5 June 2026
8 June 2026
Фотография
click to show
click to show
በሀረሪ ክልል የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተናዎች ከሰኔ 02-12/2018 ዓ.ም ይሰጣሉ። - የክልሉ ትምህርት ቢሮ
የ6ኛ ክፍል ፈተና
➫ ከሰኔ 02 እስከ 04/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
የ8ኛ ክፍል ፈተና
➫ ሰኔ 11 እና 12/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
በክልሉ 6,418 የ6ኛ ክፍል እና 4,624 የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች በተገለፁት ቀናት ፈተናቸውን እንደሚወስዱ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አርሰላን አብዲ ተናግረዋል፡፡
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
143 · Фотография
click to show
click to show
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የ2018/2019 ዓ.ም የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች ዝውውር አጠናቆ በየደረጃው በሚገኝ የትምህርት መዋቅር ይፋ አድርጓል።
በክልሉ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ዝውውሩ ለሁለት ዓመት ተቋርጦ መቆቱን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደምስ እንድሪስ አስታውሰዋል።
ቢሮው አዲስ የዝውውር መመሪያ በማዘጋጀትና በየደረጃው ለሚገኙ አካላት ግንዛቤ በመፍጠር ዝውውሩን ተግባራዊ ማድረጉን ገልፀዋል፡፡
ከቅድመ አንደኛ እስከ 2ኛ ደረጃ መምህራንና የትምህርት አመራሮች ዝውውር የሞሉ ሲሆን፤ ከነዚህ ውስጥ 6,378 መምህራንና የትምህርት አመራሮች የዝውውር ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
187 · Фотография
click to show
click to show
በድሬዳዋ አስተዳደር የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተናዎች ከሰኔ 02-12/2018 ዓ.ም ይሰጣሉ። - የአስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ
የ6ኛ ክፍል ፈተና
➫ ከሰኔ 02 እስከ 04/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
የ8ኛ ክፍል ፈተና
➫ ሰኔ 11 እና 12/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
159 · Фотография
click to show
click to show
በትምህርት ሚኒስቴር እና በክልል ትምህርት ቢሮዎች ትብብር እየተገነቡ የሚገኙ 1,452 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን እስከ መጪው ነሐሴ መጨረሻ ድረስ ለማጠናቀቅ እየተሠራ ነው፡፡ - ትምህርት ሚኒስቴር
ከአጠቃላይ 1,452 የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል 726 በትምህርት ሚኒስቴር እና 726 በክልል ትምህርት ቢሮዎች አማካኝነት የሚገነቡ ናቸው።
ትምህርት ቤቶቹን በ2019 የትምህርት ዘመን ለአገልግሎት ለማብቃት የግንባታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆናቸውን በሚኒስቴሩ የትምህርት ቤቶች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ ከተማ መስቀላ (ዶ/ር) ገልፀዋል።
እስካሁን በትምህርት ሚኒስቴር እና በክልሎች የሚገነቡ ከ400 በላይ ትምህርት ቤቶች የኮንትራት ስምምነት ከተቋራጮች ጋር ተፈርሞ ወደ ሥራ የተገባ መሆኑን የገለፁት ሥራ አስኪያጁ፤ 25 ትምህርት ቤቶች የግንባታ ሥራቸውን በይፋ መጀመራቸውን አብራርተዋል።
በተለያዩ ምክንያቶች የግንባታ ሒደታቸው የዘገየባቸው ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች፣ ትምህርት ቤቶቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ በቀሪው ጊዜ አስፈላጊውን ትኩረትና ክትትል እንዲያደርጉ ኃላፊው አሳስበዋል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
110 · Фотография
click to show
click to show
በቤኒሻንጉል-ጉሙዝ ክልል የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ፈተናዎች ከሰኔ 11-16/2018 ዓ.ም ይሰጣሉ። - የክልሉ ትምህርት ቢሮ
የ6ኛ ክፍል ክልል አቀፍ ፈተና
➫ ሰኔ 15 እና 16/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
የ8ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና
➫ ሰኔ 11 እና 12/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
137 · Фотография
click to show
click to show
ከ560 ሺህ በላይ ተፈታኞች የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ለመውሰድ ተመዝግበዋል። - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍልብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 24/2018 ዓ.ም እስከ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም ይሰጣል።
የመልቀቂያ ፈተናውን ለመውሰድ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከ560 ሺህ በላይ ተፈታኞች መመዝገባቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር እሸቱ ከበደ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።
ከተመዘገቡት ውስጥ አብዛኛዎቹ ተማሪዎች ፈተናውን በበይነ-መረብ እንደሚወስዱ የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የመሰረተ ልማት ውስንነት ባሉባቸው አካባቢዎች ፈተናው በወረቀት እንደሚሰጥ ገልፀዋል።
የፈተና ሒደቱ በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢንተርኔት እና የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት አስተማማኝነትን ለማረጋገጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር እየተሠራ መሆኑን ኃላፊው ጠቁመዋል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
137 · Фотография
click to show
click to show
#WachemoUniversity
ከዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ ተመርቃችሁ ዋናውን ዲግሪ (Original Degree) ያልወሰዳችሁ እና እንዲሠራላችሁ የምትፈልጉ የተቋሙ ምሩቃን ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ዋናው ዲግሪ ከማተሚያ ቤቱ በቀጥታ ታትሞ የሚመጣ በመሆኑ ከታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ እንድትመዘገቡ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡
እስከ ሰኔ 20/2018 ዓ.ም የምትመዘገቡ ብቻ በመጀመሪያ ዙር ህትመት የሚደረግላችሁ ሲሆን፤ ከግንቦት 20/2018 ዓ.ም በኋላ የምትመዘገቡ በሁለተኛው ዙር የሚታተምላችሁ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ምዝገባ ለማድረግ 👇🏼
https://forms.gle/QnLVmNFTi9K7YdJh7
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
160 · Фотография
click to show
click to show
የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና አኃዛዊ መረጃዎች
564,219 ➫ ለፈተናው የተመዘገቡ ተማሪዎች
306,964 ➫ የተፈጥሮ ሳይንስ መስክ ተፈታኞች
257,255 ➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች
570 ➫ ለፈተናው የተዘጋጁ የክልል ማዕከላት
667 ➫ በልዩ ሁኔታ የተዘጋጁ ማዕከላት
122,000 ➫ ለፈተናው የተዘጋጁ ኮምፒውተሮች
97 ➫ ፈተናው የሚሰጥባቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
🔔 የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከ9-12ኛ ክፍል ባሉ መማሪያ መጻሕፍት ላይ ብቻ ተመስርቶ የተዘጋጀና ከአዲሱ ስርዓተ ትምህርት ጋር ሙሉ ለሙሉ የተጣጣመ መሆኑ ተገልጿል፡፡ - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
239 · 9 June 2026
Фотография
click to show
click to show
የ2018 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት የቅድመ-ምረቃ የመውጫ ፈተና በ52 ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ይሰጣል፡፡
የመውጫ ፈተናው ከ48ቱ የመንግሥት ዩኒቨርሲዎች በተጨማሪ በኢትዮጵያ መከላከያ ዩኒቨርሲቲ፣ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ፣ በኢትዮጵያ ፐብሊክ ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ፣ በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ፣ በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት እንዲሁም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ እንደሚሰጥ በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የወጣው የፈተና መስጫ መርሐግብሩ ያሳያል፡፡
የመውጫ ፈተናው ከሰኔ 04-12/2018 ዓ.ም የሚሰጥ ሲሆን፤ ስለፈተናው አጠቃላይ ገለጻ ለተፈታኞች እንደሚሰጥ በመርሐግብሩ ላይ ተመላክቷል፡፡
ተፈታኞች ፈተናው ከሚጀመርበት አንድ ቀን አስቀድመው በተመደቡበት ዩኒቨርሲቲ/ከፍተኛ ትምህርት ተቋም በመገኘት የመፈተኛ ክፍላቸውን ሊያዩ ይገባል ተብሏል፡፡
ፈተናውን ለመውሰድ የተመዘገባችሁ ተፈታኞች የግል መረጃችሁን በራስ በማረጋገጥ የፈተና መግቢያ ትኬታችሁን ፕሪንት በማለት መያዝ ይጠበቅባችኋል፡፡
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
295 · 17 June 2026
Фотография
click to show
click to show
#MoH
የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከሰኔ 17-19/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡
ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ የጤና ባለሙያዎች ፈተና ከሰኔ 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት እንደሚሰጥ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡
የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና መርሐግብር፦
17/10/2018 ዓ.ም
Medicine, Public Health, Medical Laboratory Science, Midwifery, Medical Radiology Technology እና Pediatric and Child Health Nursing.
18/10/2018 ዓ.ም
Nursing, Human Nutrition, Optometry, Physiotherapy እና Surgical Nursing.
19/10/2018 ዓ.ም
Pharmacy, Anesthesia, Dental Medicine, Emergency and Critical Care Nursing, Environmental Health እና Psychiatric Nursing.
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
210 · Фотография
click to show
click to show
#ተጨማሪ
ከሰኔ 17-19/2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና የምትወስዱ ተመዛኞች ማክሰኞ ሰኔ 16/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ መከታተል ይኖርባችኋል ተብሏል፡፡
የተመዛኞች ስም እና የተመደቡበትን የፈተና ማዕከል ዝርዝር በ https://t.me/M0H_EThiopia/2842 እና https://t.me/M0H_EThiopia/2851 ላይ ማየት ይችላሉ፡፡
በፈተናው ወቅት የብሔራዊ መታወቂያ እንዲሁም ሲስተሙ የሚሰጠውን QR Code ያለው የፈተና መግቢያ (ስሊፕ) ፕሪንት አድርጋችሁ መያዝ ይኖርባችኋል፡፡
ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነፅር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች እና ባዶ ወረቀቶች እንዲሁም ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ ወደ ፈተና ክፍል መግባት አይፈቀድም፡፡
በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት) የፈተና ክፍሉን ለቀው ከመውጣታቸው በፊት አቴንዳንስ ላይ መፈረም ይጠበቅባቸዋል።
ተመዛኞች ስማቸው ከተጠቀሰበት የመፈተኛ ጣቢያ ውጪ በፍጹም ፈተናውን መውሰድ አይፈቀድም፡፡
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
231 · 23 June 2026
Ссылка
click to show
click to show
#ExitExamComplaints
ሰሞኑን የተሰጠውን የ2018 ዓ.ም የቅድመ-ምረቃ የመውጫ ፈተናን ከ224 ሺህ በላይ ተማሪዎች መውሰዳቸውን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መግለፁ ይታወቃል።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በ88 ማዕከላት እና በ287 የፈተና አይነቶች በተሰጠው ፈተና ላይ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና የትምህርት ክፍሎች "ቅሬታ አለን" ያሉ ተፈታኞች ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
የፋርማሲ ተማሪዎች "የፈተናው ጥያቄዎች አስቀድመው ተሰርቀው ለተወሰኑ ተማሪዎች ተሰራጭተዋል" የሚል ቅሬታ አቅርበዋል።
ኃላፊነት በማይሰማቸው አካላት አማካኝነት ፈተናው ቀድሞ ወጥቶ መሰራጨቱን የሚያሳዩ መረጃዎች እንዳላቸው ቅሬታ አቅራቢዎቹ ገልፀዋል። ይህ መሆኑም በከፍተኛ ጥረትና በራሳቸው ልፋት የተፈተኑ ተማሪዎችን ስነ-ልቦና የጎዳና ፍትሃዊነትን የጎደለው ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል። የሚመለከታቸው የበላይ አካላት እንዚህ ጉዳይ ላይ ምርመራ እንዲያደርጉና ምላሽ እንዲሰጡበት ጠይቀዋል።
ሌላው፣ በአንዳንድ የትምህርት ዘርፍ ውስጥ ካሉ ተፈታኞች ዘንድ የተነሳው ቅሬታ ፈተናው ከተቀመጠው የይዘት መመሪያ (Blueprint) ውጪ መውጣቱ ነው።
ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በተላከ የቅሬታ መልዕክት የሂሳብ፣ የፊዚክስ፣ የጂኦሎጂ እና የሰርቬይንግ ኢንጂነሪንግ የተለያዩ ጥያቄዎች ከተቀመጠው መመሪያ (Blueprint) ጋር የማይጣጣሙ ሆነው እንዳገኟቸው ገልፀዋል። በተመሳሳይ ከቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በተላኩ መልዕክቶች የእንስሳት ጤና (DVM) የመውጫ ፈተና የተለያዩ ጥያቆዎች ከBlueprint ጋር የማይገናኙ እንደሆኑ አመልክተዋል።
ከዚህ ባለፈ መልስ የሌላቸው ስህተት የሆኑ ጥያቄዎች እንደነበሩ ተመሳሳይ ምርጫዎች መደገማቸውንም ተማሪዎች ጠቁመዋል። በአንዳንድ የትምህርት ዘርፎች ላይ የሰዓት እጥረት እንደነበር ተፈታኞቹ ጠቁመዋል።
በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ (ASTU) እና በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲዎች ያጋጠመው ተደጋጋሚ የመብራት መቋረጥ በፈተናው ሂደት ላይ እንቅፋት እንደነበር የገለፁ ተፈታኞች ነበሩ። በተለይም በዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የጤና ኢንፎርማቲክስ ተማሪዎች ፈተና ወቅት መብራት አራት ጊዜ በመጥፋቱ ምክንያት የባከነው ሰዓት ሳይተካላቸው ቀርቶ፣ የ100 ጥያቄዎችን ፈተና በአንድ ሰዓት ውስጥ ብቻ እንዲያጠናቅቁ መገደዳቸውን ተማሪዎቹ ገልፀዋል።
በተመሳሳይ እንደ አካውንቲንግ ባሉ የሂሳብ ስሌት በሚጠይቁ ዘርፎች ካልኩሌተር እና የማሰቢያ ወረቀት መከልከላቸው ጥያቄዎችን በግምት ለማጥቆር እንደዳረጋቸውና ከፍተኛ ጫና እንደፈጠረባቸው ተማሪዎቹ ለቲክቫህ አብራርተዋል።
ተፈታኞቹ ትምህርት ሚኒስቴር እና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የነበሩትን እንቅፋቶች ፈትሸው ፍትሃዊ መፍትሄ እንዲሰጡ፣ ስህተት ያለባቸው ጥያቄዎች እንዲመረመሩ እና ውጤት ሲገለጽ ያጋጠሙትን የቴክኒክ ችግሮች ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን ጠይቀዋል።
እስካሁን ድረስ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት በተነሱት ቅሬታዎች ላይ ያለው ነገር የለም። መ/ቤቱ ትናንት ባወጣው አጭር መግለጫ፣ ፈተናው "በሰላም መጠናቀቁን" ብቻ ገልጿል። አገልግሎቱ በተነሱት ጉዳዮች ላይ የሚያወጣውን መረጃ የምናደርሳችሁ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
131 · Фотография
click to show
click to show
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ የማታ እና የእረፍት ቀናት ፕሮግራም ተማሪዎች የ2018 ዓ.ም የክረምት ትምህርት ምዝገባ ከሰኔ 17-19/2018 ዓ.ም የሚካሔድ መሆኑን ገልጿል፡፡
የ2ኛ ዓመትና ከዚያ በላይ የሆኑ ተማሪዎች ምዝገባ ከሰኔ 17-19/2018 ዓ.ም እንዲሁም የ1ኛ ዓመት ተማሪዎች ምዝገባ ከሰኔ 18-19/2018 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል፡፡
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
104 · Фотография
click to show
click to show
#Motivation
የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ቅዳሜ ሰኔ 20/2018 ዓ.ም የተማሪዎች የምረቃ ስነ-ስርዓት ያካሒዳል፡፡
ዩኒቨርሲቲው በዕለቱ ከሚያስመርቃቸው ተማሪዎች መካከል በኢትዮጵያ የመጀመሪያው በሀገር ውስጥ የሰለጠነ የኒውክሌር ሳይንስና ምህንድስና ተመራቂ (Ethiopia’s first locally trained Nuclear Science and Engineering Graduate) ይገኝበታል፡፡ 👏👍
ውባንተ ደሴ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የኒውክሌር ሪአክተር ቴክኖሎጂ የልህቀት ማዕከል የማስተርስ ዲግሪ ትምህርቱን ተከታትሎ አጠናቋል፡፡
የMSc ጥናቱ በNuclear Materials ላይ ትኩረት የያደረገ ሲሆን፤ ምርምሩ የኒውክሌር ኃይል ስርዓቶችን ደኅንነት በከፍተኛ ደረጃ ለማረጋገጥ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ተገልጿል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
123 · Фотография
click to show
click to show
#Commencement
በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን በዚህ ሳምንት ያስመርቃሉ።
➫ አርሲ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 16/2018 ዓ.ም)
➫ ራያ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 16/2018 ዓ.ም)
➫ ሠመራ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 17/2018 ዓ.ም)
➫ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 18/2018 ዓ.ም)
➫ ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 18/2018 ዓ.ም)
➫ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 18/2018 ዓ.ም)
➫ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 18/2018 ዓ.ም)
➫ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 18/2018 ዓ.ም)
➫ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 18/2018 ዓ.ም)
➫ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ጅማ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ዲላ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ አክሱም ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ቀብሪደሃር ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ወራቤ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ደምቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20/2018 ዓ.ም)
➫ ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 21/2018 ዓ.ም)
➫ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ (ሰኔ 20 እና 21/2018 ዓ.ም)
[https://t.me/allethioschool]
128 · Фотография
click to show
click to show
ውጤትዎን ይመልከቱ!
ከሰኔ 04-12/2018 ዓ.ም የተሰጠው የ2018 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ውጤት መታየት ጀምሯል።
ውጤትዎን ለማየት 👇
https://result.ethernet.edu.et
ሊንኩን ከተጫኑ በኋላ 'Exit Examination' ላይ 'View Results' የሚለውን በመጫንና Username በማስገባት ውጤትዎን ይመልከቱ።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
141 · Фотография
click to show
click to show
#EHPLE
የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከነገ ሰኔ 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል፡፡
ነገ ሰኔ 17/2018 ዓ.ም የሚሰጡ ፈተናዎች፦
● ሕክምና
● ማኅበረሰብ ጤና
● ሜዲካል ላቦራቶሪ ሳይንስ
● ሚድዋይፈሪ
● ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ
● የሕጻናት ሕክምናና የሕጻናት ጤና ነርሲንግ
ተፈታኞች በዛሬው ዕለት አጠቃላይ የፈተና ገለጻ የተሰጣቸው ሲሆን፤ የመለማመጃ ፈተና (Mock Exam) እየወሰዱ ነው።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
152 · Фотография
click to show
click to show
Фотография
click to show
click to show
Фотография
click to show
click to show
ቅሬታዎን ያስገቡ!
በመውጫ ፈተና ውጤትዎ ላይ ቅሬታ ካለዎት ቅሬታዎን በኦንላይን ያስገቡ፡፡
➫ ውጤትዎ ያልተገኘ ከሆነ
➫ Disqualified የተባሉ ከሆነ
➫ ፊርማ ቢፈርሙም NG የተባሉ ከሆነ
➫ የተሳሳተ ጾታ ከመረጡና መሠል ቅሬታ ካለዎ ማቅረብ ይችላሉ፡፡
የመውጫ ፈተና ውጤት ባዩበት ሊንክ (https://result.ethernet.edu.et) ላይ Submit Complaint የሚለውን ይጫኑ፣ Complaint Category ከሚለው ይምረጡ፣ Description የሚለው ባዶ ቦታ ላይ ቅሬታውን አጠር አድርገው ይግለፁ፣ ስልክ ቁጥርዎን ያስገቡና Submit Complaint የሚለውን በመጫን ያጠናቅቁ፡፡
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
163 · Фотография
click to show
click to show
ቅሬታችሁን እስከ ሰኔ 23/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ ማቅረብ ትችላላችሁ። - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት
ከመውጫ ፈተና ውጤት ጋር በተያያዘ ቅሬታ ያላችሁ ተፈታኞች፣ ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል።
ውጤት ያያችሁበትን ሊንክ https://result.ethernet.edu.et/usernamepage በመጠቀም፣ በገፁ ላይ የሚገኘውን "Submit Complaint" የሚለውን አማራጭ በመጫን ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን አገልግሎቱ አስረድቷል።
ቅሬታ የማቅረቢያ ጊዜ 👇
ከሰኔ 17-23/2018 ዓ.ም
ቅሬታ አቅራቢዎች በአካል ወደ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መሔድ ሳይጠበቅባችሁ በኦንላይን ብቻ ቅሬታችሁን እንድታቀርቡ ተብሏል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
167 · 24 June 2026
Фотография
click to show
click to show
#MizanTepiUniversity
ከሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ተመርቃችሁ ዋናውን ዲግሪ (Original Degree) ያልወሰዳችሁ እና እንዲሠራላችሁ የምትፈልጉ የተቋሙ ምሩቃን ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ዋናው ዲግሪ የመጀመሪያ ዙር ህትመት ለማድረግ ከታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም ድረስ አስፈላጊውን መረጃ እንድትሞሉ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል፡፡
ከሰኔ 30/2018 ዓ.ም በኋላ የምትመዘገቡ በሁለተኛው ዙር የሚታተምላችሁ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በወጭ መጋራት የተማራችሁ አመልካቾች ዋናውን ዲግሪያችሁን ለመውሰድ ክፍያ መፈፀማችሁን ወይም በአገልግሎት መወጣታችሁን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ እና ደረሰኝ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል ተብሏል፡፡
ምዝገባ ለማድረግ 👇🏼
https://forms.gle/9ymN9vsQP6Df5y1y8
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
184 · Фотография
click to show
click to show
#RayaUniversity
ራያ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ሳምንት የተጠናቀቀውን የመውጫ ፈተና ከወሰዱ የተቋሙ ተማሪዎች መካከል 98.98 በመቶዎቹ የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ገልጿል።
ዩኒቨርሲቲው ለአገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ካስቀመጣቸው 295 እጩ ተመራቂዎች መካከል 292 ተማሪዎች ወይም 98.98% ማለፉቸውን አሳውቋል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
116 · Фотография
click to show
click to show
#WolkiteUniversity
ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከወሰዱ የተቋሙ የመደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች መካከል 92.5% የሚሆኑት እጩ ተመራቂ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ገልጿል።
ባለፈው ሳምንት የተጠናቀቀውን የመውጫ ፈተና ካስፈተኑት 17 የተቋሙ ትምህርት ክፍሎች መካከል ዘጠኙ ሙሉ በሙሉ (100%) በማሳለፍ የላቀ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገልጿል።
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
142 ·