Фотография
click to show
click to show
ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ ሦስት ካምፓሶች ለተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች አድርጎት የነበረውን ጥሪ ዘግይቶ በድጋሜ ማራዘሙ በተማሪዎች እና ወላጆቻቸው ላይ ቅሬታ ፈጥሯል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ታህሳስ 16/2018 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጥሪ ወደ ጥር 01/2018 ዓ.ም መራዘሙን መግለፁ ይታወቃል።
ይሁን እንጂ ለዋናው ግቢ፣ ቦዲቲ ግቢ እና ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ የተመደቡ የሪሚዲያል ተማሪዎች ምዝገባ ወደ ጥር 07 እና 08/2018 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ታህሳስ 29/2018 ዓ.ም ባወጣው ማስታወቂያ ገልጿል።
ተማሪዎች እና ልጆቻቸውን ለመሸኘት በበዓል ከቤታቸው የየወጡ ወላጆች፣ በጉዞ ላይ እና መንገድ ላይ ሆነው የጥሪ ማስታወቂያው በድጋሜ መመራዘሙ የሚያሳዝንና እንግልት ላይ የጣለቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
አንድ ወላጅ ልጃቸውን ይዘው መንገድ ጀምረው ጅማ ከተማ ገብተው ካደሩ በኋላ የመግቢያ ጥረው መራዘሙን እንደሰሙ ተናግረዋል። በዩኒቨርሲቲው ድርጊት እጅግ ማዘናቸውን የገለፁት እኚህ ወላጅ፤ የሚመለከተው መንግሥታዊ አካል ለጉዳዩ አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጥሪ አቅርበዋል።
በርካታ ተማሪዎች ከሰሜን፣ ከደቡብ፣ ከምስራቅ እና ምዕራብ የሀገሪቱ አካባቢዎች ተነስተው መንገድ ጀምረው በርከቶቹ በነጋተው ጉዟቸውን ለመቀጠል በተለያዩ ከተሞች አድረው ባሉበት ጥሪ መራዘሙን እንደሰሙ ለቲክቫህ ተናግረዋል።
"ቤተሰብ በሌለው አቅሙ የትራንስፖርት ከፍሎ፣ በበዓል ከቤት ከወጣን በኋላና በየከተማው አድረን ጉዞ ልንጀምር ስንል ተራዘመ መባሉ አሳዛኝ ነው" ብለዋል።
ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ በጉዳዩ ዙሪያ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ እና ትምህርት ሚኒስቴርን ለማናገር ያደረገው ጥረት አልተሳካም፡፡
ለበለጠ መረጃ እና
👇
[https://t.me/allethioschool]
268 ·