ChatCrawlersearch across public Telegram Open the app
E

ETHIO ≈ SCHOOL

2 511 members
23 December 2025
Фотография
click to show
#JinkaUniversity በ2018 ዓ.ም ለሪሚዲያል ፕሮግራም ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ የሪሚዲያል ተማሪዎች በሙሉ የማርበርግ ቫይረስ ሙሉ በሙሉ መጥፋቱ በጤና ሚኒስቴር ተረጋግጦ ጥሪ እስከሚደረግላችሁ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል። በሌላ መረጃ፤ ከአሪ እና ደቡብ ኦሞ ዞኖች በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዳችሁ የሪሚዲያል ትምህርት ለመከታተል ከጂንካ ዩኒቨርሲቲ ውጪ በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የተመደባችሁ ተማሪዎች ታህሳስ 15 እና 16/2018 ዓ.ም ወደ ጂንካ ዩኒቨርሲቲ ገብታችሁ የ21 ቀናት Quarantine ወስዳችሁ በዩኒቨርሲቲው ነፃ የምግብ እና የመኝታ አገልግሎት እያገኛችሁ በመቆየት ከማርበርግ ቫይረስ ነፃ መሆናችሁ ሲረጋገጥና የምስክር ወረቀት ከተሰጣችሁ በኋላ ወደየተመደባችሁባቸው ዩኒቨርሲቲዎች እንድትገቡ ትምህርት ሚኒስቴር ወስኗል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
191 ·
Фотография
click to show
#Update የ2018 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም የመውጫ ፈተና የምዝገባ ጊዜ ተራዝሟል። የምዝገባ ጊዜው ከተቋማት በቀረበ ጥያቄ እና ሌሎች ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት እስከ አርብ ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ስዓት ድረስ የተራዘመ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል። ሁሉም የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች እንዲሁም የግል ተፈታኞች ምዝገባችሁን በተራዘመው ጊዜ እንድታጠናቅቁ ተብሏል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
225 ·
F
Фотография
click to show
በአማራ ክልል ከ27 ሺህ በላይ ለሚሆኑ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ ምዘና ይሰጣል። በአማራ ክልል በዚህ ዓመት ከ27 ሺህ በላይ ለሚሆኑ መምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የሙያ ፈቃድ ምዘና ለመስጠት እየተሠራ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደምስ እንድሪስ ገልፀዋል። ለ21,669 ነባር እና 5,559 ከመምህራን ትምህርት ኮሌጅ ለሚመረቁ እጩ መምህራን ምዘና እንደሚሰጥ እንደሚሰጥ ምክትል ኃላፊው ጠቁመዋል። መምህራኑ እና የትምህርት ቤት አመራሮቹ የሙያ ፈቃድ ምዘና ማረጋገጫ ሰርተፊኬት መያዛቸው የበለጠ ተወዳዳሪ ለመሆን ያስችላቸዋል ተብሏል። በሞዴል እና አዳሪ ትምህርት ቤቶች ለማስተማር መምህራን ከሚጠየቁት ማስረጃዎች መካካል የሙያ ፈቃድ ምዘና ማረጋገጫ ሰርቲፊኬት መሆኑ ይታወቃል። ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
237 ·
24 December 2025
F
Фотография
click to show
Фотография
click to show
Фотография
click to show
ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም ወደ ተቋሙ አዲስ የተመደቡ የአቅም ማሻሻያ (ሪሚዲያል) ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ይገኛል፡፡ ዩኒቨርሲቲው አዲስ ገቢ የሪሚዲያል ተማሪዎች ታህሳስ 15 እና 16/2018 ዓ.ም በተቋሙ ዋናው ግቢ፣ (ሆሳዕና ከተማ) እና ዱራሜ ካምፓስ (ዱራሜ ከተማ) ሪፖርት እንዲያደርጉ ጥሪ ማስተላለፉ ይታወሳል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
309 ·
25 December 2025
Фотография
click to show
የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ታህሳስ 23 እና 24/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ - ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቁ የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ታህሳስ 23 እና 24/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ የፈተናው መርሐግብር ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም Public Health, Pharmacy, Medical Laboratory Science, Medical Radiology Technology, Environmental Health እና Human Nutrition. ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም Medicine, Nursing, Anesthesia, Midwifery, Dental Medicine, Psychiatric Nursing, Emergency and Critical Care Nursing, Pediatric and Child Health Nursing, Surgical Nursing እና Physiotherapy. ሁሉም ተፈታኝ ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት በመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ-ገለጻ (Orientation) መከታተል፣ የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራት እና የመፈተኛ ክፍሉን መለየት ይኖርበታል ተብሏል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
202 ·
Фотография
click to show
#ተጨማሪ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ቴዎድሮስ ካምፓስ መፈተኛ ጣቢያ የመረጣችሁ የብቃት ምዘና ፈተና ተመዛኞች ወደ ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጂ የፈተና ጣቢያ የተመደባችሁ መሆኑ ተገልጿል፡፡ አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ መፈተኛ ጣቢያ የመረጣችሁ የ Public Health, Pharmacy, Medical Laboratory Science, Medical Radiology Technology, Environmental Health እና Human Nutrition ሙያ ተመዛኞች ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (ጥቁር አንበሳ) የፈተና ጣቢያ እንዲሁም የ Medicine, Nursing, Anesthesia, Midwifery, Dental Medicine, Psychiatric Nursing, Emergency and Critical Care Nursing, Pediatric and Child Health Nursing, Surgical Nursing እና Physiotherapy ሙያ ተመዛኞች ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ (5 ኪሎ) የፈተና ጣቢያ የተመደባችሁ መሆኑ ተመላክቷል፡፡ ተመዛኞች ስማችሁ ከተጠቀሰበት የመፈተኛ ጣቢያ (ተቋም) ውጪ በፍፁም ፈተናውን መውሰድ እንደማትችሉ ተገልጿል፡፡ (ለፈተናው ብቁ ሆነው የተመረጡ ተመዛኞችን ዝርዝር፣ የተቋም እንዲሁም የፈተና ማዕከል ዝርዝር በጤና ሚኒስቴር ድረ-ገፅ እና ማኅበራዊ ሚዲያ አድራሻዎች ማግኘት ይቻላል፡፡) ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
204 ·
Фотография
click to show
#EHPLE_Exam_Protocol ተመዛኝ የጤና ባለሙያዎች በፈተናው ዕለት ታህሳስ 23 እና 24/2018 ዓ.ም ማንነታችሁን የሚገልጽ መታወቂያ (የቀበሌ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድ ወይም ሌላ በግልጽ የሚታይ ህጋዊ መታወቂያ) ይዛችሁ በፈተና ማዕከል መገኘት ይኖርባችኋል፡፡ ከላይ ከተጠቀሱት ነገሮች ውጪ ምንም አይነት የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያ (ስልክ፣ የእጅ ሰዓት፣ መነጽር (የተረጋገጠ የዕይታ ችግር ከሌለ በስተቀር)፣ ቦርሳ እና ሌሎች እቃዎች፣ ምንም አይነት ማጣቀሻዎች፣ እንዲሁም ባዶ ወረቀቶች፣ ምግብ ወይም መጠጥ (የተረጋገጠ የጤና ችግር ከሌለ በስተቀር) ይዞ መግባት አይፈቀድም፡፡ በፈተናው ወቅት ተመዛኞች በሁለቱም ክፍለ-ጊዜ (ጠዋት እና ከሰዓት) አቴንዳንስ ላይ በአግባቡ ካልፈረሙ ፈተናቸው የማይያዝ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ማንኛውም ተመዛኝ ወደ ፈተና ጣቢያ ሲሔድ ሲስተሙ የሚሰጠውን QR Code ያለው የፈተና መግቢያ ስሊፕ Print አድርጎ ካልያዘ፣ ፈተናውን መውሰድ አይችልም ተብሏል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
216 ·
Фотография
click to show
#FellowshipOpportunity በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የራዲዮሎጂ እና MRT ትምህርት ክፍል ለ2018 ዓ.ም በ Radiology Fellowship ፕሮግራም ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ መቀበል ይፈልጋል። ለዚህ ዓመት ሁለት (2) የፌሎውሺፕ ዕድሎች መኖራቸውን ኮሌጁ ገልጿል። የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ ጥር 02/2018 ዓ.ም የቅበላ መስፈርት፦ ዕውቅና ካለው የከፍተኛ ትምህርት ተቋም በህክምና ትምህርት ዲግሪ ያለው/ያላት እና በአጠቃላይ ራዲዮሎጂ ስፔሻሊቲ ሰርተፊኬት ያለው/ያላት (ዝርዝር መስፈርቶች፣ የምልመላ ሒደት እና የጥናት ዘርፎች በኮሌጁ ድረ-ገፅ እና ማኅበራዊ ሚዲያ ፕላትፎርሞች ያገኛሉ፡፡) የማመልከቻ ቦታ፦ በሬጅስትራር ቢሮ ወይም በራዲዮሎጂ እና MRT ትምህርት ክፍል እንዲሁም በኢሜል አድራሻ [email protected] አመልካቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ፦ ➫ CV ➫ የስፔሻሊቲ ሰርተፊኬት እና የውጤት መግለጫ ➫ የማመልከቻ ደብዳቤ ➫ የምርምር ህትመቶች ➫ የድጋፍ ደብዳቤ ➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ ➫ ለተጨማሪ ሥራዎች የተሰጠ የአድናቆት ደብዳቤ (ቢቻል ከሰርተፊኬት ጋር) ➫ የድኅረ ምረቃ ፈተና ውጤት ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
238 ·
F
Фотография
click to show
#ጥቆማ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ለትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን በተለያዩ የሥራ መደቦች ባለሙያዎችን አወዳድሮ በቋሚነት መቅጠር ይፈልጋል፡፡ ➤ የሥራ መደብ፦ በተለያዩ የሥራ መደቦች ➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 10 ➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ ሁለተኛ ዲግሪ (ከአንድ የሥራ መደብ በስተቀር) ➤ የሥራ ልምድ፦ 2 ዓመት እና በላይ ➤ የቅጥር ሁኔታ፦ በቋሚነት ➫ ከዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ በላይ የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃ ያላችሁ አመልካቾች ማመልከት ትችላላችሁ፡፡ ➫ ከ2015 ዓ.ም ጀምሮ የዲግሪ የትምህርት ማስረጃ የምታቀርቡ አመልካቾች የመውጫ ፈተና ያለፋችሁበትን መረጃ ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡ ➫ ከግል ተቋማት የሚቀርቡ የሥራ ልምድ ማስረጃዎች የስራ ግብር የተከፈለባቸው መሆን ይኖርባቸዋል። ➫ አመልካቾች ለሚያቀርቡት የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃ ህጋዊነት ኃላፊነት ይወስዳሉ። ➫ ለፈተና ለሚመለመሉ አመልካቾች ፈተና የሚሰጥበት ቀንና ቦታ በማስታወቂያ የሚገለፅ ይሆናል። የምዝገባ ጊዜ፦ ከታህሳስ 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሰባት ተከታታይ የሥራ ቀናት የምዝገባ አድራሻ፦ https://forms.gle/tun2LsxSk4pJLr3x7 ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
239 ·
26 December 2025
F
Фотография
click to show
#WSU ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም በዋናው ግቢ እና በዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ለተመደቡ ተማሪዎች ለታህሳስ 23/2018 ዓ.ም አድርጎት የነበረውን የምዝገባ ጥሪ አራዝሟል። በተለያዩ ምክንያቶች የምዝገባ ጊዜው ለጥር 01/2018 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ቦዲቲ ካምፓስ የተመደባቹ ተማሪዎች ለጥር 01/2018 ዓ.ም ተደርጎ የነበረው ጥሪ ላይ ለውጥ አለመደረጉ ተገልጿል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
314 ·
27 December 2025
Фотография
click to show
ዛሬ ይጠናቀቃል! የተራዘመው የ2018 አጋማሽ ዓመት የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመውጫ ፈተና የምዝገባ ጊዜ ዛሬ ይጠናቀቃል። የምዝገባ ጊዜው ዛሬ ታህሳስ 17/2018 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 ሰዓት የሚያበቃ ይሆናል። የመንግሥት እና የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች እንዲሁም በድጋሜ የምትፈተኑ የግል ተፈታኞች በቀሩት ሰዓታት ምዝገባችሁን አድርጉ። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
264 ·
F
Фотография
click to show
#ማስታወሻ የ2018 ዓ.ም የብሔራዊ ህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (Ethiopian Residency Matching Program/ERMP) ምዝገባ ከታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ጀምሮ በመካሔድ ላይ ይገኛል፡፡ ጤና ሚኒስቴር ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በህክምና ዲግሪ ያላቸውንና የስፔሻሊቲ ስልጠና በ2018 ዓ.ም መከታተል የሚፈልጉ አመልካቾችን በብሔራዊ የህክምና ስፔሻሊቲ መግቢያ ፈተና አወዳድሮ ለማሰልጠን ምዝገባ እያደረገ ነው፡፡ የዘንድሮው ስልጠና በ22 የማሰልጠኛ ተቋማት እና በ23 የህክምና ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች ይሰጣል፡፡ የምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው፦ ታህሳስ 20/2018 ዓ.ም ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች በጤና ሚኒስቴር ድረ-ገፅ (https://www.moh.gov.et) ላይ በመግባት በምትፈልጉት የጤና ስፔሻሊቲ መስክ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
300 ·
28 December 2025
F
Фотография
click to show
#MoH የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ታህሳስ 23 እና 24/2018 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር መግለፁ ይታወቃል። የብቃት ምዘና ፈተናውን ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ የጤና ባለሙያዎች በተጠቀሱት የፈተና ቀናት የብሔራዊ መታወቂያ (National ID) ይዛችሁ በፈተና ጣቢያ መገኘት እንዳለባችሁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
330 ·
30 December 2025
F
Фотография
click to show
#GAT የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) የፊታችን ሰኞ ታህሳስ 27/2018 ዓ.ም ይሰጣል፡፡ የተፈታኞች ዝርዝር እና የመፈተኛ ማዕከላት በቀጣይ ቀናት ይፋ እንደሚደረግ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። የመግቢያ ፈተናውን ለመውሰድ ያመልካቾች ምዝገባ ከህዳር 30/2018 ዓ.ም ጀምሮ ሲከናወን የቆየ ሲሆን፤ ነገ ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም ይጠናቀቃል፡፡ ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
294 ·
31 December 2025
Фотография
click to show
#EHPLE ታህሳስ 23 እና 24/2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ያጠናቀቃችሁ የጤና ባለሙያዎች፥ ገለጻ እንድትከታተሉ እና የቅድመ ፈተና ልምምድ እንድታደርጉ ሚኒስቴሩ አሳስቧል። በዚህም ነገ ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት በየተመደባችሁበት የመፈተኛ ጣቢያ በመገኘት ስለፈተናው አሰጣጥ ቅድመ ገለጻ (Orientation) መከታተል እና የቅድመ ፈተና መለማመጃ ጥያቄዎችን መስራት እንደሚጠበቅባችሁ ተገልጿል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
277 ·
F
Фотография
click to show
#ጥቆማ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ በ2018 ዓ.ም በኅብረተሰብ ጤና ትምህርት የፒኤችዲ ፕሮግራም (PhD in Public Health) ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ የምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው፦ ታህሳስ 25/2018 ዓ.ም የፈተና/Synopsis ማቅረቢያ ቀናት፦ ጥር 07 እና 08/2018 ዓ.ም ለመመዝገብ ተከታዩን ሊንክ ይጠቀሙ 👇 https://portal.sphmmc.edu.et/Web/Announcement (ዝርዝር መስፈርቶችን ለማግኘት የኮሌጁን ድረ-ገፅ https://sphmmc.edu.et/ ይጎብኙ፡፡) ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
287 ·
1 January 2026
Фотография
click to show
በ2018 ዓ.ም በመደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ የ“Winter In-Service" ፕሮግራም የምቶማሩ ነባር እና አዲስ ተማሪዎች ምዝገባ ጥር 04 እና 05/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። ትምህርት ጥር 06/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል። በተመሳሳይ በወለጋ ዩኒቨርሲቲ የእንስሳት ጤና ሳይንስ የበጋ መረሐግብር የ2018 ዓ.ም ምዝገባ ጥር 04 እና 05/2018 ዓ.ም የሚከናወን መሆኑ ተገልጿል። ጥር 06/2018 ዓ.ም ትምህርት ይጀምራል ተብሏል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
254 ·
F
Фотография
click to show
#ጥቆማ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ የ Oral and Maxillofacial Surgery ትምህርት ክፍል ለመማር ፍላጎት ያላቸውና ብቁ የሆኑ አመልካቾችን ይቀበላል። የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ ጥር 22/2018 ዓ.ም የመግቢያ ፈተና የሚሰጠው፦ ጥር 29/2018 ዓ.ም አመልካቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች፦ ➫ በጥርስ ህክምና (DDS or DDM) የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ➫ ሁለት ዓመትና በላይ ተዛማችነት ያለው የሥራ ልምድ፣ ➫ በጥሩ የአካላዊና አዕምሯዊ ጤንነት ላይ የሚገኝ/የምትገኝ፣ ➫ ዕድሜ ከ40 አመት ያልበለጠ/ያልበለጠች፣ ➫ የNGAT ፈተና ወስደው ያለፈ/ያለፈች፣ ➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ ከቀጣሪ ተቋማቸው ማቅረብ የሚችሉ አመልካቾች የበለጠ ይበረታታሉ። ፍላጎት ያላችሁ አመልካቾች የማመልከቻ ሰነዶቻችሁን ለትምህርት ክፍሉ በኢሜይል አድራሻ [email protected] በመላክ ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
297 ·
3 January 2026
Фотография
click to show
#ጥቆማ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2018 የትምህርት ዘመን በሁለተኛው ወሰነ ትምህርት በግል ከፍለው ወይም በመስሪያ ቤታቸው ስፖንሰር አድራጊነት ከፍለው መማር ለሚፈልጉ በመደበኛው እና በማታው መርሐግብር የ2ኛ ዲግሪ እና የ3ኛ ዲግሪ አመልካቾችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ የማመልከቻ ጊዜ፦ ከታህሳስ 24/2018 ዓ.ም እስከ የካቲት 10/2018 ዓ.ም የትምህርት መስኮች ዝርዝር እና የመግቢያ መስፈርቶችን ከዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ድረ-ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ መመልከት ይችላሉ፡፡ የመመዝገቢያ ጊዜ የካቲት 26 እና 27/2018 ዓ.ም ሲሆን፤ ትምህርት የካቲት 30/2018 ዓ.ም ይጀምራል ተብሏል፡፡ ⤴️ ዩኒቨርሲቲው የማንበቢያና መመራመሪያ ቢሮ እንዲሁም የዶርም አገልግሎት የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል። 20 ተማሪዎች በኖርዌይ የልማትና ትብብር ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ በተጀመረው የስነ-ትምህርት የሁለተኛ ዲግሪ፥ በሒሳብ እና በሳይንስ ስነ-ማስተማር (MED in Educational Sciences: Teaching of Mathematics and MED in Educational Sciences: Teaching of Science Subjects) ፕሮግራሞች ቅበላ የሚሰጣቸው ይሆናል። ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች/ማስረጃዎች፦ ➫ የትምህርት ማስረጃ ዋናውና ኮፒው፣ ➫ ኦፊሻል ትራንስክሪፕት፣ ➫ በመስሪያ ቤት ስፖንሰርነት ለሚያመለክቱ አመልካቾች ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት የስፖንሰርሽፕ ደብዳቤ፣ ➫ ለማመልከቻ የተከፈለበት ደረሰኝ ብር 300፣ ➫ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም መግቢያ ፈተና (NGAT) የማለፊያ ውጤት። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
250 ·
F
Фотография
click to show
#ጥቆማ #EthiopianAviationUniversity የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራም ትምህርት ለመከታተል የሚፈልጉ አመልካቾች ምዝገባ በማድረግ ላይ ይገኛል። የተቀመጡ መስፈርቶችን የምታሟሉ አመልካቾች ከታች በተገለፀው የምዝገባ ጊዜ አስፈላጊ ሰነዶችን ለዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ቢሮ በማስገባት ማመልከት እንደምትችሉ ተገልጿል። የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦ ጥር 01/2018 ዓ.ም ትምህርት የሚጀምረው፦ የካቲት 09/2018 ዓ.ም ሊያስገቧቸው የሚገቡ ሰነዶች፦ ➫ የትምህርት ማስረጃዎች፣ ➫ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና ውጤት (NGAT and GAT)፣ ➫ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና ውጤት ሰርተፊኬት፣ ➫ የማመልከቻ ክፍያ የማይመለስ ብር 400፣ ➫ ሁለት የቅርብ ጊዜ ፓስፖርት መጠን ፎቶግራፍ። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
268 ·
4 January 2026
F
Фотография
click to show
#AAU #GAT በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) ለመውሰድ የተመዘገባችሁና ነገ ሰኞ ታህሳስ 27/2018 ዓ.ም የሚሰጠው የፈተና መርሐግብር ውስጥ ያልተካተታችሁ አመልካቾች መኖራችሁን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል። እነዚህ አመልካቾች ተከታዩን ሊንክ 👇 https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSc1WoR6gikog5SrwKseX--ocSicMM2-SMTAopi4viYvZBl0QA/viewform?usp=header በመጠቀም የምታገኙትን ቅፅ በፍጥነት እንድትሞሉ ተጠይቋል። ⤴️ የእነዚህ አመልካቾች ፈተና ሰኞ ታህሳስ 27/2018 ዓ.ም ከሰዓት እንደሚሰጥ ተገልጿል። ጥያቄ ያላችሁ አመልካቾች በፎረም ህንፃ 4ኛ ወለል በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፈተና ማዕከል እስከ ረፋዱ 5:00 ሪፖርት ማድረግ ይኖርባችኋል። ለፈተናው ምዝገባ ያደረጉበትን የቅበላ ቲኬት እና የቴሌብር ደረሰኝ ይዘው መቅረብ ይኖርብዎታል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
332 ·
8 January 2026
F
Фотография
click to show
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በዋናው ግቢ፣ ቦዲቲ ግቢ እና ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ለተመደቡ ተማሪዎች አድርጎት የነበረውን ጥሪ በድጋሜ አራዝሟል። ዩኒቨርሲቲው ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጥሪ ወደ ጥር 01/2018 ዓ.ም መራዘሙን መግለፁ ይታወቃል። ይሁን እንጂ "በተለያየ ምክንያት የመመዝገቢያ ቀኑን ማራዘም አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ" ለዋናው ግቢ፣ ቦዲቲ ግቢ እና ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ የተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች ምዝገባ ወደ ጥር 07 እና 08/2018 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው በዛሬው ዕለት ታህሳስ 29/2018 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል። ትምህርት ጥር 11/2018 ዓ.ም (የጥምቀት በዓል ቀን) ይጀመራል ሲልም ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል። ለበለጠ መረጃ እና አስተያየት ካለዎት      👇👇👇 [https://t.me/allethioschool] [https://t.me/allethioschool]
244 ·
Open in Telegram Feed t.me/s Каталог площадок Искать в ChatCrawler

A snapshot of an open public feed from the search index ChatCrawler — “Google for public Telegram”; refreshed as the venue is crawled. Times are UTC.

Public content only, official Telegram API. About · FAQ · What we do not do · Remove a page · Catalog