በላይ ሲሆን፤ ለአካል ጉዳተኞች እና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ደግሞ 45% እና ከዚያ በላይ ሆኖ ተቀምጧል። ፈተናውን ካስፈተኑ 1,538 ትምህርት ቤቶች መካከል 1,017 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ማሳለፋቸውን የገለፁት ኃላፊው፤ ዘንድሮ አንድም ተማሪ ያላሳለፈ ትምህርት ቤት የለም ብለዋል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
111 ·
Фотография
click to show
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ተለቋል።   ተማሪዎች ቀጥሎ ባለው ሊንክ መለያ ቁጥራችሁን እና ስማችሁን በማስገባት ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ 👇 http://ce.ministry.et   ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
86 ·
Фотография
click to show
6ኛው ዙር የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዛሬ መሠጠት ጀምሯል። በዚህ የመጨረሻው ዙር ፈተና፣ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከዛሬ ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ፈተናቸውን በኦንላይን የሚወስዱ ይሆናል። ምስል፦ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
108 ·
F
Фотография
click to show
#ጥቆማ   በ2019 የትምህርት ዘመን ወደ ሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (SIT) ለመግባት ያመልክቱ!   የማመልከቻ ጊዜው የሚያበቃው 👇 ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም   የትምህርት መስኮች ● Electrical Engineering ● Biotechnology ● Space Science ● Mechanical Engineering ● AI ● Nuclear engineering   መስፈርቶች ● የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል አማካኝ ውጤት 90% ● የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት 95 ፐርሰንታይል ● ከ500-700 ቃላት የግል መግለጫ መጻፍ ይኖርብዎታል ● የድጋፍ ደብዳቤ ከ2ኛ ደረጃ መምህርዎ/ሜንተርዎ ማጻፍ ● የማኅበረሰብ በጎ አገልግሎት የሰጡት ካለ ቢያይዙ ጥሩ ነው ያመልክቱ 👉 https://sitedu.info የማመልከቻ ሒደቱን የሚያስረዳ ቪዲዮ ለመመልከት 👇 https://web.facebook.com/share/v/1Bg5mV7Kur/   ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
129 ·
23 July 2026
Фотография
click to show
Фотография
click to show
#የሥራ_ቅጥር_ዕድል_ጥቆማ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፍላጎት ያላቸውና ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን አወዳድሮ ለሐረማያ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መቅጠር ይፈልጋል፡፡ ➤ የሥራ መደብ፦ በተለያዩ የስራ መደቦች ➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 23 ➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ ከመጀመሪያ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ ➤ የሥራ ቦታ፦ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ➤ ልምድ፦ ዜሮ ዓመት እና 2 ዓመት ➤ የቅጥር ሁኔታ፦ በቋሚነት አመልካቾች ከሐምሌ 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሰባት (7) የሥራ ቀናት በአካል ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ (መስፈርቶችን ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ፡፡) አመልካቾች CV እና ሙሉ የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውና የማይመለስ ኮፒ በመያዝ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ክላስተር ቢሮ ቁጥር 1 ወይም አዲስ አበባ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ወኪል ቢሮ፣ አራት ኪሎ፣ የቀድሞው የጀርመን ባህል ኢንስቲትዩት ህንፃ ቢሮ ቁ. 15 በአካል በመቅረብ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡ ለቃል ፈተና የተመረጡ አመልካቾች የማመልከቻው ጊዜ ባበቃ በጥቂት ቀናት ጥሪ ይደረግላቸዋል ተብሏል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
139 ·
Фотография
click to show
በሲዳማ ክልል የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ አለመደረጉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አረጋግጧል፡፡ በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ቻናሎች ላይ በክልሉ የተፈታኞች ውጤት ተለቀቀ በሚል እየተሰራጭ ያለው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን ቢሮው ገልጿል፡፡ የተፈታኞቹ ውጤት በቅርቡ በክልሉ ትምህርት ቢሮ በኩል ይፋ እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን፤ እስከዛ ድረስ ከሐሰተኛ መረጃ እንዲጠበቁና ውጤት ይፋ እስከሚደረግ በትዕግስት እንዲጠብቁ ቢሮው ጠይቋል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
96 ·
Фотография
click to show
#EHPLE ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቃችሁ የጤና ባለሙያዎች በነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር የሚሰጠውን የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና ለመውሰድ ከሰኔ 30/2018 ዓ.ም ጀምሮ መረጃችሁን በማስተሳሰር ላይ እንደምትገኙ ይታወቃል፡፡ መረጃችሁን ወደ ሲስተም ያላስገባችሁ ነባር እና አዲስ ተመዛኞች ማስተሳሰር የምትችሉት እስከ አርብ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ መሆኑን ተገንዝባችሁ በ https://hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባት የብሔራዊ መታወቂያ መለያ ቁጥር (16 Digit FAN) በማስገባት አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት ለምዝገባ እንድትዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል። 🔔 መረጃ የማስተሳሰር ሒደት እንዳለቀ የፈተና ጣቢያ መረጣ ሒደት ይቀጥላል ተብሏል፡፡ በሰኔ 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈትናችሁ ያለፉችሁ ተመዛኞች የስም ዝርዝራችሁን በተማራችሁበት ተቋም አማካኝነት ወደ ሲስተም ማስጫን የሚጠበቅባችሁ መሆኑ ተገልጿል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
91 ·
Фотография
click to show
በሲዳማ ክልል ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች በክረምት መርሐግብር ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ ፕሮግራም ለማሻሻል ስልጠና ለመከታተል ሐምሌ 11/2018 ዓ.ም የመግቢያ ፈተና በበይነ መረብ የተፈተናችሁና 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ መምህራን የስልጠና ቦታ በሀዋሳ ዩኒቨርርቲ እና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡ በዚህም በታሪክ ትምህርት የተፈትናቸሁና ያለፋችሁ መምህራን ብቻ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምትሰለጥኑ ሲሆን፤ ሌሎች ቀሪ ሰልጣኞች በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምትሰለጥኑ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የመግቢያ ቀን በቀጣይ የሚገለፅ መሆኑን ቢሮው አሳውቋል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
111 ·
Фотография
click to show
#MekelleUniversity በትግራይ ብሔራዊ ክልል በወረቀት የሚፈተኑትን ተፈታኞች ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ የሚሰጠው 4ኛው ዙር የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የወረቀት ፈተና ከሐምሌ 22-24/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል። ​መቐለ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ ለተመደቡ ተፈታኞች የፈተናውን መርሐግብር ይፋ አድርጓል። ● ​ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም አቀባበል፣ ምዝገባ እና የመኝታ ክፍል ምደባ ● ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም ስለፈተናው አሰጣጥና ደንቦች አጠቃላይ ገለጻ ● ከ​ሐምሌ 22-24/2018 ዓ.ም ሀገራዊ ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ ተፈታኞች ​የግል መታወቂያ እና ሀገራዊ ፈተና መለያ ካርድ፣ ለፈተና የተፈቀዱ የመጻፊያ ቁሳቁሶች እና የግል አልባሳት ይዛችሁ መሔድ ይጠበቅባችኋል። ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ዲጂታል ሰዓት፣ ጌጣጌጦች እና መሠል የተከለከሉ ነገሮችን ይዞ ወደ ተቋሙ መሔድ አይፈቀድም። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
199 ·
F
Фотография
click to show
Фотография
click to show
በኦሮሚያ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 86 በመቶ የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለፀ። በክልሉ የ8ኛ ክፍል ከተፈተኑ 415 ሺህ ተማሪዎች መካከል 354 ሺህ ተማሪዎች (86 በመቶ) 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት በማምጣት ወደ 9ኛ ክፍል መሸጋገራቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ቡልቶሳ ኢርኮ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል። ተፈታኞች ውጤታቸውን https://oromia.ministry.et/#/ ላይ በመግባትና የአድሚሽን ካርድ ቁጥር በማስገባት ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ገልፀዋል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
249 ·
2 August 2026
Фотография
click to show
Фотография
click to show
#AREB በአማራ ክልል የ2018 ትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል። በክልሉ 173,699 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፤ 135,003 (77.72%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት በማስመዝገብ ማለፋቸውን የክልሉ ትምህርሮ አሳውቋል። ውጤት ለማየት 👇 https://amhara.ministry.et/#/result አድራሻውን ከተጫኑ በኋላ የተማሪውን መለያ ቁጥር እና ስም በአማርኛ በማስገባት 'Check your result' የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማየት ይችላሉ፡፡ በቴሌግራም ቦት ለማየት 👇 @emacs_ministry_result_qmt_bot የቴሌግራም ቦት ላይ ከገቡ በኋላ Start የሚለውን ይጫኑ፣ ክፍልዎን ይምረጡ፣ ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ፣ የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት ውጤትዎን ማየት ይችላሉ። ቅሬታ ለማቅረብ 👇 https://amhara.ministry.et/#/complaint VPN የምትጠቀሙ ከሆነ በቅድሚያ ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡ በክልሉ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ይፋ እንደሚደረግ ቢሮው ገልጿል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
169 ·
F
Фотография
click to show
Фотография
click to show
#AREB በአማራ ክልል የ2018 ትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል። በክልሉ 173,699 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ፈተናውን የወሰዱ ሲሆን፤ 135,003 (77.72%) ተማሪዎች 50% እና በላይ ውጤት በማስመዝገብ ማለፋቸውን የክልሉ ትምህርሮ አሳውቋል። ውጤት ለማየት 👇 https://amhara.ministry.et/#/result አድራሻውን ከተጫኑ በኋላ የተማሪውን መለያ ቁጥር እና ስም በአማርኛ በማስገባት 'Check your result' የሚለውን በመጫን ውጤትዎን ማየት ይችላሉ፡፡ አልሰራ ካላችሁ በውስጥ መስመር code & id ይላኩልን 👇👇👇 @gashtiman1990 የቴሌግራም ቦት ላይ ከገቡ በኋላ Start የሚለውን ይጫኑ፣ ክፍልዎን ይምረጡ፣ ከዚያም ክልልዎን ይምረጡ፣ የምዝገባ መለያ ቁጥር እና የመጀመሪያ ስምን በማስገባት ውጤትዎን ማየት ይችላሉ። ቅሬታ ለማቅረብ 👇 https://amhara.ministry.et/#/complaint VPN የምትጠቀሙ ከሆነ በቅድሚያ ማጥፋት ይኖርባችኋል፡፡ በክልሉ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ይፋ እንደሚደረግ ቢሮው ገልጿል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
157 ·
4 August 2026
F
Фотография
click to show
#MekelleUniversity   በ2018 ዓ.ም ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ የክረምት ስልጠና መርሐግብር ለመከታተል በመቐለ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ መምህራን ምዝገባ ከሐምሌ 27/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት በዩኒቨርሲቲው ዓዲ ሓቂ ግቢ ይካሔዳል፡፡   ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ● አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ ● የ8ኛ ክፍል ካርድ፣ የCOC IV ምስከር ወረቀት ዋናውና ኮፒው ● የመታወቂያ ካርድ እና ጉርድ ፎቶግራፍ   ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
134 ·
5 August 2026
Фотография
click to show
የተፈተነችውን ፈተና በሙሉ 100% ያመጣችው የ6ኛ ክፍል ተማሪ ተማሪ ነጅዋ ሰይድ እሸቱ ትባላለች። በአማራ ክልል ኮምቦልቻ ከተማ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና ወስዳ፣ ሁሉንም የትምህርት አይነቶች 100% በማምጣት እጅግ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች።   ተማሪ ነጅዋ የወሰደቻቸውን የትምህርት አይነቶች በሙሉ 60 ከ 60 ማርክ ያመጣች ሲሆን፤ በአጠቃላይ ውጤት፣ በፐርሰንታይል እና በአማካይ 100% ማስመዝገብ ችላለች፡፡  👏👏   ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
112 ·
Ссылка
click to show
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ዓ.ም የ8ኛ እና የ6ኛ ክፍል ውጤቶች ይፋ ተደርገዋል፡፡ በክልሉ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ማለፊያ ነጥብ 50 ሲሆን፤ ድጋፍ ለሚሹ ደግሞ 48 የማለፊያ ነጥብ እንደሆነ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አብዮት ደምሴ ገልፀዋል፡፡ በዚህም በክልሉ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 78,203 ተማሪዎች መካከል 47,307 ተማሪዎች (60.4%) የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡   540 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ማሳፍ ሲችሉ፤ 155 ትምህርቶች ደግሞ ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ኃላፊው ጠቁመዋል። በተመሳሳይ በክልሉ የ6ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 126,224 ተማሪዎች መካከል 110,566 ተማሪዎች (63.8%) የማለፊያ ነጥብ አምጥተዋል፡፡   የ6ኛ ክፍል ፈተና ያስፈተኑ 476 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ሲያሳልፉ፤ 81 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም ብለዋል። የ8ኛ ክፍል ውጤት ለማየት 👇 https://se.ministry.et/#/result የ6ኛ ክፍል ውጤት ለማየት 👇 https://se6.ministry.et/#/result    ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
145 ·
F
Фотография
click to show
የተፈተነውን ፈተና በሙሉ 100% ያመጣው የ8ኛ ክፍል ተማሪ   ተማሪ ዳዊት አማረ አለምየ ይባላል። በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዳውንት ወረዳ የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና ወስዶ፣ ሁሉንም የትምህርት አይነቶች 100% በማምጣት በትምህርት ዘመኑ የክልሉን ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል።   ተማሪ ዳዊት የወሰዳቸውን 6 የትምህርት አይነቶች በሙሉ 60 ከ 60 ማርክ ያመጣ ሲሆን፤ በአጠቃላይ ውጤት፣ በፐርሰንታይል እና በአማካይ 100% ማስመዝገብ ችሏል፡፡  👏👏   ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
187 ·
10 August 2026
F
Фотография
click to show
Фотография
click to show
#ጥቆማ   የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2019 የትምህርት ዘመን በምስራቅ ጎህ የሳይንስ ልህቀት ማዕከል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ9ኛ-12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ይፈልጋል፡፡   በሳይንስ ልህቀት ትምህርት ቤቱ ለመማር የምትፈልጉ ተማሪዎች እስከ ነሐሴ 07/2018 ዓ.ም ድረስ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን ቢሮው ገልጿል፡፡   የመመዝገቢያ ሊንክ 👇 https://bs.ministry.et   (ዝርዝር መስፈርቶችን ከላይ ከተያያዙት የቢሮው ማስታወቂያ ይመልከቱ፡፡)   ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
121 ·
Архив по месяцам
Open in Telegram Feed t.me/s Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog