ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

ETHIO ≈ SCHOOL

2 511 members
15 December 2025
Фотография
click to show
#ExitExam በጥር ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ያድርጉ! የተፈታኞች የምዝገባ ጊዜ፦ ከታህሳስ 06-13/2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተናውን የምትፈተኑ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባችሁን በተጠቀሱት ቀናት ማድረግ ይጠበቅባችኋል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
211 ·
Фотография
click to show
#ETA የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና በዓመቱ አጋማሽ ለመስጠት ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት የተፈታኞች ምዝገባ ከዛሬ ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለማካሔድ የታቀደ መሆኑን የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ለሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው ሰርኩላር ገልጿል፡፡ በዚህም አስፈታኝ የሆኑ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምዝገባ ከታህሳስ 06-13/2018 ዓ.ም ስለሚካሄድ በተጠቀሱት ቀናት ብቻ ተፈታኞች እንዲመዘገቡ አስፈላጊውን እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡ ተቋማቱ ፈቃድ በተሰጣቸው የትምህርት መስኮች፣ የትምህርት ደረጃ፣ መርሐግብር እና ካምፓስ በ2018 ዓ.ም አጋማሽ ለሚሰጠው የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚፈተኑ እጩ ምሩቃን ዝርዝር መረጃ ከታች በተያያዘው ቅፅ መሰረት ዝርዝር መረጃውን በተጠቀሱት ቀናት ከዚህ በፊት በምታስገቡበት ሲስተም እንደታስገቡ ባለሥልጣኑ አሳስቧል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
215 ·
F
Файл
DATA_TEMPLATE_LATEST_2018_UPDATED_PRIVATE.xlsx · 20 KB · click to show
በጥር 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና የሚወስዱ እጩ ምሩቃን ዝርዝርና ሙሉ መረጃ መሙያ ቅፅ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
198 ·
16 December 2025
Фотография
click to show
#MekelleUniversity በ2018 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ ትምህርት (ሪሚዲያል ፕሮግራም) መቐለ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት ማድረጊያ ቀን ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ከዛሬ ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ የተዘጋጀውን የGoogle Form (https://forms.gle/FYhfCg3dLhTFyQ477) በመጠቀም መረጃችሁን እንድትሞሉ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል። የምዝገባ ቦታ፦ ➫ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች በዋናው ግቢ፣ ➫ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች በዓዲ-ሓቂ ግቢ። ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦ ➫ የ12ኛ ክፍል ውጤት መግለጫ፣ ➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ፓስፖርት መጠን ጉርድ ፎቶግራፍ፣ ከላይ የተዘረዘሩትን የትምህርት ማስረጃዎች እና ፎቶግራፍ ስካን በማድረግ በተዘጋጀው ሊንክ https://forms.gle/FYhfCg3dLhTFyQ477 ላይ ማያያዝ/መላክ ይጠበቅባችኋል። የለሊት አልባሳት ማለትም አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ መያዝ ይኖርባችኋል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
189 ·
Фотография
click to show
#ERMP የ2018 ዓ.ም የብሔራዊ ህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (Ethiopian Residency Matching Program/ERMP) ምዝገባ ተጀምሯል፡፡ ጤና ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በህክምና ዲግሪ ያላቸውንና የስፔሻሊቲ ስልጠና በ2018 ዓ.ም መከታተል የሚፈልጉ አመልካቾችን በብሔራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ መግቢያ ፈተና አወዳድሮ ለማሰልጠን ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ የዘንድሮው ስልጠና በ22 የማሰልጠኛ ተቋማት እና በ23 የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች ይሰጣል፡፡ የምዝገባ ጊዜ፦ ታህሳስ 06-20/2018 ዓ.ም ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች በጤና ሚኒስቴር ድረ-ገፅ (https://www.moh.gov.et) ላይ በመግባት በምትፈልጉት የጤና ስፔሻሊቲ መስክ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
199 ·
F
Фотография
click to show
#ExitExam በጥር ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ የሚወስዱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ ትናንት ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም መጀመሩ ይታወቃል። ምዝገባው እስከ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም ይቆያል። እነዚህ ተማሪዎች በተቋም ደረጃ ምዝገባቸውን በተጠቀሱት ቀናት አድርገው መረጃቸው ለትምህርት ሚኒስቴር የሚላክ መሆኑ ተገልጿል፡፡ የፈተና አስተዳደር ክፍያ 750 ብር በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት በኩል በመክፈል፥ የከፈላችሁበትን ኦሪጅናል ደረሰኝ ከነሙሉ ስማችሁ ለየትምህርት ክፍላችሁ መላክ ይጠበቅባችኋል፡፡ 🔔 የመውጫ ፈተናውን በድጋሜ የምወስዱ አመልካቾች ምዝገባ የምታደርጉት በራሳችሁ ነው፡፡ ፈተናውን በድጋሜ የምትወስዱ ይመዝገቡ 👇 https://exam.ethernet.edu.et የምዝገባ ሒደቱን የሚያሳይ ቪዲዮ👇 https://youtu.be/C9KkQ9AHd2o ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
244 ·
17 December 2025
F
Фотография
click to show
#ተጨማሪ በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተወዳድራችሁ ያለፋችሁና በየትምህርት ቤቶቹ የተመደባችሁ የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 11 እና 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል። ተማሪዎች ወደየተመደባችሁበት ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ስትሔዱ ከወላጅ፣ ከአሳዳጊ ወይም ኃላፊነት ካለው ተጠሪ ጋር መሆን እንዳለበት ተገልጿል። ወላጅ፣ አሳዳጊ ወይም ተጠሪው ግለሰብ በትምህርት ቤቱ የተዘጋጀውን የስምምነት ሰነድ ፈርመው ለትምህርት ቤቱ አመራር ማስረከብ ይኖርባቸዋል ተብሏል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
207 ·
18 December 2025
Фотография
click to show
#ጥቆማ የኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ሀገር አቀፍ የግእዝ ጉባኤ ከሚያዚያ 15-17/2018 ዓ.ም ያካሒዳል፡፡ ለጉባኤው የሚሆኑ የምርምር ጽሑፎችን ከስር በተገለፁት የምርምር ጭብጦች ዙሪያ እንዲያቀርቡ ተጋብዘዋል፡፡ የምርምር ጭብጦች፦ ➫ የጊዜ እሳቤ እና የዘመን መንፈስ በፍልስፍና እና በግእዝ ሥነ ጽሑፍ፣ ➫ የዘመን ስሌትና ጥንታዊ የሥነ ፈለክ (አስትሮኖሚ) ምርምር፣ ➫ ሰው መሆን፣ ባህል፣ እምነት እና ጊዜ በግእዝ ሥነ ጽሑፍ፣ ➫ የኢትዮጵያ የዘመን ቀመር በግዕዝ ድርሳናት፣ ➫ የአቡሻኽር የዘመን አቆጣጠርና የእቆጣጠሩ ብልኃት፣ ➫ የዘመን አከፋፈልና የጊዜ እሳቤ በሥነ ተፈጥሮ ጥናት በቅዱስ ያሬድ ሥራዎች፣ ➫ የግዕዝ የሒሳብ ስሌት ከዘመናዊ የሒሳብ ስሌት ጋር ሲነፃፀር፣ ➫ የግዕዝ ፊደልና ቀመረ ፊደል፣ ➫ የገዳማት አስተዋጽኦ በጥንታዊው የዘመን ስሌት፣ ➫ የግእዝ ስነ-ጽሁፋዊ ሀብቶች ጥበቃ ከኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ አንጻር፣ የአኅጽሮተ ጽሑፍ ማስረከቢያ ጊዜ፦ ከታህሳስ 1-20/2018 ዓ.ም የተመረጡ የምርመር ጽሑፎች ማሳወቂያ ጊዜ፦ ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም ሙሉ ጽሑፍ ለጉባኤው አዘጋጆች የሚላክበት ጊዜ፦ ከመጋቢት 25-30/2018 ዓ.ም የምርምር ሥራዎች የሚላኩበት አድራሻ፦ ➫ በኢትዮጵያ ቤተመዛግብትና ቤተመጻሕፍት አገልግሎት አቶ መኮንን ከፋለ ስልክ ቁ. 0933225306 ኢሜይል፦ [email protected] ➫ በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ የባህል፣ ታሪክ እና ቋንቋ ልማት ማዕከል ኢሜይል፦[email protected] የሚቀርቡ ጥናቶች ከዚህ በፊት ያልቀረቡና ያልታተሙ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡ ለበለጠ      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool]
163 ·
Фотография
click to show
#ጥቆማ ጥምር የማስተርስ እና የፒኤችዲ ፕሮግራም ትምህርት እድል ተጠቃሚ ለመሆን ያመልክቱ! ፕሮግራሙ (Joint MA and PhD Program Global Studies: Peace and Security in Africa) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና በሌፕዚግ ዩኒቨርሲቲ በጋራ የሚሰጥ ነው፡፡ በሁለቱ ዩኒቨርሲቲዎች ማለትም ሦስት ተርሞች በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና አንድ ተርም በሌፕዚግ ዩኒቨርሲቲ ቆይታ ይኖርዎታል፡፡ ሁሉም ኮርሶች በእንግሊዝኛ የሚሰጡ ናቸው፡፡ የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ የካቲት 21/2018 ዓ.ም የኦንላይን ቃለመጠይቅ፦ መጋቢት 2018 ዓ.ም የመጨረሻ ቅበላ ውሳኔ፦ ሚያዝያ 2018 ዓ.ም ተጨማሪ ያንብቡ 👉 bit.ly/48Mvn9A ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
163 ·
F
Фотография
click to show
#Update በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተወዳድራችሁ ያለፋችሁና በየትምህርት ቤቶቹ የተመደባችሁ የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 11 እና 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ሚኒስቴሩ መግለፁ ይታወቃል። ይሁን እንጂ፥ በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት የተመደባችሁ ተማሪዎች "ያልተሟሉ ነገሮች" ስላሉ የመግቢያ ጊዜ የተራዘመ መሆኑን ሚኒስቴሩ በዛሬው ዕለት ገልጿል። ወደ ትምህርት ቤቱ የምትገቡበትን ቀን እስከሚገለፅ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ ሚኒስቴሩ ጠይቋል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
195 ·
19 December 2025
Фотография
click to show
የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበዋል? ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ17 የጤና ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በታህሳስ 2018 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና ይሰጣል፡፡ በመሆኑም አዲስ እንዲሁም ነባር የመንግሥት እና የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን http://hpe.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንድትመዘገቡ አሳስቧል፡፡ የኦንላይን ምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው፦ እሑድ ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም ከተጠቀሰው የምዝገባ ጊዜ በኋላ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ Print አድርጋችሁ መያዝ እንዳለባችሁ ገልጿል፡፡ ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ ተመዛኞች ምዝገባውን ለማካሔድ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ግዴታ በመሆኑ፣ የፋይዳ መለያ ልዩ ቁጥር (FIN) በትክክል እንድታስገቡ አሳስቧል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
194 ·
Фотография
click to show
#ጥቆማ #BahirDarUniversity የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ፍላጎትና ብቃት ያላቸው የምህንድስና ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ➤ የሥራ መደብ፦ የህክምና 3D ቴክኖሎጂ ኢንጂነሮች እና ሳይንቲስቶች ➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 03 ➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ የመጀመሪያ ዲግሪ ➤ የሥራ ልምድ፦ ዜሮ ዓመት ➤ የቅጥር ሁኔታ፦ በኮንትራት ➤ የሥራ ቦታ፦ ባህር ዳር የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች አስፈላጊ የትምህርት ማስረጃዎችን በኢሜይል አድራሻ [email protected] በመላክ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
163 ·
Фотография
click to show
Фотография
click to show
#ExitExamUpdates በጥር ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ ከታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል። ፈተናውን ለመጀመሪያ ጊዜ የምትወስዱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባችሁን በተቋም ደረጃ በተጠቀሱት ቀናት አድርጋችሁ መረጃችሁ በምትማሩበት ከፍተኛ ትምህርት ተቋም አማካኝነት ለትምህርት ሚኒስቴር የሚላክ ይሆናል፡፡ ⏩ የክፍያ ጉዳይ፦ ቴሌብር በመጠቀም Payment የሚለውን በመጫን ከዛም Education fee የሚውን በመንካት ከሚመጡ ዝርዝሮች "Educational Assessment and Examinations Service" የሚለውን በመጫን የፈተና አስተዳደር ክፍያ 750 ብር መፈፀም ይጠበቅባችኋል፡፡ (ምስል 2) ⏩ የመውጫ ፈተናውን በድጋሜ የምወስዱ አመልካቾች ምዝገባ የምታደርጉት በራሳችሁ ነው 👉🏽 https://exam.ethernet.edu.et ⏩ የመፈተኛ Password እና የመግቢያ ትኬት የፈተና ጊዜው ሲደርስ የሚሰጣችሁ ይሆናል፡፡ ⏩ Username የረሳችሁ forgot username በመጠቀም ማግኘት ትችላላችሁ፡፡ ⏩ ከዚህ ቀደም በተለያየ ሁኔታ ከአንድ ጊዜ በላይ ከተመዘገባችሁ ሲስተሙ ሁሉንም Username ያሳያል፤ አንዱን በቻ ይዛችሁ መመዝገብ ይኖርባችኋል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
179 ·
Фотография
click to show
የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ተመዝግበዋል? ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ17 የጤና ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በታህሳስ 2018 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና ይሰጣል፡፡ በመሆኑም አዲስ እንዲሁም ነባር የመንግሥት እና የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን http://hpe.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንድትመዘገቡ አሳስቧል፡፡ የኦንላይን ምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው፦ እሑድ ታህሳስ 12/2018 ዓ.ም ከተጠቀሰው የምዝገባ ጊዜ በኋላ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ Print አድርጋችሁ መያዝ እንዳለባችሁ ገልጿል፡፡ ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡ ተመዛኞች ምዝገባውን ለማካሔድ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ግዴታ በመሆኑ፣ የፋይዳ መለያ ልዩ ቁጥር (FIN) በትክክል እንድታስገቡ አሳስቧል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
124 ·
Фотография
click to show
#ጥቆማ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በኅብረተሰብ ጤና ትምህርት የፒኤችዲ ፕሮግራም (PhD in Public Health) ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ የምዝገባ ጊዜ፦ ከታህሳስ 09-25/2018 ዓ.ም የፈተና/Synopsis ማቅረቢያ ቀናት፦ ጥር 07 እና 08/2018 ዓ.ም ለመመዝገብ ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ 👇 https://portal.sphmmc.edu.et/Web/Announcement (ዝርዝር መስፈርቶችን ለማግኘት የኮሌጁን ድረ-ገፅ https://sphmmc.edu.et/ ይጎብኙ፡፡) ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
160 ·
F
Фотография
click to show
#ጥቆማ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በኅብረተሰብ ጤና ትምህርት የፒኤችዲ ፕሮግራም (PhD in Public Health) ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ የምዝገባ ጊዜ፦ ከታህሳስ 09-25/2018 ዓ.ም የፈተና/Synopsis ማቅረቢያ ቀናት፦ ጥር 07 እና 08/2018 ዓ.ም ለመመዝገብ ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ 👇 https://portal.sphmmc.edu.et/Web/Announcement (ዝርዝር መስፈርቶችን ለማግኘት የኮሌጁን ድረ-ገፅ https://sphmmc.edu.et/ ይጎብኙ፡፡) ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
224 ·
20 December 2025
Фотография
click to show
#ጥቆማ #HawassaUniversity የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ዳዬ ካምፓስ ፍላጎትና ብቃት ያላቸው መመህራንን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል። ➤ የሥራ መደብ፦ መምህራን ➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 04 ➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ ሁለተኛ ዲግሪ ➤ የሥራ ልምድ፦ ዜሮ ዓመት እና በላይ ➤ የሥራ ቦታ፦ ዳዬ ከተማ (ከሃዋሳ ከተማ 130 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ) የመመዝገቢያ ቀናት፦ ለሥራ መደቡ በትምህርት ሚኒስቴር የተቀመጠውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 (ሰባት) ተከታታይ የሥራ ቀናት ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ የብቃትና ሰው ኃይል አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ እና በዳዬ ካምፓስ የብቃትና ሰው ኃይል አስተዳደር ሥራ አስፈፃሚ ቢሮ 2ኛ ፎቅ በአካል በመገኘት ወይም በተወካይ አማካይነት መመዝገብ ይችላሉ ተብሏል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
155 ·
Фотография
click to show
#ማስታወሻ በ2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ትምህርታችሁን በመከታተል ላይ የምትገኙ ተማሪዎች የፋይዳ መታወቂያ ማውጣት ይጠበቅባችኋል። የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ ያላደረጋችሁ በከተማዋ የምትገኙ የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ቅዳሜ እና እሑድ በሁሉም የምዝገባ ጣቢያዎች በመገኘት ምዝገባ በማድረግ መታወቂያውን መውሰድ ትችላላችሁ። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
145 ·
Фотография
click to show
#ETA ሁሉም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2018 ዓ.ም የተመዘገቡ አዲስ ተማሪዎቻቸውን ዝርዝር መረጃ እንዲልኩ የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ጠይቋል። ተቋማቱ ፈቃድ በተሰጣቸው የትምህርት መስኮች፣ የትምህርት ደረጃ፣ መርሐግብር እና ካምፓስ በ2018 ዓ.ም የመዘገቧቸውን አዲስ ተማሪዎች ብቻ ከዚህ በፊት በባለሥልጣኑ በተላከው ቅጽ መሰረት ዝርዝር መረጃውን እስከ ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም በሶፍት እና በሃርድ ኮፒዎች እንዲልኩ ባለሥልጣን መስሪያቤቱ አሳስቧል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
151 ·
Фотография
click to show
በቀጣይ ራስ ገዝ ሆነው የሚቋቋሙ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ለሚያደርጉት የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች ግብዓት የሚሆን የሽግግር ረቂቅ መመሪያ ላይ ምክክር ተደረገ። በመጪው ዓመት ራስ ገዝ ለመሆን እየሠሩ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች፥ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በተጀመረው ራስ ገዝ የመሆን ሂደት የተገኙ ተሞክሮዎች እና ፈተናዎችን በመለየት በቂ ዝግጅት እንዲያደርጉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) አሳስበዋል። በመድረኩ ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የራስ ገዝነት ሽግግር የተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ውይይት ተደርጎበታል። ረቂቅ ሰነዱ ለራስ ገዝነት ሽግግር የሚያበቁ መስፈርቶችና ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች የተካተቱበት ሲሆን፤ ዩኒቨርሲቲዎች በዚህ ረቂቅ መመሪያ እየተመዘኑ ሽግግር የሚያደርጉ መሆኑ ተገልጿል። በመድረኩ በቀጣይ ራስ ገዝ በመሆን ለሚቋቋሙ ዩኒቨርሲቲዎች ተሞክሮ እንዲሆን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዝነት ሽግግርን የተመለከተ የዳሰሳ ጥናት ቀርቦ ወይይት ተደርጎበታል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
168 ·
Фотография
click to show
#MoE የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የ2018 ዓ.ም የመረጃ አሰባሰብ (HEMIS) ያለበት ሁኔታ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሪፎርም ሥራዎችን የተመለከተ የምክክር መድረክ በትምህርት ሚኒስቴር ተዘጋጅቷል። መድረኩ ታህሳስ 14 እና 15/2018 ዓ.ም ይካሔዳል። በዚህም ስማችሁ ከላይ በምስሉ የተዘረዘሩ ተቋማት፣ የተቋም ባለቤት/የበላይ አመራር እና ከተገለፀው ሥራ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው አንድ ባለሙያ የተቋሙን የተሟላ መረጃና ለሥራ የሚሆን ላፕቶፕ በመያዝ ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 በትምህርት ሚኒስቴር ትንሹ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንድትገኙ ጥሪ ተላልፏል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
230 ·
F
Фотография
click to show
ተራዝሞ የነበረው ጋምቤላ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከታህሳስ 12-15/2018 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል። ለበለጠ መረጃ የጋምቤላ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር 0911590938 በመደወል መጠየቅ ትችላላችሁ። ከከተማው ወደ ዩኒቨርሲቲው የምትሄዱበትን ትራንስፖርት ለማመቻቸት እንዲረዳ ጋምቤላ የምትደርሱበትን ቀን እና ሰዓት አስቀድማችሁ በተጠቀሰው ስልክ ቁጥር እንድታሳውቁ ሚኒስቴሩ ጠይቋል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
262 ·
23 December 2025
Фотография
click to show
#SpecialBoardingSchools በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተወዳድረው ያለፉና የተመደቡ ተማሪዎች ወደየተመደቡበት ተቋም በመግባት ላይ ይገኛሉ። ወሊሶ የተመደቡ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ሀጫሉ ሁንዴሳ ካምፓስ፣ ቡኢ የተመደቡ ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ፣ ቦንጋ የተመደቡ ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ፣ እንዲሁም ጅግጅጋ የተመደቡ ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ እየገቡ መሆኑ መሆኑ ተገልጿል። ተራዝሞ የነበረው ጋምቤላ ፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተመደቡ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ከታህሳስ 12-15/2018 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
194 ·
F
Фотография
click to show
ዛሬ ይጠናቀቃል!! በጥር ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና የሚወስዱ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ ዛሬ ታህሳስ 13/2018 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡ መዝገባው ከታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል። የመውጫ ፈተናውን በድጋሜ ለመውሰድ ምዝገባ ያድርጉ 👉🏽 https://exam.ethernet.edu.et ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
187 ·
Open in Telegram Feed t.me/s Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog