6 July 2026
Фотография
click to show
154 · click to show
7 July 2026
Фотография
click to show
click to show
የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ ፈተና በነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም ይሰጣል። - ጤና ሚኒስቴር
ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ለተመረቃችሁ የጤና ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ ፈተና በነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገልጿል።
በመሆኑም መረጃችሁን ወደ ሲስተም ያላስገባችሁ ነባር እና አዲስ ተመዛኞች ከሰኔ 30 እስከ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ https://hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባት የብሔራዊ መታወቂያ መለያ ቁጥር (FAN 16 Digit) በማስገባት አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት ለምዝገባ እንድትዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡
መረጃ የማስተሳሰር ሂደት እንዳለቀ የፈተና ጣቢያ መረጣ ሂደት እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡
🔔 በሰኔ 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈትናችሁ ያለፉችሁ ተመዛኞች የስም ዝርዝራችሁን በተማራችሁበት ተቋም አማካኝነት ወደ ሲስተም ማስጫን ይጠበቅባችኋል ተብሏል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
137 · Фотография
click to show
click to show
#ጥቆማ
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ2019 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ሴሚስተር የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች አመልካቾችን በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ለ Masters ፕሮግራም በመደበኛ እና በኤክስቴንሽን መርሐግብሮች እንዲሁም ለ PhD ፕሮግራም በመደበኛ እና በኤክስቴንሽን መርሐግብሮች አመልካቾችን ይቀበላል፡፡
የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞቹን ዝርዝር በ https://admission.aau.edu.et/GraduatePrograms መመልከት ይችላሉ፡፡
አመልካቾች በቅድሚያ በዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) መውሰድና ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የ GAT ማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው 👇
ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
122 · Фотография
click to show
click to show
#AAU #GAT
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) ለመውሰድ ይመዝገቡ!
የ GAT ማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው👇
ነሐሴ 05/2018 ዓ.ም
➫ https://portal.aau.edu.et ይግቡ።
➫ 'Online Exams' የሚለውን ይጫኑ።
➫ Quick Links ከሚለው ስር 'Apply for GAT' የሚለውን ይጫኑ።
➫ 'Test Taker Registration' የሚለውን ቅፅ ይሙሉ።
➫ የፓስፖርት መጠን ያለው ፎቶ ያስገቡ።
➫ 'Submit' የሚለውን ይጫኑ።
➫ ሲስተሙ የሚሰጥዎን የመለያ ቁጥር ይያዙ።
➫ ቴሌብር በመጠቀም የምዝገባ ክፍያ ይፈፅሙ።
➫ አድሚሽን ቲኬትዎን በማውረድ ፕሪንት ብለው፡፡
የ GAT ፈተና በሁለት ዞሮች እንደሚሰጥ የዩኒቨርሲቲው መርሐግብር ያሳያል👇
ከሐምሌ 20-24/2018 ዓ.ም እና ከነሐሴ 07-08/2018 ዓ.ም
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
156 · Фотография
click to show
click to show
#MoE
ትምህርት ሚኒስቴር በ2019 ዓ.ም በዘጠኝ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና የ10ኛ ክፍል ተማሪዎችን በኦንላይን መዝግቦ በማወዳደር ለማስተማር ይፈልጋል።
ሚኒስቴሩ ለ2019 የትምህርት ዘመን በ2018 ዓ.ም ትምህርት በጀመረባቸው አምስት የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በአራት አዲስ በሚጀምሩ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የ9ኛ እና 10ኛ ክፍል ተማሪዎችን አወዳድሮ ለማስተማር ይፈልጋል።
በመሆኑም በእነዚህ ዘጠኝ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ተመዝግባችሁ ለመማር የምትፈልጉ ተማሪዎች የመግቢያ ፈተና ስለሚኖር ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
የምዝገባ ጊዜው በቀጣይ የሚገለፅ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
156 · 8 July 2026
Фотография
click to show
click to show
#ETA
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2016 አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ ብቻ ሀ፣ ለ እና ሐ ተብሎ ተጨምሮ በተዘጋጀው ማሻሻያ ረቂቅ ላይ የትምህርት ማኅበረሰቡ እና ባለድርሻ አካላት እስከ ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም ከዚህ በታች በተቀመጡት አማራጮች አስተያየታቸውን እንዲሰጡ ጠይቋል።
https://forms.gle/ndRhodE2yoHSn2P5A ሊንክን በመጫን አስተያየት መስጫውን ማግኘት ትችላላችሁ፤ አስተያየታችሁን ሞልታችሁ ስትጨርሱ (Submit) የሚለውን በመጫን አስተያየታችሁን መላክ የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።
ማሻሻያ የተደረገበትን ረቂቅ አዋጅ በባለሥልጣኑ ድረ-ገፅ www.neta.gov.et ላይ ማግኘት ይቻላል።
ለሚኖራችሁ ማንኛውም አስተያየት በባለሥልጣኑ ኢ-ሚይል አድራሻ [email protected] ላይ አስተያየታችሁን ሞልታችሁ መላክ ትችላላችሁ ተብሏል።
በአካል ቀርባችሁ መረጃዎችንና አስተያየታችሁን መስጠት ለምትፈልጉ የፊት ለፊት የመወያያ መድረክ በቅርቡ እንደሚያዘጋጅ ባለሥልጣኑ ገልጿል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
152 · Фотография
click to show
click to show
Фотография
click to show
click to show
Фотография
click to show
click to show
የ2018 ዓ.ም 3ኛ ዙር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የመልቀቂያ ፈተና በዛሬው ዕለት መሠጠት ጀምሯል።
በዚህ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በወረቀት እና በኦንላይን ፈተናቸውን ከዛሬ ሐምሌ 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይወስዳሉ።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
202 · Фотография
click to show
click to show
Фотография
click to show
click to show
Фотография
click to show
click to show
Фотография
click to show
click to show
#ጥቆማ
የኢፌዴሪ የቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት የክረምት አጫጭር ስልጠና ለመስጠት የአመልካቾች ምዝገባ እያደረገ ነው።
የስልጠና መስኮች፦
- አዲቲቭ ማኑፋክቸሪንግ (3D Printing)
- ማሽን ዲዛይን (SolidWorks & RHINO 8 Design)
የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን ጨምሮ ማንኛውንም በዘርፉ ፍላጎት ያለው የግል ሰልጣኝ መመዝገብ ይችላል ተብሏል።
የምዝገባ ጊዜ 👇
ከሐምሌ 01-10/2018 ዓ.ም
የምዝገባ አማራጮች፦
በአካል ወይም በኤ-ሜይል [email protected]
ስልጠናው ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም ይጀምራል።
አመልካቾች የዲዛይን ሶፍትዌሮችን በደንብ ማስተናገድ የሚችል የራሳችሁን ላፕቶፕ መያዝ ይጠበቅባችኋል።
አድራሻ፦
አዲስ አበባ፣ ወሰን አካባቢ በሚገኘው የቴክኖሎጂና ብየዳ ልህቀት ማዕከል ግቢ ውስጥ
ለተጨማሪ መረጃ፦
0116464455 / 0985112035
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
171 · 10 July 2026
Фотография
click to show
click to show
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን በመከታተል ላይ የሚገኙ ከትግራይ ክልል የመጡ ተማሪዎች፣ የክረምት ወራት የእረፍት ጊዚያቸውን በዩኒቨርሲቲው እንዲቆዩ ዩኒቨርሲቲው ፈቅዷል፡፡
ተማሪዎቹ በትግራይ ክልል አለ ባሉት "አስገዳጅ የውትድርና ምልመላ" እና የፀጥታ ስጋት ምክንያት ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለስ እንደማይችሉ በመግለፅ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር በክረምት የዕረፍት ወራት የማደሪያ አገልግሎት (Dormitory Service) እንዲፈቅድላቸው በቲክቫህ ኢትዮጵያ በኩል ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡ ተማሪዎቹ ወደ ትግራይ የሚሔዱ ከሆነ ትምህርታቸው ሊቋርጥባቸው እንደሚችልም ስጋታቸውን ገልፀው ነበር፡፡
አሁን ላይ ተማሪዎቹ እስከሚቀጥለው የትምህርት ዓመት ድረስ አስፈላጊውን የምግብ እና የዶርም አገልግሎት እያገኙ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እንዲቆዩ የተፈቀደላቸው መሆኑን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከተማሪዎቹ ሰምቷል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኮምዩኔኬሽን ዳይሬክተር ኤልያስ ወርቁ (ዶ/ር) ተማሪዎቹ በዩኒቨርሲቲው እንዲቆዩ መፍቀዱን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አረጋግጠዋል። "አስፈላጊው በጀት እንዲመጣ ተደርጎ ተማሪዎቹ በግቢው እንዲቆዩ ተደርጓል" ብለዋል።
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄይሉ ዑመር (ዶ/ር) ተማሪዎቹ በግቢው ያሉ መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ላቀረቡት ቅሬታም ምላሽ የተሰጠ መሆኑን ገልፀዋል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
173 · Фотография
click to show
click to show
ጅማ ዩኒቨርሲቲ 10 የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞቹ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ማግኘታቸውን ገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው ከፈረንሳይ የጥናትና ከፍተኛ ትምህርት ግምገማ ኤጀንሲ (High Council for the Evaluation of Research and Higher Education - HCERES) በአስር የመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራሞች ዓለም አቀፍ ዕውቅና አጊኝቷል።
ፕሮግራሞቹ ዕውቅና ያገኙት ሳይንሳዊ የዕውቅና አሰጣጥ ሂደቶችን በማለፍ የፊት ለፊት የመስክ ላይ ምልከታ፣ የሰነዶች ግምገማና ትንተና እንዲሁም በተቋም ደረጃ ጥልቅ ግለ ግምገማ ከተካሔደ በኋ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡
በግምገማውም ዘጠኝ ፕሮግራሞች ሙሉ የአምስት ዓመት እውቅና ሲያገኙ፣ አንድ ፕሮግራም ደግሞ የሦስት ዓመት እውቅና ከተጨማሪ ክትትል ጋር ተሰጥቶታል።
ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያገኙ 10 ፕሮግራሞች፦
● ከጤና ሳይንስ ፋኩሊቲ (ነርሲንግ እና ሚድዋይፈሪ)
● ከሕክምና ሳይንስ ፋኩሊቲ (ሕክምና እና አንስቴዢያ)
● ከቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (ሲቪል ምህንድስና፣ ኬሚካል ምህንድስና እና ሜካኒካል ምሕንድስና)
● ከኮምፒዩቲንግና ኢንፎርማቲክስ (ኮምፒዩተር ሳይንስ፣ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ኢንፎርሜሽን ሳይንስ)
ዓለም አቀፍ ዕውቅናው ጅማ ዩኒቨርሲቲ ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን ለመሳብና የዩኒቨርሲቲውን ተመራቂዎች ዓለም አቀፍ ተፈላጊነት ለማሳደግ ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል ተብሏል፡፡
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
193 · 14 July 2026
Ссылка
click to show
click to show
#ETA
የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በትምህርት ማስረጃ ማረጋገጫ እና የአቻ ግመታ መመሪያ 990/2016 ላይ ያደረጋቸው ማሻሻያዎች ምን ይላሉ?
ባለሥልጣኑ በመመሪያው አንቀጽ 5 ንኡስ አንቀጽ 5 ላይ ማሻሻያዎች ያደረገ ሲሆን፤ በረቂቅ ማሻሻያዎቹ ላይ የትምህርት ማኅበረሰቡ እና ባለድርሻ አካላት እስከ ሐምሌ 13/2018 ዓ.ም አስተያየታቸውን እንዲሰጡ መጠየቁ ይታወቃል።
ማሻሻያዎቹ፦
በቀድሞው ዲፕሎማ / ከ12+2 /ከ10+3 ወይም ከቴክኒክና ሙያ ደረጃ አራት ስልጠና ተመርቀው ያጠናቀቁ ትክክለኛነቱ በባለሥልጣን መስሪያ ቤቱ ወይም በፌደራል ወይም በክልል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋም የተረጋገጠ ኦሪጅናል የስልጠና ማስረጃ ወይም ዲፕሎማ እና ትራንስክሪፕት ኖራቸው ነገር ግን የደረጃ አራት የብቃት ማዕቀፍ ሳይኖራቸው በመጀመሪያ ዲግሪ ተምረው የተመረቁ የትምህርት ማስረጃ የሚረጋገጥላቸው፦
ሀ) ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ ይህ መመሪያ እስከተሻሻለበት ጊዜ የተመረቁ እና የመውጫ ፈተና ተፈትነው ያለፋ የትምህርት ማስረጃቸው የሚረጋገጥላቸው ይሆናል፡፡
ለ) ሆኖም ከላይ በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ ፩ (ሀ) የተጠቀሰው ቢኖርም ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ሳይፈተኑ የመጀመሪያ፣ ሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ የያዙ ባሉበት የትምህርት ደረጃ (BA, MA, and PhD) ላይ ሚኒስቴሩ በሚያወጣው በያዙት የትምህርት ደረጃ ፈተና ተፈትነው ሲያልፉ የትምህርት ማስረጃቸው የሚረጋገጥላቸው ይሆናል።
ሐ) ይህ መመረያ ተሻሽሎ በስራ ላይ ከዋለበት ጊዜ ጀምሮ ማንኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ያለበት ትምህርት ሚኒስቴር ወይም ማንኛውም የሚመሰከተው አካል የሚያወጣውን የመግቢያ መስፈርት ብቻ ተከትሎ ተማሪዎች ተቀብሎ ማስተማር አለበት።
በማሻሻያዎቹ ላይ አስተያየት ይስጡ 👇
https://forms.gle/ndRhodE2yoHSn2P5A
ሊንኩን በመጫን አስተያየት መስጫውን ማግኘት ትችላላችሁ፤ አስተያየታችሁን ሞልታችሁ ስትጨርሱ Submit የሚለውን በመጫን አስተያየታችሁን ይላኩ።
በተጨማሪ ለሚኖራችሁ ማንኛውም አስተያየት በባለሥልጣኑ ኢ-ሜይል አድራሻ [email protected] ላይ አስተያየታችሁን ሞልታችሁ መላክ ትችላላችሁ ተብሏል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
345 · Фотография
click to show
click to show
#ጥቆማ
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2019 የትምህርት ዘመን 60 የዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋለ፡፡
በመሆኑም በ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና የተፈተናችሁና ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተማሪዎች በ https://forms.gle/rpgGP8r3Ea6LrEPUA አማካኝነት ምዝገባ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡
የመግቢያ መስፈርቶች
➫ የ8ኛ ክፍል ማጠቃለያ ክልላዊ ፈተና Percentile ውጤት ለወንድ 85% እና ለሴት 80%
➫ የእንግሊዝኛ እና የሂሳብ ትምህርት የ8ኛ ክፍል አማካይ ውጤት ለወንድ 85% እና ለሴት 80%
የመመዝገቢያ ጊዜ
ከሐምሌ 04-20/2018 ዓ.ም
የመግቢያ ፈተና ሐምሌ 25/2018 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ግቢ ውስጥ ይሰጣል። የመግቢያ ፈተናው እንግሊዝኛ፣ ሂሳብ፣ የተፈጥሮ እና ማኅበራዊ ሳይንስ ትምህርቶችን ያካትታል፡፡
የመግቢያ ፈተና ውጤት ሐምሌ 30/2018 ዓ.ም ይፋ የሚደረግ ሲሆን፤ ያለፉ ተማሪዎች ምዝገባ ከነሐሴ 18-21/2018 ይካሄዳል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
117 · Фотография
click to show
click to show
በቀዶ ሕክምና የስፔሻሊቲ ትምህርትን በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የታገዘ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ፡፡
ይህ የተገለፀው የኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ ሕክምና ማኅበር 11ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሔደበት ወቅት ነው።
ጤና ሚኒስቴር ለስፔሻሊስት ሐኪሞች በሚሰጠው የቀዶ ሕክምና ትምህርት በAI የታገዙ ኮርሶችን አካቶ ለመተግበር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ደኤታ ሳህረላ አብደላ ገልፀዋል፡፡
የጤና ስርዓቱ በቴክኖሎጂ የተቃኘ እንዲሆን ሚኒስቴሩ ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር አብሮ ለመሥራት ከስምምነት መድረሱን ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ ጤና ሚኒስቴር ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የታገዙ የጤና አገልግሎቶችን መተግበር መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡
የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የሕክምና አሰጣጥን ለማሳለጥ፣ አንዳንድ የዲያግኖስቲክ ችግሮችን ለማወቅ የሚፈጀውን ጊዜ ለማሳጠር፣ የላቦራቶሪ ውጤት ትክክለኛነትን ለማሻሻል፣ በሰው ዓይን ሊታዩ የማይችሉ ነገሮች ጎልተው እንዲታዩ ለማድረግና በሌሎችም ሕክምናዎች ላይ ከፍተኛ ዕገዛ እያደረገ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ ሕክምና ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብሩክ ዓለማየሁ አብራርተዋል።
ይሁን እንጂ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የሚሰጣቸው መረጃዎችን የማጥራት እንዲሁም የቁጥጥር ሥራዎች ሊጠናከሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ #ሪፖርተር
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
137 · Фотография
click to show
click to show
Фотография
click to show
click to show
ትምህርት ሚኒስቴር በክረምት የመምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና አዲስ ማዕቀፍ አዘጋጅቷል።
ማዕቀፉ መምህራን በክረምት ስልጠና ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የሚሸጋገሩበት መሆኑ ተገልጿል።
ሚኒስቴሩ በቀን 06/11/2018 ዓ.ም ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ፣ ከአጠቃላይ ትምህርት ሥርዓተ ትምህርት ለውጥ ጋር ተያይዞ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በክረምት የመምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ማስገባት መቋረጡን አስታውሷል፡፡
ይሁን እንጂ በቀጣይ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት በተዘጋጀ የስልጠና ማዕቀፍ፣ በክረምት የመምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል።
በ2018 ዓ.ም የክረምት ስልጠናውን ለመስጠት ስምንት አሰልጣኝ ዩኒቨርሲቲዎች መመረጣቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።
ለክረምት ስልጠናው የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች፦
1. ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ
2. ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
3. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
4. መቐለ ዩኒቨርሲቲ
5. ጅማ ዩኒቨርሲቲ
6. ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
7. ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
8. አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ
ተቋማት እና የስልጠናው አሰጣጥ አግባብነት ከትምህርት ሚኒስቴር እስከሚገለጽ ድረስ ከላይ ከተገለፁት ዩኒቨርሲቲዎች በስተቀር በክረምት መምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና መስጠት የማይቻል መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳስቧል።
ከ2011 ዓ.ም በፊት ስልጠና ጀምረው ያላጠናቀቁ መምህራን ከዚህ በፊት በተሰጠው ውሳኔ መሰረት እንዲያጠናቅቁ እንዲደረግ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከው ደብዳቤ ይገልጻል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
317 · 16 July 2026
Фотография
click to show
click to show
#ጥቆማ
ለ2019 የትምህርት ዘመን በዘጠኝ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ምዝገባ በቅርብ ቀን ይጀመራል።
ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ለቀጣይ ዓመት የ9ኛ አና 10ኛ ከፍል እንዲሁም የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች (አዲስ ሥራ በሚጀምሩት) ምዝገባ ያደርጋሉ።
በ2018 ዓ.ም ትምህርት መስጠት የጀመሩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች፦
1. ወሊሶ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
2. ቡኢ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
3. ቦንጋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
4. ጅግጅጋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
5. ጋምቤላ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
በ2019 ዓ.ም አዲስ ወደ ሥራ የሚገቡ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች፦
1. አርባ ምንጭ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
2. አሶሳ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
3. ባህርዳር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
4. ድሬዳዋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
133 · Фотография
click to show
click to show
Фотография
click to show
click to show
#ጥቆማ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ትምህርት ቢሮ ገላን የወንዶች እና እቴጌ መነን የልጃገረዶች መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል በከተማ አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በማወዳደር ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡
በ2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተምራችሁ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ወደ 7ኛ እና 9ኛ ክፍል የተዘዋወራችሁ ተማሪዎች ለወንድ ተማሪ በገላን የወንዶች መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም ለሴት ተማሪዎች በእቴጌ መነን የልጃገረዶች መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በውድድር ለ2019 ዓ.ም ቅበላ ይደረጋል፡፡
ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች በአዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ለመግባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡
(ዝርዝር መስፈርቶችን ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ፡፡)
የምዝገባ ጊዜ
ከሐምሌ 13-17/2018 ዓ.ም
ኦንላይን ይመዝገቡ 👇🏼
● ለገላን ወንዶች አዳሪ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመልካቾች፦ https://bs.ministry.et
● ለእቴጌ መነን ልጃገረዶች መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመልካቾች፦ https://bs.ministry.et
የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን
● 9ኛ ክፍል ለሚገቡ ተወዳዳሪ ተማሪዎች ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም
● 7ኛ ክፍል ለሚገቡ ተወዳዳሪ ተማሪዎች ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም
● የፈተና ቦታና ሰዓት በቀጣይ ይገለጻል፡፡
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
221 ·