ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

ETHIO ≈ SCHOOL

2 542 members
24 June 2026
F
Фотография
click to show
#UoG የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ለስምንት የተቋሙ ምሑራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እድገት አጽድቋል። ከተባባሪ ፕሮፌሰርነት ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እድገት ያደጉ ምሑራን፦ 1. ዶ/ር በውቀቱ መሐሪ 2. ዶ/ር ሞላ ተፈራ 3. ዶ/ር ምሳዬ ሙላቴ 4. ዶ/ር ጌትነት ማስረሻ 5. ዶ/ር ደሴ ጥበበ 6. ዶ/ር ማስተዋል ብርሀን 7. ዶ/ር አስማማው አጥናፉ 8. ዶ/ር አስማማው ዓለሙ ​የአካዳሚክ ማዕረግ እድገቱ በትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ መሠረት ምሑራኑ በምርምር፣ በማስተማር እና በላቀ ተቋማዊ አመራር ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የተሰጠ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
185 ·
25 June 2026
Фотография
click to show
#ArsiUniversity አርሲ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከወሰዱ የተቋሙ የመደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች መካከል 94.14% የሚሆኑት እጩ ተመራቂ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ገልጿል። ባለፈው ሳምንት የተጠናቀቀውን የመውጫ ፈተና ካስፈተኑ የትምህርት ክፍሎች መካከል ሰባቱ ሙሉ በሙሉ (100%) በማሳለፍ የላቀ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገልጿል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
193 ·
Фотография
click to show
#InjibaraUniversity እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን ከ2,900 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል፡፡ ከተመራቂዎቹ መካከል 178ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው። ተቋሙ በ2018 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ካስፈተናቸው የመደበኛ እና የተከታታይ ፕሮግራም ተማሪዎች መካከል 87.4 በመቶ ተማሪዎች ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ያሳለፈ መሆኑን የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) ገልፀዋል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
187 ·
F
Фотография
click to show
#UoG ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የድንቅነሽን ቅሪተ አካል ላገኙት አሜሪካዊ ምሑር ፕሮፌሰር ዶናልድ ጆሀንሰን የክብር የሳይንስ ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ4 ሺህ በላይ ተማሪዎች አስመርቋል፡፡ ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ፣ በሦስተኛ ዲግሪ እንዲሁም በስፔሻሊቲ እና በሰብ-ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች ስልጠናዎች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው። ዩኒቨርሲቲው “ሉሲ” ወይም “ድንቅነሽ” በመባል የምትታወቀውን የ3.2 ሚሊዮን ዓመት እድሜ ያላትን የሰው ዘር ቅሪት አካል በአፋር ክልል ላገኙት አሜሪካዊ ምሑር ፕሮፌሰር ዶናልድ ካርል ጆሀንሰን የክብር የሳይንስ ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
259 ·
28 June 2026
Фотография
click to show
#MoH በሰኔ 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለወስዳችሁ የጤና ሙያ ተመራቂዎች የብቃት ምዘና ፈተና #በሐምሌ ወር 2018 ዓ.ም መጨረሻ ለመስጠት መታቀዱን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል። ለዚህም በቅርብ ቀን ምዝገባ እንደሚጀመር ሚኒስቴሩ ገልጿል። በመሆኑም በሰኔ ወር የመውጫ ፈተና የወሰዳችሁ የጤና ሙያ ተመራቂዎች ለብቃት ምዘናው የሚያስፈልጉ የትምህርት ማስረጃዎችን እንድታሟሉ እና ለምዝገባው ዝግጁ እንድታደርጉ ተብሏል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
226 ·
F
Фотография
click to show
Фотография
click to show
Фотография
click to show
#DebreBerhanUniversity ‎ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በቅድመ እና በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን 897 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል። 35 A+ ያመጣው ተማሪ ብሩክ ደግነት ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የፕ/ር አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የፋርማሲ ትምህርት ክፍል ተመራቂ ነው። ብሩክ ከወሰዳቸው አጠቃላይ ኮርሶች 35 A+ በማምጣት እና 3.97 ውጤት በማስመዝገብ የሜዳልያ እና የዋንጫ አሸናፊ ሆኗል። 👏👏 ከሴቶች የከፍተኛ ውጤት ባለቤቷ ተማሪ ትርንጎ ገዛኸኝ ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የማኔጅመንት ትምህርት ክፍል በላቀ ማዕሰግ ተመርቃለች። ከዘንድሮ ሴት ተመራቂዎች ከፍተኛ የሆነውን 3.96 አጠቃላይ ውጤት በማስመዝገብ የክብር ዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች። 👏👏 ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
246 ·
1 July 2026
Фотография
click to show
Фотография
click to show
በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 95.85% ተማሪዎች ማለፋቸውን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል። በአዲስ አበባ የ2018 ትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 95.85% ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ገልጿል። በመዲናዋ የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዳችሁ ውጤታችሁን ለመመልከት 👇 https://aa.ministry.et/#/result በአዲስ አበባ ከተማ ሰኔ 11 እና 12/2018 ዓ.ም የተሰጠውን ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና፣ ከ86 ሺህ በላይ ተማሪዎች መውሰዳቸው ይታወሳል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
174 ·
F
Фотография
click to show
ትምህርት ሚኒስቴር ላለፉት ዓመታት አቋርጦት የቆየውን የመምህራን የክረምት ትምህርት ስልጠና ዘንድሮ ሊጀምር ነው። በኮቪድ-19፣ በጦርነት እና በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የቆየው የመምህራን የክረምት ትምህርት ስልጠና በዚህ ዓመት ሊጀመር እንደሆነ ተሰምቷል። የስልጠና ፕሮግራሙ በዲግሪ ፕሮግራም በስምንት የትምህርት አይነቶች በተያዘው ዓመት በድጋሚ ሊጀመር መሆኑ ታውቋል። እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ጂኦግራፊ፣ ታሪክ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በክረምቱ ወራት ስልጠና የሚሠጥባቸው የትምህርት አይነቶች መሆናቸው ተገልጿል። የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ያጠናቀቁ እና የሙያ ብቃት ምዘና ያለፉበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መምህራን ለክረምቱ የዲግሪ ፕሮግራም ስልጠና ማመልከት ይችላሉ ተብሏል። አመልካቾች ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን ማቅረብ የሚችሉ፣ ቢያንስ የሦስት ዓመት የሥራ ልምድ ያላቸው እና እድሜአቸው ከ50 ያልበለጠ እንዲሆኑ ይጠበቃል። ትምህርት ሚኒስቴር ባለፉት ሁለት ዓመታት ልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የክረምት ስልጠና መስጠቱ ይታወቃል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
166 ·
2 July 2026
F
Фотография
click to show
በአራት ዘርፎች ከ6ዐ በመቶ በላይ የሚያመጡ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ይሆናሉ። - ትምህርት ሚኒስቴር የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በአስተዳዳር፣ በፋይናንስ፣ በሰው ኃይል አደረጃጀት እና በአካዳሚክ መለኪያዎች መሠረት ተገምግመው ከ6ዐ በመቶ በላይ ውጤት ካስመዘገቡ ራስ ገዝ መሆን እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡ ራስ ገዝ መሆን የሚፈልግ ዩኒቨርሲቲ የራሱን ተቋማዊ ግለ ግምገማ በማድረግ ወደ ራስ ገዝነት ለመሸጋገር የሚያስችል ውጤት 6ዐ በመቶና ከዚያ በላይ ማገኘቱን ሲያረጋግጥ በዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አፀድቆ፣ ለትምህርት ሚኒስቴር ግምገማ እንዲካሄድለት በደብዳቤ ጥያቄ ማቅረብ እንዳለበት ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. በትምህርት ሚኒስቴር የወጣው መመሪያ ያዛል፡፡ ሚኒስቴሩ በመመሪያው መሠረት 60 በመቶና ከዚያ በላይ ላስመዘገበ ተቋም የራስ ገዝነት ሽግግር ሒደት እንዲጀምር ፈቃድ ይሰጣል። ሚኒስቴሩም የቀረበለትን የግምገማ ውጤቱ መሠረት በማድረግ 6ዐ በመቶና ከዚያ በላይ ያገኘ ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲነት የሚያሸጋግረውን የሚፈቅድ የማቋቋሚያ ደንብ ከተቋሙ ጋር ተመካክሮ በማዘጋጀት፣ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲፀድቅለት ጥያቄ እንደሚያቀርብ በመሪያው ሠፍሯል። የዩኒቨርሲቲው የግምገማ ውጤት ዝቅተኛ ሆኖ ከተገኘ በታዩ ክፍተቶች ላይ የማሻሻያ መርሐግብር ተቋሙ እንዲያዘጋጅ አቅጣጫ በማስቀመጥና ውጤቱን እንዲያሻሽል ክትትል በማድረግ፣ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ግምገማ እንዲካሄድ ሁኔታዎችን ማመቻቸትም የሚኒስቴሩ ተግባር መሆኑ ተመልክቷል፡፡ #ሪፖርተር ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
179 ·
3 July 2026
Фотография
click to show
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ አዶርጓል። በአስተዳደሩ የ6ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች (ወላጆች) ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመግባት የፈተና መለያ ቁጥራችሁን (Registration Number) በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ ተብሏል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
143 ·
F
Фотография
click to show
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ አዶርጓል። በአስተዳደሩ የ6ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች (ወላጆች) ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመግባት የፈተና መለያ ቁጥራችሁን (Registration Number) በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ ተብሏል። ውጤት ለማየት 👇 https://www.diresrms.org ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
167 ·
4 July 2026
Фотография
click to show
Фотография
click to show
Фотография
click to show
#AAEB የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2019 ትምህርት ዘመን ዓመታዊ የጊዜ ሰሌዳ ለሁሉም ክ/ከተሞች ትምህርት ጽ/ቤቶች እና በከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ ሦስት አዳሪ ትምህርት ቤቶች ልኳል። በዚህም፦ ከሐምሌ 19 እስከ ነሐሴ 22/2018 ዓ.ም የነባር እና አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ይከናወናል። ከነሐሴ 26 እስከ ጳጉሜን 5/2018 ዓ.ም የአዲስ ገቢ የ7ኛ እና የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች ምዝገባ ይከናወናል። መስከረም 05/2019 ዓ.ም የመጀመሪያ ቀን የመጀመሪያ መደበኛ ትምህርት ክፍለ ጊዜ ይጀመራል። (የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ለሁሉም ክ/ከተሞች ትምህርት ጽ/ቤቶች እና በከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኙ ሦስት አዳሪ ት/ቤቶች የላከው ሙሉ የ2019 ዓ.ም የትምህርት ካሌንደር ከላይ ተያይዟል።) ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
131 ·
F
Фотография
click to show
Фотография
click to show
Фотография
click to show
189 ·
6 July 2026
Фотография
click to show
ማክሰኞ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም ይጠናቀቃል! የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ከ1ኛ-12ኛ ክፍል ለሆናችሁ ተማሪዎች በተከታዮቹ መስኮች ላይ የክረምት ስልጠና ዕድል አዘጋጅቷል። ➫ ፈንዳሜንታል ኦፍ ኤ.አይ. ➫ ፕሮግራሚንግ ➫ ማሽን ለርኒንግ ➫ ሮቦቲክስ እና IOT ➫ ዳታ ሳይንስ እና በሌሎችም የኤ.አይ. ዘርፎች እስከ ማክሰኞ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም ድረስ በ https://aii.et/summercamp ላይ በመግባት ምዝገባዎን ያድርጉ! ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
150 ·
Фотография
click to show
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ውጤት ነገ ይፋ እንደሚደረግ የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ገልጿል። በመዲናዋ የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከሰኔ 8 -10/2018 ዓ.ም በ199 የመፈተኛ ጣቢያዎች ለሦስት ቀናት መሰጠቱ ይታወሳል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
128 ·
Фотография
click to show
በትግራይ ክልል በወረቀት ለመፈተን ለተመዘገቡ 15,325 የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች ፈተናው ከሐምሌ 22-24/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። ተፈታኞቹ በተገለፁት ቀናት በመቐለ እና በአክሱም ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በወረቀት እንደሚፈተኑ አገልግሎቱ ገልጿል። ተፈታኞች ወደተገለፁት ዩኒቨርሲቲዎች ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም በመግባት እና ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም ላይ ኦሬንቴሽን በመውሰድ መፈተን የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ አብራርቷል። በተያያዘ በትግራይ ክልል በበይነ መረብ ለመፈተን የተመዘገቡ 14,755 ተፈታኞች በስድስቱ ዙር ከሰኔ 23/2018 ዓ.ም ጀምሮ ፈተናው እየተሰጠ መሆኑ ተመልክቷል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
129 ·
Фотография
click to show
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ6ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ካስፈተኑ 768 ትምህርት ቤቶች፥ 543ቱ ተማሪዎቻቸውን ሙሉ በሙሉ ማሳለፋቸው ተገለፀ። የአዲስ አበባ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ አድርጓል። በከተማ አስተዳደሩ በ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 97.48% የሚሆኑት 50% እና በላይ በማስመዝገብ ወደ 7ኛ ክፍል መዘዋወራቸውን ቢሮው አሳውቋል። በመዲናዋ ፈተናውን ከወሰዱ 84,257 የ6ኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል 82,137 ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ሆኖ የተቆረጠውን 50 በመቶ እና በላይ አስመዝግበዋል። ተማሪዎች ውጤት ለማየት 👇 https://aa6.ministry.et/#/result ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
128 ·
F
Фотография
click to show
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ የሁለተኛ ዙር ፈተና እየሠጠ ነው። ሰኔ 26/2018 ዓ.ም መሠጠት የጀመረው የሁለተኛ ዙር የኦንላይን ተፈታኝ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ፈተና ነገ ይጠናቀቃል። የሦስተኛ ዙር የተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች የወረቀት እና የኦንላይን ፈተና ከረቡዕ ሐምሌ 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል። ተፈታኞች ፈተናውን ወደሚወስዱበት ተቋማት መግባት ጀምረዋል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
116 ·
Open in Telegram Feed t.me/s Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog